“ጉዳዩ “ ጅቡቲ ደርሷል….
“ጅቡ…ቲም!?” ምን አልባት በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህቺ የምስራቋ ጎረቤታችን መሪዋን ኢስማኤል ኦማር ጊሌህን ተቃውማ ሰልፍ ወጣች፤ በሐሰን ጉሌድ ኧብቲዶን ስታዲየም። ጅቡቲያውያንም ለውጥ ሽተዋል። አዲስ አበባም በጣህሪር አደባባይ የወጣቶች አብዮት ቀልቧ ከተወሰደ ሰንበትበት ብሏል። ዐይኗ ከአልጀዚራ ላይ አልተነቀለም። ከዚህ ቀደም የሙዚቃ፣ እግር ኳስ እና የፊልም ቻናሎችን ብቻ በመክፈት የሚታወቁት የከተማዋ ካፌዎች ጣቢያዎቻቸውን ወደ አልጀዚራ እና ቢቢሲ [...]
“ጅቡ…ቲም!?” ምን አልባት በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህቺ የምስራቋ ጎረቤታችን መሪዋን ኢስማኤል ኦማር ጊሌህን ተቃውማ ሰልፍ ወጣች፤ በሐሰን ጉሌድ ኧብቲዶን ስታዲየም። ጅቡቲያውያንም ለውጥ ሽተዋል። አዲስ አበባም በጣህሪር አደባባይ የወጣቶች አብዮት ቀልቧ ከተወሰደ ሰንበትበት ብሏል። ዐይኗ ከአልጀዚራ ላይ አልተነቀለም። ከዚህ ቀደም የሙዚቃ፣ እግር ኳስ እና የፊልም ቻናሎችን ብቻ በመክፈት የሚታወቁት የከተማዋ ካፌዎች ጣቢያዎቻቸውን ወደ አልጀዚራ እና ቢቢሲ ቀይረዋል። ብዙዎች “በሰላሙ” ዘመን ሊያዩ የማይሹትን የግብጽን ሰንደቅ ዓላማ አክብረውታል። ግብጽን እንደ ድሮው ከአባይ ውኃ ጋራ እያቆራኙ ተዘቆ ስለማያልቀው ፖለቲካዊ ተንኮላቸው እና ዘላለም የተዳከመች ኢትዮጵያን ለማየት ስለማይሰንፈው አቋማቸው የሚያወራ ጠፍቷል። ግብጽ አሁን ሌላ ነች። አዲስ አበባንም የጨነቃት.. ሌላ ነው። እኛስ እንደ ግብጾች . . .ብሎም እንደ ሊቢያውያን፣ ደግሞም እንደ ጀቡቲያውያን መኾን እንችላለን? የሚለው ነው አስጨናቂው ነጥብ።
ሁሉም የአዲስ አበባ ሚዲያዎች የግብጽን የወጣቶች አብዮት ሸፋን ሰጥተው ዘግበውታል። የአዲስ አበባ ጋዜጦች የፊት ገጾቻቸው በጣህሪር አደባባይ ትዕይንት ደምቋል። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የቱኒዚያውን የጃስሚን አብዮት አድበስብሶ የዘገበው ቢኾንም የግብጹን ንቅናቄ ግን ከሚጠበቀው በላይ ሽፋን ሰጥቶታል። ሬዲዮ ፋና ደግሞ ብዙዎችን ባስገረመ መልኩ ሰፊ እና ማራኪ ሽፋን ስጥቶታል። የኢትዮጵያ ብሎጎስፌርም ከብርቱካን ሚደቅሳ ከእስር የመፈታት ዜና በኋላ የተነቃቃው ሞሐመድ ቡአዚዝ ራሱ ላይ እሳት ለኩሶ የጃስሚን አብዮት መነሻ ከኾነበት ቀን ጀምሮ ነው። በስተመጨረሻም ቤን አሊም፤ ሙባረክም ሄዱ።
ብዙዎች የግብጽን አብዮት ስለ አብዮትነቱ ብቻ አልተከታተሉትም። የጃስሚን አብዮት ነፋስ አዲስ አበባን ይጎበኛልን? የሚለውን ጥያቄ በኅሊናቸው እያውጠነጠኑ ነው። ለዚህ አጠር ያለች ሐተታ ያነጋገርኳቸው አስተያየት ሰጭዎች በአዲስ አበባ ያለው መንፈስ ጥቁርም፣ ነጭም ነው ለማለት አልደፈሩም። በኢትዮጵያ እንደ ግብጽ አብዮቱ ሊነሳ የሚችልባቸው ከበቂ በላይ ምክንያቶች አሉ። ላይነሳ የሚችልባቸውም ምክንያቶች እንዲሁ።
ሰዎች ምን ይላሉ?
