Melotica: Terrorism Ethiopian Style (አሸባሪ ያልሆናችሁ እጃችሁን አውጡ? መሎቲካ!)
ምን ሆንን? አንድም ማኅበረሰቡ ትልቅ ቀውስ ውስጥ ነው፤ አለዚያም ለወንጀል የተሰጠው የሕግና የፖለቲካ ትርጉም ከመሠረታዊ የሰውል ልጅ መብት፣ ፍላጎትና ባሕርይ ጋራ የሚቃረን ነው። የኢትዮጵያው ቀውስ ምክንያት ወንጀል በዘፈቀደ የሚተረጎም ከመሆኑ የሚመነጭ ነው። ጋዜጠኛ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ የሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አባል፣ የ“ሕገ” ወጥ ፓርቲ አባል፣ ከገዢው ቡድን ጋራ ጥቂት እንኳን የሐሳብ ልዩነት ያለውና ይህ “ወንጀሉ” የተደረሰበት፣ የኢሕአዴግ አባል አልሆንም ያለ፣ አዋጣ የተባለውን ገንዘብ ያላዋጣ፣ ውጭ ሆኖ በተቃውሞ የሚጽፍ ወይም የሚናገር ወዘተ. ሁሉ እንደወንጀል የሚያስከስስ ሆኗል፤ ወይም ብዙዎች እንደዚያ እንዲያምኑ የሚያስገድድ ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህ ምን አይነት ፖለቲካ ነው? ምን አይነት ዴሞክራሲ ነው? ምን አይነት አገር ነው? ፖለቲካው “መሎቲካ” ይባላል (መልቲ ፖለቲከ ወይም የመለስ ፖለቲካ)፤ ዴሞክራሲው “አብዮታዊ ዴሞክራሲ”።
በደንበኛው የሕግ ፍልስፍና ማንም ሰው በሕግ እና በተገቢው የሕግ ተርጓሚ አካል (ፍርድ ቤት) እስካልተረጋገጠበት ድረስ ወንጀለኛ እንዳልሆነ ይቆጠራል። እንዲህ ያለውን፣ ሕግ በንጹሕነቱ የሚያውቀውን ሰው መጠርጠር ብቻ የሰውየውን ንጹሕነት አያሳጣውም። የተጠረጠረውን ሰው ወንጀለኝነት፣ ከጥርጣሬ በላይ ሊያስረዳ በሚችል ማስረጃ የማረጋገጥ ሸክሙ የሚወድቀውም በከሳሽ ላይ ነው። ስለዚህ ዜጎች ያለፍርሐት፣ ያለስጋት ሕይታቸውን ይገፋሉ። የሚፈሩት፣ የሚሰጉት ጥቂት ወንጀለኞች ናቸው።
ይህ ግን በሁሉም ቦታና ጊዜ የሚሠራበት መርሕ አይደለም። በአንዳንድ አገሮች መርሑ የሚሠራው በተገላቢጦሽ ነው። “ማንኛውም ሰው ንጹሕ መሆኑን፣ ወንጀል አለመፈጸሙን ከጥርጣሬ በላይ ሊያስረዳ በሚችል ማስረጃ እስካላስረዳ ድረስ ወንጀለኛ ነው” እንደማለት። በዚህ መርሕ በሚተዳደር ማኅበረሰብ ዜጎች በወንጀለኝነትና በንጹሕነት መካከል ያለውን መስመር በእርግጠኝነት አያውቁትም፤ ስለሆነም ዘወትር በሰቀቀን፣ በፍርሃት ይኖራሉ። ሲብስም መኖር በራሱ የወንጀለኝነት ምንጭ/መነሻ ሆኖ ይሰማቸዋል። ብልቃጥ ውስጥ እንዳለች አይጥ መኖራቸውን ከብልቃጡ ለመውጣት ካላቸው እድል ጋራ ብቻ ለማቆራኘት ይገደዳሉ። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ በዋናነት በሥራ ላይ የሚገኘው ይህ የኋለኛው መርሕ ይመስላል።
ዛሬ ዛሬ “አሸባሪው ማነው?” ብሎ ከመፈለግ ይልቅ “አሸባሪ ያልሆነው ማነው?” ብሎ መጠየቅ የሚቀል ሆኗል። አንድ ወዳጄ ሕይወት “አንድ እግር መርካቶ፣ አንድ እግር ቃሊቲ” ሆኗል ሲል የዘመኑን ኑሮ ገልጾልኛል። ዜጎች እንዲህ ብለው እንዲተርቱ የሚያደርጋቸው የሕይወት እውነታቸው ነው። ብዙ ዜጎቹ ወንጀሎች የሆኑበት ወይም “ወንጀለኞች ናቸው” ተብሎ የሚታሰብበት ማኅበረሰብ ጤናማ ማኅበረሰብ ሊሆን አይችልም። በዚህ ሞድ (አንድ እግር መርካቶ፣ አንድ እግር ቃሊቲ) የሚኖር ዜጋ በነጻነት ሥራው ማከናወን፣ መፍጠር ወዘተ አይችልም።
