"; _gaq.push(['_trackPageview']);(function() { var ga = document.createElement('script'); ga.type = 'text/javascript'; ga.async = true; ga.src = ('https:' == document.location.protocol ? 'https://ssl' : 'http://www') + '.google-analytics.com/ga.js'; var s = document.getElementsByTagName('script')[0]; s.parentNode.insertBefore(ga, s); })();

News

RSS feed for this section

መንግሥት በእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጉዳይ “ሽምግልና” ጀመረ

ከጊዜ ወደጊዜ ከሙስሊም ምእመናን የሚደርስበት ተቃውሞ ሞልቶ መገንፈል የጀመረውን “የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት” (መጅሊስ) ለመታደግ መንግሥት “ሽምግልና” መጀመሩ ተሰማ። በዛሬው ዕለት በመጅሊሱ መሪዎች እና ሰፊውን ምእመን ይወክላሉ በተባሉ ጊዜያዊ ወኪሎች መካከል ሊደረግ የነበረው ውይይት ሳይካሄድ ቀርቷል።

ዛሬ ረቡዕ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ በሽፈራው ወልደማርያም እና በሚኒስትር ጁነዲን ሳዳ አወያይነት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ንግግር ሳይጀመር የቀረው በምን ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም። ሆኖም በተደራዳሪዎቹ በኩል ማለትም በመጅሊሱ እና በአዲሱ የተወካዮች ቡድን መካከል እውቅና የመስጠት ጉዳይ ሳይነሳ እንዳልቀረ አንድ ምንጭ ጠቁመዋል።

Read more

ፍርድ ቤቱ በእነኤልያስ ክፍሌ ክስ ከ14 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እስራት በየነ

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን አሰምቶ እንደጨረሰ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ “አጠቃላይ ሁኔታው የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ነው። ከጥርጣሬ ባሻገር ምንም ዓይነት ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ነው የፈረዳችሁብን” በማለት ቅሬታውን ገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ሊቀ መንበር አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚያብሔር በበኩላቸው “እኔ ጥፋተኛ አይደለሁም፣ ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በተቃዋሚ ፓርቲ በመሰለፌ ነው ይሄ ቅጣት የተወሰነብኝ” በማለት ለፍርድ ቤቱ ቅሬታቸውን ያሰሙ ሲሆን የቀኝ ዳኛው ሙሉጌታ ኪዳኔ ቆጣ ብለው አሁን ዝም በሉ ቅሬታ ካላችሁ ይግባኝ መጠየቅ ትችላላችሁ ብለዋል፡፡

Read more

በእነአንዷለም መዝገብ 24ቱ ተከሳሾች ተከላከሉ ተባሉ

(ሙሉ ገ./ኢዲስነገር ኦንላይን)
ዛሬ ከሰአት በኋላ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ በዋለው ሦስተኛ ወንጀል ችሎት የመሐል ዳኛ እንዳሻው አዳነ የፍርድ ቤቱን ብይን በንባብ አሰምተዋል። የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ ካቀረባቸው ስድስት ክሶች ውስጥ በ1ኛው ክስ ሁሉም የተከሰሱ ሲሆን አንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ዮሐንስ ተረፈ፣ ሻምበል የሸዋስ ይሁንአለም፣ ክንፈሚካኤል ደበበ፣ ምትኩ ዳምጤ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አያሌው፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ውቤ ሮቤ፣ መስፍን አማን፣ ዘለሌ ጸጋ ስላሴ፣ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም፣ አበበ በለው፣ ኦባንግ ሜቶ የተባሉት ተከሳሾች ወንጀሉን ስላለመፈጸማቸው እንዲከላከሉና እንዲያስረዱ፤ በአንፃሩ በኤፍሬም ማዴቦ፣ አበበ ገላው፣ ንአምን ዘለቀ፣ ኤልያስ ሞላ፣ ደሳለኝ አራጌ ዋለ፣ ኮ/ል አለበል አማረ በተባሉት ተከሳሾች ላይ ግን ዐቃቤ ሕግ ክሱን የሚያስረዳ በቂ ማስረጃ ባለማቅረቡ መከላከል ሳያስፈልጋቸው ነጻ ወጥተዋል ብሏል- ፍርድ ቤቱ፡፡ ክሱ በጸረ ሽብር ሕጉን አንቀጽ 3/1-4፣ አንቀጽ 4 እና 6 የተደነገገውን በመተላለፍ በሚል የቀረበ ነው። በክስ ቻርጁ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በዚህ ክስ ቢካተቱም በኋላ ዐቃቤ ሕግ 23ኛ እና 24ኛ ተከሳሾች “በታይፕ ስሕተት” መግባታቸውን በመጥቀስ ከዝርዝሩ ወጥተዋል። የክሱ ጭብጥ በጥቅሉ የሽብር ድርጊት መፈጸም ወይም ለዚሁ መዘጋጀትንና ማሴርን፣ እንዲሁም ሽብርተኝነትን ማበረታታን የሚመለከት ነው።

