የኢትዮጵያ መንግሥት ቦንድ ምን ያህል አስተማማኝ ነው?
አሁን ወደ ኢትዮጵያ መንግሥት ቦንድ ልመለስ። የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጣው ቦንድ የ5፣ የ7 እና የ10 ዓመት የመብሰያ ጊዜ (Maturity date) ያላቸው ሲሆኑ የወለድ መጠናቸውም እንደቅደም ተከተላቸው 4%፣ 4.5% እና 5% ነው (በ1% የወለድ መጠን ልዩነት ብቻ የ10 ዓመቱ ቦንድ ከ5 ዓመቱ ቦንድ እንዴት የተሻለ ሳቢ ኢንቨስትመንት (attractive investment) ሊሆን እንደሚችል አልገባኝም!!!):: እንደ ማንኛውም ኢንቨስትመንት ቦንድም የራሱ የሆኑ የአክሳሪነት ወይም የአትራፊነት እጣ እድል አለው:: ምናልባትም ያሉትን የአክሳሪነት አደጋዎችን እዚህ በመዘርዘር እጅግ አስፈላጊ ነው።
አንዱ የቦንድ አደጋ (Bond risk) የወለድ ምጣኔ መዋዠቅ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ይሄ በጣም ሲበዛ የሚከስት እና አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ ነጻ ባልሆነ እና በህወሃት የፖለቲካ እሽክርክሪት ስር ያለ ማዕከላዊ ባንክ ባለበት ሁኔታ መሆኑ የአደጋውን (Risk level) ደረጃ ከፍ ያደረገዋል:: መንግሥት የሚሸጠው ቦንድ ዋጋ ምን ያህል ከወለድ ምጣኔ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ምንም የሰጠው መረጃ ባለመኖሩ ያለዚህ መረጃ እንዴት ሰዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለመጠየቅ እንደደፈረ የሚደንቅ ነገር ነው::

(ሳ. ግርማ)
የኢትዮጵያ መንግሥት የሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች የሰሞኑ አሰልቺ ሙዚቃ “ቦንድ፣ ቦንድ፣ ቦንድ” ሆኗል:: የገንዘብ እና የንግድ አስተምሮት እምብዛም ባልጠናበት እንደ ኢትዮጵያ ባለ ማኅበረሰብ ውስጥ መደናገር ቢበዛ አይደንቅም:: ስለዚህም ጊዜው የመረጃ እንደመሆኑ ለራሴ ግንዛቤ ለመጨበጥ ይረዳኝ ዘንድ አስተማማኝ የሆኑ የመረጃ ምንጮችን ፈተሽኩ::ለራስ አውቆ ለሌላው አለማካፈልን ስላልወደድኩት ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ እንደሚከተለው ከትቤ እነሆ ብያለሁ:: “እውነት ግን ቦንድ ምንድነው?” ከሚለው ጥያቄ እንጀምር።
ይህን ጥያቄ ለመመለስ ከመሞከሬ በፊት እንደዚህ አይነት እንግዳ እና መጤ ቃላት በኅብረተሰባችን ውስጥ ለፖለቲካም ይሁን ለሌላ ማደናገሪያነት እንዴት እንደሚያገለግሉ ያሳይ ዘንድ እውቁ የኮሜዲ ሰው ተስፋዬ ካሳ በአንድ ወቅት ያካፈለንን ጨዋታ ለመንደርደሪያ ማስታወሱ አይከፋም። ምናልባት ቀልዱን ቃል በቃል ላላስታውስ እችል ይሆናል፤ ይሁን እንጂ መሠረታዊው መልዕክት ግን እንዳለ ነው::
ሰውዬው በሰፈሩ ባለሥልጣን ወይም የአንድ ፕሮጄ መሪ ብጤ ይመስለኛል:: ‘የሰፈሩን ሰው ሰብስቦ “ፈንዱ” አዲስ መንገድ ይሠራላችኋል:: “ፈንዱ” አዲስ ትምህርት ቤት እንዲኖራችሁ ያስችላችኋል:: “ፈንዱ” አዲስ ጤና ጣቢያ ያሠራላችኋል::…’ እያለ የ“ፈንዱ”ን ጥቅም ወይም አስፈላጊነት ይደሰኩራል:: ታዲያ ይሄኔ ነው አንዲት የሴት አዛውንት እጃቸውን ለጥያቄ ያነሱት:: እንዲህም ሲሉ ጠየቁ “እንደው ለምሆኑ ካልፈነዳን በቀር ይህ ሁሉ የምትለን ነገር አይሆንም ማለት ነው ወይ?” ብለው ጠየቁ ብሎ ጨዋታውን በዚህ ደመደመ:: አቤቱ የተስፋዬን ነፍስ ማር! መቼም “ቦንዱ”ም የ“ፈንዱ”ን ያህል ብዙዎችን ሳያደናግር ብዙዎቹንም ሳያሰለች አይቀርም ባይ ነኝ::
