ማሃሙድ ጋ ጠብቂኝ! [ክፍል ሁለት]
በየትያትር ቤቶች እጅህ እስኪቀጥን ያጨበጨብክለት ድርሰት የተፈጠረው ዶሮ ማነቂያ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡ የድርሰቱ ቃለ ተውኔት የሚሸመደደውም በእነ “መካ ቤት” የጫት ጉዝጓዝ ላይ ነው፡፡ ደግሞ አርቲስት ብቻ አይምሰልህ የዶሮ ማነቂያን መታወቅያ የወሰደው፡፡ የተማሩና የተመራመሩ፣ ኢትዮጵያ ጨረቃ ላይ ከወጣች መወጣጫ መሰላሉን ያዋቅራሉ የሚባሉ ምሁራን ተራ ሰው መስለው ዶሮ ማነቂያ ይሽሎኮሎካሉ፡፡ ማን መሆናቸውን የምታውቀው ግን ከእነርሱ ጋር ለማውራት እድሉ ሲገጥምህ ብቻ ነው፡፡ እውቀታቸው መሬትን ከሰማይ ይደባልቃል፡፡ እነርሱ ግን ከዶሮ ጋር አባሮሽ ይጫወታሉ፡፡
ዶሮ ማነቂያ ሺሻና ጫት ቤቶቿ በየጊዜው በዘመቻ ይታሸጉባታል፡፡ በዚያ ስታልፍ በቤቶቹ በር ላይ በቀይ ቀለም “ታሽጓል” የሚል ጽሑፍም አንብበህ ይሆናል፡፡ ግን እውነት የታሸገ እንዳይመስልህ፡፡ በጀርባ በኩል መስኮት የሚመስል በር አለው፡፡ የቤቱ ደንበኞቹ ብቻ ናቸው በር መሆኑን የሚያውቁት፡፡ ቀበሌዎችን ለማዘናጋት ዶሮ ማነቂያዎች የፈጠሯት መላ ናት፡፡

(መሀመድ ሰልማን)
ዶሮ ማነቂያ
በዶሮ ማነቂያ ዶሮ አይታነቅም፡፡ ሰው ግን ይታነቃል፡፡ለምሳሌ ኑሮ አልሞላ ሲለው፤ ወይም ዶሮ እጅግ አምሮት መግዣ ሲያጣ…ኑሮን ቀለል አድርገው መኖር የሚሹ ዜጎች ዶሮ ማነቂያን ይመርጣሉ፡፡ አንተም ኪስህ ቢነጣ፣ መሄጃ ብታጣ ፒያሳ እንደ ቦሌ “ሂድ ከዚህ!” ብላ ውሻ አታደርግህም፡፡ ቦሌ ብዙ ፎርጅድ የቦሌ ልጆች እየተሳቀቁ የሚስቁባት ሰፈር እንደሆነች ልንገርህ፡፡ ፒያሳ ግን 32 ጥርስና 12 ጥርስ ያላቸው ዜጎች እኩል የሚስቁባት ቦታ ናት፡፡ “የቦሌ ልጅ የለውም አባይ” ሲባል ሰምተህ ይሆናል፣ የፒያሳ ልጅ ደግሞ የለውም ፎርጅድ፡፡ ድሃና ሀብታም እየተጋፉ የሚዝናኑባት ድንቅ ስፍራ፡፡ ከብሪቲሽ ካውንስል ጀርባ እንደ ፍልፍል ሹልክ እያሉ የሚወጡ ልብን ወከክ የሚያደርጉ ቆነጃጅትን ዐይተህ ይሆናል፡፡ ቤታቸውን ብታየው ትገረማለህ፤ ኩሽና ነው፡፡
