በመርካቶ ሻጭና ሸማች ተፋጠዋል

ከሁለት ቀናት በፊት 35 ጌጅ ቆርቆሮ በብር 83 ብር ይሸጥ ነበር። ከሰዓት በኋላ ሪፖርተሮቹ በተዘዋወረው የጎበኟቸው አንዳንድ የሕንፃ መሣሪያ መደብሮች በአንድ ቆርቆሮ ላይ የ9.65 ብር ጭማሪ በማድረግ 92 ብር አካባቢ ሲሸጡ ተመልክተዋል። ሌሎች ሸማቾች በአንጻሩ በቀጣዮቹ ቀናት ከዚህም የበለጠ ጭማሪ ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት በተባሉት ዋጋ ለመግዛት ፍላጎት ሲያሳዩም ተስተውለዋል። በሌላ መልኩ ደግሞ አንዳንድ አከፋፋዮች በመጋዘን ያከማቹት ዕቃ ይበልጥ ዋጋ እንደሚያወጣላቸው በማሰብ ለሸማቾች ከመሸጥ ሲቆጠቡ ታይተዋል።

ከትላንት በስተያ ድንገተኛ የኾነው የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ሲታወጅ ያሻቀበው ታይቶ በማይታወቅ ኹኔታ ነበር። ወደ 2፡50 ሣንቲም የሚጠጋ ብር በአንድ የዶላር ዋጋ ላይ ጨምሮ መጥቷል። የዚሁ የዶላር ምንዛሪ የፈጠረው ግሽበት ትላንት ከሰዓት በኋላ እና ዛሬ በአንዳንድ ዕቃዎች ላይ የተጋነነ ጭማሪ ማሳየት ጀምሯል። እንዲያውም አንዳንድ የጅምላ ነጋዴዎች እና አከፋፋዮች ዕቃው በመጋዘን እና በየሱቆቻቸው ቢኖርም ለሽያች ለማቅረብ ፈቃደኛ ሳይኾኑ የሚቀሩበት አጋጣሚም ሲስተዋል ነበር። የአዲስ ነገር ዘጋቢዎች በሲዳሞ ተራ፣ በምስማር ተራ፣ በዱባይ ተራ እና በኤግዚብሽን ማእከል ጭምር የግብይት ኹኔታው ምን እንደሚመስል ተዘዋውረው ሲመለከቱ ያገኙት የመገበያያ መደብሮቹ በሸማች እና በሻጭ መካከል አለመግባባት እና መፈራራት እንደሚስተዋልባቸው ነበር።

ከሁለት ቀናት በፊት 35 ጌጅ ቆርቆሮ በብር 83 ብር ይሸጥ ነበር። ከሰዓት በኋላ ሪፖርተሮቹ በተዘዋወረው የጎበኟቸው አንዳንድ የሕንፃ መሣሪያ መደብሮች በአንድ ቆርቆሮ ላይ የ9.65 ብር ጭማሪ በማድረግ 92 ብር አካባቢ ሲሸጡ ተመልክተዋል። ሌሎች ሸማቾች በአንጻሩ በቀጣዮቹ ቀናት ከዚህም የበለጠ ጭማሪ ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት በተባሉት ዋጋ ለመግዛት ፍላጎት ሲያሳዩም ተስተውለዋል። በሌላ መልኩ ደግሞ አንዳንድ አከፋፋዮች በመጋዘን ያከማቹት ዕቃ ይበልጥ ዋጋ እንደሚያወጣላቸው በማሰብ ለሸማቾች ከመሸጥ ሲቆጠቡ ታይተዋል። በምስማር ተራ የሚገኙ አንድ ነጋዴ ለአዲስ ነገር ሪፖርተሮች እንደገለጹት “አሁን ለመሸጥም ኾነ ላለመሸጥም መወሰን አዳጋች ነው።” ሲሉ ያብራራሉ። ፋብሪካዎች እና ዋና ዋና አከፋፋዮች በምን ያህል ፐርሰንት ጭማሪ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ሳያውቁ ትክክለኛ እና ተመጣጣኝ የሚባል ጭማሪ ለማድረግ እንደሚያዳግታቸው የሚናገሩት እኚኹ ነጋዴ በመጪዎቹ ሦስት እና አራት ቀናት የተሻለ የገበያ መረጋጋት ይኖራል ብለው እንደሚጠብቁም ይናገራሉ።

