እዚህ ብርሃኑ፤ እዚያ መለስ

ዶ/ር ብርሃኑን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት የቅንጅት አመራሮች ከእስር በተፈቱ ማግስት ነበር። ያን እለት በጎብኚዎቹ ብዛት እፎይታ ያጣው ብርሃኑ በልቡ ምን እንደሚያብሰለስል ለመረዳት የሚያስቸግር ነበር፤ የጠረጠርን ብንኖርም። ስለ ቀጣዩ እርምጃ አንሥቶ ለመጨዋወትም ሁኔታው የሚፈቅድ አልነበረም። ይህ ማለት ግን ብርሃኑ ቀጥሎ ስለሚያደርገው ነገር፣ ስለሚይዘው አቋም አላሰበበትም ማለት አልነበረም። አሁን ብርሃኑ በብዙ መልኩ አልተለወጠም፤ በብዙ መልኩ ተለውጧልም። በአካላዊ ቁመናው፣ በአነጋገሩ እና በአቀራረቡ አልተለወጠም፤ በክርክር አካሔዱም ቢሆን የ97ቱ ወይም የኢኮኖሚክ ባለሞያዎች ማኅበሩ “ርዕይ 2020”ው ብርሃኑ ነው። የሚያምንበትን በጋለ ስሜት፣ በሰላ የአመክንዮ ክርክር እና በተራ ሰው ቋንቋ ማቅረብን አልተወም፤ ሲያስፈልገውም ሐልዮታዊ ትንተና ማቅረብ ይጀምራል። አሁንም ይስቃል፣ ፈገግ የሚያሰኙ መልሶችን ይሰጣል። በንግግሩ ይዘትና በፖለቲካ አቋሙ ግን ተቀይሯል። አሁን የጀርመን ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ባዘጋጀው ስሚ ላይ እንዲገኝ የጋበዘውና እግረ መንገዱን ስቶኮልም ያረፈው ብርሃኑ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ በሚያቀርበው የመጀመሪያ ደረጃ የመፍትሔ አማራጭ “የነጻነት ጎሕ ሲቀድ”ን ከጻፈው ብርሃኑ ይለያል።

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ስብሰባ፤ ስቶክሆልም መጋቢት 2፣ 2003

እዚህ፣ አሁን እየሆነ ያለው በምንም መልኩ እዚያ አሁንም ሆነ በቅርቡ ሊካሄድ የሚችል አይደለም። እዚህ ሰውየው በሚያራምደው ሐሳብ ምክንያት በወንጀልኝነት አይፈረጅም፤ እዚያ ግን የሞት ፍርድ የተበየነበት ተፈላጊ “ወንጀለኛ” ነው። አድማጮቹና ተወያዮቹም እንዲሁ እዚህ በወንጀል ተባባሪነት የሚከሳቸው የለም፤ እዚያ ግን በአቶ መለስ ፍርድ ቤት በአባሪነት ሊከሰሱ እንደሚችሉ ያውቁታል።

  ስቶክሆልም መጋቢት 3፣ 2003 የ ግንቦት 7 ሕዝባዊ ስብሰባ

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፤ ስቶክሆልም መጋቢት 3፣ 2003

ይህ የስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም ነው፤ ሰውየው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፤ አድማጮቹና ተወያዮቹ ደግሞ እዚህ የሚኖሩ “የግንቦት 7” አባላት፣ ደጋፊዎች እና ሰውየውን ለመስማት የተሰበሰቡ ሌሎችም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ያ ደግሞ የእነዚህ ሰዎች ነፍስና ደም የታተመበት አገር ነው- ኢትዮጵያ። ሆኖም እነርሱ እዚህ አሁን ስለሚነጋገሩበት ጉዳይ እዚያ በአደባባይ መነጋገር የሚታሰብ አይደለም፤ የሰሜን አፍሪካው አብዮት፣ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ እና እነርሱ…።

የመጋቢት 3 (ማርች 12) የስቶክሆልም ሕዝባዊ ስብሰባ በተካሄደበት አዳራሽ መግቢያ ላይ እና በየግድግዳዎቹ ላይ የተለጠፈው “ማስታወቂያ/ማሳሰቢያ” ለእንግዳ ተመልካች ጥያቄን የሚያጭር ሊሆን ይችላል። “ከተፈቀደላቸው አካላት ውጭ” ፎቶ ማንሣት፣ ድምጽም ሆነ ምስል/ቪዲዮ መቅረጽ ተከልክሏል። “ሕዝባዊ ስብሰባ ጠርቶ ፎቶ ማንሣትና ቪዲዮ መቅረጽን መከልከል ምን ይሉታል?” ብሎ የሚጠይቅ መልሱን የሚያገኘው በኢትዮጵያውያን የስደት ፖለቲካ ጥልፍልፍ ውስጥ ነው። ወደ አገር ቤት በተለያየ ምክንያት የሚመላለሱ በተለይም በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ከመንግሥት ጋራ የሚያገናኛቸው ሥራ ያላቸው ስደተኞች ተቃዋሚዎች በሚያዘጋጁዋቸው ስብሰባዎች ላይ መገኘታቸው በኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰዎች እንዲታወቅ አይፈልጉም። ስብሰባው “ግንቦት 7” የጠራው፣ ብርሃኑ ነጋ የሚገኝበት ሲሆን ደግሞ የእነዚህ ሰዎች ስጋት ይጨምራል።

ተሰብሳቢዎቹ በከፊል፤ ፎቶ ginbot7.org


ስለዚህም በዚህ ስብሰባ መገኘታቸውን የሚጠቁም ፎቶም ሆነ ቪዲዮ መኖሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ፍላጎታቸውን አደጋ ውስጥ ሊከት እንደሚችል ይቆጠራል። አንድ ወዳጄ እንዳጫወተኝ ከሆነ በ1997/98 (እ.ኢ.አ) ምርጫ ወቅት ቅንጅትን በመደገፍ በተጠሩ ሰልፎች ይሳተፉ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በኋላ ፓስፖርት ለማሳደስ/ለማስለወጥም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ወደ ኤምባሲ ሲሔዱ በሰልፍ መሳተፋቸው እንደጥፋት እየተጠቀሰ፣ ፎቶዎች እንደማስረጃ እየቀረቡ ተወቅሰዋል፤ አንዳንዶቹም ተገቢውን “ግለ ሒስ” ባለማድረጋቸው በዜግነታቸው ብቻ ሊያገኙት ይገባ የነበረውን አገልግሎት ተከልክለዋል።

የዚያኑ ያህል ደግሞ በዚህ መሰል ስብሰባዎች ላይ መገኘት እና ዶ/ር ብርሃኑን ከመሰሉ ታዋቂ የፖለቲካ መሪዎች ጋራ ፎቶ መነሣቱን የሚፈልጉትም አሉ። እነዚህ አንድም ፎቶውን ለታሪካዊ ፋይዳው ብቻ ይፈልጉታል፤ አሊዚያም ጥገኝነት ለማግኘት አንድ ማስረጃ ሊሆናቸው ይችል እንደሆነ ያብሰለስላሉ።