ከጃሰሚን አብዮት መባት በኋላ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ቢያንስ በትንሹ ፖሊስ በመንገድ ላይ ያሉ አዟሪዎችን ማሳደድ አቁሟል። ለዚህ ጽሑፍ አስተያየታቸውን የሰጡ ሰዎች እንደሚገልጹት ከኾነ አብዛኛው ሕዝብ “ካይሮ በታየው ሕዝባዊ ተቃወሞው ሰላማዊ እና የተደራጀ መኾን ቀንቷል። በሰልፈኞቹ እና በሠራዊቱ መካከል ባለው መተባበርም ተገርሟል”። አንዳንዶችን ደግሞ የግብጽ ከፍተኛው ወታደራዊ ምክር ቤት ሥልጣን በመያዙ ከ35 ዓመት በፊት ደርግ ሥልጣን የጨበጠበትን ዘመን እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል። ግብጻውያን የማንኛውንም የፖለቲካ ፓርቲ አጀንዳ ሳያነግቡ “ሙባረክ ይውረድ” በሚለው መፈክር ስር መጠቃለላቸው፤ የሐይማኖት ልዩነት እና ጎሰኝነት ሳያጠቃቸው መሰለፋችው እና ዋነኛውን ጠላት ለይተው (አንጥረው) መነሳታቸው ብዙዎች የሚያበሰለስሉት ቁም ነገር ኾኗል። የግብጽ አብዮትን እና በአንድ ቀን ከ200 መቶ በላይ ዜጎች የተገደሉበትን የ 1997 የሕዝባዊ መነሳሳት መልሶ በማስታወስ በወቅቱ ከነበረው ኹኔታ ጋራ ያነጻጸሩም ጥቂት አይደሉም።
በአዲስ አበባ የተፈጠረው ይሄ ብቻ አይደለም፤ “በግብጽ እና በቱኒዝያ ያሉ እንቅሰቃሴዎችን በሳተላይት ቴሌቪዥን እና ፌስቡክን በመሳሰሉ የሶሻል ኔትዎርክ ድረ ገጾች ኅብረተሰቡ መከታተል መቻሉ” ያስቀናቸው “እኛስ? በሚል መንፈሳዊ ቅንዓት ውስጥ እንዲያልፉ አድርጓቸዋል” ይላሉ ያነጋገርኳቸው አስተያየት ሰጭዎች። በብዙዎች ላይ የሚነበበው “እኛስ” የሚለው መንፈሳዊ ቁጭት ነው። የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የዴሞክራሲ እና ነጻነት እጦት፣ ቅጥ ያጣ አድሎዓዊነት፣ ጎሰኝነት እና ሙስና፣ የዋጋ ግሽበት፣ የሥራ አጥ ቁጥር በተለይ በከተሞች ውስጥ በከፍተኛ ቁጥር መናር እና ሥር የሰደደ ድህነት መንሰራፋቱ ለቁጭቱ ዐቢይ ምክንያቶች ናቸው ብለው ያምናሉ። “ከዕለት ወደ ዕለት ቅጥ እያጣ የመጣው የአቶ መለስ አስተዳድር የአፈና አገዛዝ ዜጎች በፍርኀት መንፈስ ተሸማቅቀው እንዲኖሩ ማድረጉ የጣህሪር አደባባይ መንፈስን ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ግድ ይለዋል” ሲሉም አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