መንግሥታት የሚከተሉትን የፖለቲካ ስርዓት ሳልጠቅስ የግል እና የወል ንብረት ማፍራትን የሚፈቅዱ ሲቀጥልም እንደ ስቶክ ማርኬት እና ቦንድ ማርኬት የመሳሰሉ የገንዘብ እና የንብረት ባለቤትነትን እና መገበያየትን ከዚህ ጋር ተያይዞም ዝውውርን የሚያስችሉ የገበያ ስርዓቶችን በዘረጉ አገራት ውስጥ ቦንድ እንግዳ ነገር አይደለም:: በዘርፉ ቋንቋ የጋራ ባለቤትነት የሚገለጽበት ቃል ሴኪዩሪቲ (Security) ይባላል:: በዋናነት ሦስት አይነት የወል አንዳንዴም በግል የንብረት ባለቤትነት የሚገለጹባቸው የሴኪዩሪቲ አይነቶች አሉ:: እነርሱም ስቶክ (Stock)፣ ቦንድ(Bond)፣ እና ዴሪቬቲቭ (Derivative) ይባላሉ:: (እነዚህ ቃላት አቻ የአማርኛ ፍቺ እንዳላቸው አላውቅም:: ምናልባት በሰፋ ዝርዝር ለማየት ለፈለገ ሌሎች በቁጥር የበዙ የሴኩዩሪቲ አይነቶች ሞልተዋል:: ከነዚሁም ውስጥ treasury notes, treasury bills, debentures እያለ ይቀጥላል::)
የጽሑፌ ዋና አላማ ቦንድ እንደመሆኑ ሐሳቤን ወደ ቦንድ ልመልስ እና ጽሑፌን ልቀጥል:: ከሴክዩሪቲ አይነቶች ውስጥ ቦንድ የቋሚ ገቢ (fixed-income security) ሴክዩሪቲ አይነት ሲሆን ከሦስቱ የንብረት አይነት መደቦችም (Asset classes) ውስጥ አንዱ ነው:: ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ስቶክ (Stock) እና “የገንዘብ አቻ” (Cash equivalents) ተቀማጭ ገንዘብ ወይም ገንዘብን ሊተኩ የሚችሉ እንደወርቅ አይነት የንብረት መደቦች ናቸው:: ቦንድ ማለት በግርድፉ ሲፈታ የ’አለብኝ’ ስምምነት ነው:: ይህም ማለት ቦንድ የሚሰጠው ወይም የሚሸጠው አካል ለገዢው ሰው “ይህን ያህል እዳ አለብኝ” (በእንግሊዘኛው I owe you እንደሚባለው ማለት ነው) ብሎ እንደ ማስረጃ የሚሰጠው ማስረጃ ነው:: ቦንድ ገዢዎች ማንኛውም ትርፍ ፈላጊ ኢንቨስተር ሲሆኑ፤ ቦንድ ሻጭ ደግሞ በኩባንያ ደረጃ የሕግ እውቅና የተሰጠው አካል ወይም አንድን አገር የሚያስተዳድር መንግሥት (መንግሥት ሲባል የክልል እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት መንግስታትንም ይጨምራል) ሊሆን ይችላል:: ቦንድ ሲሸጥ ለአንድ ሁነኛ ፕሮጀክት ወይም ለተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሊሆን ይችላል:: ቦንዱን የሚሸጠው ወይም የሚሰጠው አካል ቦንዱን ሲሸጥ የሚኖረውን ወለድ (coupon/interest rate) እንዲሁም ቦንዱ የተገዛበትን ዋና የገንዘብ መጠን (Bond principal) እና የሚመለስበትን ጊዜ በግልጽ ማሳወቅ ይኖርበታል:: ይህም ጊዜ “የመብሰያ ጊዜ” (Maturity date ) ተብሎ ይታወቃል ::
ቦንድ በራሱ እንደ ቦንድ ሻጩ አይነት እና እንደሚከፈልበት ጊዜ (maturity duration) ርዝመት የተለያየ አይነት ስያሜ አለው:: ከእነዚህ ውስጥ በማዕከላዊ ባንኮች የሚሰጡ/የሚሸጡ እንደ “የግምጃ ቤት ሰነዶችን” (Treasury bills/Treasury notes) የመሳሰሉትን ማንሳት ይቻላል:: ቦንድ በደፈናው ከስቶክ ማርኬት አይነት የንብረት መደቦች ጋር ሲነጻጸር አስተማማኝ የገንዘብ ማቆያ መንገድ ተደርጎ ይወሰዳል:: ይህ ማለት ግን ሁሉም ቦንዶች እኩል ዋስትና አላቸው ማለት አይደለም:: ለምሳሌ የአሜሪካን መንግስት ማዕከላዊ ባንክ የሚሸጣቸው/የሚሰጣቸው