ዶ/ር ብርሃኑን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት የቅንጅት አመራሮች ከእስር በተፈቱ ማግስት ነበር። ያን እለት በጎብኚዎቹ ብዛት እፎይታ ያጣው ብርሃኑ በልቡ ምን እንደሚያብሰለስል ለመረዳት የሚያስቸግር ነበር፤ የጠረጠርን ብንኖርም። ስለ ቀጣዩ እርምጃ አንሥቶ ለመጨዋወትም ሁኔታው የሚፈቅድ አልነበረም። ይህ ማለት ግን ብርሃኑ ቀጥሎ ስለሚያደርገው ነገር፣ ስለሚይዘው አቋም አላሰበበትም ማለት አልነበረም። አሁን ብርሃኑ በብዙ መልኩ አልተለወጠም፤ በብዙ መልኩ ተለውጧልም። በአካላዊ ቁመናው፣ በአነጋገሩ እና በአቀራረቡ አልተለወጠም፤ በክርክር አካሔዱም ቢሆን የ97ቱ ወይም የኢኮኖሚክ ባለሞያዎች ማኅበሩ “ርዕይ 2020”ው ብርሃኑ ነው። የሚያምንበትን በጋለ ስሜት፣ በሰላ የአመክንዮ ክርክር እና በተራ ሰው ቋንቋ ማቅረብን አልተወም፤ ሲያስፈልገውም ሐልዮታዊ ትንተና ማቅረብ ይጀምራል። አሁንም ይስቃል፣ ፈገግ የሚያሰኙ መልሶችን ይሰጣል። በንግግሩ ይዘትና በፖለቲካ አቋሙ ግን ተቀይሯል። አሁን የጀርመን ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ባዘጋጀው ስሚ ላይ እንዲገኝ የጋበዘውና እግረ መንገዱን ስቶኮልም ያረፈው ብርሃኑ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ በሚያቀርበው የመጀመሪያ ደረጃ የመፍትሔ አማራጭ “የነጻነት ጎሕ ሲቀድ”ን ከጻፈው ብርሃኑ ይለያል።

መለስን በሙባረክና በጋዳፊ ውስጥ

ብርሃኑ አገራቸውን በሰሜን አፍሪካው አብዮት (ሕዝባዊ አመጽ) ውስጥ ለመረዳትና ለመተንተን ከሚሞክሩት በሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው። ለዚህም ነው የቱኒዚያውን ቤን አሊንና ‘ክብርት’ ሌባ ባለቤታቸውን ካባረረው አመጽ ጀምሮ ባደረጋቸው ንግግሮች ሁሉ አብዮቱን የምር ለመረዳትና ለማስረዳት ሲሞክር የሚታየው። ይህ አብዮት ግን የብርሃኑን የልጅነት ሕልም ከበላው የኢትዮጵያ አብዮት የተለየ ነው፤ በብዙ ምክንያቶች።

ዛሬም ብርሃኑ አነሰም በዛም የሚያቀርበውን ንግግር በጽሑፍ አዘጋጅቶ የማቅረቡን ጥሩ ልማድ አልተወም። በስቶክሆልሙ ስብሰባ ያቀረበው ንግግር (ፌብርዋሪ 12 እና 13) ዳላስ እና ሂውስተን ላይ ከሰሜን አፍሪካው አብዮት በመነሣት ስለኢትዮጵያ ካቀረበው ሙግት የቀጠለ መሆኑን በንግግሩ መጀመሪያ ገልጿል። “የሰሜን አፍሪካ አብዮቶች ስለ አምባገነኖች ያለንን ግንዛቤ አዳብረውታል” የሚለው ብርሃኑ የኢትዮጵያውን አምባገነን በቤን አሊ፣ በሆስኒ ሙባረክ እና በጋዳፊ ውስጥ ለመመልከት፣ ለመረዳት እና ለመተንኮስ ይፈልጋል፤ ለአድማጮቹ ማካፈል የሚፈልገውም ይህንኑ ነው። ይህ ግን የንግግሩ ቁልፍ ግብ አይደለም፤ በመጨረሻ ስለተግባራዊ ምላሽ በስሜት ሲቀሰቅስ ታገኙታላችሁ።

ለብርሃኑ ጊዜው የሕዝባዊ አመጽና አብዮት ነው፤ በኢትዮጵያ ጭምር። ለዚህም ይመስላል ብርሃኑ “ደርሷል፤ ቀርቧል” ስለሚለው አብዮት ተግባራዊ ስልቶች መናገርን የመረጠው። አብዮቱ በአገራችን በተሳካ ሁኔታ እንዲጀመርና እንዲጨረስም ሦስት ስልቶች ከወዲሁ ሊሠራባቸው ይገባል ብሎ ያምናል።

1.ጠላትን መነጠል
ዶ/ር ብርሃኑም ይሁን የሚራው ድርጅት (ግንቦት 7) የወቅቱ የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ብለው የሚለዩት ቡድን ብዙዎች እንደሚያስቡት ሰፊ አይደለም ወይም እየጠበበ ነው። በዚህ ስብሰባም ሆነ በድርጅቱ ድረ ገጽ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እንደሚታየው እነዶ/ር ብርሃኑ ጠላታቸውን በስምም ሆነ በተግባር በግልጽ የመለየትን አስፈላጊነት ትኩረት ሰጥተውታል። እነብርሃኑ “ወያኔ” የሚለውን በተለምዶ ብዙ ተቃዋሚዎች የአቶ መለስን ድርጅትና አገዛዝ የሚጠሩበትን ስያሜም እየተዉት ነው። በምትኩም “የትግራይ ገዢ ጉጅሌ” የሚል ስም አውጥተውላቸዋል፣ ለነአቶ መለስ። “ጉጅሌ” ማለት በትግሪኛ “ቡድን” ወይም “ኮሚቴ” እንደማለት ነው። “ቡድኑን ከትግራይ ሕዝብና ከወያኔ አባላት ጭምር መለየት” የትግሉ አንድ ስልት መሆኑን ብርሃኑ ለተሰብሳቢዎቹ አስረድቷል። ይህ ስልት በአቶ መለስና በቡድናቸው ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶችን በትግራይ ሕዝብ ላይ የተነጣጠሩ እያስመሰሉ ለሚያቀርቡ መድኀኒት ነው ብሎ ያምናል።

“ጉጅሌው የትግራይ ሕዝብና የኢትዮጵያ ጠላት እንደሆነ ማመንና ማሳመን አለብን…የምንታገለው የትግራይን ሕዝብ ነው የሚል አንድምታ የሚሰጥ ነገር እንዳናደርግ መጠንቀቅ አለብን።” ይህ በከፊል ስጋት የፈጠረው ስያሜ ብዙዎች የሚያነሡ የሚጥሉትን ፖለቲካዊ አደጋ ለማስቀረት ያለመ ነው። ዶ/ር ብርሃኑ እንደሚለው በአቶ መለስ ዙሪያ የተሰበሰበውና “አገር ለማተራመስ የማይመለሰው” “ጉጅሌ” አባላት በጣት ተቆጥረው የሚያልቁ ናቸው፤ ከ15 አይበልጡም። በማስታወሻ ደብተሬ አስፍሬ ሳልጨርሳቸው እርሱ ወደ ሌላ ጉዳይ ገባ፤ መለስ ዜናዊ፣ አዜብ መስፍን፣ ሥዩም መስፍን፣ በረከት ስምኦን…። ጀሌዎች ግን አሏቸው። ሕወሃትን ለሚወዱ ሰዎች “አሁን ያለው ህወሓት የቀድሞ ህወሓት አለመሆኑን” ማስረዳት እንደሚገባ ጭምር የሚያምነው ብርሃኑ ጉጅሌው ተነጥሎ ብቻውን የሚቆምበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ይጠብቃል። “ድሮ የምታውቁት ህወሓት የለም።”

2. ወዳጅን ማብዛት
ፖለቲካ ቢቻል ወዳጅ ባይቻል ደግሞ ደጋፊ የማብዛት “ጨዋታ” ነው። ለእነብርሃኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወዳጅ ማብዛት የሚያስፈልግበት ወቅት ነው። ወዳጅ በማብዛቱ ስትራቴጂ ውስጥ የመጀመሪያው ተጠቃሽ መከላከያ ሠራዊቱ ነው። “መከላከያ ሠራዊቱ የኢትዮጵያ አለኝታ መሆኑ እንዲሰማው ማድረግ አለብን” የሚለው ብርሃኑ “ሕልማችን ከሕልማቸው ጋር ተመሳሳይ ነው” ብሎ ያምናል።