Read more

ፍርድ ቤቱ በውብሸት፣ በርዕዮትና በሌሎቹ ላይ “የጥፋተኝነት” ውሳኔ አስተላለፈ

ሐሙስ ጥር 10 ቀን 2004 ዓ.ም፡- የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት መንግሥት በነኤልያስ ክፍሌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል በከሰሳቸው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሔር እና ወ/ሮ ሂሩት ክፍሌ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አሳለፈ፡፡ የቅጣትውሳኔ ለማስተላለፍ ለጥር 17 ቀን 2004 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

Read more

በጋምቤላ ክልል ግምገማ ሹም ሽር እየተካሔደ ነው

ከዛሬ ጀምሮ በሚደረገውና እስከ ጥር 10 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ በሚቆየው ክፍል ሁለት ግምገማ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የአመራር አባላት፣ የዞንና የወረዳ አመራር አባላት ሁሉ በተዋረድ የሚሳተፉበት ሲሆን ከፍተኛ ሹም ሽር ሊኖር እንደሚችል አንድ የክልሉ የዞን አመራር አባል ለሪፖርተራችን ገልጸዋል፡፡

Read more

“የጸረ ሽብር ሕጉ የፈጠረው ቀውስ በጋዜጠኞች ስልጠና ሊታከም ነው”

ይሄን ሥልጠና ለማዘጋጀት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሥልጠናውን ማንዋል ያዘጋጀ ሲሆን ጋዜጠኞቹን የማስተባበር ሥራ በአቶ አንተነህ አብርሃም ለሚመራው “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት” (ኢብጋሕ ) የተሰጠ ኃላፊነት ሲሆን የሠልጣኝና የአሰልጣኞችን አበል ጨምሮ አጠቃላይ የዝግጅቱ የገንዘብ ወጪ ደግሞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የተሰጠ ኃላፊነት ነው ተብሏል፡፡ የዚህ ኮሚሽን መሪ በቅርቡ ከአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ተከሰው መታሰራቸውን እንደማያውቁ መናገራቸው ይታወሳል።

Read more

Zenawi calls jailed Swedish journalists terror accomplices

New York, October 11, 2011–Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi’s public accusations on Monday against two imprisoned Swedish journalists compromise the presumption of their innocence and predetermine the outcome of their case, the Committee to Protect Journalists said today. The journalists were arrested in Ethiopia in July and charged with terrorism for associating with armed separatists. [...]

Read more

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን በክረምት የእረፍት ወቅት በ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ለማጥመቅ ታቅዷል

(በፍቃዱ አድነው) በቀጣይ የተማሪዎች የእረፍት ወቅትን ተከትሎለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች “ስለ አብዮታዊ ዴሞክራሲ የፖለቲካ ፍልስፍና እና በኢትዮጵያ ስላስገኘው ልማት”፤ በአባይ  ወንዝ ላይ ይገነባል ስለሚባለው  ግድብ እና ኢህአዴግ እሳካሁን ተሳኩልኝ የሚላቸውን የግንባታ ልማቶችን ዋቢ እያደረገ ለተማሪዎች ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የአዲስ ነገር ምንጮች አሳወቁ። የኢህ አዴግ  መንግስት  በድንገት ትምህርት ሚንስቴር ዓመታዊ የትምህርት መርሃ- ግብሩን በአስቸኳይ እንዲያቋርጥና ወደ [...]

