የሙስሊሞች ተቃውሞ ቀጥሏል፤ “አባይ ይገደባል፤ መጅሊስ ይወገዳል”
በአወሊያ ትምህርት ቤት አስተዳደር ጉዳይ የተለኮሰው የሙስሊሞች ተቃውሞ በአዲስ አበባና በደሴ ቀጥሏል። የመረጃ ምንጮች እንዳሉት ሙስሊም ምእመናን በአወሊያ ትምህርት ቤት በየሳምንቱ ዓርብ የሚያደርጉት ተቃውሞ አራተኛ ሳምንቱን አስቆጥሯል። ከዓርብ የጁምአ ስግደት ጋራ ተያይዞ በሚደረገው በዚህ የተቃውሞ ስብስብ ጎልተው የወጡት ተቃውሞዎች ምእመናን “የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቱን” (መጅሊሱን) አመራርና አሠራር እንዲሁም የመንግሥትን ጣልቃ ገብነትን የሚመለከቱ ናቸው። ተሰብሳቢዎቹ “አባይ ይገደባል፣ መጅሊስ ይወገዳል” የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ መሰንበታቸውን ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል።
Read more

Recent Comments