መንግሥት በእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጉዳይ “ሽምግልና” ጀመረ

ከጊዜ ወደጊዜ ከሙስሊም ምእመናን የሚደርስበት ተቃውሞ ሞልቶ መገንፈል የጀመረውን “የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት” (መጅሊስ) ለመታደግ መንግሥት “ሽምግልና” መጀመሩ ተሰማ። በዛሬው ዕለት በመጅሊሱ መሪዎች እና ሰፊውን ምእመን ይወክላሉ በተባሉ ጊዜያዊ ወኪሎች መካከል ሊደረግ የነበረው ውይይት ሳይካሄድ ቀርቷል።

ዛሬ ረቡዕ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ በሽፈራው ወልደማርያም እና በሚኒስትር ጁነዲን ሳዳ አወያይነት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ንግግር ሳይጀመር የቀረው በምን ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም። ሆኖም በተደራዳሪዎቹ በኩል ማለትም በመጅሊሱ እና በአዲሱ የተወካዮች ቡድን መካከል እውቅና የመስጠት ጉዳይ ሳይነሳ እንዳልቀረ አንድ ምንጭ ጠቁመዋል።

(ሩቂያ ሰ./ አዲስ ነገር ኦንላይን)

በአወሊያ ትምህርት ቤት በተነሣውና በመጅሊሱ ጣልቃ ገብነት ተፈጠረ በተባለው አለመግባባት የተለኮሰው የተማሪዎች ተቃውሞ እየሰፋ ሔዶ ብዙኀኑ ሙስሊሞች መጅሊሱ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ያላቸውን ጥያቄ ወደ ማንጸባረቅ መሸጋገሩ ይታወሳል። ከወር በላይ ባስቆጠረው በዚህ ሕዝባዊ ተቃውሞ ምእመናኑ በሳምንታዊው የዓርብ ጸሎት ወቅት ከወትሮ በተለየ በመሰባሰብ ይህንኑ ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። የምእመናኑ ዋነኛ ጥያቄም ምክር ቤቱ/መጅሊሱ በአመራሩ የመንግሥት የፖለቲካ መጠቀሚያ ሆኗል፣ የምእመናንን ፍላጎትና ጥያቄ መወከል አይችልም፣ አመራሮቹም በሕዝብ የተመረጡ ሳይሆኑ በፖለቲካ ጫና የተቀመጡ መሆናቸውን የሚመለከት ነበር። ምእመናን መሪዎቻቸውን የመምረጥ መብታቸው እንዲከበር እና የመጅሊሱ አመራር እንዲቀየር ሲጠይቁ ሰንብተዋል። ለጊዜው ጉዳዩን ችላ ያሉ ለመምሰል የሞከሩት መጅሊሱ እና መንግሥት ጥያቄውን “የአክራሪዎች ነው” በማለት ለማጣጣል ቢሞክሩም በመጨረሻ “ሕዝቡን ለማነጋገር” መወሰናቸውን ለመረዳት ተችሏል። ሆኖም፣ መንግሥት ጉዳዩን አብዛኛው ሙስሊም በሚፈልገውና መሠረታዊ የመብትና የሕግ ጥያቄዎቹን በሚመልስ መልኩ ለማስተናገድ ይወስን ወይም እንደተለመደው ነገሩን የማድበስበሻ ስልት ፍለጋ ከወዲሁ አልታወቀም።

መንግሥት ከወራት በፊት “አሐበሽ” የተባለውን አስተምህሮ ከተቀሩት የእስልምና አስተምህሮዎች መርጦ፣ በሃይማኖቱ መምህራን ላይ ለመጫን ያደረገው ሙከራ ከፍተኛ ተቃውሞና ውጥረት ፈጥሮ መሰንበቱ ይታወቃል። “ይህን ውጥረት ለማርገብ የሚያስችል አንዳችም ምልክት በመንግሥት በኩል አልተሰጠም” ብለዋል አንድ ታዋዊ የሃይማኖቱ ቃዲ ለአዲስ ነገር ሪፖርተር። ይህ ውጥረት ባለበት፣ በኢሕአዴግ ካድሬዎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ እንደሚመራ የሚታማው ምክር ቤት በአወሊያ ትምህርት ቤት አስተዳደር ጣልቃ በመግባት የፈጠረው አዲስ ቁጣ ነገሩን እንዳባባሰው በርከት ያሉ ምእመናን ያምናሉ። ይህም ሲብላላ የቆየው የመጅሊሱ ሕጋዊነትና ተቀባይነት ጥያቄ የአደባባይ ጥያቄ እንዲሆን አድርጎታል። በመጅሊሱ ላይ ቅሬታ ያላቸው የሃይማኖቱ ተከታዮች በተለያየ ጊዜ ተቃውሞዋቸውን እና መፍትሔውን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ለሚመለከታቸው ሁሉ ቢያቀርቡም ሰሚ ሳያገኙ መቆየታቸውን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የአዲስ ነገር ምንጮች ጠቁመዋል።

በመጅሊሱ መሪዎች እና በተወካዮቹ ኮሚቴ መካከል ሊደረግ የነበረው የዛሬው ውይይት አጀንዳ ምን እንደነበረ ባይታወቅም የካቲት 5 ቀን በድጋሚ ለመገናኘት ቀጠሮ መያዙን ለማወቅ ተችሏል።

No comments yet... Be the first to leave a reply!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

Bad Behavior has blocked 1470 access attempts in the last 7 days.