የቦንድ አይነቶች በጣም አስተማማኝ በመሆን ይታወቃሉ:: ይህም ሊሆን የቻለበት ምክንያት የአሜሪካን መንግሥት ሁሌም ቢሆን ቋሚ ፣ ጠንካራ እና በማይነቃነቁ የዴሞክራሲ መሠረት ላይ የተተከለ ስለሆነ፣ ዛሬ ያለው መንግሥት የተበደረውን (ቦንድ ማለት ብድር መሆኑን አይዘንጉ!!) ተከታታይ መንግሥታት የመክፈል ግዴታውን ማክበራቸው ስለማያጠራጥር ነው:: ሌላው ምክንያት ደግሞ የተበዳሪዎችን ብድር የመክፈል ደረጃ የሚያወጡ ገለልተኛ የገንዘብ ተቋማት ደረጃ መዳቢዎች (Credit rating agencies) የአሜሪካ መንግሥትን ብድር በመመለስ የባለ ሶስት ኮከብ ታላቅ ደረጃ ስለሚሰጡት ነው:: ምናልባት እንኳን አሁን እየሆነ እንዳለው የአሜሪካን መንግሥት ገንዘብ ቢያጥረው መቼም ቢሆን ታክስ ከፍ በማድረግ እዳውን መክፈል እንደሚችል ስለሚታወቅ ሰዎች የአሜሪካን መንግሥት ማዕከላዊ ባንክ የሚሰጠውን/የሚሸጠውን ቦንድ በመግዛት ሃብትን ለወደፊት፣ ለክፉ ጊዜ፣ ወይም ለጡረታ እና ለልጆች ከፍተኛ ትምህርት ያኖራሉ::
እንደውም የአሜሪካን አገር ፖለቲካን ልብ ላለ ሰው የሰሞኑ የፖለቲካ ጭቅጭቅ የአገሪቷን የብድር ጣሪያ ከፍ በማድረግ እና ባለማድረግ ላይ ነው:: ክርክሩም በፖለቲካ ፍልስፍናቸው ከፕሬዚዳንቱ ወገን ባሉ እና ጣራው ከፍ መደረግ አለበት (ጣራው ከ14 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ነው) የሚሉት ወገኖች የሚያነሱት መከራከሪያም “ይህ ጣሪያ በጊዜ ከፍ ካልተደረገ የአሜሪካን የብድር ነጥብ (Credit score) ይጎዳል:: ወደፊትም ማዕከላዊ መንግሥቱ ብድር በየትኛውም መንገድ ቢፈልግ ለማግኘት ይቸግረዋል : ስለዚህም ጣራውን በጊዜ ከፍ ማድረግ አለብን” የሚል ነው፤ በሌላው ወገን ያሉት ሪፐብሊካኖች ደግሞ “የለም መንግሥት የሚያጠፋውን የገንዘብ መጠን ካልቀነሰ እና ወጪ የሚያስወጡ መርሃ ግብሮችን ካላጠፈ የብድር ጣሪያውን ከፍ አናደርግም” የሚል ነው::
የኢሕአዴግ ቦንድ
አሁን ወደ ኢትዮጵያ መንግሥት ቦንድ ልመለስ። የኢትዮጵያ መንግሥት ያወጣው ቦንድ የ5፣ የ7 እና የ10 ዓመት የመብሰያ ጊዜ (Maturity date) ያላቸው ሲሆኑ የወለድ መጠናቸውም እንደቅደም ተከተላቸው 4%፣ 4.5% እና 5% ነው (በ1% የወለድ መጠን ልዩነት ብቻ የ10 ዓመቱ ቦንድ ከ5 ዓመቱ ቦንድ እንዴት የተሻለ ሳቢ ኢንቨስትመንት (attractive investment) ሊሆን እንደሚችል አልገባኝም!!!):: እንደ ማንኛውም ኢንቨስትመንት ቦንድም የራሱ የሆኑ የአክሳሪነት ወይም የአትራፊነት እጣ እድል አለው:: ምናልባትም ያሉትን የአክሳሪነት አደጋዎችን እዚህ በመዘርዘር እጅግ አስፈላጊ ነው።
አንዱ የቦንድ አደጋ (Bond risk) የወለድ ምጣኔ መዋዠቅ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ይሄ በጣም ሲበዛ የሚከስት እና አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ ነጻ ባልሆነ እና በህወሃት የፖለቲካ እሽክርክሪት ስር ያለ ማዕከላዊ ባንክ ባለበት ሁኔታ መሆኑ የአደጋውን (Risk level) ደረጃ ከፍ ያደረገዋል:: መንግሥት የሚሸጠው ቦንድ ዋጋ ምን ያህል ከወለድ ምጣኔ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ምንም የሰጠው መረጃ ባለመኖሩ ያለዚህ መረጃ እንዴት ሰዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለመጠየቅ እንደደፈረ የሚደንቅ ነገር ነው:: ይሄ ነገር በብዙዎች እንደተገመተው የፖለቲካ እይታን ለማንሸዋረር ወይም ገንዘብ ለማግበስበስ በአጭር ጊዜ ብዙም ሳይታሰብበት የተጀመረ ለመሆኑ አንድ ማስረጃ ሊሆን ይችላል:: ወለድ ሁለት አይነት ነው፤ ይኸውም የአገር ውስጥ የገንዘብ ወለድ ምጣኔ ሲሆን ከውጪ አገር በሌላ አገር ገንዘብ ለሚገዙ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ ምጣኔም (Exchange rate) ሌላ ተጨማሪ አደጋ ወይም እድልንም ሊሰጥ እንደመቻሉ የቦንድ ግዢ ውሳኔ ስሌት ውስጥ ማስገባት ግድ ይላል::
ሌላው አስተውሎት የሚፈልግ የቦንድ ሁነኛ አደጋ ደግሞ የዋጋ ግሽበት ነው። ይህም አሁን ቦንዱ በተገዛበት ወቅት ያለው የገንዘብ ዋጋ እና ቦንዱ የመብሰያ (Maturity date) ጊዜው ደርዶ በገንዘብ ሲለወጥ ያለው የመግዛት አቅም ሲነጻጸር የሚኖረውን ልዩነት ማለት ነው:: አሁን ያለውን የዋጋ ግሽበት ላስተዋለ ሰው እና ለምሳሌ ከአምስት ዓመት በፊት 500 ብር ሊገዛ የሚችለውን ነገር እና ዛሬ ላይ 500 ብር ሊገዛ የሚችለውን በማወዳደር፣ ከዚያም ተነስቶ ከዛሬ ላይ ወደፊት አምስት ዓመት በመሄድ 500 ብር ሊገዛ የሚችለውን ነገር ወይም ሊኖረው የሚችለውን የመግዛት አቅም በማገናዘብ መረዳት ይቻላል:: አሁን ባለው መንግሥት ባመነው እና በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን ባወጣው የዋጋ ግሽበት አሃዝ የ25% የዋጋ ግሽበት አለ። በዚህ ስሌት ብቻ አንድ ቦንዱን የገዛ ሰው በቦንዱ የመብሰያ ጊዜ (maturity date) የዋጋ ግሽበትን ተከትሎ በሚፈጠር የመግዛት አቅም መውደቅ ምክንያት አብዛኛውን የገንዝቡን መጠን ሊያጣ እንደሚችል ግልጽ ነው።
ብድር ያለመክፈል (Credit/Default risk) አደጋ ሌላው የዝርዝሩ አካል ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት “የምከፈለው ብር አቅም የለኝም” ካለ የለኝም ነው:: ምን ታረገዋለህ/ታረጊዋለሽ?! ቦንድ ምንም ማስያዣ (Collateral) የሌለው የብድር አይነት ነው:: እንደ ኢትዮጵያ ሕግና ፍርድ ቤት የገዢዎች መቀለጃ በሆነበት አገር ወደ ፈጣሪ እንባን ረጭቶ ዝም ከማለት የተለየ አማራጭ ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል። አለቀ ደቀቀ::
ሌላው እና ሊሆን የሚችለው አደጋ የሊኩዊዲቲ (Liquidity) አደጋ ሲሆን ይህም ፕሮጄው ከእነአካቴው አክሳሪ እና የማያዋጣ ሆኖ የመገኘቱ ጉዳይ ነው:: ለመሆኑ ቦንዱን የሚገዙ ዝርዝር የአዋጭነት ጥናት (Feasiblity study) አይተዋልን? ፕሮጀክቱ አዋጭ ነው ወይ? ምናልባት ሁለት ዓመት ከተሰራ በኋላ የፕሮጄ ወጪው በፍጹም ሊያዋጣ የማይችል ሆኖ ቢገኝስ? ቀጣይነቱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ቢገባስ? ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነገር ጀምሮ ማቆም ብርቅ አይደለም:: የጣና በለስ እና የአልዌሮ ግድቦች በምሳሌነት ይወሳሉ:: ሌሎች የብድር ደረጃ ማቆልቆልን (Rating downgrades) የመሳሰሉ አደጋዎች የኢትዮጵያ መንግሥት ሲጀምርም የብድር ደረጃ ስለሌለው እምብዛም አይመለከቱትም::