ምክንያቶቹ ከበቂ በላይ ቢኾኑም መሬት ላይ ያሉት እውነታዎች አዲስ አበባ ውስጥ አብዮት ይነሳል ወይስ አይነሳም የሚለውን በድፍረት ለመናገር የማያስችሉ ናቸው። አንድ ዐቢይ ምሳሌ ተደርጎ የሚነሳው ባለፉት 30 ዓመታት ኢትዮጵያውያን ያለፉባቸው ለሰው ሕይወት ቁብ የማይሰጡ ሥርዐቶች ያሳረፉት የጭካኔ በትር አሰቃቂ ትዘታ ነው። የግብጽ እና የቱኒዚያ ሕዝቦች እንደ ኢትዮጵያ ሕዝብ ዘግናኝ የቅርብ ጊዜ ትዝታ የለውም። ኢትዮጵያውያን የአእምሮአቸው ጓዳ በቀይ ሽብር እና በ1997/98 ዓ.ም በተፈጸመው ግድያ እንደተሞላ ነው። እነዚህ ድርጊቶች ተከትሎ የደረሰው ማህበራዊ ትርምስምስ እና ትራጄዲ አሁንም የሩቅ ትዝታ አይደሉም። ብዙዎች መሰዋዕትነት ሊከፍሉ ይችላሉ። ግን መስዋዕትነቱ ፍሬ እንዲያፈራ እንጂ እንደ ከዚህ ቀደሙ ደመ ከልብ ኾኖ እንዲቀር አይሹም።
በግብጽ፣ በቱኒዚያ፣ በሱዳን እና በሊቢያ አፈናው እና አምባገነንነቱ የለየለት ቢኾንም የኢትዮጵያውያንን ያህል ዘግናኝ እና አረመኒያዊ አይደለም። የኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ኹኔታ እንድ ግብጽ ወደ አደባባይ ሊወጡ የሚችሉ ልሂቃን ጠራርጎ አስወጥቷል። የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት እጅግ ውስን ከመኾኑ ባሻገር የአፈና ሰለባ ነው። ኢትዮጵያ እጅግ ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ያለባት አገር ናት። በግብጽ እና በቱኒዚያ ፌስ ቡክ እና ትዊተር የጸረ ጭቆናው አቀጣጣይ ናቸው።
ዋና ግቡን ልዩነትን በማሰፋት ላይ ብቻ ያደረገ የሚመስለው የማንነት ፖለቲካ (ሐይማኖት፣ ጎሳ) ሌላ የቤት ሥራ መኾኑን ያምናሉ ሐሳባቸውን ያካፈሉኝ አስተያይት ሰጭዎች። ከዚህም በተጨማሪ ጠንካራ መነሾ ሊኾን የሚችል ሁሉንም የሚያስተባብር ፍንትው ብሎ የወጣ የአንድነት ምክንያት (Articulated Cause ) በሁሉም ዘንድ አለመኖሩ ሕዝቡ ወደ ዐመጽ ቢያመራ እንኳን ውጤቱ እንደሚታሰበው አልጋ ባልጋ እንደማይኾን የሚሰጉም አሉ። በ1966ቱ አብዮት መሬት ላራሹ እና የብሔር ጥያቄ ሁሉንም በዘውድ ሥርዐቱ ላይ እንዲነሳ ማስተባበር የቻሉ ነጥረው የወጡ እና ሁሉን ማነሳሳት የቻሉ የአንድነት ምክንያቶች ነበሩ። በወቅቱ በኢትዮጵያ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ የሚገኙ የኢትዮጵያ ተማሪዎች በሚያሳትሟቸው የኅትመት ውጤቶች እና በየጊዜው የሚደረጉ ውይይቶች የመሬት ላራሹ እና ሌሎች ጥያቄዎች እንዲሠርጹ እና ብሎም “ወደ ቁስ አካልነት እንዲቀየሩ” አድርገዋል። አሁን ባለው እውነታ በኢትዮጵያ ጠንካራ ነጻ ተቋማት ማጣት እና እዚህም እዚያም የተበታተነ ሐሳብ መኖሩ የሚፈለገው የለውጥ ኀይል (Critical Mass) እንዳይመጣ እንቅፋት ሊፈጥር እንደሚችል ብዙዎች ይሰጋሉ።
የተቃዋሚዎች ኹኔታ. . .