ለነገሩ ድፍን አዲስ አበባ ውስጥ ብትዞር ከፎቅ ጀርባ ፎቅ አታገኝም፡፡ በቅርቡ የተወለዱትን ቦሌ መድኀኔዓለምንና አዲሱን ካዛንቺስን ትተህ እግርህ እስኪቀጥን ብትዞር በአዲሳባ ከፎቅ ጀርባ ፎቅ አታገኝም፡፡ካላመንክ እንወራረድ፡፡ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የፎቅ ጥቅም በስንት እንደሚከፈል ታውቃለህ? በሁለት ካልክ ትክክል ነህ፡፡ የመጀመርያው የፎቁ ባለቤት ብ…ዙ መስታወት እንዳለው ማስመስከር ሲሆን ሁለተኛውና ዋነኛው ግን ከፎቁ ጀርባ ያለውን ገመና መሸፈን ነው፡፡ ገመና ስልህ የሰፈሩ ወይም የፎቁ ባለቤት ገመና ሊሆን ይችላል።
ይህ ካልገባህ ሂድ ቦሌ፡፡ የአገርህ ቴሌቪዥን የሚኮራባቸው እነ “ሸራተን” እነ “ደምበል”፣ እነ “ጌቱ ኮሜርሻል”፣ እነ “አበሩስ” ጀርባ ማንም ሳያይህ ግባ፡፡ ትበረግጋለህ፡፡ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ፎቆችን ታከብራለህ፡፡ ፎቆች ለአገርህ የዋሉት ውለታ እየታሰበህ ዕንባህ በዐይንህ ግጥም ይላል፡፡ “አገሬ ኢትዮጵያ ተራራሽ አየሩ፣ ፏፏቴሽ ይወርዳል በየሸንተረሩ፣ ልምላሜሽ ማማሩ” የሚለው ዘፈን ለምን ፎቆቹን ገሸሽ እንዳረገ አይገባህም፡፡
ቆራጡ መንጌ ፎቅ አልደርስልህ ሲለው አይደል እንዴ ወሎ ሰፈር ሎሊ ህንፃ ፊትለፊት ያሉትን ገመናዎች በግንብ ፕላስተር የጋረዳቸው? መሌ እሳቱ ግን ረጋ ብሎ አሰበ “ችግሩን መቅረፍ ያለብን ከምንጩ ነው” አለ፡፡ ጭርንቁስ ሰፈሮችን ቡልዶዘር ላከባቸው፡፡ የተማረ ይግደለኝ!!
ፒያሳ ፎቅ አልባ ናት፡፡ በእርግጥ የቀድሞው የአገሪቱ ሰማይ ጠቀሱ ሕንጻ “አራዳ” አራዳ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ በእርግጥ በጃንሆይ ጊዜ 8 ሚሊዮን ብር የተከሰከሰበት የማዘጋጃ ቤት ሕንጻ ደረቱን ነፍቶ የቆመው በፒያሳ እምብርት ነው፡፡ ግን ፒያሳ ከነቦሌ ጋር ስትነጻጸር ብዙ ፎቆች አሏት ለማለት አያስደፍርም፡፡ ስለዚህ ፒያሳ ብዙ ፎቅ ከሌላቸው የምስራቅ አፍሪካ ሰፈሮች አንዷ ናት ብለን መናገር እንችላለን፡፡
ፒያሳ ፎቅ አልባ ናት ካልን “ገመናዋን ማን ሸፈነላት?” የሚለው ጥያቄ ይከተላል። መልሱ ቀላል ነው፤ ወርቅ ቤቶች፡፡ በፒያሳ ወርቅ ወርቁን ስታይ ከጀርባ ምን እንዳለ ትረሳለህ፡፡ በፒያሳ ቆንጆ ኮረዶች ሽው እልም ሲሉ ስታይ ማሰቢያህ ይሰለባል፡፡ ደፈር ብለህ አንዷን የፒያሳ ቆንጆ ዳሌ ዳሌዋን እያየህ ብትከተላት ግን በብሪትሽ ካውንስል ወይ በአምፒር ወይ በሠራተኛ ሰፈር ቀጭን መንገድ ውስጥ ትገባለች፡፡ መጨረሻዋን ልይ በለህ ትከተላታለህ፤ እስከ ውስጥ፡፡ ድንገት ትሰለብብኻለች፡፡ በዚህ ቅፅበት ምን ሰወራት ብለህ ለራስህ ስታንሾኳሽክ ከጭርንቁስ ቤቷ ወጥታ “ምን አልክ?” ልትልህ ትችላለች፡፡ ስለዚህ የፒያሳ ልጅ አትከተል፡፡ ከተከተልክም እጇን ይዘህ ተከተላት።
