የፍትሕ ጋዜጠኞች በከፍተኛ የስላዮች ወከባ ውስጥ ወድቀዋል፤ ደበበ እሸቱ ለርዕዮትና ለውብሸት ተከላካይ ምስክር ሆኖ ሊቀርብ ይችላል
ሳምንታዊው “ፍትሕ” ጋዜጣ በደኅንነት ሠራተኞች ግልጽ ከበባ ሥር መውደቁ ታወቀ። የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ የጋዜጣው አዘጋጆች፣ ሪፖርተሮችና ሠራተኞች በሙሉ በደኅንነት ሠራተኞች የክትትል ቀለበት ሥር ገብተዋል ሲሉ የጋዜጣው ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ትላንት ረቡዕ ታህሳስ 11 ቀን 2004 ዓ.ም ከሰአት በኋላ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በመቅረብ የፍትህ ጋዜጣ ዓምደኛ ለሆነችው ርዮት ዓለሙ የመከላከያ ምሥክር ሆኖ የቀረበው የፍትሕ ጋዜጣ አዘጋጅ ኀይለመስቀል በሸዋምየለህ ከፍርድ ቤት መልስ ስድስት ኪሎ አፍንጮ በር አካባቢ ወደሚገኘው የፍትሕ ጋዜጣ ቢሮ ገብቶ ትንሽ ከሰራ በኋላ ከቀኑ 11፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ከቢሮው ፊት ለፊት ባለ ሱቅ ውስጥ በመገበያየት ላይ ሳለ ፍርድ ቤት ውስጥ ሲከታተሉት በነበሩት አራት የደኅንነት ሠራተኞች ለተወሰነ ጊዜ እንዳገቱት ከጋዜጣው ሠራተኞች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሐሙስ ታህሳስ 12 ቀን 2004 ዓ.ም፡- ሳምንታዊው “ፍትሕ” ጋዜጣ በደኅንነት ሠራተኞች ግልጽ ከበባ ሥር መውደቁ ታወቀ። የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ የጋዜጣው አዘጋጆች፣ ሪፖርተሮችና ሠራተኞች በሙሉ በደኅንነት ሠራተኞች የክትትል ቀለበት ሥር ገብተዋል ሲሉ የጋዜጣው ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ትላንት ረቡዕ ታህሳስ 11 ቀን 2004 ዓ.ም ከሰአት በኋላ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በመቅረብ የፍትህ ጋዜጣ ዓምደኛ ለሆነችው ርዮት ዓለሙ የመከላከያ ምሥክር ሆኖ የቀረበው የፍትሕ ጋዜጣ አዘጋጅ ኀይለመስቀል በሸዋምየለህ ከፍርድ ቤት መልስ ስድስት ኪሎ አፍንጮ በር አካባቢ ወደሚገኘው የፍትሕ ጋዜጣ ቢሮ ገብቶ ትንሽ ከሰራ በኋላ ከቀኑ 11፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ከቢሮው ፊት ለፊት ባለ ሱቅ ውስጥ በመገበያየት ላይ ሳለ ፍርድ ቤት ውስጥ ሲከታተሉት በነበሩት አራት የደኅንነት ሠራተኞች ለተወሰነ ጊዜ እንዳገቱት ከጋዜጣው ሠራተኞች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ጋዜጠኛ ኀይለመስቀል በእገታ ላይ ሳለ ስልኩን እንደነጠቁትና ሲም ካርዱን ብቻ አውጥተው የሞባይል ቀፎውን እንደመለሱለት፣ የድብደባ ዛቻ ስብዕናን እና ሙያተኝነትን የሚያንቋሽሽ አስቀያሚ ስድቦችን በመስደብ ሊያበሳጩት እንደሞከሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ትላንት ምሽት ላይ በፍትህ ቢሮ የጋዜጣው ሥራ ምን ላይ እንደደረሰ የክትትል ስብሰባ (ራፕ ሀፕ ሚቲንግ) ለማድረግ የተሰባሰቡት አዘጋጆች የደኅንነት ሠራተኞች ክትትሉና ከበባው ስለበጠበጣቸው ወደ አራት ኪሎ ሻሎም ካፌ በግልጽ ሻይ እየጠጡ ለመወያየት በመወሰን ሲንቀሳቀሱ የደኅንነት ሠራተኞች ተከታትለዋቸዋል፡፡
የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝና አዘጋጆች ኀይለመስቀል በሸዋምየለህ እና ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ክትትሉ ሲበረታ ወደ ኢንተረሜዞ ካፌ ያመሩ ሲሆን ከበባው ኀይለኛና ጸብ የሚጋብዝ በመሆኑ የጀመሩትን ሻይ እየጠጡ መወያየት በማቋረጥ ወደ አራትኪሎ ወወክማ አካባቢ በማምራት የጸጥታ ሠራተኞቹን ለማብረድ እንደሞከሩ ምንጮቻችን አስረድተዋል፡፡
ይሁን እንጂ የጸጥታ ሠራተኞቹ ለአፍታ ከተሰወሩ በኋላ እንደገና ከበባቸውን የቀጠሉ ሲሆን የፍትሕ ጋዜጣ ጋዜጠኞች መለያየቱ እንደሚጎዳቸው በመነጋገር ቀበና አካባቢ በሚገኘው የጋዜጠኛ ተመስገን ቤት ለማደር በመወሰን ከታክሲ ሲወርዱ የደኅንነት ሠራተኞቹ ቀድመዋቸው በተመስገን ቤት አካባቢ ጠብቀዋቸው ከበባውን ቀጥለዋል፡፡
የፍትህ ጋዜጣ ጋዜጠኞች ከሱቅ ለስላሳ በመግዛት ወደ ቤት ገብተው ቆልፈው የተቀመጡ ሲሆን ጠዋት ላይ ነግቶ ሲወጡ ከበባው እንደቀጠለ ነበር። ሦስቱ ጋዜጠኞች የአራት ኪሎ ታክሲ ሊይዙ ሲሉ የደኅንነት ሠራተኞቹም እንደተሳፋሪ በመቅረባቸው በእግር ወክ በማድረግ ሲጓዙ ከበባው አልተለያቸውም። ሁኔታው ያላማራቸው ጋዜጠኞቹ ቀበና ከግሪን ቪው ሬስቶራን አጠገብ ካለ ህንፃ አንድ ካፌ ውስጥ በክትትል ሥር ሆነው ቁርሳቸውን በልተው ስድስት ኪሎ ወደ ሚገኘው ቢሯቸው ሲያመሩ የደህንነት ሠራተኞች ቀድመው ተገኝተዋል፡፡ ይህን ሪፖርት በምናደርግበት ጊዜ ሁሉ ክትትሉ እንደቀጠለ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ አርቲስት ደበበ እሸቱ ዛሬ በእነ ኤሊያስ ክፍሌ የክስ ፋይል ላይ የተከላካይ ጠበቆች በሚያቀርቡት ምስክርነት ላይ ቀርቦ “በፍትሕ” ጋዜጣ ዓምደኛ ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ እና በአውራምባ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ለነበረው ውብሸት ታዬ ተከላካይ ምስክር ሆኖ ይቀርባል ሲሉ ምንጮቻችን ለሪፖርተራችን ገልጸዋል፡፡
No comments yet... Be the first to leave a reply!