የመከላከያ ሠራዊት መሪዎችና አባላት በሰሞኑ ሕዝባዊ አብዮቶች ውስጥ የተጫወቱትን “ቁልፍ” ሚና ለሚገነዘብ ተመልካች የብርሃኑ ንግግር ትርጉም ይሰጣል። ሆኖም ብርሃኑ ሠራዊቱን ከመሪዎቹ ለይቶ ይመለከታል፤ ይህም በሰሜን አፍሪካው አብዮት አንድ ሆኖ የቀረበው የየአገሮቹ ጦር ሠራዊትና አመራሩ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ የተለየ ገጽታ ሊኖረው እንደሚችል የሚጠቁም ነው።

“ጥርጣሬያችን በጥቂት አመራሮቹ ላይ እንጂ በሠራዊቱ ላይ አይደለም” የሚለው የንግግሩ አካል እነዚህ አመራሮች የሕዝባዊ ንቅናቄው አካል የመሆናቸው እድል አነስተኛ ስለመሆኑ የታመነበት ያስመስላል። “ግንቦት 7” ከወራት በፊት ባወጣው አንድ ጥናት አከል ጽሑፍ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ እና ቁልፍ የአመራር ቦታዎች ፍትሐዊና ርትአዊ ባልሆነ መጠን በአንድ ብሔር ተወላጆች የተያዘ መሆኑን ያሳያል። ምናልባትም የዶ/ር ብርሃኑ ስልት እነዚህ ከፍተኛ የሠራዊቱ መኮንኖች የቁርጥ ቀን ሲመጣ “ከጉጅሌው” ጋራ ይቆሙ ይሆናል ብሎ እንደሚሰጋ መገመት አይቸግርም። ብርሃኑም ሆነ የመናገር እድል ያገኙት ተሰብሳቢዎች ደጋግመው ያነሱትም የሠራዊቱ አባላት ከሆኑ የቤተሰባችን አባሎችና ጓደኞቻችን ጋራ በግልና በጋራ ከወዲሁ መነጋገር እንዳለብን ነው።

አንድ የሠራዊት አባል የሆነ ዘመዳችንን አግኘነው እንበል፤ ምን እንለዋለን? “የግብጽና የሊቢያ ጦር የሚያደርጉትን እየተከታተልክ ነው? ግን እንደው አሁን እዚህ አገር ሕዝባዊ ተቃውሞው ገንፍሎ ቢወጣ አንተና ጓደኞችን ምን ታደርጋላችሁ? በዚህ ጉዳይ ከጓደኞችህ ጋር ትነጋገራላችሁ? አለቆቻችሁ ሕዝቡ ላይ ተኩሱ ቢሏችሁ ጨክናችሁ ትተኩሳላችሁ?…” ጥያቄ፣ ስጋት፣ ንግግር፣ ክርክር….ይቀጥላል። ብርሃኑ ይህ ንግግር ከወዲሁ መጀመር አለበት ሲል ይጎተጉታል፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም የጦሩ አባላት ለሆኑ ዘመዶቻቸውና ወዳጆቻቸው እየደወሉ እንዲያናግሯቸው ይፈልጋል። ብርሃኑ ሠራዊቱን “ የሚደርስብህን መከራ እናውቃለን፤ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ወገኖችህ ላይ እጅህን አታንሳ” ሲል ይጠራዋል።
ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወዲህ ብዙም የማይነገርለት የኢትዮጵያ ጦር ምን እያሰበ ይሆን?

“የወዳጅ ማብዛት” ስትራቴጂው ሌላው ኢላማ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶችና አባሎቻቸው ናቸው። ብርሃኑ “ሰው ባርነቱን ለማወቅ ስንት ዓመት ይፈጅበታል?” በሚል ጥያቄ የድርጅቱ አባል ፓርቲዎች “የጉጅሌው” አገልጋዮች መሆናቸውን በሚሸነቁጥ ጥያቄ ለማስታወስ ሞክሯል። “እነርሱ [እነመለስ] ከተቃዋሚዎች በላይ የሚንቁት እናንተን ነው፤ ጉጅሌው የተደላደለ ቢመስልም መሠረት የለውም…ይናዳል…” በማለትም ራሳቸውን እንዲያገሉ ወትውቷል።
3. ጥቃት መጀመር
ሰውየው “ዛሬ አጥቂዎች እኛ ነን፤ ይህንንም አሁን መጀመር አለብን” ብሎ ያምናል። በአገር ቤት እርሱና ድርጅቱ በተጨባጭ ምን እየሠሩ እንደሆነ በዝርዝር መናገር አይፈቅድም። ለዚህም የድርጅቱ አወቃቀርና አገር ቤት ያለው አፈና “የማርያም መንገድ” ሰጥተውታል። ብርሃኑ የማግኘት እድል የገጠመው ማንኛውም ሰው በጉጉት የሚጠይቀው የመጀመሪያ ጥያቄ ይህ ቢሆን አይገርምም። በተመሳሳይም ድርጅቱ አገር ቤት ምን እየሠራ እንደሚገኝ በዝርዝር መግለጽ የዓላማውን አራማጆች አደጋ ውስጥ መክተቱ እንደማይቀር የታወቀ መሆኑ አድማጮቹ የብርሃኑን አማራጭ እንዲቀበሉት ይጠይቃል።

ይናገራል! ከግንቦት 7 የስቶክሆልም ተወካይ ከአቶ ቸኮል ጌታሁን እና ከፕሮግራሙ አስተዋዋቂ የቀድሞ የኢቲቪ ጋዜጠኛ ጋራ(ፎቶ፤ginbot7.org)


ይሁንና “የሚቀጥሉት ሳምንታትና ወራት ወደፊት የሚያራምደን አንድ ነገር ይዘው ይመጣሉ” የሚል ማስተማመኛ ከመስጠት ወደ ኋላ አይልም።
ኢትዮጵያ ውስጥ የመለስን አገዛዝ የሚያስወግድ ለውጥ በቅርብ መምጣቱ የሚያጠራጥራቸውን ሰዎችም “አትጠራጠሩ” የሚል ማረጋገጫ ይሰጣል። በስቶክሆልሙ ስብሰባ ደጋግሞ ያለው ይህንን ነው፤ Stay tuned!

ከአገር ውጭ የሚገኙ የመለስ ተቃዋሚዎች ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት የተሸጋገሩበት ወቅት መሆኑ ከዶ/ር ብርሃኑ ንግግር የምንረዳው አንድ ነገር ነው። በሚዲያው ዘርፍ “ኢሳት ጉጀሌውን ወደ ተከላካይነት አውርዶታል።” ብርሃኑ እንደሚለው ከሆነ በሬዲዮኖች እና በፌስቡክ የሚደረገው “ማጥቃትም” መነቃቃትን እየፈጠረ ነው።
ብርሃኑ በውጭ ከሚኖረውና የመለስን አገዛዝ ከሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን ተጨባጭ ተግባራዊ ምላሽ እንደሚፈልግ ደጋግሞ ይናገራል። በማጥቃት እንቅስቃሴውም ሁሉም በየተሠማራበት የጥቃቱ ተሳታፊ እንዲሆን ይከራከራል፤ ከግብጽ፣ ከሊቢያና ከቱኒዚያ ተሞክሮ በመነሳትም የማጥቃቱን አድማስ አስፍቶ ለማሳየት ይሞክራል። “ለወያኔ ባለሥልጣናት ዲግሪ ሲያድሉ የከረሙ ዩኒቨርሲቲዎች” ከጋዳፊ ልጅ እርዳታ እንደተቀበለው የለንደን ስኩል ኦፎ ኢኮኖሚክስ በአደባባይ ሀፍረት እንዲለብሱ ማድረግ የማጥቃቱ አንድ ምሳሌ ሆኗል። የ“ጉጀሌው አባላት ምን ንብረት አላቸው? ልጆቻቸውን ለማስተማር ስንት ይከፍላሉ፣ ስንት ቤት አላቸው…” የሚሉትን መረጃዎች ይፋ ማድረግም እንዲሁ ከሚዲያ ዜናነት ያለፈ ፋይዳው ያለው ነው። እንግዲህ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በውጭ ያለውን፣ አገር ውስጥ ያሉት ደግሞ የዚያን እንዲያጋልጡ ነው ጥሪው።