ከመንግሥት ቦንድ መግዛቱ ጥቅሙም ሆነ ክፋቱ ምኑ ላይ ነው? ለሚሉ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ልሞክር:: አንድ በፌስ ቡክ ላይ በወዳጅነት ፖለቲካ የምናወጋ ወዳጄ ቦንዱ እየተሸጠለት ያለው ግድብም ሆነ ቦንዱ እራሱ በኔ እምነት ለጊዜያዊ የፖለቲካ ፍጆታ የመጡ አዲስ ስልቶች መሆናቸውን ለማስረዳት እና ምንም እናኳን ቦንዱን የመዛግትም ሆነ ያለመግዛት የመጨረሻ ውሳኔ የግል ቢሆንም እኔ የመሰለኝን ሃሳብ ሳስረዳ ምን አለችኝ መሰላችሁ:: “ቀነኒሳ በቀለ እንኳን ቦንድ ገዝቷል።” ነገርዬው ፈገግ አደረገኝ:: እኔም ለጠቅ አድርጌ “ታዲያ ቀነኒሳ ከመቼ ጀምሮ ነው የዎል ስትሪት ባንከር የሆነው ብዬ?” ለምላሹ ሌላ ጥያቄ ሰነዘርኩ:: መቼም ነገሩ ፕሮፖጋንዳ አይደል? ቀነኒሳ ስለገዛ አንተም፣አንቺም ግዛ ነው ነገሩ:: ለነገሩ ቀነኒሳ ምናልባት አውቆትም ይሁን ሳያውቅ ዛሬ በዚህ ቢከስር ነገ ሮጥ ብሎ ብር ሊያመጣ የሚችልበት አቅምም በገንዘብ ሊሸጥ የሚችልም ስም ስላለው ለሱ ብዙም ሊያሳስበው አይችል ይሆናል:: ለእንደ እኔ አይነት ብዙኀን ለፍቶ አዳሪዎች ግን ደግመው ደጋግመው አስበው ሊያደርጉት የሚገባ ውሳኔ ነው::
እስቲ አስቡት የኢትዮጵያ መንግሥት ኤልክትሪክ እሸጣለሁ ካለ ይኸው ስምንት ዓመት አለፈው:: ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው ከእንግዲህ ወዲያ ከተራ ዜጎች ገንዘብ ሰብስቦ ግድብ ሰርቶ ከዛ በኋላ ችስታ ለሆኑ ሌሎች ጎረቤት አገሮች ኤሌክትሪክ ሸጦ ከዛ በኋላ ከነወለዱ ለእኛ በጊዜ ገንዘባችንን ሊመልስ የሚችለው? ከኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ቦንድ ቢገዙ ገንዘቡን ከማጣት በላይም (አዎን ይህ ሊሆን የሚችል ነገር ነው) ገንዘብ ሰዶ እንግልት ማምጣት ይኖራል:: ቤት ሰርተው ያከራዩ ሰዎች እንደ ወንጀለኛ አሻራ አምጡ እየተባሉ ሲንገላቱ ይኸው እያየን አይደል! ከሥራ ፈቃድ ወስደው ከአሜሪካ ኢትዮጵያ ድረስ አሻራ ለመስጠት ሄደው የተንከራተቱ ሰዎችን በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ እሮሮ ሲያሰሙ ማድመጤን አስታውሳለሁኝ:: በገዛ ዳቦዬ ልብ ልቡን አጣሁኝ ማለት ይህ ነው::
ነገሬን ለማጠቃለል እንደ ኢሕአዴግ የመሳሰሉ በሕዝብ ውክልና የሌላቸው መንግሥታት ዕድሜ መተንበይ አዳጋች በሆነበት በዚህ ወቅት ለታማኝነት ብዙም ዝና ከሌለው መንግሥት ጋር የገንዘብም ሆነ ሌላ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል ውል መዋዋል የኢኮኖሚ አስተዋይነት (Economically prudent) አድርጌ አልወስደውም::
I am glad that ANO continued providing top-notch well informed articles. Thanks!!
This is the most informative article I have ever read regarding this bond issue. Thank you S. Girma and Addis Neger.
መንግስታችን አባይን ለስም ተጠቀመ እንጅ ያባይ ቦንድ ወይም የሚሊንየሙ ግድብ ቦንድ የሚባል ነገር የለም!!! ግሩም ነው መቸም። አቶ መለስ ስርቆትን ያውቅበታል። አባይን ጠርቶ ገንዘብ መሰብሰብ ምን ይሉታል?
ነገሬን ለማጠቃለል እንደ ኢሕአዴግ የመሳሰሉ በሕዝብ ውክልና የሌላቸው መንግሥታት ዕድሜ መተንበይ አዳጋች በሆነበት በዚህ ወቅት ለታማኝነት ብዙም ዝና ከሌለው መንግሥት ጋር የገንዘብም ሆነ ሌላ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል ውል መዋዋል የኢኮኖሚ አስተዋይነት (Economically prudent) አድርጌ አልወስደውም::