ምን ሆንን? አንድም ማኅበረሰቡ ትልቅ ቀውስ ውስጥ ነው፤ አለዚያም ለወንጀል የተሰጠው የሕግና የፖለቲካ ትርጉም ከመሠረታዊ የሰውል ልጅ መብት፣ ፍላጎትና ባሕርይ ጋራ የሚቃረን ነው። የኢትዮጵያው ቀውስ ምክንያት ወንጀል በዘፈቀደ የሚተረጎም ከመሆኑ የሚመነጭ ነው። ጋዜጠኛ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ የሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አባል፣ የ“ሕገ” ወጥ ፓርቲ አባል፣ ከገዢው ቡድን ጋራ ጥቂት እንኳን የሐሳብ ልዩነት ያለውና ይህ “ወንጀሉ” የተደረሰበት፣ የኢሕአዴግ አባል አልሆንም ያለ፣ አዋጣ የተባለውን ገንዘብ ያላዋጣ፣ ውጭ ሆኖ በተቃውሞ የሚጽፍ ወይም የሚናገር ወዘተ. ሁሉ እንደወንጀል የሚያስከስስ ሆኗል፤ ወይም ብዙዎች እንደዚያ እንዲያምኑ የሚያስገድድ ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህ ምን አይነት ፖለቲካ ነው? ምን አይነት ዴሞክራሲ ነው? ምን አይነት አገር ነው? ፖለቲካው “መሎቲካ” ይባላል (መልቲ ፖለቲከ ወይም የመለስ ፖለቲካ)፤ ዴሞክራሲው “አብዮታዊ ዴሞክራሲ”። አገሩን ታውቁታላችሁ::
የስታትስቲክስ ባለሥልጣን ወንጀለኛ ያልሆኑት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ስንት እንደሆነ ሊነግረን ይችላል? (ለመቁጠር እንዲቀለን) እስቲ ወንጀለኛ፣ አሸባሪ ያልሆናችሁ ወይም አሸባሪ/ወንጀለኛ ልትባሉ እንደማትችሉ በእርግጠኝነት የምታምኑ እጃችሁን አውጡ! You are a terrorist or potential terrorist till proven innocent!
Mesfin Negash
What is this anti-terrorism Hype?
It appears that you people are living on your nerves
I can’t stress enough but there is a sort of organized counter offense on the new proclamation anti-terrorism law.
Mesfin you are more than welcomed to join this organization.
Helloooooo, I got you, you went extra mile to cut the cheese in the middle, leaving the terrorism danger and act in Ethiopia unaddressed.
But the good thing, this inflated and misleading claim against the law is shambolic by any sort of measurement and any sensible citizen of Ethiopian will consider your claim as useless idea. Sorry you have few things to say here
Nice one, Mesfine.
Keep it up!