ኤርትራ – ኦኤንኤልኤፍ – ብርሃኑ

ብርሃኑ ስለ አዲሱ “ሁለ ገብ” ስትራቴጂ ያለውን አመለካከት ለመፈተን ከኤርትራ ጉዳይ የተሻለ ፈተና ማቅረብ ይቸግራል። የስቶክሆልሙ ስብሰባ ለጥያቄና መልስ እንዲሁም ለውይይት ሲከፈት መጀመሪያ የቀረበው ጥያቄም ይኸው ነበር። የ”አንድነት/መድረክ” አባል የሆኑ አንድ ተሰብሳቢ “ግንቦት 7” ከኤርትራ እና ከኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ONLF) ጋር መሥራቱ እንደማይዋጥላቸው በማብራራት በትብብሩ የሞራል እና የተግባር ተጠየቅ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ አንጸባርቀዋል። “በኤርትራ ተመክቼ አዲስ አበባን ነጻ አወጣለሁ ብዬ አይታየኝም” ነበር ያሉት።

ይህ ጥያቄ በተለይም ብርቱካን ሚደቅሳ በድጋሚ እስክትታሰር ድረስ ተስፋቸውን በሙሉ በአገር ውስጥ ሰላማዊ ትግል ላይ ብቻ ጥለው በነበሩ ዜጎች በተደጋጋሚ የሚነሳ ነበር። የብርቱካን መታሰርና የአፈታቷም ብሽቅነት፣ በባሰ መልኩ ደግሞ የ2002ቱ አሳፋሪ ምርጫ ብዙዎች ቢያንስ እነብርሃኑን የሚወቅሱበትን የሞራልና የተግባር መሠረት በድጋሚ እንዲመረምሩ አድርጓል። ሆኖም ጥያቄው አሁንም በተለያየ መልኩ ይቀርባል።

ጥያቄውን ለመመለስ የተዘጋጀው ሰው ይህንን እውነታ በሚገባ የተረዳው ይመስላል። ምናልባትም እርሱ ራሱ አሁን ከሚያቀነቅነው አቋም ላይ ለመድረስ በዚሁ አጣብቂኝ በሚመስል ‘ፈተና’ አልፎ ይሆናል። ከኤርትራ ጋራ የሚፈጠረውን ትብብር በፍርሃት የሚመለከተው ስጋት “ከዝቅተኝነት ስሜት የሚመነጭ ነው” በማለት ክርክሩን ይጀምራል። “ዓላማዬ ኢትዮጵያ ነጻ እንድትሆን ነው። ይህቺ አገር እንድትፈጠር የእኔ አመለካከት ካላቸው ወገኖች እገዛ ባገኝ እወድ ነበር። ይህ ካልሆነ ከሌሎች አመለካከቱን ባይጋሩም ሊረዱኝ ከሚፈልጉ ወገኖች እገዛ ባገኝ አልጠላም።” ይህም የትብብሩ ዋነኛ መሠረት ተግባራዊ ፍላጎት (pragmatic) እንጂ የግድ ሐልዮታዊና ሞራላዊ መመሳሰል አለመሆኑን ለማጠየቅ ይመስላል። ዴሞክራትነቱን ማንም የማይጠይቀውን አንድ ጀግና በምሳሌነት ያነሣል፤ ማንዴላ። “ማንዴላ ከእስር እንደተፈታ ጋዳፊንና ካስትሮን በክፉ ቀን ስለሰጡት ድጋፍ አመስግኗቸዋል፤ ይህ ማንዴላን ኢዲሞክራት ያደርገዋል?” ይጠይቃል።

ብርሃኑ ከኤርትራ ጋራ የሚደረግን ማንኛውንም ትብብር የሚቃወሙ ሰዎችን ወይም አስተያየቱን ያለርህርሄ ለመተቸት የወሰነ ይመስላል። “ከኤርትራ ጋራ ባለመነካካት የተሳሳተ የንጹሕነት፣ ያለመነካካት ስሜት ያላችሁ ይመስላል” በማለት የተቺዎቹን (ሐሳባዊ ወይም ተጨባጭ) የሞራል መሠረት ለመናድ ይሞክራል። አስከትሎም “ተግባራዊ ፖለቲካንና የወሬ ፖለቲካን መለየት አለብን። ይህን ጥያቄ የሚያቀርቡ ሰዎች እውነት ጥያቄውን ያስቡበታል ወይ? ታስቡበታላችሁ ወይ? አንድ ነጥብ ለማስቆጠር የሚደረገው ፖለቲካ አልፎበታል፤ this is a serious politics፤ አገርን ነጻ ማውጣት is a serious business።”
የኦኤኔኤልኤፍ ጉዳይም እንዲሁ ለብርሃኑ ከሌሎች በብሔር ከተደራጁ ድርጅቶች ጋራ ሁሉ የፈጠሩትን ትብብር የሚያጠቃልል ጥያቄ ነው። መልሱ ጥያቄው የቆመበትን አንድ እሳቤ (assumption) መልሶ በመጠየቅ ይጀምራል። “ጥያቄው እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያውያን አደሉም ነው?” “ግንቦት 7”ም ይሁን “አንድነት”ን የመሳሰሉ ፓርቲዎች (የስትራቴጂ ልዩነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ) በብሔር ከተደራጁ ድርጅቶች/ፓርቲዎች ጋር በሚፈጥሩት ትብብር ተደጋግሞ የሚነሣው አንዱ ጥያቄ “ትብብሩ እነግንቦት 7 ቆመንለታል የሚሉትን የኢትዮጵያ አንድነት መልሶ የሚጎዳ ነው” የሚል ነው።

ብርሃኑ ይህን አይቀበለውም። “የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈልጉ ኀይሎች ከማንም በላይ ማነጋገር እና መግባባት ያለባቸው ‘በኢትዮጵያ አንድነት ውስጥ ሰላምና ዴሞክራሲን አናገኝም’ የሚል ስጋት ካለባቸው ኀይሎች ጋራ ነው” ብሎ ያምናል። “እነዚህ ሰዎች ተበድለናል፣ ተጨቁነናል የሚሉ ናቸው። ስለዚህ አሁን በጋራ የምንፈጥራት አገር ይህን ችግር እንደምታስወግድ ማረጋገጥ አለብን” ይላል፡፡ ይህ አመለካከት አሁንም ከስልት ልዩነት ውጭ “አንድነት” መድረክን ለመቀላቀል ከተጓዘበት የአመለካከት ለውጥ በመሠረቱ ተመሳሳይ ይመስላል። ሆኖም ሂደቱ “አንድነት”ን ለከፍተኛ ውስጣዊ ነውጥ እንደዳረገው ማስታወሱ የጉዳዩን ስሱነት ያስታውሳል። ሆኖም ብርሃኑ በኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች መካከል በአሁኑ ወቅት ከመቼውም ጊዜ በተሻለ መግባባት ተፈጥሯል ብሎ ያምናል።