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ኀይሎች ያሉበት የተበታተነ እና የዘቀጠ ኹኔታ በሂደት ትግሉን መርቶ ውጤት ለማምጣት የሚያስችሉ ትክክለኛ ኀይሎች እንዳልኾኑ እና አግባብነት የሌላቸው (Relevant) እንዳያደርጋቸው ሰግተዋል። “ሕዝቡ ምንም እንኳን ሕዝባዊ ቁጣውን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች (በተለይ አልጀዚራ) መከታተሉ ንቃተ ኅሊናው እና የትኩረት አቅጣጫው ያስደሰታቸው ቢኾንም፤ ሕዝባዊ ተቃወሞው በወጣቶች እና ልሂቃን የተቆሰቆስ ቴክኖሎጂ መር እና ሕዝብ ወለድ አብዮት በመኾኑ ራሳቸውን እንዲያዩ ያሰገደዳቸዋል” ይላሉ አንድ ለአንድነት፤ ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ቀረብ ያሉ ውስጥ አዋቂ። ለዚህም በቅርቡ አንድነት ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የጥናት ቡድን ለአምስት ዓመት ያውጣው ስትራቴጂ እና የአፈጻጸም ዕቅድ አስመልከቶ የሰጠውን መግለጫ ከዚህ ደወል ጋራ ያገናኙታል።
ባለፉት አምስት ዓመታት ዋነኛ መለያቸው መከፋፍል የነበረው የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ስለ አንድነት እና መተባበር ማሰብ እንዳለባችው የግብጹ እንቅስቃሴ የበለጠ ነግሯቸዋል። ያለ ጠንካራ አደረጃጀት የየትኛውም ሕዝብ ትግል ዳር አይደርስም። የተለያዩ የፖለቲካ ኀይሎች እና ቡድኖች በኢትዮጵያ ስለሚመሠረተው የፖለቲካ ሥርዐት ብቻ ሳይኾን “ኢትዮጵያ” ስለምትባለው አገር ማንነት ስምምነት የላቸውም ወይም ስምምነት ላይ ለመድረስ ሲሞክሩ አይታዩም።
የመለስ ትምህርት. . .
መለስ ዜናዊ፣ ሮበርት ሙጋቤ፣ ቤን አሊ፣ አልበሽር፣ ሆስኒ ሙባረክ፣ መንግሥቱ ኀይለማርያም… ምን አንድ ያደርጋቸዋል? በሚገዟቸው ሕዝቦች ኅሊና ውስጥ ስላላቸው “እውነተኛ” ቦታ እና ስለራሳቸው እና ሰለሚመሩት አገር ባላቸው ቅዥት። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከቀደሞው የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ፔንግ በምን ዐይነት ኹኔታ የተለይ ሊያስቡ ይችላሉ? ሊ ፔንግ በ1994 እ.ኤ.አ የታይናሚን አደባባይ ጭፍጨፋን በተመለከት ለሬውተር እንዲህ ብለው ነበር ስል- 1989 ጭፍጨፋ። “ታሪክ ፍርዱን ሰጥቷል። . . . በሚቀጥሉት ዐሥር እና ኻያ ዓመታት የወሰድናቸው ርምጃዎቸ ለቻይና ደኅንነት እና መረጋጋት እንዲሁም ለዓለም ሰላም ወሳኝ እንደ ነበሩ ትገነዘባላችሁ።” ብለው ነበር የታያሚን አደባባይን ጭፍጨፋ አስፈላጊነት ሲያስረዱ። ሁሉም አምባገነን የሚፈጽመውን ግፍ አስፈላጊነት ይናገራል። የአቶ መለስ መንግሥትም ከሙባረክ፣ ከቤን ዐሊ እና ከመንግሥቱ ትምህርት ለመውሰድ ሐሳብ ያለውም አይመስልም። ምን አልባት አቶ መለስ የሚማሩት እና የተማሩት ሕዝባዊ መነሳሳቱ እውን ቢኾን እንዴት ማኮላሸት እንደሚቻል ማውጠንጠንን ብቻ ነው።
በኢሕአዴግ በኩል በሶሻል ድረ ገጾች ላይ የሚታየው የተቃውሞ ዝንባሌ እና ሕዝቡ ለግብጽ እና ለቱኒዚያ ሕዝባዊ መነሳሳት የሰጠው ትኩረት ድንጋጤን እየፈጠረ እንደኾነ የፓርቲው ምንጮች ይናገራሉ። ባለፈው ሳምንት “ኢንተርኔት ላይ ባቀረብካቸው ጽሑፎች እና ለተለያዩ መገናኛ ብዙኀን በሰጠኀቸውም ቃለ-ምልልሶች ኢትዮጵያም ውስጥ ግብጽና ቱኒዝያን መሰል ዐመፅ እንዲጀመር ለመቀስቀስ ሞክረኻል” በሚል የጋዜጣ ፈቃድ ለዓመታት የተነፈገውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የደረሰው ወከባ የአቶ መለስ አስተዳደር ያለበትን እውነታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። ነገር ግን አገዛዙ ለኑሮ ውድነቱ ተጠያቂነቱን ወደ ነጋዴው በማዞር ለችግሩ መፍትሄ የሰጠ ያስመሰለበትን ጊዜያዊ የማስቀየሻ ታክቲክ የተሳካ የገበያ ዋጋ ማረጋጊያ አድርጎ ቆጥሮታል። በዚህም ቢያንስ የሰሞኑን ነፋስ ሊያልፈው እንደሚችል ተማምነዋል። በተወሰኑ ሸቀጦች ላይ የወጣው የዋጋ ተመን ይህን የሰሞኑን ኹኔታ አሰቀድሞ ከመገመት ጋራ አያይዘው ያዩትም አልጠፉም።
አገሪቱ ካለችበት የጸጥታ ኹኔታ፣ የሠራዊት አመሠራርት እና አደረጃጀት አንጻር ሕዝቡ ወደ ዐመፅ ቢያመራ ጦሩ ሕዝባዊውን ዐመፅ እንደማያግዝ በፓርቲው ሰዎች ዘንድ መተማመን አለ። የአገዛዙ የስለላ እና የአፈና መዋቀር መጠናከር (ሊግ፣ ፎረም …አንድ ለአምስት የመሳሰሉት) የበለጠ ማን አለብኝነትን እንዲያሳይ እያደረገው ነው። በተለይ ደግሞ አብዛኛው ሕዝብ በተቃውሞ ፖለቲካ ተስፋ መቁረጡ እና በአንጻራዊ ኹኔታ መንግሥታዊ ሥልጣን ለመያዝ የሚችል የተደራጀ ኀይል አለመኖሩ የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ዐመፅ ይነሳል ብለው እንዳይገምቱ አድርጓቸዋል። “ጉዳዩ” ጅቡቲ እና ሊቢያ ደርሶም።


Let’s not harbor any illusions, the situation of Ethiopia is very different from the north Africans political momentum. The simple justification is the Ethiopian people leading usual regular and peaceful life while the political uprising is escalating is in most Arab countries.