ቆንጆ የፒያሳ ልጅ ጠብሰህ ተሳክቶልህ ያውቃል? እንግዲያውስ ልሸኝሽ አትበላት፡፡ ትቀየምኻለች፡፡ “ለምን?” ብለህ ከጠየከኝ ልጅቷ አምልጣሃለች።
ኢትዮጵያዊ ጨዋ፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ያደረበት፣ የሰው የማይመኝ ሕዝብ እንደሆነ ለመመስከር ፒያሳ በቂ ናት፡፡ ፒያሳ የሚገኝን አንድ ቱባ ወርቅ ቤት በህሊናህ አስብ፡፡ ከጀርባው ያለውን ቤትና ቤተሰቡንም ለማስታወስ ሞክር፡፡ ትገረማለህ፡፡ የኋለኛው ቤት ባለቤትና አስራምናምን ልጆቹ ወርቅ ቤቱን ሰርስሮ ስለመግባት አስበው አያውቁመም፡፡ የሸዋ ዳቦ በልተው ሆዳቸውን እያከኩ ወርቅ ቤቱን ተደግፈው ኅብረ-ትርዒት እያዩ ይተኛሉ፡፡
ወርቅ ቤቶችን ከተደገፉ ቤቶች በአመዛኙ የሚገኙት በዶሮ ማነቂያ ነው፡፡ በመሆኑም ለዶሮ ማነቂያ ክብር ስንል ሰፈሩን በዶሮ በረር እንቃኛለን፡፡
ሂድ ዶሮ ማነቂያ፡፡ ውስጥ ውስጡን፡፡ ፒያሳን ፒያሳ ያደረጋት አንዱ ሀብቷ ምን ይመሰልሃል? ዶሮ ማነቂያ ነው፡፡ በሃያ ብር 24 ሰዓት ቀብረር ብለህ የምትኖርባት ጉደኛ የፒያሳ ጓዳ፡፡ በቸርነቷ የሚስተካከሏት “አራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ሰፈር” እና “አውቶብስ ተራ” ብቻ ናቸው፡፡ እስኪ ለአፍታ የዶሮ ማነቂያን ድርሳን እንግለጥ፡፡
መቼ ለታ ዶሮ ማነቂያ ሄድኩ፡፡ ኪሴ ማፍሰስ ስለጀመረ ሰፈሩን ከሞሉት ማዘር ቤቶች ወደ አንዱ ጎራ አልኩኝ፡፡ ሁሉም የምግብ ዝርዝሮች የቤቱ ግድግዳ እየተፋቀ ተጽፈዋል፡፡ የምግቦቹ ዋጋ ከ10 ብር እንዳይዘል ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጓል፡፡ ለምሳሌ “ጥብስ 9ብር ከ75 ሳንቲም” ይላል፡፡ በዚህ ድንቅ ቤት ድንቅ ምሳ በልቼ ልወጣ ስል እንዲህ የሚል ጽሑፍ ከበሩ የውሰጠኛው ክፍል አነበብኩ፡፡ “ቅሬታዎን ለኛ፣ አድናቆትዎን ለጓደኛ!!” በመጨረሻም ተመጋቢዎቹ ከቤቱ ከመውጣታቸው በፊት ከተሰነጣጠቀው የቤቱ ግድግዳ ቀጭን እንጨት ሲመዙ አየሁ፡፡ ስቲኪኒ መሆኑ ነው፡፡ ሲሉ ሰምታ ዶሮ ታንቃ ሞተች!