The whole explanation of the piece made after you set the above ridiculous conclusion first. You raised an economical related question but you reached at a political decision but despite your deceivingly colored explanation you won’t garb the attention of the majority of Ethiopians but only few of your mind like readers.
You guys are surely involved in a risky and dreadful political game. It is enough to see the set of serial arguments and the pattern of change in the content of the argument against this Grand renaissance Dam the last few months. Actually these set of arguments were appeared to be for few ones’ frustration, and for the majority ones’s salivation.
To mention few of these deceivingly set arguments;
1. I think it was last year few extreme Diaspora politicians protest against the idea of constructing Dam in front of Colombia University in Washington DC.
( This was proved to be wrong, that idea was pretty dealt with the government)
2. Few months ago, you were saying that the government raised this issue because there was a cloud of fear of North Africans style of political uprising
( This was again proved to be wrong, Ethiopia is continuing as peaceful and the most stable East African countries)
3. In the last month, you were saying the government raised this issue because it is only to rub the national feeling of the Ethiopian people and even this renaissance Dam was not there in the five years Growth and transformation plan. you were adamantly saying this is done for political decoration and consumption.
( This was again proved to be wrong that even the Egyptian government was much concerned and believed that the Ethiopian government is highly committed to construct this Historical Dam)
4.In the last few weeks, when the Ethiopian people was involved and committed to be part and parcel of this historical Dam, you were saying the people was pressurized by the government to buy bonds.