Read more

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከፍተኛ የውሃ እጥረት ተክስቷል

(በፍቃዱ አድነው) በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሚገኙ ልዩ ልዩ ወረዳዎች ውስጥ ካለፉት ሦስት ወራት ጀምሮ የተከሰተው የውሃ እጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለሪፖርተራችን አስታወቁ፡፡ በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በተፈጠረው የውሃ እጥረት ሳቢያ ሃያ ሊትር የሚይዘው አንድ ጀሪካን ውሃ በጥቂቱ ከ20 እስከ 25 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን አንድ በርሜል ውሃ ደግሞ ከ200 ብር በላይ እንደሚሸጥ የዐይን [...]

Read more

የአገር ቤት ጋዜጠኞች ምን ጻፉ? (ሚያዚያ 24- ግንቦት 1 ፣ 2003)

“ቢንላንደን ለአሜሪካ አሸባሪ ይሁን እንጂ ለእኛ ልማታዊ ባለሀብት ነው፡፡ እሱ ባይኖር በባይደዋና በሞቃዲሾ ሽብርተኛን የማሳደድ የኮንትራት ስራ ማን ይሰጠን ነበር?”

“ፍትህ” ጋዜጣ በ“አራትኪሎ ጫወታ” አምዱ
—–
“የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን” ባሳለፍነው ሳምንት “ኢትዮጵያን በሚመጥን መልኩ” በሂልተን ሆቴል ተከብሯል፡፡…
“ይሄ ቀን የእኛ ነበር፡፡ እነርሱ በዓመት 365 ቀን በተለያዩ ሚዲያዎች ፕሮፓጋንዳቸውን ይነግሩናል፡፡ እኛን ደግሞ በዓመት ቢያንስ አንድ ቀን እንዳንናገር ያፍኑናል፡፡”…
—–
“አዲስ አድማስ” እንደጻፈው ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 11ሺህ ኢትዮጵያዊያን ወደ ኩዊት፣ ሳኡዲና ዱባይ ተሰደዋል፡፡ የስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችና የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚሰደዱት ሰዎች መጨመር ጋር ተመጣጣኝ አገልግሎት እየሰጡ አይደለም፡፡
—–
ደራሲ ጋሽ ስብሐት ገብረ እግዜአብሔር 75ኛ የልደቱ ባልደመቀ መልኩ ተከብሯል፡፡ ሐሙስ ሚያዚያ 27 ጋሽ ስብሐት ልደት ላይ የተገኙት አራት ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡
——
“ ኢትዮጵያ ከአባይ ውሃ መጠቀም አለባት፡፡ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስላልተስማማን ከሕዝቡ ጥቅም በተቃራኒ ይቆማሉ ብሎ የሚጠብቅ ሰው ሞኝ ብቻ ነው፡፡”

“አዲስ አድማስ” ጋዜጣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ከተናገሩት የወሰደው፤ አንባቢዎች “ኢሳያስ መለስን ጉድ ሰሯቸው” ሲሉ ተሰምተዋል።
—–