“ግንቦት 7” እና የአገር ውስጥ ተቃዋሚዎች

‘“ግንቦት 7” አገር ቤት የሚታገሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን ለምን አይደግፍም?’ ወይም “ለምን ይቃወማል?” የሚለው ጥያቄ ብርሃኑና የድርጅቱ አመራሮች በተገኙበት ሁሉ ይቀርባል። እንደገና ይቀርባል፤ ይመለሳል…። “እኛ እነርሱን መቼ ተቃውመን እናውቃለን? ከእነርሱ ጋር የሚያጣላን ጉዳይ የለም፤ ባመኑበት መንገድ ቢሄዱ ምንም ችግር የለብን” የሚለውን መልስ ማስረጃ በማጣቀስ ያስረዳል። ነገር ግን አድማጮቹ ያለጥያቄ እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠሩ ድርጅቶችን መረዳት አለባችሁ ሲባል ‘ምን ስላደረጉና ምን እንዲመጣ’ የሚለውን መመለስ አለባችሁ። በስሜት ሳይሆን በስሌት መንቀሳቀስ አለብን። ትግሉን አንድ ጋት ወደፊት ማንቀሳቀስ እስከቻሉ በረዱ ችግር የለብኝም። ” ምን ስላደረጉና ምን እንዲመጣ?

“የመጀመሪያው” ስልክ እና መጪው ጊዜ

“ግንቦት 7” በምእራባውያን ዘንድ እንዴት እንደሚታይ ማወቅ የሚፈልጉ ብዙ ናቸው። አዲስ አበባም ላይ ይሁን ዋሽንግተን አለዚያም ለንደን ላይ ስለዚህ የሚወራው ብዙ ነው፤ የወሬው ምንጭና ግብም እንዲሁ የተለያየ ነው። ሁሉም ግን የዋህ ተመልካችን ግራ ለማጋባት በቂ ናቸው። “ግንቦት 7” ከተመሠረተ ጀምሮ ከበርካታ መንግሥታት ጋራ ግንኙነት ማድረጉ የአደባባይ ምስጢር ቢሆንም “ምን ያህል የምእራብ አገራት ዓላማውን ደግፈውለታል?” የሚለው ጥያቄ ለመመለስ የሚያስቸግር ነበር፤ በሁለት ምክንያቶች።

አንደኛው የምእራባውያን ስጋት “ግንቦት 7”ን በይፋ መደገፍ ከሕዝብ ግንኙነት አንጻር በዚህ ዘመን የትጥቅ ትግልን እንደማበረታት እንዳይቆጠር፤ በሌላ በኩል ደግሞ አገር ቤት ያሉትን ተቃዋሚዎች ተስፋ የሚያስቆርጥና መለስንም አለቅጥ የሚያስቆጣ ሆኖ ጠቅልለው ወደ ቻይና ጉያ እንዳይገቡ የማስታመም ስትራቴጂ ነው። ከሁሉም በላይ ደግሞ ምእራባውያንን ወክሎ ሶማልያን በቅርብ ርቀት የሚከታተል ሌላ መሪ በአካባቢው አለመኖሩም አንድ ታሳቢ ስጋት ነው። ይህ ማለት ግን ሰዎቹ የ “ግንቦት 7”ን አመራሮች እየጋበዙ አላወያዩም ማለት አይደለም። ምናልባትም በዚህ ደረጃ መጋበዙ በራሱ ለድርጅቱ እንደ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ ሊቆጠር ይችል ይሆናል።

ዶ/ር ብርሃኑ እንደተናገረው “ግንቦት 7” ከተመሠረተ ጀምሮ ከምእራባውያን መንግሥታት በሚደረጉ ጥሪዎች የተጣበበው በቅርቡ ነበር፤ “ግንቦት 7 የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አደረገ” በተባለ ማግስት። አቶ በረከት ስምኦንን እና የዚያን ጊዜ ምክትላቸው (ዛሬ በአሜሪካ በጥገኝነት ይገኛሉ) “መፈንቅለ መንግሥት” የሚል የፕሮፓጋንዳ ፈጠራ አዘጋጅተው አሰራጩ። ወዲያው ዜናው ጠላታቸው መጠንከሩን የሚያሳይ መሆኑ ሲገባቸው ቃላቸውን ቀየሩ። ምእራባውያኑ ግን ነገሩን በቀላሉ አልለቀቁትም። ወደ “ግንቦት 7” ሰዎች ስልክ መቱ። “እውነት ነው? አድርጋችሁታል?…” “ግንቦት 7” መፈንቅለ መንግሥቱንም ሆነ በኋላ ተጠርጣሪዎቹ “ጥፋተኛ” ሆነው ተገኙበት በተባለው ድርጊት (ለዚያውም ተደርጎ ከሆነ ነው) አለመሳተፉን አስታውቋል። የአቶ መለስ መንግሥት ከሻእቢያ ቀጥሎ ለማንኛውም ነገር ተጠያቂ የሚያደርገው “ግንቦት 7”ን ነው፤ በዚህ በኩል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ድርጅቱ የኦነግን ቦታ ወስዷል ማለት ይቻላል።

እንደማንኛውም የፖለቲካ መሪ ዶ/ር ብርሃኑ የምእራባውያን ዓላማ ፍላጎታቸውን ማስቀደም እንጂ የእኛን ፍላጎት መደገፍ አለመሆኑን ይናገራል። ስለዚህ ግንኙነት ለቀረበው ጥያቄ ሲመልስም “እኔ በፈረንጆች ብዙ እምነት የለኝም…እነርሱ ይቺን ታህል እንደማያመጡልን ግልጽ ነው…ነገር ግን መለስን በጭፍን በመደገፍ የሚፈልጉትን ዘላቂ መረጋጋት ሊያገኙ እንደማይችሉ እነግራቸዋለሁ።…ሕዝባዊ አመጹ ከተነሣ በኋላ ምንም ማድረግ አይችሉም፤ አሁን ግን ማድረግ የሚችሉትን ነገር ለማሰብ የሚያስችል ጊዜ አለ።” ይህ ግን የ “ግንቦት 7” እና የምእራባውያኑ ግንኙነት መጨረሻም መጀመሪያም አይደለም። ድርጅቱ ጉልበቱንና ሕልውናውን ባጠናከረ መጠን ሊያዳምጡት ይዘጋጃሉ። ይህን እውነት እነ ብርሃኑ እንደተረዱት ይናገራሉ።

መጪው ጊዜ የማናውቀውን ብዙ ነገር ይዟል። የሰሜን አፍሪካው ሕዝባዊ አብዮት በኢትዮጵያ ቢከሰት ብለው ማሰብ ሲጀምሩ ስጋት የሚጫጫናቸው ብዙ ናቸው። ብርሃኑ እነዚህ ሰዎች ለማረጋጋት ይሞክራል። አንደኛ “አብዮት እንደሚመጣ ጥርጥር አይግባችሁ፤ የትና መቼ እንደሚጀመር ብቻ ነው የማናውቀው።” ሁለተኛ፤ ከአብዮቱ ጋር ሊፈጠሩ የሚችሉ የማናውቃቸው ስጋቶች “ማድረግ ያለብንን ከማድረግ ሊከለክሉን አይገባም።” “የእኔ ሥራ የሚፈራው ነገር እንዳይመጣ መሥራት ነው፤ እጄን አጣጥፌ መቀመጥ አልችልም። ቀላሉ ነገር ግን ዝም ብሎ መቀመጥ ነው፤ ሕሊናን ማሳመን ከተቻለ።”

ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ኀይሎች “ጊዜ ያለ” አይመስልም፤ ነገሮች ዶ/ር ብርሃኑ እንደሚለው ከሄዱ። “አሁን የፖለቲካ ትግሉ ፈጣን ነው። ‘በሚቀጥለው ዓመት እንደርስበታለን’ የሚለው አሁን አይሠራም። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኀይሎች ያለን የጊዜ ማእቀፍ (timeframe) አጭር መሆኑን ከልብ ማመን ይገባናል።” በእርግጥም የሰሜን አፍሪካ አብዮቶች ለፖለቲካ ተዋንያን ያረጋገጠው አንዱ ሐቅ የሕዝቡ የነጻነት ጥማት ፖለቲከኞቹ ከሚያስቡት እጅግ የፈጠነ መሆኑን ነው። ይህን ሐቅ እነብርሃኑን ጨምሮ ሌሎቹ ተቃዋሚዎች እና እጣ ፈንታቸውን የመወሰን እድላቸው አሁን ከእጃቸው ያልወጣችው አቶ መለስ እንዴት እንደሚረዱት ጊዜ ያሳያናል።

“እነርሱ ለጥፋት ያላቸውን ጉብዝና ያህል እኛ ጥፋቱን ለማስቀረት የለንም፤ እኛ ውስጥ የሚያናድዱ ደደብነቶች (ስቱፒዲቲዎች) አሉ።…ነጻነት ዋጋ ይፈልጋል። ኤርትራውያን ከገቢያቸው 2 በመቶ ሲያዋጡ እኛ 10 በመቶ እናወራለን። እነርሱ 2 በመቶ ካዋጡ ለምን አያሸንፉም?….” ይህን መሰል ቁጭት የተሞላባቸው ወቀሳዎች ብርሃኑ በስተመጨረሻ የሰነዘራቸው ናቸው። አድማጮቹ የሆነ ነገር እንዲያደርጉ ለማሳመን ከራሳቸው ጋራ እንዲፋጠጡ የገፋበት ክርክር። ይህን መሰሉ የብርሃኑ እና የሌሎቹም ተቃዋሚዎች ስብሰባዎች ወደ ተጨባጭ አስተዋጽኦዎች ይለወጣሉ ወይስ 10 በሞተ የወሬ መዋጮዎች ኾነው ይቀራሉ? በዚህ ስብሰባ መጨረሻ ያነጋገርኳቸው ጥቂት ወጣቶች የብርሃኑ ውተወታ የወቀሳቸው ይመስላሉ።

ሰውየው ሰዎችን አግኝቶ የሚያነጋግርበት አጋጣሚና መድረክ ካገኘ ብዙዎችን ማሳመን እንደሚችል አይጠራጠርም። ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም መልእክቱን ለማድረስ ሲጥር የምናገኘውም በዚህ ምክንያት ነው። ብርሃኑን ከ“ቅንጅት” ጋራ በማያያዝ የሚያስታውሱትን በቁጭትና ጥርጣሬ የሚመለከቱት ሰዎች ቁጥር ጥቂት አይደለም። አሁን አገር ቤት ቢኖርና ይህን ንግግር ቢያቀርብ ስንት ሰው ይገኝ ነበር? ስንቱ ይከተሉት ነበር? ከዚያስ? አሁን መልእክቱን በተለያየ መንገድ አገር ቤት ሆነው የሚሰሙትስ ሰዎች ምን ይላሉ?

እዚህ ብርሃኑና አድማጮቹ በነጻነት የሚነጋገሩበት ሕዝባዊ የዴሞክራሲ አብዮት እዚያ በምስጢር የሚጠበቅ ጉዳይ ነው። የፖለቲካ ፓርቲዎችም ይሁኑ ሌሎች ዜጎች በቱኒዚያ ምሳሌ፣ በግብጽ ፈለግ ሰልፍ መውጣት ቀርቶ ስለ ሊቢያ ጮኽ ብለው ለማውራት የሚፈሩባት የአቶ መለስ “ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ” ምናልባት የራሷን ድግስ እያዘጋጀች ይሆን? ለጊዜው እዚህ የአድማጮቹ የነጻነት ፍላጎት ተምሳሌት ብርሃኑ ነው፤ እዚያ ደግሞ የአፈናው ተምሳሌት መለስ ናቸው።

29 Responses to “እዚህ ብርሃኑ፤ እዚያ መለስ”

  1. There is no way that Shabia want to see a stable and free Ethiopia. It just doesn’t make any sense.

  2. Berhanu Nega:- among all the opposition politicians, I rate him the most. That is not because I agree with his present engagements, which I think could never work, but because he simply has that quality of being a choice.
    Always, there is nothing thoughtless about his talks. If you have not started taking this man seriously, you are making a fool out of yourself. For me, however, he just chose the wrong playing card this time around.
    I think Berhanu is a certified power monger, manipulative, and at times deceptive. Also, it is difficult to deny the mighty of his glib tongue with which he can play off of the emotions of people. Personally, I don’t know any good practical politician who doesn’t have those characters.

    If there was an undo button in life, I would have wished Berhanu to reconsider his decision of this non sense ‘hulegeb tigil’.

    • Shedding Corocodile tears!!!

      I can’t help reading the converse of some of your statments. Then, it makes sense.

      Good Job, kkkkkkkkkkkk

  3. ቢ.አስፋው 19 March 2011 at 7:35 am

    ስለ ብርሃኑ ንግግሮች ለማለት የሚቻለው ነገር ቢኖር ስላመነበት ጉዳይ ጠንከር ብሎ ስሜታዊ በሆነ መንገድ የማቅረብ ችሎታው ከብዙ ሰዎች የላቀ እንደሆነ ነው። ችግሩ ግን ከቅድመ ራዕይ 2000 በፊት የነበረው ብርሃኑ፣ በቅንጅት ወቅት የነበረው ብርሃኑና የአሁኑ ብርሃኑ ልዩልዩ ሰዎች
    መሆናቸው ነው። ኢህአዴግ በነዚህ ጊዝያት ውስጥ መሰረታዊ የባህርይ ለውጥ አድርጓል ብለን ካልተቀበልን በቀር ብርሃኑ ምናልባት አሁን ነው የኢህአዴግ ምንነት የተገለጠለት ለማለት ያስደፍራል።
    በፈለገ ብልጣብልጥነት ለማለፍ ቢሞከርም ሻዕቢያን ይዞ የነፃነት ጉዞ የህልም ጉዞ ከመሆን አያልፍም። የነፃነት ጉዞ ምን ረጅም ወይ አድካሚ ቢሆን ሊሳካ የሚችለው የራስን ወገን አሳምኖ፣አደራጅቶ በሚደረግ ትግል እንጂ እናንት እምቢ ካላችሁ ሻቢያንም ቢሆን ይዤ በሚል የማይሆን ማስፈራሪያ አይደለም።
    የያዝከው መስመር ምን ትክክል ቢመስልህና በጥራቱ ራስክን ብታሞካሽ ብዙ ህዝብ አሳምነህ፣ አደራጅተህ፣ ታግሎ ማታገል ካልቻልክ ከንቱ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ስለዚህ ህዝብን መውቀሱን ተወት አድርገን ጥሪው አሁንም አሁንም በጋራ በሚይስማሙን ጉዳዮች ዙሪያ እንደራጅ ቢሆን ይመረጣል።

