የተስፋዬ ገብረ አብ “ፖለቲካ”
ተስፋዬ በሁለቱ “ማስታወሻ”ዎች በወቅታዊ ፖለቲካ ላይ የሚጻፉ “ኢልቦለዳዊ-ፈጠራዎችን” በተከታታይ በማቅረብ ፈር ቀዳጅ ነው። ፖለቲካችንን ከግኡዝ የመንግሥት መዋቅር እና የፓርቲ ፖለቲካ ውጭ እነዚህን ማሺኖች በሚያንቀሳቅሱት ሰዎች ማንነት በኩል ለመረዳት ለሚሹ ሁሉ ማስታወሻዎቹ መነበብ የሚገባቸው ናቸው። መጻሕፍቱ ዓላማቸው “ማጋለጥ” ብቻ ቢመስልም ፖለቲከኞቻችንን ለመረዳትም በር የመክፈት አቅም አላቸው። ማንም ሰው የተስፋዬን “ማስታወሻዎች” እንዲጀምራቸው እንጂ እንዲጨርሳቸው አይመከረም፤ ከጀመረ አያቆማቸውማ። “ማስታወሻዎቹ”ን ለመረዳት የተለየ እውቀት አያስፈልግም፤ ስለ ሰዎች ስለተጻፈ። የ“ማስታወሻዎቹ”ን ፋይዳ ለመተንተን ግን “የተስፋዬን ፖለቲካ” እና “ፖለቲከኛውን ተስፋዬን” በሚገባ ማወቅ ይጠይቃል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ወይም የአማርኛውን ክፍል ይጎብኙ)



Mesfin, thanks for sharing your critical review on Tesfaye’s books. Great reflection! I also doubt Tesfaye’s intent. He is against Siye’s group….and less critical on Melese and his colleagues, which led me to see his motive through “blood is thicker than water” lens?? I am not sure..but, skeptical of his motive….unfortunately, many have started seeing him as a liberator….good to doubt…
He (Tesfaye Gebreab) is for sure among the culprits of the woyane regime. I say so because I find it hard to believe that ‘Ye Burqa zimita’ is written with good intent. If anyother individual had written it, he would have been persecuted by the woyane.
እናንተ ብቻ እውነት ተናገሩ እውነት ፃፉ፡፡ የሚከሰቱ ነገሮች ለበጎ ነው ብላችሁ ተቀበሉ፡፡
Cherulli, an Itlian colonizer, a Bento Mussoloni representative in Ethiopia and a racist fascist party member, started the story(teret teret) about the so called Oromos “Geda System” in order to make it fit for his divide & conquer ruling system. n the same token, Prof. Asmerom Legesse finished this fiction for the same purpose ( a la Chrulli and on a specila assignment from Shabia to give Ethiopia “100 years of home work” and disintegrate Ethiopia in to 100 ethnic pieces. And Tesfaye Gebereab glorfied the Oromo’s culture oppression through his “burka Zemeta, Yegazetegnaw and Yederasew Mastawesha. Like his “hero” Asmerom, Tesfaye also want tell us how the Oromo was treated differently by the rest of Ethiopians ignoring the poor oppressed and Bana Lebash (sheep skin) Menze and Gondare.
Therefore, Cherulli, Asmerom Legesse & Tesfaye Gebreab are three in one, with the same motive to spread hate, divsion and ultimately/finally to destroy Ethiopia as a nation. Please God protect our country from those evils !
I have read every book he has written. his books are the most DANGEROUS material I have ever read in my entire life. they contradict each other. I recently read yederasiw mastawesha This is not a political memoir.it is nonfiction memoir filled with fabrications, falsehoods, other fakery.I figured he is a writer, you know, he doesn’t tell everything that’s factual and true.
haw can i find this book as PDF data??? can u help me pls
Please buy and read it.
