ምርጫ ቦርድ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ስም ከሊቀመንበርነት ማንሳቱ ቅሬታ አስነሳ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር የኾኑትን የወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ስም በምክትላቸው መተካቱ በፓርቲው አባላት ዘንድ ቅሬታ አስነሳ።  ምርጫ ቦርድ የሊቀመንበሯን ስም መጠቀሙን ትቶ በምትኩ የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር የኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን ስም ያሠፈረው በኦፊሺያላዊ ድረ ገጹ ላይ ነው። “በኢትዮጵያ በሕጋዊነት ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስም፣ አመራሮች እና አድራሻቸው” በሚለው የድረ ገጹ ክፍል ላይ በሰንጠረዥ መልክ የተቀመጠው ይህ መረጃ “ፖለቲካዊ አንድምታ” አለው ሲሉ የፓርቲው አባላት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

(ሙሉ ገ.)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር የኾኑትን የወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ስም በምክትላቸው መተካቱ በፓርቲው አባላት ዘንድ ቅሬታ አስነሳ።  ምርጫ ቦርድ የሊቀመንበሯን ስም መጠቀሙን ትቶ በምትኩ የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር የኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራውን ስም ያሠፈረው በኦፊሺያላዊ ድረ ገጹ ላይ ነው። “በኢትዮጵያ በሕጋዊነት ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስም፣ አመራሮች እና አድራሻቸው” በሚለው የድረ ገጹ ክፍል ላይ በሰንጠረዥ መልክ የተቀመጠው ይህ መረጃ “ፖለቲካዊ አንድምታ” አለው ሲሉ የፓርቲው አባላት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

በአንድነት አመራሮች በሥነ ምግባር ጉድለት እንደተባረሩ ክስ የሚቀርብባቸው እና “መርህ ይከበር” በሚል  የተሰባሰቡ አባላት በበኩላቸው የቦርዱን መረጃ እንደእማኝ በማቅረብ የፓርቲውን አመራር አባላት “አምባገነን” በማለት በመኮነን ላይ ይገኛሉ። “ወ/ት ብርቱካን ያለ ሕጋዊ አግባብ ተሽረው፣ በምትካቸው ኢንጂነር ግዛቸው ተሹመዋል” ሲሉም የፓርቲውን አመራሮች ያወግዛሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግን የወይዘሪት ብርቱካንን ስም በምክትላቸው የተካሁት “በስኅተት እንጂ ኾነ ብዬ አይደለም” ሲል አስተባብሏል። “በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ሊቀመንበር በሌለበት ምክትል ሊቀመንበር ተጠሪ እንደኾነ ስለሚገልጽ፣ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር የኾኑትን የኢንጂነር ሽፈራውን ስም ተጠቅመናል” ሲሉ የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት ባልደረባ አቶ ተስፋለም ዐባይ ይናገራሉ። “ነገር ግን “የሊቀመንበሩ ሙሉ ስም“ በሚለው ሰንጠረዥ ላይ የምክትሉን ሥም ማስፈራችን ስኅተት ነው፤ ይስተካከላል” ብለዋል።

የኢንጂነር ግዛቸውን የፓርቲ ሥልጣንም “ምክትል ሊቀመንበር“ በሚል እንደሚስተካክልም ያስረዳሉ። ኾኖም  ወ/ት ብርቱካን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ የሊቀመንበሯን ቦታ ተክተው እየሠሩ የሚገኙት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው በመኾናቸው ቦርዱ ለሥራ ግንኙነት ሲባል እርሳቸውን መጠቀሙን እንደሚቀጥል አቶ ተስፋለም ይገልጻሉ።

4 Responses to “ምርጫ ቦርድ የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ስም ከሊቀመንበርነት ማንሳቱ ቅሬታ አስነሳ”

  1. what is the deal here .Is there any political implication ? is it a deliberate action of the melese selection board to deny Brtukans UDJ leadership?or is it a coup-detat against Burtukan by a few udj ring leaders notably by the current chairman Enjinner Shiferaw and his coherts by locking horns with the Kangaroo board.No body knows what is there in store.But sooner or later truth will prevail .

  2. It is really silly to think that Gizachew did this purposely. I wonder if some people really think. When they know that a lot dirtier things are done by the board!

  3. THIS IS TO TEST eTHIOPIAN PEOPLE ATTENTION.

  4. UDJ is actually a dying party. Gizachew is politically inept though he is power monger. He has been making many political blunders that weakened the party while making it an easy prey for Meles Zenawi. One problem all oppositions have is they tend to make the leadership positions a permanent tenure. Why don’t they try to create fixed terms for leadership positions? Then the leaders have to work hard and show their capacity and creativity to stay in power. All the infighting and havoc within opposition parties is the result of power mongers that are trying to consolidate a life time hold on the top positions.

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.

Bad Behavior has blocked 2470 access attempts in the last 7 days.