  4. ayenew leyenew 19 March 2011 at 7:45 am

    ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ እንዲህ አለች፤ “አጭር የትግል ተሳትፎ ታሪኬ ብዙ ነገሮችን አስተምሮኛል። በኢትዮጵያ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትግል በበርካታ ጥቅሞችና ፍላጎቶች ግጭትና ፍትጊያ የሚፈጠርና ውስብስብም በመሆኑ የጎለበተ እውቀት እንደሚጠይቅ ተገንዝቤአለሁኝ።” የበሰለ ሐሳብ ይሉታል ይሕ ነው። የብርሐኑ ትንተና ለኔ ውሃ የሚቋጥር አይደለም። በመሰረቱ እሱ በአሲምባውም ሆነ በቅንጅቱ አመራሩ ውጤት አልባ ስለሆነ ገለል ማለት ነው ያለበት። ከሁሉም በላይ ደግሞ ለመሪነት የሚያስፈልገን በትግሉ ሜዳ ጸንቶ የሚገኝ እንጂ የሚሸሽ አይደለም። ብርሃኑ ልብ ያላለው አንድ ነገር አለ። የቱኒዚያውም ሆነ የግብጹን አብዮቶች የተመሩት ከቂም በቀል በጸዱ የፌስ ቡክ ትውልድ አባላት እንጂ የመጠላለፍ ፖለቲካ ኤክስፐርቶች አይደሉም። ለውጥ ያስፈልገናል። መሪም። ብርሃኑ አይመጥንም።

  5. እውን ዶር ብርሀኑ ከሻቢያ ጋር ድጋፍ ፍለጋ የሚደረገው መሞዳመድ ላይ ስጋት ያላቸው ሰዎች የስጋታቸው መሰረቱ ‘ከዝቅትኘነት ሰሜት የሚመነጭ ነው’ ብሎ ያምናል ወይስ እንደው የስነ ልቦና ጦርነት በማካሄድ ከተጠያቂነት ለማምለጥ የታለመ ስልት?
    የሻእቢያን ፀረ ኢትዮጵያ አቐም በሚመለከት የጠራ አቐም እስካሊያዙ ድረስ የህዝብ ድጋፍ ማሰባሰብ አዳጋች እንደሚሆን ምነው እስታሁን ተሳናቸው?

  6. Ayzogne Berehanu Nega !!! Come on G7 !!!

  7. Doctor I am feeling the way you feel it. Now you gave us all hope. The time is creeping nearer and nearer.

    “ሰው ባርነቱን ለማወቅ ስንት ዓመት ይፈጅበታል?” I don’know what these people are thinking of. Please let’s do something, anything to throw this despot regime!!

    Thanks

  8. What a nice piece!I loved it.Positive, inclusive and serious strugle for freedom and change is in the making. We have got one who said, come on this is time for action and wake us up from deep sleep. He inspired and had his audiance listening attentively.

  9. እኛ ውስጥ የሚያናድዱ ደደቦቶች (ስቱፒዲቲዎች)…these guy is one of the stupids, …..
    @ mesfin negash…….ዶሮ ነገር ነህ፡፡

  10. All ethiopian people are thinking,when will this regime remove,the revolution will come but when,(We ethiopian where the first to search in google about libya revolution acording to google),if once the uprising is started nothing will stop,what i want to tell for meles is to implement a genuine democracy i mean a genuine for that we will forgive past other wise we will eat him alive!!

  11. Great Job!!!

    • እኔ እንደሚመሰለኝ ዶ/ር ብርሃኑ እውነተኛ ኢትዮጵያን ከዚህ ዘረኛ አገዛዝ የማላቀቅ ረዕይ ያለው ሰው ይመሰለኛል። እሱ እነደብዙዎቹ ለሆዱና ለጥቅሙ ብሎ ወደ ፖለቲካ የገባ ሰው አይደለም። ለራሱ ከበቂ በላይ ሃብትና ዕዉቀት ያለው ሰው ነውና። አሁን ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች እውነቱን ለመናገር ለሀገራችን ቂንጣት ፍቅር የለላቸውና እኛን በዘርና በጎሳ በመከፋፈልና እርስ በርሳችን እንድንጋጭ በማድረግ ያገሪቱን ሃብት አሟጠው እስከክመዘብሩ ድረስ በስልጣን ለመቆየት ብቻ እየሰሩ ያሉ ሰዎች ናቸው። እነ ባለኝ መረጃ መሰረት ያገራችን ዕድገት ተብሎ የሚለፈፈውና የውጪ መንግስታት ሳይቀሩ መሰከሩልን እያሉ ሚያደነቁሩነ ያገሪቱን አጠቃላይ ምርት (GDP) ብቻ መሰረት በማድረግ ነው። ይህ ደግሞ ጥቂት የገዢ መደብ ሰዎችና እነሱን የተጠጉ ሰዎች በከፍተኛ ደረጃ ሃብት በማካበታቸው ምክንያት የመጣ እንጂ ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠግቦ በማደሩ የመጣ አይደለም። ማደግ የሚለካው ድህነትን በመፈክር ሳይሆን በተግባር ማጥፋት ስቻልና በተረጋጋ የገበያ ሁኔታ የነፍስወከፍ ገቢን ማሳደግ ስቻል ብቻ ነው። ስለዚህ ያገራችንን ማደግ አለማደጓን የሚናውቀው እኛው ህያው ምስክሮች እነጂ ከመንግስትም ሆነ ውጫዊ ሽፋንን ብቻ በመየት አደጋችሁ የሚሉንን የውጪ መንግስታት አንስማቸው።

      እኔ ባለኝ መረጃ መሰረት ባገራችን ጉዳይ ብዙ ማለት ብችል መልካም ነበር። ግን በዚች መሰኮት ከዚህ በላይ ማለት ስለማለችል እዚህ ላቁም። ዶ/ር ብርሃኑ እዉነተኛ ያገራችን ፍቅር ያለው ሰው በመሆኑና የሚታገለውም ለራሱ ርካሽ ቁሳዊ ጥቅም ለማግኘት ሳይሆን እኛን ከዘረኛ ገዢዎቻችን ለመታደግ በመሆኑ ሰውየውን ባላውቀውም ሀሳቡንና አላማውን እደግፈዋለሁ።

  12. It is well said and brief description about what we need currently for our country to start the revolution soon.But still the peoples in home didn’t understand exactly the mission and vision of Ginbot 7, Specially related to the Eritrea government in the way that the leadership of Esayas has the intention to get some thing from oppositions. Therefore Ginbot 7 radio program ( i left the web site because now it is blocked in the country) should create the awareness and make the people to stand with them. Still the revolution is possible in our country. The current regime try to make frustration in the community in the way that if revoution occur in our country majority of the people we die due to hunger until it settled. But the death for freedom is better than living under slavery with comfortable life. Those of who are living out side Ethiopia should copy and paste on the not part of your facebook, because direct access to such type of websites are blocked in the country.
    Freedom for us……….

  13. Compared to all recent posts, this topic has got the highest attention. A substantial of the comments are also against the subject of the article. It appears that some type of the audience are having difficulty of accessing the site???

    My question is ‘what is going on’? Dear ANO editors are you realy in control of your blog? I doubt it!!!

    • What is that type of audience?…haven’t you realized it has been diluted long time back? That is the truth, face it.

  14. Oh we are always proud of you Dr.! i wish i could tell you my deepest appreciation and love. i feel very happy finding you’re speech. You have a largest space in the heart of Ethiopians people from North to South and from West to East….. you are the best politician and intellectual person thank you….!