-ያገር ልጅ
ስለተስፋዬ ገብረ አብ ሸጋ ያማርኛ ቋንቋ ብእርተኝነት እንዳዲስ እዚህ ላይ አላነሳም። በጣም ብዙ ብዙ ተቺዎችና አስተያየት አንጓቾች በቁጥራቸው መጠን ብለውታል። ደራሲው ተስፋዬና የፕሮፓጋንዳ መጣጥፍ ጣፊው ተስፋዬም የብእር ውበት ለዛቸው አንድ ነው። ልዩነታቸው ከዘላቂው የፈጠራ ሥነ ጽሁፍ ሰብእናና ካላፊው ከረጋፊው የፕሮፓጋንዳ ሰውነት ላይ ብቻ ነው።
ተስፋዬ ሸጋ ብእሩን ለፕሮፓጋንዳ ሥራ ባርነት ከሚያውለው ይልቅ ለዘላቂው ሕያው የደራሲነት የሕይወት ጥሪ ቢሰዋው እንደሚሻል ሳይረፍድበት የነቃ አራዳ ነው። ቤልጅግ አሊ የተባሉ ጸሃፊ በቅርብ ቀን ለንባብ ባበቁት ደህና መጣጥፋቸው ላይ “ምነው ተስፋዬ ተስፋዬ ብቻ በዛ? እሱ ብቻ ነውንዴ ባማርኛ ጥኡም ጥሁፍ ያቀረበ? የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን የሕይወት ማስታወሻ ያየ ይለም እንዴ?” እያሉ ትክን ብለው የተመናመነውን የኛኑ አንባቢ አምባ በጥያቄ አፋጠውታል። ምንም እንኳን የተስፋዬን ያሁኑን ሥራ “የደራሲው ማስታወሻ”ን ላለማንበብ የራሳቸውን ምክንያት ቢሰጡም፣ እንደሚዛናዊ ትጉህ አንባቢና አስተያየት ሰጪ ሁሉ በተቃራኒው ቢቆሙ ኖሮ ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆኑ ነበር እላለሁ። ተደራሲዎቻቸውም ይበልጥ ከነአምንክዮዋዊ ምክንያታቸው ልባቸውን በርግደው ይቀበሏቸው ነበር እላለሁ። ምክንያቱም ጸሃፊው ከተቹዋቸው ሳያነቡ የሚተቹ ሰዎችና ከኒያ ወያኒ የቅርብ ጎረቤታቸው ቢያንስ ቢያንስ ራቅ ብለው መቆማቸውን ያረጋግጡልን ነበር።
አንድ ተጨማሪ እውነታቸውን ግን ልንይዝላቸው ይገባል። የጠቀሱት የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ሥራ ላብነትነት የሚወሰድና እጅጉን መነበብ ያለበት የበንተሱ አጻጻፍ ብልሃት ማስተማሪያ ነው። ይህን የሳቸውን መጽሃፍ አንብቦ የጨረሰ ማንኛውም ትሁት አንባቢ፣ በማግስቴው የራሱን የሕይወት ታሪክ ለመጻፍ ብእርና ደብተር ማዘጋጀቱ አይቀሬ ነው። ባጭሩ ደህና ገድል ያላቸውን ብዙ ሰዎች፣ እንዴት የራሳቸውን የሕይወት ታሪክ በራሳቸው መንገድ መጻፍ እንደሚችሉ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው። ፕሮፌሰር እውነትም አባት መምህር፣ አባት የኔታ መሆናቸውን አሳይተውናል።