ሂድ ዶሮ ማነቂያ፤ እነ “መካ ቤት”፣ እነ “ሸመሱ ቤት”፣ እነ “ኑሪያ ቤት”፣ እነ “ቦስ ሺሻ ቤት”፡፡ በቴሌቪዥን ተንሰፍስፈህ የምታያቸው አርቲስቶች አንድ ጥግ ይዘው በነጻነት ሲጋራቸውን ሲያቦኑት፣ በርጫቸውን ቦርጫቸው ላይ አስቀምጠው ሲበርጩት ትመለከታለህ፡፡ ከዚህ ስፍራ ማንም ፈርሙልኝ አይላቸውም፡፡ ማንም አይቁለጨልጭባቸውም፡፡ እነርሱን ከዶሮ አስበልጦ የሚያያቸው ሰው በድፍን ዶሮ ማነቂያ አታገኝም ፡፡ ስለዚህ ነጻነታቸውን ለመጎናጸፍ ዶሮ ማነቂያን መረጡ፡፡ እርሷም የነጸነት መሬታቸው ሆነች፡፡
በየትያትር ቤቶች እጅህ እስኪቀጥን ያጨበጨብክለት ድርሰት የተፈጠረው ዶሮ ማነቂያ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡ የድርሰቱ ቃለ ተውኔት የሚሸመደደውም በእነ “መካ ቤት” የጫት ጉዝጓዝ ላይ ነው፡፡ ደግሞ አርቲስት ብቻ አይምሰልህ የዶሮ ማነቂያን መታወቅያ የወሰደው፡፡ የተማሩና የተመራመሩ፣ ኢትዮጵያ ጨረቃ ላይ ከወጣች መወጣጫ መሰላሉን ያዋቅራሉ የሚባሉ ምሁራን ተራ ሰው መስለው ዶሮ ማነቂያ ይሽሎኮሎካሉ፡፡ ማን መሆናቸውን የምታውቀው ግን ከእነርሱ ጋር ለማውራት እድሉ ሲገጥምህ ብቻ ነው፡፡ እውቀታቸው መሬትን ከሰማይ ይደባልቃል፡፡ እነርሱ ግን ከዶሮ ጋር አባሮሽ ይጫወታሉ፡፡
ዶሮ ማነቂያ ሺሻና ጫት ቤቶቿ በየጊዜው በዘመቻ ይታሸጉባታል፡፡ በዚያ ስታልፍ በቤቶቹ በር ላይ በቀይ ቀለም “ታሽጓል” የሚል ጽሑፍም አንብበህ ይሆናል፡፡ ግን እውነት የታሸገ እንዳይመስልህ፡፡ በጀርባ በኩል መስኮት የሚመስል በር አለው፡፡ የቤቱ ደንበኞቹ ብቻ ናቸው በር መሆኑን የሚያውቁት፡፡ ቀበሌዎችን ለማዘናጋት ዶሮ ማነቂያዎች የፈጠሯት መላ ናት፡፡
ዶሮ ማነቂያ የራሷ መግባቢያም አላት። ለምሳሌ በዶሮ ማነቂያ “ዛሬ የፈረንሳይ ምርጥ ካራቴ ይታያል!” የሚል ማስታወቂያ አንብበህ ይሆናል፡፡ የፒያሳ ልጅ ካልኾንክ ግን ይህ ምን እንደኾነ አይገባህም፡፡ የወሲብ ፊልም ማስታወቅያ ነው፡፡
የሰፈረህ አውራ ዶሮ በቤትህ ጓሮ ሄዶ ሴት ዶሮህ ላይ ቂብ እንደሚለው ሁሉ በዶሮ ማነቂያም ሰዎች እንደዚያ ሲያደርጉ በቴሌቪዥን ታያለህ፡፡ ያለ ምንም ሐፍረት፤ ያውም ሻይ እየተፈላልህ፤ ያውም ለውዝ እየተፈለፈለልህ፡፡ ይህን የሚያሳይህ ቤት የግራና ቀኝ ግድግዳዎቹ በኳስ በምታብድላቸው የአውሮፓ ቡድኖች ፎቶ የተሞላ ነው፡፡ ማዘናጊያ ነው፡፡እግር ኳስ የሚታይ እንዲመስል የተሰቀሉ ናቸው፡፡ በዚህ ቤት ግን እውነት እልኻለሁ ነግቶ እስኪመሽ የአልጋ ጨዋታ ካልኾነ የሜዳ ጨዋታ አይታይም፡፡