Read more
Hertizg

ለመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጀርመናዊ ፕሬዝዳንት ተሾመ

ለመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶችን የመሾም ሥልጣኑ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነው፡፡ ከትናንተ በስቲያ በይፋ ሥራ የጀመሩት አዲሱ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዶክተር ያኺም ሄርዝ ይባላሉ፡፡ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ መቀሌ ዩኒቨርሲቲን ዓለም አቀፍ ደረጃዉን ወደ ጠበቀ ግዙፍ የትምህርትና የምርምር ዩኒቨርሲቲ የመለወጥ ግዴታ ተጥሎባቸው በፕሬዝዳንትነት ተሹመዋል፡፡…
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ የበታች ውሳኔዎችን ያለገደብ የመሰረዝ፣ የዲኖች ካውንስል ውሳኔዎችን ድምፅን በድምፅ የመሻር እንዲሁም ለማንኛውም አፋጣኝ ጥያቄዎች የተለመዱ የአስተዳደር ሰንሰለቶችን አልፈው በቀጥታ ከመንግሥት አካላትና ከትምህርት ሚኒስትር ጋር ግንኙነት የማድረግ ልዩ ሥልጣን እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡ጀርመናዊው ፕሬዝዳንት ከዚህም ባሻገር ምንም አይነት አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ከመንግሥትም ሆነ ከክልሉ እንዳይደረግባቸው ስምምነት ተደርሷል፡፡

Read more

“መርህ ይከበር” ከአንድነት ፓርቲ ጋር ሲያደርገው የነበረው ውይይት መቋረጡን ገለጸ

(ኤፍሬም ካሳ) ከአንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ በመውጣት “መርህ ይከበር” በሚል ይንቀሳቀስ የነበረው የአባላት ስብስብ ከፓርቲው አመራር አባላት ጋር ላለፉት ሰባት ወራት ሲያደርገው የነበረው የእርቅ ውይይት ያለውጤት መቋረጡን ገለጸ። በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የሚመራው የ“መርህ ይከበር” ስብስብ ማክሰኞ ዕለት ለብዙሃን መገናኛ በበተነው መግለጫ እንደገለጸው ሰባት ወራት የፈጀው ውይይት አንድም ውጤት ሳያሳይእንዲቆም የተደረገው “ኃላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች [...]

Read more

Addisnegeronline.com is back

Addisnegeronline.com is back.
Thank you for your patience, encouraging words and helping hands. …

We would like to call ALL Addis Neger friends and fans to:

1. Copy and paste stories posted on addisnegeronline.com and the Facebook page on
your personal facebook walls
2. Let’s invite others to JOIN AddisNeger Facebook and other pro-democracy
pages/sites
3. Find ways to Share information on the ground more effectively

Akbariwochachihu

THE ADDIS NEGER TEAM

Read more
RSF

Newspapers and journalists face threats and legal pressure

Reporters Without Borders is alarmed by the steadily worsening climate of harassment and intimidation that the Ethiopian authorities have imposed on the media, especially the private media…

Eskinder Nega (picture), a former journalist jailed along with his wife in 2005 for supporting the protests that followed legislative elections, is again under pressure from the authorities…

The state prosecutor has brought more than 30 charges against the Amharic-language weekly Fitih. On 22 January, the editor, Temesgen Desalegne, was summoned by police to hear the charges against him. Accusations included “tarnishing the image of the ruling coalition.” He was released after posting bail of 500 US dollars…

The Facebook page of Addis Neger, an Addis Ababa-based weekly that voluntarily suspended publication in December 2009, is mysteriously unavailable.

[Read the full content of the statement issed by Reporters Without Borders, Click Read more]

Read more

ኢሕአዴግ ነባር አባላቱን በማራገፍ በአዲስ መልሶ ሊያደራጅ ነው

(በፍቃዱ አድነው) ኢህአዴግ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ አባሎቹን የየመልሶ ማደራጀትና የማጠናከር ሥራውን አቀላጥፎ መቀጠል እንዳለበት ከበላይ አካል ትዕዛዝ መተላለፉን በአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት የሚገኙ የዜና ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ የኢህአዴግ የመልሶ ማደራጀትና ቀደም ሲል የነበረውን መዋቅር የማጠናከር ሥራው በስፋት የሚካሄድባቸው መዋቅሮች በእናት ድርጅቶች (የየአካባቢው ነዋሪዎች) በሴቶች ሊግ፣ በወጣት ሊግ፣ በመንግሥታው ተቋማት- የቢሮ አደረጃጀት እና በመምህራንና ተማሪዎች አደረጃጀት ላይ [...]

Read more

Bad Behavior has blocked 1832 access attempts in the last 7 days.