ምንም ይሁን ምን አንድ አነጋጋሪ የብእር ሥራ ተነቦና ተበራይቶ ፋይዳው በያንጣሩ እየነጠረ ቢቀርብ፣ ለራስም ሆነ ለሌሎች አብነትነቱ ዋጋ አለው። የኛ ችግር ትናንትም ሆነ ዛሬ (የነገን አናውቅም) ሳናነብ ሳንፈትሸው አንድ ደራሲ የደከመበትን ሥራውን እየዞሩ ባሉባልታ ማብጠልጠል ነው። ቤልጅግ ያሉት ከስልክ ማውጫ በላይ በቤቱ የመጻህፍት ዘር ያልተዘራበትን ጉረኛ ዲያስፖረኛ ፊት ለፊት ማሳፈር እጅግ አስፈላጊ ነው። የንባብ ባህሉን ባዳበረ ህብረተሰብ ውስጥ እየኖርንም እንደመጽሃፍ ማንበብ የመሳሰሉ መልካም ባህሎችን ለማዳበር አለመቻላችን መረገም ነው። እናም ተስፋዬ ምንም ይጻፍ ምን የሚነበብ ደራሲ ነው። ተነቦም እንደየተደርሷችን ልንተቸው፥ ልንወደው ያለያም ልንጠላው መብት ያለን ነጻዎች ነን።
የተስፋዬን ሥራዎች አብዛኞቹን ካነበቡት ተደራሲዎች ጎራ ልትመድቡኝ ትችላላችሁ። ተስፋዬ በነዚህ ላይነንባብ ባበቃቸው ሥራዎቹ አማካኝነት ያማርኛን የሥነ ጽሁፍ ደረጃ በዚህ ዘመን ከፍ ካደረጉ ደራስያን ጎራ የሚያስመድቡት አሻራዎች ጥሏል። በራሱ መንገድ ያጎለበታቸውን ውብ ያጻጻፍ ስልቱን ልንዋብበት ግድ ይለናል። በትረካ ጥበቡ ውስጥ እራሱን እንዳንድ ገራገር ገጸ ባህሪ ዱሎ፣ በራስ ላይ ምጸታዊ ትችትን (satire) ማካሄድን ይሁነኝ ብሎ ተላምዶ እያላመደን መምጣቱን ልብ እንለዋለን።
ተስፋዬ በነዚህ በኢልቦለድ ሥራዎቹ እራሱን እያሳታፈ (ባንደኛ መደብ ትረካ አንጻር) እንደሚያማልለን ሁሉ፣ በእውቀቱ ሥዩም የተባለ አንድ ወጣት ደራሲም እንዲህ ከወደ ሸገር ባጫጭር ልቦለዶቹና በትርክቶቹ (በሦስተኛ መደብ ትረካ/ ሁሉን አወቅ አንጻር) ይህን የራስ ምጸታዊ ትችት አጻጻፍ ስልትንም እያዳበረ መምጣቱን ያስተዋልንም እንኖራለን። ይህ ያጻጻፍ እስታይል ባገራችን እምብዛም ያልተለመደ ከመሆኑም በላይ ብዙውን ጉዳዩን ተሸፋፍኖ ለሆነው ህብረተስባችን እንደስድብም እንደነውርም የሚታይ ነው። ተስፋዬ ደፍሮና ውጦት ያንን ማህበራዊ ደምባችንን (social norms) እየተረማመደ ግልጸትን፥ ቤተኝነትን፥ አብሮነትን ወዘተ… ያሳየናል። ታዲያ የፕሮፌሰር ጌታቸውም “አንዳፍታ ላውጋችሁ” ትንሽ የማይባል የግል የራስን ገመና የመግለጽ ተመሳሳይ ደገኛ አሻራ መጣሉን ሳናሰምርበት አናልፍም።
ሌላው በተስፋዬ የመጨራሻዎቹ ሁለቱ መጻህፍቶቹ ውስጥ የምናየው አዳዲስ የጭብጥ አመራረጥና ያንን ይዞ ወደሚፈልጉት የኢልቦለድ ፋይዳ መድረስን ነው። ይህን የደራሲው ማስታወሻ የተባለን ለናሙናነት ብንወስድ፣ በርካታ ችፍቻፊ ታሪኮችን በሃያ አምስት ክፍሎች ከፋፍሎ አቅርቦት እናገኛለን። አንዱ ክፍል ከሌላው ክፍል ታሪክ ጋር ቀጥተኛ የደምና የሥጋ ትሥሥር ላይኖረው ይችላል። ነገር ግን ዝምድና አለው… ያውም የቅርብና የሩቅ እያልን ልንበልተው የምንችለው። ታዲያ የማያያዣ ሐረጉና የደም ሥሩ “የደራሲው ማስታወሻ” የተባለው ቢጋር ነው!… ይህ ቢጋር አሪፍ በሆነ መልክ እነዚያን ችፍቻፊ ታሪኮች ካራምባም ይሁን ከቆቦ እያመጣ ከገጽ ወደገጽ በፍጥነት እንድንጓዝ ያተጋናል። ደራሲው በመግቢያው ላይ እንዳለውም ሁሉ፣ የቀዳሚ ሥራው “የጋዜጠኛው ማስታወሻ” 2ኛ መጽሃፍ ተብሎም ሊጠቀስ ይችላል። ሁለቱም ያንድ ጸሃፊ “የሕይወት ማስታወሻ – Memoir” መሆናቸው ነው ቁምነገሩ።