በእርግጥ የአልጋ ጨዋታንና የኳስ ጨዋታን እያፈራረቁ የሚያሳዩ ቤቶች በዶሮ ማነቂያ የሉም አልልህም፡፡ ለምሳሌ “አድማሱ ቤት”፣ “ቴዲ ቤት”፣ “ገዛኸኝ ሚስት ቤት” “አንደርግራውንዱ ቤት” ይህንን ያደርጋሉ፡፡ ቀሪዎቹ ግን ለማዘናጊያ ካልሆነ ኳስ ድቡልቡል መሆኗንም የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ በነገራችን ላይ የወሲብ ፊልምን የሚያስኮመኩሙት ቤቶች ቁጥር ከዓመት ዓመት እየተመናመነ መሆኑን ስነግርህ በታላቅ ኀዘን ነው፡፡ ዛሬ አንድ ሰባት የሚሆኑ ጓሮዎች ብቻ ናቸው በድፍን ዶሮ ማነቂያ ወሲብ የሚያስኮሞኩሙት፡፡ ሰዎች የራሳቸውን ፊልም ወደመሥራት አዘንብለዋል ወይም ሌላ ተፎካካሪ ማሳያዎች በአጎራባች ሰፈሮች ተፈጥረዋል ማለት ነው።
በጠቀስኩልህ ቤቶች ግን ልቅ ወሲብ ከማለዳው ሦስት ሰዓት እስከ ሌሊቱ ስድስት ሰዓት ይታጨዳል፡፡ የጠጅ ቤት አግዳሚ ወንበሮች ተዘርግተው፣ መብራት ጠፍቶ፣ ትንፋሽ ተውጦ፣ ዝምታ ነግሶ ወሲብ ይነግሣል፡፡ የአረብ ወሲብ፣ የህንድ ወሲብ፣ የፈረንሳይ ወሲብ፣ የቻይና ወሲብ፣ የአፍሪካ ወሲብ፣ ሊፍት ውስጥ፣ ጫካ ውስጥ፣ መኪና ውስጥ፣ ኮሪደር ውስጥ፣ ማድቤት ውስጥ፣ ሶፋ ላይ፣ ሼልፍ ላይ፣ ወለል ላይ፣ ደረጃ ላይ፣ በቡድን በተናጥል በተመሳሳይ ፆታ፣ በተቃራኒ ፆታ፣ ከፈረስ ጋር፣ ከሜዳ አህያ ጋር፣ በመጨረሻም ከዶሮ ጋር ይወሰባል፡፡በዶሮ ማነቂያ፡፡ በቴሌቪዥን፡፡
የዶሮ ስጋና ዶሮ ማነቂያ
ዶሮ ማነቂያ ስድስት ሰዓት ሲሆን በአራራ ታብዳለች፡፡ ድሬዳዋን ታስንቃለች፡፡ ሰዎች ባህርያቸው ይለወጣል፡፡ ይገላምጡኻል፡፡ በዚህ ሰዓት አንደበትህን ለመግራት ሞክር፡፡ በአራራ ጫማ ጥፊ ትመታለህ፡፡
ዶሮ ማነቂያ ቡናን እየተካ ያለውን አረንጓዴ ቅጠላችንን ለፒያሳ ሕዝብ ኤክስፖርት በማድረግ ትራንስፎርሜሽኑን በማፋጠኑ ረገድ የምትጫወተው ሚና የዋዛ አይደለም፡፡ ዶሮ ማነቂያ ጫትን በብዛትና በስፋት ለዜጎቿ በማዳረስ ከሲኒማ ራስ ቀጥሎ በምስራቅ አፍሪካ አንደኛ እንደሆነች በሬዲዮ ሰምቻለሁ፡፡ ያም ሆኖ ከዶሮ ማነቂያ እሴቶች መሀል ወሲብ ቤቶችንና ጫት ቤቶችን ብቻ ዘርዝሮ ይህንን ጽሑፍ መዝጋት የበሉበትን ወጪት መስበር ይሆናል፡፡ በመሆኑም የዶሮ ማነቂያን ድርሳን የምንዘጋው በመልካም ዜና ይሆናል፡፡
የጨርቆስ ልጆች “ከሰፈሮች ሁሉ ማንን ትወዳላችሁ?” ቢባሉ “ዶሮ ማነቂያን አሉ” አሉ፡፡ ለምን ይመስልኻል? በዶሮ ማነቂያ ስጋ እንደተራ ምግብ በየበረንዳው በመስቀያ ተሰቅሎ ስለሚያዩ ነው፡፡ የጨርቆሶችን የሥጋ ፍቅር ደግሞ ያው እንደምታውቀው ነው፡፡ ከራሱ አስበልጦ ሥጋን ይወዳል፡፡ ሥጋን የፈጠረ አምላክ ከፈቀደ “ጨርቆስና ሥጋ” የሚል መጽሐፍ አሳትም ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል?