The kind of expression ”ጅቡ…ቲም!?” is just a bed time story books of children and thank you for your wise and kind hearted but the Ethiopian people have no ears to listen this something for nothing mentality.
By the way never loss sight of the fact by considering Ethiopians as only Adissabebans. Doing that is both troubling and unhelpful.
I just want to ask you one question. Egypt and Tunisa have more economical strength than ours but the people still ask there is no economical power and comparing Ethiopia to one of this countries we are not even near them. SO do you think we shouldn’t ask the same question they did, if not why?
Brother Girma, your anaysis and forecast on the subject matter is perfect. I couldn’t pin point an iota from your article. Joro yalew yisima engdih!
Dear Teshome,
As the son of Libyan dictator told his people you did the same: clarified the differences b/n our situation and that of egypt and tunisia. That may help you to have good sleep but it does not hold water.
One thing has been crystal clear in the recent north african political dynamics. Whatever ideological, racial and religious differences ppl have the quest for freedom is a universal fact. Very soon we will witness that on the streets of Addis, Nazreth, Bhair Dar etc.
You better contemplate where your darling Meles and Azeb would go, Period!!!!!!!!
Nobody thought Tunisia and Egypt will end up like this. Libyan is on the same path, I think Muamar Gadafi and Meles amy have the same approach, shoot on civilians and terrorize your own public, but in the end they will face the same music-OUTRAGE OF THE OPRESSED MASSES. Our struggle can atart by capturing kebele and woreda cadres and woyane loyalists, but the end is inevitable-WOYANE AND ITS APARTHEID POLICY WILL FAIL TOGETHER WITH THE PERPETRATORS. Azeb Mesfin’s grand theft scheme and the billions of dollars Meles looted from the country will be freezed and he will have nowhere to go. He might turn to Saudi Arabia, but the revolution will follow him even there. WE WILL BE LIBERATED!
Samson
Sir, It is only enough to look back to what the diaspora politicians and their misinformed supporters have done for the past two decayed.
Currently they were totally curtain on the funny business of politics and we were their unbelievable wittiness of backpedaling propaganda of the diaspora out let media to initiate Arab style of uprising in Ethiopia. In fact they look their best on home politics- failure.
The uprising, which is remotely controlled by DC politicians, is fundamentally hum pared by several factors and the reality of that finding is much much worse than flipping a coin.
Time will tell us, You will definitely be embarrassed and will suffer by humiliating loss and At the end of the day, you know know you might be hopeless.
Teshome- tell the truth just don’t talk trash. You simply “Cadre of Woyane” better shut up!