ተስፋዬ ፖለቲካዊ ጭብጥ ያላቸውን ጉዳዮች ለሥነ ጽሁፋዊ ፍጆታ በማዋልም የበኩሉን ሚና የሚጫወት ደራሲ ነው። ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በጻፉት የዚህ መጽሃፍ መቅድም ላይ ያስቀመጡትም አስተያየት ለጥቅስ የሚበቃ ነው። “…የፖለቲካን ጉዳይ ለሥነ ጽሁፍ ውበት እንዲገዛ ማድረግ የቻለም አርቲስት ነው…” ሲሉ የመስከሩትን ብዙዎቻችን እንጋራቸዋለን። በዚህ ዓይነት የጭብጥ ምርጫው እነበዓሉ ግርማን እንደቀጸለም ልብ ይሏል። በዓሉ በረዥም ልቦለድ፥ ተስፋዬ ደሞ በታሪካዊ ልቦለድና በኢልቦለድ ሥራዎቻቸው የፖለቲካ ጭብጥ ምርጫቸው ባንድ ጎራ ያሰልፋቸዋል። “የቀይ ኮከብ ጥሪ”ና “አሮማይ” ለበአሉ የፖለቲካ ጭብጥ ምርጫው ተጠቃሽ ናቸው። “የቡርቃ ዝምታ፥ የጋዜጠኛውና የደራሲው ማስታወሻዎች” ወዘተ… ለተስፋዬ ይጠቀሱለታል።
በነገራችን ላይ የዶ/ር ብርሃኑ መቅድም ከፖለቲካ ሰዎች አምባ የፈለቀ ሳይሆን፣ ከዋሸራዎቹ አምደኞች አምባ የተሰነዘረ ሥነ ጽሁፋዊ ትሩፋት ሁኖ አግኝቼዋለሁ። ይህንን ዳጎስ ያለ መጽሃፍ በሚጣፍጥ ያቃቂር ቋንቋ በጥቂት ገጾች ቋጭተው አቅርበውታል። ለነገሩ ያንን ድንቅ የቃሊቲ ማስታወሻቸውን ያነበበ ሁሉ መች ላማርኛ ቋንቋ የገበረ ብእራቸውና ያጻጻፍ ክህሎታቸውን ስልጠት ያጣዋል? እንዴት አድርገው በዚያ የእስር ቤት የስነ ልቡናና የሁለንተናዊ መጨናነቅ ሁኔታ ውስጥ ሁነው፣ ያንን የስከነ መልካም ሥራ እንደሠሩ አስካሁን የብርታታቸው ምስጢር ሊገባኝ አልቻለም። አድናቆቴ ሁሌም ህያው ነው።
ሰው መከራውን፥ እንግልቱን፥ እስሩን፥ ወከባውን፥ ምናልባትም የሞት ቅጣቱን ፍጻሜ እለት ከሕሊናው ውስጥ ላንዴ ገለል አድርጎ፣ እንዲያ ያለ ጥብቅ የፖለቲካ ጭብጥ ያለው መጽሃፍ የመጻፉ ብርታት ሁሌም ያስደንቀኛል። እንዲህ እንደሳቸው ያለው ሽሽግ ብእርተኛ ሲመቸው ሲመቸው ብቅ እያለ የብእር እንጎቻውን ቢያቃምሰን መልካም ነው። ይህን መስሉን የበስለ ብእርተኛ ወግ ካየሁባቸው የሌላ ሌላ ሙያ ቤተኞች መካከል ጠበቃ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ ታይኔ ሳይገቡ አልቀሩም። “አባቴ ያቺን ሰዓት” በተሰኘው ሥራቸው ተጠቅሻለሁና፣ አንድ ቀን ሳልመለስባቸው የምቀር አይመስለኝም። እስቲ ሁሉም በያሉበት ይበርቱ!