የከተማችን ሥጋ በል ሕዝብ የማያባራ የስጋ አምሮቱን ከሚወጣባቸው ሰፈሮች ውስጥ ከልደታ ቀጥሎ ዶሮ ማነቂያ ትጠቀሳለች፡፡ በጊዮርጊስ በኩል ባለው የዶሮ ማነቂያ “የባህር በር” ያለውን ትእይንት ስትመለከት አዳም የተሳሳተው በበለስ ሳይሆን በሙዳ ሥጋ ሊመስልህ ይችላል፤ የበግ፣ የበሬ እና የፍየል ስጋ እንደጉድ ይነገዳል፡፡ የሚገርመው በዶሮ ማነቂያ የዶሮ ሥጋ አለመገኘቱ ነው፡፡
ገና ወደ ዶሮ ማነቂያ ግዛት አንድ እግርህን እንዳስገባህ ነጭ ጋውን የለበሱ ሥጋ አራጆች ልክ እንደ ጆፌ አሞራ እና ጭልፊት ያንዣብቡኻል፣ ያዋክቡኻል፡፡ ቢላቸውን እያፋጩ፡፡ የፒያሳ ልጅ ካልሆንክ አንተኑ አርደው የሚበሉህ ስለሚመስልህ ትፈራለህ፡፡በነጻ የሚጋብዙህ ይመስል እነርሱ ቤት እንድትገባ ያባብሉኻል፡፡ ቁራጭ ሥጋ አፍህ ውስጥ ወርውረውልህ ኪስህን ሊያራቁቱት እኮ ነው፡፡
እነ “በቀለ” እነ “ባንቡ” እነ “አዱኛ” እነ “ፋሲካ” እነ “ቤተልሄም” እነ “ታደሰ” መስኮታቸውን የሥጋ መጋረጃ አሰርተውለት እንቁልልጭ ይሉኻል፡፡ አይንህ ሥጋዎቹን በደንብ እንዲያይ ስልሳ ሻማ አምፖል በሥጋው ትይዩ ያበሩልኻል፡፡ የኃይል እጥረት በከተማችን እንዲከሰት ከሚዳርጉ ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ቀጥሎ የሥጋ ቤት አምፖሎች ዋንኛዎቹ ናቸው ብዬ ብጮኽ የሚሰማኝ አጥቻለሁ፡፡
ለማንኛውም እንደ አብዛኛው የአገርህ ዜጋ ሥጋን ለአውድ ዓመት ብቻ የምታገኝ ከሆነ ወይም እንደ ጨርቆስ ልጆች ሥጋን እንደ ኦሎምፒክ በየአራት ዓመቱ የምትበላ ከሆነ በዶሮ ማነቂያ እየተመላለስክ አምሮትህን ልትወጣ ትችላለህ፡፡ “መብላት ነበር!” እያልክ ትዝታለህ፤ ሥጋውን በቅርብ ርቀት እያየህ። ልክ ቅድመ አያቶችህ ጥልያን ላይ እንደፎከሩት፤ አንተም ታቅራራለህ፤ “መብላት ነበር!” እያልክ። በዶሮ ማነቂያ!
this piece is full of lol
i enjoyed it sooooooooooooooo much. please leave the Cherqos Lijoch aside. Ayasazinuhim?
will there be part three of this story? can’t wait to read that.
funny
I love it. You could have perhaps mentioned the red light district in the heart of doro manekia, the road from hager fikir to center doro manekia / from times of wube bereha till now – as narrated in the stories of sebhat/ where the spectators of the yalga lay chewata get to practice. I think you could write more articles just focousing on various aspects of Piassa.
And i really like it that you kept the doro theme thourght the piece.
I liked both articles about Piazza even though I’ve found many drawbacks on the mindset of the writer.The writer hasn’t yet left the cliche`d locality classifications like ‘Cherkos’ and made his judgement that way.If he desires to be an author,he should be a truly humanist.But this writer humiliates & dehumanizes all the inhabitants of cherkos(kirkos)deeply and without a matured attitude.Like other impoverished localities of Addis Ababa cherkos has produced so many intellectuals,artists,journalist,sportsmen and other fruitful citizens in all disciplines.I hate such orientations extremely.Men shouldn’t be judged by such merits.I deeply sympatize for the harsh and destructive immaturity of the writer.Take lessons and be human please.Don’t degrade noble human beings by u’r narrow,primitive and ignorant thoughts.The editors of this website shouldn’t repeat such grave mistakes.
Dear Alex,
I from Cherkos too but I don’t take it personal. Don’t forget he is an artist and he preferred this way of writing… so Alex calm down brother…
neger abrid inji….
my friend who said kirkos has not produced intellectuals. I leave there but I am one of the very few people who succeeded in education. However it is given that kirkos is still one of the most forgotten side of the city. Thanks to cooperation today youngsters are try to employ themselves which we all like. Any ways believe me the writer knows better to write such things. Even if we don’t have personal thing I am his fun since we are in Alemaya. To judge him you need to read a little bit more of his work.