( Again deadly wrong argument. Let alone bonds, people are donating money for free)
5. I think you guys are run out of steam for pseudo arguments, today you reappear from the very unusual place to say that the Ethiopian government is not honest enough to pay back the money for the purchased bond.
I see inconsistency and loose association in the thought flow. When we see those ridiculous and pseudo arguments, is it not right to think the mental health concern of these individuals? What else less than this describe the situation?
THE GRAND RENAISSANCE DAM WILL CONTINUE BEING ONE MAN’S FRUSTRATION, MANY ONES’ SALIVATION
The increasingly cadresque Teshe wrote “THE GRAND RENAISSANCE DAM WILL CONTINUE BEING ONE MAN’S FRUSTRATION, MANY ONES’ SALIVATION”. I couldn’t agree more: many people will keep salivating but not eat as long your paymasters are at the helm :)
But seriously man, the dam is not yet built, so stop making such stupid statements.
A brief information about the economic deception of tplf on Abay and Ethiopians!!
I am glad if all Ethiopians and members of ‘Melese party’ can easily grasp the point of this article!!
Appreciated!!
ብዙዎቻችሁ ፡ ቦንድ ገዝታችሁ “ድንገት ባናተርፍ” የሚለው ሃስብ እንቅልፍ እየነሳችሁ ይመስላል። ይህ ደግሞ በካፒታሊስት ስርዓት ውስጥ እንዳላችሁ ጠቋሚ ይመስለኛል።
ድፍን የእትዮጵያ ህዝብ፡ ተማሪ፡ ታራሚ፡ ቀበሌዎችና ዕድሮች ጭምር፡ ከደሞዜ፡ ከምሳዬ፡ ከገቢዬ…ይህን ያህል ይቆረጥና ግድብ ይሰራበት ሲሉ ለምን ይመስላችሁዋል?
እነኚህ ሰዎች ከናንተ ያነስ የወር ገቢ እንዳላቸው አትጠራጠሩ።
ህዝቡ እንኳን በገንዘቡ በደሙም ቢሆን አባይን ይገድባል! ታስፈለገ ዋቢ ሸበሌንም እንገድባለን። መብታችን ነው። ኢትዮጵያን ወደ ፊት ለማራመድ አማርጩ ይህ ብቻ ነውና!
አሁን አሁን ሳስበው:: የመለስ መንግስት በጣም ቸስቶ ለደመወዝ መክፈያ ከሰው በቦንድ ስም ብር እየቀፈለ ያለ ይመስለኛል:: እንዳምናው እና ካቻምናው ብር በገፍ እንዳያትም የዋጋ ግሽበቱ ጣራ ቀዶ ከወጣ ሰነበተ:: የኢትዮጵያ ብር የዚህቧብዌን ገንዘብ ሊሆን ምንም የቀረው አይመስልም:: ስለዚህ ያለው አማራጭ በድህነት አጥንቱ ገጦ የወጣውን ኢትዮጵያዊ ክብር ከዚህ በፊት ወለድ አግድ አሲይዞ ከውጪ እርዳታ እና ብድር ማምጣት(ይህች እንኳን እየከበደች የመጣች ትመስላለች) አሊያም ሰበብ እየፈጠሩ ያለ ምንም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት በቦንድ እና በ’ስጦታ’ ስም ያለውን ብር ማሽከርከር ነው:: ይህም ቢሆን አንዴ ካልሆነ ሁሌም ሊሆን የሚችል ነገር አይደለም:: ቀጥሎ ደግሞ መንኮራኩር ማርስ ላይ ልናወጣ ነው ብር አዋጡ ካላሉ ማለት ነው:: ለማንኛውም አሁን ያለውን የዋጋ ግሽበት ላስተዋለ የነሱን እርባና ቢስ የቦንድ ወረቀት ተሸክሞ ቤት ከማጣበብ አንድ ፊቱን እንካችሁ: አፈር ብሉና ብሉት ብሎ በ’ስጦታ’ መስጠት ይሻላል- ግዴታ ከሆነ ምን ይደረጋል:: ቀን እስኪወጣ ድረስ::
There will not be any Abay Dam, at least in the near future. I think the main objective of the bond is to withdraw money from the market and control the rising inflation. Meles’ government is more worried about the inflation which is skyrocketing at an alarming rate. Government bonds are always advertised on the TV and radio, though they are not attached to any kind of investment. Probably the routine way of bidding government bonds have not been effective. Now the government is trying to force people into buying one. Abay Dam is a good execuse in this respect.