ወደ ተስፋዬ ሥራ ልመለስ። ተስፋዬ በነዚህ በተለያዩ የታሪክ አንጓዎች የታደሙ ሥራውን የራሱን የፖለቲካ አተያይ፥ የሕይወት ፍልስፍና፥ ደስታና ሃዘን ወዘተ… አካቶባቸዋል። አንባቢ ሊቀበላቸው ያለያም ላለመቀበል አሁንም የተደራሲነት ነጣነቱ እንደተጠበቀ የሚቆይ ነው፡፡ ይልቅስ በዚህ ሥራው ላይ እነዚህን ሃያ አምስት ክፍል ትርክቶቹን ያስጌጠባቸው አዳዲስ ዘይቤዎቹ ሳይታወሱ መታለፍ የለባቸውም። እነሱን ለሥነ ጽሁፋዊ ፋይዳቸው ሲባል መፈትሸም ማገላበጡም የተስፋዬን ብእር ትባት እስከምን ምን ደረጃ ድረስ እየሄደ እንዳለ ለማስተዋል ይመቻል።
ተስፋዬ በዚህ አዲስ ሥራው ላይ አዳዲስ ዘይቤዎችንና ያገላለጽ ጥበባትን እንደምሽት ከዋክብት በየምእራፉ ላይ ፈነጣጥቆልናል። ሥራውን ይበልጥ ተነባቢና ማራኪ አድርጎበታል። አንድ ደገኛ ደራሲ ሁሌም ባዳዲስ ሥራዎቹ ላይ ማሳየት ያለበትን አዲስ ያጻጻፍ ጥበብንና ብልሃትን ተስፋዬ ነቄ ያለበት ይመስላል። ስለዚህም የተስፋዬ መጽሃፍት አንባቢያን ቁጥር መበርከቱ፣ ከሚያነሳቸው አንኳር ጭብጦች ባሻገር፣ ያጻጻፍ ችሎታው ሃያልነትና ማራኪነት እንደሁ መካድ እራስን ማቃቄል ነው።
“መገማሸር” የተሰኘው ዓይነት ከቶም ያልተለመደ ድንቅ አገላለጽ ተስፋዬ ለሚመርጣቸው ቃላት ጭምር ቀናኢ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል። ዱር ለዱር፥ አምባ ላምባ ሂዶ ተስማሚ ዘይቤን፥ ቃላትን፥ ብሂልን… እያደነ ለሥነ ጽሁፋዊ ሥራው ፋይዳ እንደምን እንደሚጠቀምበት በግልጽ ይስተዋላል። ይህን ከላይ የተጠቀሰውን ቃል (የዚህ መጣጥፍ ጸሃፊ እስከሚያውቀው ድረስ) ካገራችን አንጋፋ ደራሲያን መካከል አንድ ሰው ብቻ ነበር ባንዲት ግጥሙ ላይ የተጠቀመበት። ተስፋዬም የወያኔ ምርኮኛ በነበረበትና በረሃ ሳለ ካንድ ያዲስ ዘመን ቁራጭ ጋዜጣ ላይ “እንደ ታይዶንግ ወንዝ እንገማሸር” የምትለዋን የግጥሟን ሃረግ መተዋወቁን አንድ ወቅት ላይ ለወዳጆቹ ሲያወራ መደመጡን ይህ ጸሃፊ ያስታውሳል። እናም የዚህ ዓይነቱ ቅቡል ተደራሲነቱ ለብእሩ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገለት ማስተዋል ይቻላል።
ተስፋዬ አንዳንዱ ገለጻው የሥነ ግጥምን ያህል ምስል ፈጥሮ ሁነቶችን ጠልቀን እንድናስተውል ያደርገናል። ““…አገዳ ማኘክ የማይችሉ መስታወት የመሰሉ ንጹህ ጥርሶች አሉት (ገጽ 136)… …ስትራመድ ተገልብጣ በጅ የምትሄድ ነው የምትመስል (ገጽ 179)… ኢትዮጵያዊቷ አንጄላ ዴቪስ ለዋለልልኝ የተተኮሰውን ጥይት በደረቷ ተቀበለችው…” (ገጽ 263)… እነ ክንፈ ኦህዴድ የተባለውን ድፎ ዳቦ እየጋገሩ ነበረ (ገጽ 327)… “ እያለ ባዲዲስ ዘይቤዎችና ያገላለጽ ለዛዎች ከገጽ ወደ ገጽ ያገማሽረናል።
እንዲህ ወደ “ወርቃማ ዓመታት” ብሎ ወደ ሰየመው ምእራፍ ጓዳ ውስጥ ስንርመሰመስ ደግሞ አንድ ከተስፋዬ ገጠመኝ የምንማረው ነገር አለ። ደራሲ የመሆንም ሆነ ሆኖ የመገኘት ሕልምን ከማውጠንጠን ሰመመን ያወጣውን አጋጣሚ እናነባለን። ያቺ የመንትዮች እህት ያቶ እውነቱ (የሰብእና ምስላቸው ምንጊዜም እንዳይረሳኝ ውስጤ ተስሎብኛል) ልጅ ምን ያህል እንዳስጠበበችው፥ እንዳስገዘጠችው፥ እንዳስደገሰችው፥ እንዳስደገደገችው፥ እንዳስካነችው ብላም ወደ ብእርተኝነት ጎራ አጉራ እንዳስጠናችው እናስተውላለን። የፍቅር ይሁንታ ለማግኘት እሷኑ እየሳለ መልሶ ለሷዋው እያሳዬ ልቧን ሊያሸፍተው ሌት ተቀን መትጋቱን ልብ እንላለን። ብርቱ ተማሪ ማለት ይሄ ነው፡፤ በፈተና ውስጥ የሚያልፍና በብእር ጫፍ ላይ ቁሞ ዓለምን የሚማትር….