የዚሁ የገበያ መናር ጉዳይ የተስተዋለው በዱባይ ተራ በሚገኙ የልብስ ሱቆችም ውስጥ ነበር። የጅንስ ዋጋ ባልተጠበቀ ኹኔታ የተጋነነ ጭማሪ ያሳየ ሲኾን ከዶላር ዋጋ መጨመር በፊት 270 ብር ይሸጡ የነበሩ ‹‹ስኪኒ›› ሱሪዎች በዛሬው ዕለት እስከ 400 ብር በሚደርስ ዋጋ ሲሸጡ ውለዋል። ያም ኾኖ ግን በሁሉም መደብሮች የሚታየው የጭማሪ ዐይነት ተቀራራቢነት አይታይበትም። ነጋዴዎች የመሰላቸውን ጭማሪ ካወጡ በኋላ ሸማቾች ለመግዛት ሲወስኑ ሐሳባቸውን የሚቀይሩበት አጋጣሚም ታይቷል። በተመሳሳይ ኹኔታ በሌሎች የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶች ላይም ጭማሪው የተስተዋለ ሲኾን ነጋዴዎቸ የመሰላቸውን ዋጋ እየጨመሩ ሲሸጡ ውለዋል።

በተያያዘ ዜና በኤግዚብሽን ማእከል መጪዎቹን የአዲስ ዓመት፣ የኢድ አልፈጥር እና የመስቀል በዐላትን ምክንያት በማድረግ ሰፊ የሸማቾች ግብይት ተጠብቆ የነበረ ቢኾንም ከዶላር ጭማሪው ጋራ የተያያዘ በሚመስል መልኩ ግብይቱ ቀዝቀዝ ብሎ ተስተውሏል። አቶ ሙሕዲን አሕመድ የተባሉ የኤግዚብሽኑ ተካፋይ ለአዲስ ነገር እንደተናገሩት ባለፉት ሁለት የአዲስ ዓመት ባዛሮች ላይ መካፈላቸውን አስታውሰው ዘንድሮ ምክንያቱ ባልታወቀ ኹኔታ መቀዛቀዝ እንደታየ ገልጸዋል። የዶላር ጭማሪውን ተከትሎም የዋጋ ማስተካከያ ለማድረግ እንደተገደዱ የተናገሩት አቶ ሙሕዲን ቀደም ሲል በ300-400 ብር ይሸጡ የነበሩ ‹‹ጃፓንና ኮሪያ›› ብርድልብሶች በአማካይ የመቶ ብር ጭማሪ እንደተደረገባቸው ተናግረዋል። ጭማሪው ግን በቀጣይ ቀናት ዋጋ ሊንር ይችላል ከሚል ስጋት የመነጨ እንጂ ዕቃዎቹ ቀደም ሲል የገቡ በመኾናቸው የዶላር ጭማሪው ተጽዕኖ እንዳልነካቸው አልሸሸጉም።

መንግሥት ያደረገውን የዶላር ዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ የሸማች እና የነጋዴ አለመግባባት የተፈጠረ ሲኾን አንዳንድ ነጋዴዎች የሸጡትን ዕቃ ሳይቀር ብር ጨምረው ለማስመለስ ጥረት ያደረጉበት ኾኖም ታይቷል። መንግሥት “ላኪዎችን ለማበረታት” በሚል ከትላንት በስቲያ የአንድ ዶላር ዋጋ 16 ብር ከ 35 ሳንቲም እንዲኾን መወሰኑ የሚታወስ ነው።

5 Responses to “በመርካቶ ሻጭና ሸማች ተፋጠዋል”

  1. What a frustration!!I could guess we will be soon like Zimbabwe.

  2. Who are these Negadewoch? do you mean the camouflaged woyane party functionaries.well it is a forgone conclusion that these untouchables manipulate the market as they wish.No matter who said what.Mind you !the law is in the hands of these low life ,uncultured and big time ignorant gangs called THE WOYANES.They are in their commanding height to grab whatever strikes their fancy.

  3. This is just Woyane`s instrument to deepen Ethiopians suffering. Can anybody tell me why at this particular time when Ethiopians (Moslem and Christians) should buy lots of things for their celebration. It is sad but I hope the Ethiopian people sooner or later say enough is enough like the people of Mozambique.

  4. They are systematicaly impoverishing the people. Poor people are meek and docile to control, therefore they are deliberately manipulationg the economy to that effect. Remember that there are some part of the society who have escaped such vulnerability, hence every economic policy developed by Woyane will have a selective effect whether it is positve or negative. I wish someone get us information on how the change in economic profile of the Ethiopian population is in the past 20 years. I remember Tefera Waliwa was spouting a lot on such kind of issues in the wake of their ascendance to power, why doesn’t he tell us now about their achievement.

  5. wow !!!!!the 5 year plan started with devaluation of ethiopian birr,how nice.now we know what is going to happen after five years.more disaster than ever.

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.

Bad Behavior has blocked 2470 access attempts in the last 7 days.