  15. እኔን የሰለቸኝ ኑ ና እዚህ ታገሉ የሚለው ዲስኩር ነው፡፡ ከባህር ማዶ ሆኖ የታገለ ወይም ያታገለን ኃጢያተኛ፤ ሀገር ውስጥ ሆኖ የታገለውን ደግሞ ትክክለኛ ነው ያለው ማነው? ለዛውም እኮ የመታገያና የማታገያ ቦታ ሲገኝ ነው፡፡ መተቸት ወይም መደገፍ የሚገባው የትግሉን ዓላማ እንጂ የማታገያ እና የትግል ቦታውን አይደለም፡፡

  16. “እነርሱ ለጥፋት ያላቸውን ጉብዝና ያህል እኛ ጥፋቱን ለማስቀረት የለንም፤ እኛ ውስጥ የሚያናድዱ ደደብነቶች (ስቱፒዲቲዎች) አሉ።…ነጻነት ዋጋ ይፈልጋል። ኤርትራውያን ከገቢያቸው 2 በመቶ ሲያዋጡ እኛ 10 በመቶ እናወራለን። እነርሱ 2 በመቶ ካዋጡ ለምን አያሸንፉም?….”-
    ሕሊና የሚባል ነገር ካለን ይህ ብቻ በቂ ነው። እናንተ አስተያየት ሰጭዎች 21ኛው ዘመን ላይ መሆናችሁን አትርሱ። ለህሊናችሁ እውነት ነው ብላችሁ የጋታችሁትን ሃሰት እኛ ላይ አታስታውኩ። ወደዳችሁም ጠላይሁም እውነት እውነት ናት። ስለዚህ ያ እውነትና ውሸት መለየት የተሳነውን ጭንቅላታችሁን ብቻ አታሉ። እኛ አንታለልም። አሁን የሚሰራው ማንኛውም ነገር ያደባባይ ሚስጥር ነው። ብርሃኑ ማን እንደ ሆነ መለስ ማን እንደ ሆነ ማንበብና መጻፍ ለሚችል ይቅርና ለማንኛውም ማህይም የተደበቀ አይደለም። ስለዚህ የተቀመጣችሁበት ውሸት ውስጣችሁን ሲያውካችሁ እኛ አታፍጡ ወደ እኛም ለማስነበብ አትሞክሩ። ውስጣችሁን ረጅም ጊዜ ወስዳችሁ አድምጡ። በዚህ ምድር ላይ ምን ያህል ልትኖሩ እንደምትችሉ ራሳችሁን ጠይቁ፤አለም ምን ደረጃ ላይ እንደ ደረሰች አምብቡ ያኔ ለምትሰጡት አስተያየት ትንቃቄ ታደርጋላችሁ። ከናንተ ቀድመው ኢትዮጵያ በአጥፊዎች እጅ ወድቃለች ከሚሉት ሰዎች ጎን መሰለፍ ትጀምራላችሁ።

    ለዚህም የሚሰራ በጎ ህሊና እንዲኖራችሁ ምኞቴ ነው።

    ኢትዮጵያ ነጻ ትወጣለች።

  17. @ ermias don’t loose hope those who say come and fight here(Ethiopia) are TPLF supporters yes we can fight TPLF/MELES out side Ethiopia
    BRAVO DR. You are the only Opposition LEADER that stand strong since 1997 election
    GOD BLESS YOU DR.

    • Why is Berhanu the only? he didn’t even claim so. Berhanu and G7 are saying there is no only way, we have to use any means available to oust the dictatorial regime in Ethiopia and establish a democratic system. every body seems to agree on having a democratic system as a solution for the long lasted misery in our country. It looks the strategy to get there is mainly the line which divides many oposition parties.

  18. You can never make positive change in Ethiopia by siding with Shabia.That is final…Let’s forget about the idea of bringing democracy and stability to Ethiopia by relying on Shabia. What we need to do is focus on our own efforts…We are responsible

  19. Some Points:

    ******************

    1. True; etiquetting the Melesse clique with “Woyane” etc. was and is counter-productive and “inacceptable” ( to use the new arrogant “diplomatic” language of these days!). Intended or not; I think “Woyane” has taken in between in the political perception of the opposition a new meaning: “bad” and some sort of stuff like “the bad other” with the outcome of unconsciously polarizing the political constituents along ethnic lines.

    2. “ጉጅሌ” “የትግራይ” …. What is the purpose of employing these new specifications too; to indicate “the Melesse clique” ? – Out of a similar consideration, this signification is meaningless too, albeit the reference in the context of the language employed makes it necessary
    *

    The promotion of an all encompassing Ethiopian social transformation has to be free of the slightest indication of any bias and prejudice of ethnic or religious character.
    ************************

    Along this line here are some of the points I share:

    http://berhane-aymero.blogspot.com/2011/02/from-new-egypt-short-lessons.html

    One fact is true! History has witnessed innumerable times, once a regime loses its mass base or doesn’t have a mass base, no party structure whatsoever can save a regime. That was the case with all ancient regimes, that was the case with the communist block, that was the case in the “social-tsunami” of Tunisia or Egypt etc. this year, dysfunctioning their ruling parties to null and nil… But still these are neither “paper tigers” nor natural tigers; but they are simply normal “sick” people who can cause all kinds of pains until they lose their old sick teeth or until they get their correct shock-therapy! The social tsunami! And the big question remains:
    Is the social tsunami looming around the corner! Are the constituents volatile enough to call for IT? Or…. or….is it only a “concert wish” with a bitter consequence? And there lies the responsibility of a serious political leadership! Nonetheless, we know that even science has its problems in the exact prediction of earth-quakes and tsunamis – The “Japan – disaster” of these days speaks!

    And what about the social-tsunamis ? Which are the signals and indications? That is the big point!

  20. why you people always blame Eritrea for your failures,don’t be emmtionals all the time,Even your master Woyanne trained in Eritrea,ask Sudan for help

  21. Isayas/EPLF/Shabea has been fighting all his life against the interest of Ethiopia. He finally succeeded and achieved his goal by his own effort and with cooperation of traitors who believed that they will achieve their goals by cooperating with him. Ethiopians have reached consensus that those traitors are TPLF leaderships, and they have no Ethiopians interest in their heart. Birhanu is trying to copy the model set by TPLF leadership and attempt to achieve whatever goal he set for himself. He is telling us Isayas/Shabea is holy of the holiest, just like he helped TPLF leaderships achieve their goal, Isayas will provide the same help for Birhanu. This line of thinking seems very confused and contradictory.

  22. I wonder how many of you guys on this forum are under 30

  23. every thing is ok as long as it is birhanu that is doing it. peaceful struggle is ok. armed struggle is ok. coopoerating with isayas afework or shabia is ok..mending fences with tplf is ok. confessing to a crime and leaving behind the people is ok. not being concerned or worried for what could happen to the country is ok. in fact any one who questioned all his moves is lashed out and mocked by the good doctor…there is a pattern here for any one who cared. the guy is ‘the i know it all attention seeker power maniac’.


    how can he compare libya to south africa with eritrea to ethiopia. isnt that looking down and underestimating the intelligence of his audience.

  24. Guys accept critical thinking and serious, free disagreement. mesfin negash asks critical questions.
    We need to stop the herd mentality. whatever the leader says is right, be it birhanu , hailu, meles etc… all meles` followers talk the same , so are birhanus`. we need to focus on doctrinal clarity, priciples, programs and above all BUILD institutions instead of worshiping individuals, AQQQQQQQ
    Thank you Mesfin negash, for questioing the unpopular.

  25. Dr Berhanu came up with very stupid answer in regards to Working with Shabia .
    He thinks he can avoid the serious question by opening a physchological warfare.
    Another confusion regarding working with OLF and ONLF ‘ጥያቄው እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያውያን አደሉም ነው?” Yes, we believe they are Ethiopian but what Dr Berhanu missed is ONLF and OLF are claiming they are not Ethiopians. Go and read their websites. Before dancing and flirting with OLF and ONLF, persuade them to revise their crazy political programes and advise them to stop their endless lies against our history.

Bad Behavior has blocked 2468 access attempts in the last 7 days.