“መጻፍ እንዴት ደስ ይላል? ለመሆኑ የመጻፍን ያህል የሚያረካ ነገር ይኖር ይሆን?
“ወፍራም መጽሃፍ!
“ቶልስቶይ እንደሚጽፈው፤ አንደ በዐሉ ግርማ! እንደ ጸጋዬ ገብረ መድህን ቅኔዎችን መቋጠር፣ ድምቢጥ ወፍ የመሳሰሉ ውብ ቃላት (አቤት ያንተ ያለህ…ከየት ነው የምትፈለፍላቸው ተስፉ?) እንደ ቀጫጭን ጅረቶች፥ ጋዣውን እያስተኙ እንደሚጓዙ…
“እንዲያ እያልኩ አልም ነበር።”” ገጽ 106/107 (በቅንፍ ያለው ከራሴ)
ይህን ከላይ የጠቀስኩትን እንደወስከምባይ ወስዳችሁልኝ፣ “ትኩረት መሳብ ከቻልኩ በሚል በየቀኑ አንድ አጭር ልቦለድ (?) በመጻፍ ልጅቱን ለመማረክ ስቃይና ፍዳ መቀበል ጀመርኩ። “ (ገጽ 101) የሚለውን የቀዳሚ ገጹን ኑዛዜ ደሞ እንደመሶቡ ውሰዱልኝ። የተስፋዬና የሥነ ጽሁፍ አድባር መገጣጠም እንዲህ እንደወስከምባዩና እንደመሶቡ ልከኛ አገጣጠም በዚያች የደብረዘይት ቆንጆ አዚም አማካኝነት እንዴት እንደጎመራ እናስተውላለን። ድንቅ ገጠመኙን ውብ በሆነ ትረካ እራሱን አንስቶ እየጣለ እስከ ላንዳፍታ እብደት ድረስ እንዴት እንደተጓዘ ያወጋናል። የነብር ጭራን እንደያዘ ሁሉ በርትቶ ገፍቶም ያ የትናንቱ እራሱን ጅላጅል እያለ የሚተርብ የሆራ ልጅ ዛሬ የሁላችንም መታደሚያ ባለጉዳይ ሆኖናል። ወይም አኛ ባለጉዳይ ሆነን የሱን ደጃፍ እያንኳኳን ነው እንበል።
ይሄ እንደስሙ ሁሉ ተስፋ የሚጣልበት ደራሲ እውነታን ስንቁ አድርጎ፣ ጥላቻንና መለያየትን በሕዝቦች መሃል የሚያጓስሩ ያለያም የሚያሟጅሩ ጭብጦችን እየገደፈ ከተጓዘ፣ ተስፋዬ ዓይነተኛ ደራሲ ሁኖ የማይዘልቅበት ምክንያት የለም። በልጅነትና፥ ባልበሰለ የሕይወት ገጠመኝ ዙሪያ የምናነሳቸውና የምንጽፍባቸው ጭብጦች ምን ያህል በተደራሲያን ዘንድ እንደሚያንገጫግጩን ከተስፋዬ የተሻለ የተማረ ያለ አይመስለኝም። ሕይወትን ከነምናምንቴዋ (ይቅርታችሁ ይቸረኝና ከነንፍጥዋ ጭምር ማለትን እደፍራለሁ) አውቆ መጻፍና በድፍረት ብእርን ማንሳት እጅግ የተለያዩ ግባቶች ናቸው። እናም ተስፋዬ ደገኛውን ትምህርት ሁሉ ወስዶ በወዲያ ወዲያኛው ሥራዎቹ ሁሉ የሚያረካንና ያማርኛ ሥነ ጽሁፋችንን ደረጃ የሚታደግ የበኩሉን ድርሻ እንደሚያበረክት ጥርጥር የለኝም። “እንዴት?” ቢሉ… ተስፋዬ የተገማሻሪ ብእር ጌታ ነውና ነው… መልሱ።
Hi, thank you Yager lidj. I have enjoyed your commentary. Wawooooooooooo!