Execellent as usual.
NO agree with the above comment.
Look Alex. this is the one characteristics of literature. There is some kind of legend focusing that place called Cherqos. i also grown up partly there. I know it is not the place as the writer put it or comedians depict it. But is is still in the society. Writers, as i believe have the right to reflect the society. MUHAMED did the same.
i love piassa and i love Cherqos too. and i love the writer as well. Take it easy man
Heny,I’ve got the same sentiment in part 1 of this story.Take a look at that story and observe what Mohammed did with a similar connotation.It seems deliberate or the writer is 4 decades behind the latest advancement in human thought and philosophy.Love,respect and humility to all and hatered,degradation and disrespect to no one.As I said earlier,no matter what,human beings are noble by spiritual manners.And writers are the most kind,sensitive,humanist,generous,neutral,unique and creative above all.They preach love,equality and justice not the opposites.
Dear writer,
Thank you for writng. I would say this scenario is not unique to Addis or piazza or chercos; the divide is much worse if you go to big cities like Bombay, Nairobi…So, as long as there are human beings,there will always be a chasm b/n the have’s and have not’s.Life is full of contrast and you can not avoid this. The point is let’s be humane,minimise over-consumption, share our resources and add value to our existence.
Many thanks
This is the real image of DORO MANEKIA
ለ ደራሲው
የኛ ሰፈር ነው እንጂ ጫትን ለከተማዋ ሰፕላይ የምታረገው ለዶሮ ማነቂያ ማነው የሰጣቸው ሳሪስን የሚያህል ጫት በማከፋፈል ደሞ የሚያክል ሰፈር አለ እንዴ ?
ewnethn new
Very Entertaining!!
የዶሮ ማነቂያ ጉድ ተነግሮ ስለማያልቅ እንዲያው ዝም ማለቱ ሳይሻል አይቀርም…
Dear readers, in my opinion the writing is not about Doro Manekiya or Cherkos. Its about life in general. If you read between the lines its about the line that divides the poor and the rich in Addis Ababa. Almost all characters of the neighborhood is common to most others; Chat bet, Video bet, sega Bet, ETC. its about how people even with poor income live in harmony with their super rich neighbors. Its about how we live in a society with its merits and demerits. But all written in an entertaining, funny yet hidden ways. My gratitude goes to the author.
በጣም አሪፍ ጽሁፍ ነው፡፡ ፒያሳ የሚል ‘ብሎግ’ ተከፍቶ ስለ ፒያሳ መጻፍ አለበት እንጂ በአንድና በሁለት ክፍል ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ፒያሳ በጉያዋ የያዘቸው ጉድ ፣ በየቀኑ የሚታዩት ክስተቶች፣ ፒያሳ በማታ፣ የፒያሳ ሴቶች፣ የፒያሳ ወንዶች…የመሳሰሉት ታሪኮች ቢጻፉ ቢጻፉ ብዕሩ ያልቃል እንጂ አይቋጭም፡፡ ስለ አረንጓዴው አብዮት(ጫት)አቀንቃኞች ታሪክ ገና ምን ተነካና፡፡ ከሲኒማ ኢትዮጵያ ጀርባ ያለው ታሪክ እንኳን በአንድ ገጽ በአንድ አመትስ ተነግሮ ያልቃል?
I agree with the above comments. Eyob and Tesfegnaw
The author shall not stop writing until he covers all the Ethiopian vicinities. He can even compile it as a book. Addisneger can publish it as a book.
i am really enjoying it
where is the next chapter. cannot wait
people just enjoy it don,t make it serious
please mehamed keep going i like the way ypu write!!!!!!!1
i like his article and i need to read extra if it is possible…about piazzor any otherplace for instance saris…”yekenwa saris yematawa paris”… i apreciate the writers
I really loved your article. your expression skill is amazing. You repeatedly put smile on my face. Keep on writting man. Bravo
I love both pieces so much, Way to go man!
Believe these wont be the last…
Hey Alex because you are not “ye doro manekiya lej” you don’t understand… go to shewa dabo and line up…
I love your article…please writem more about piazza bars…blue nile and….