ተሾመ
መቼም ዘንድሮ የአቡዬን ጸበል የጠጣ…..እንዲሉ ገና ሳይጠይቋችሁ የሰራችሁት ግፍ ያስለፈልፋችኋል:: ባለፈው ም/ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከአንድ የህንድ ቴሌቪዥን ጋር ቃለመጠይቅ ሲያደርግ ሳይጠየቅ ‘land grab’ እያለ ሲለፈልፍ አየነው:: መለስ ዜናዊም ሰሞኑን ገና ሳይጠየቅ ስለ ሃብት ክፍፍል እና ጂኒ ኮኢፊሸንት(gini coefficient)ማላዘኑ ቀዳሚ ስራው አድርጎታል::እንዲሁ ሳወጣ ሳወርደው: ይሄ ሰውዬ የሃብት ክፍፍሉ(ሃብትም ካለ ነው!!!) እጅግ የተዛባ መሆን ሃሳብ ላይ የጣለው ይመስላል::
ወዳንተ ስመለስ በእውነቱ ከሆነ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ተነጥለው ሊታዩ የማችይሉ በጣም የተሳሰሩ ነገሮች ናቸው:: በተለይ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በጣም አንገብጋቢ የሆኑ ጉዳዮች ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ በአንድ ግለሰብ የግል ውሳኔ እና ፍላጎት(whim) ላይ በተንጠላጠለበት ሁኔታ የፖለቲካው እና የኢኮኖሚው ትሥሥር የሁለት ተጣብቀው የተወለዱ መንታዎች(Siamese twins) ያህል ነው:: ስለዚህ ስለኢኮኖሚው ለማውራት ፖለቲካውንም አብረህ ማሰብ ግድ ይላል::
Insightful article. Considering these bonds as an investment is an utter stupidity and an extraoridinary financial igrorance. From investment point of view they are junk bonds, and rational investors would demand very high level of interest to compensate them for default risk, inflation, illiqyidity, and long maturity periods.
One striking paradox is: very liquid and short term saving accounts in one of the private banks pay about 5% interest per annum, why would I lock up my money with corrupt government for 5/10 years to get the same interest?
I think most people wish what you say are correct. It is good to support wholeheartedly but it misses the point. Reading all your five point arguments, I was thinking, hey there are people out there who think that way. Don’t forget, we criticizes and even demonize our government simple because we think we deserve better government. Many people including me think over and over again before we accept any proposal from the government. Do you have to be blind and support everything to survive?
Really informative article by S. Girma and well explained so that a layman can even understand the idea behind the article. I salute Mr S. I like this one “ቦንድ ማለት በግርድፉ ሲፈታ የ’አለብኝ’ ስምምነት ነው::”
What I would add to this piece is what makes this bond more successful than previous bonds the government issued and failed like the bond by EPPCO? And I dont know if you can get the necessary information but under what context is the people buying the bond/ Are they really thinking it as an investment or a charity to the project?
I must say most people dont know it is investment and they consider the contribution done under their name by their offices is similar to the one when there was a border conflict with our neighbor. So the EPRDF’s strategy is as said earlier stealing from the poor under the pretext af a threat from Egypt for the construction of the dam.
The diaspora community is well informed of the facts their small drama to steal from them failed faster than a lil kid who is tryin to walk for the first time. The buzz in the country due to the dam is because every suck up member at the management position of government offices is tryin to please his boss with contribution and forcing an employee to give away his money..
If possible will try to write a post abt the dam from an investment point of view? is it a good investment? is the people’s wealth fairly distributed if the project proceeds in this environment?
Power to the people!!
Given TPLF’s record of treachery, it won’t be surprising if at some later date they come up with explanation to not pay up when the bond mature. They do not seem to be long term thinkers they just do what gets them out f a bind today. This frenzy of ye enat ager teri was seen during the derg years. About five years ago the dollar was going for about 10 birr today it goes for nearly 20 that is 100% rise. 5% interest rate does not even account for inflation. As they squandered that national sentiment during the Eritrean war 10 years ago, they are reapting that today. When they are done they will have abused every national feeling and nobody will respond to such feelings that stirr national feeling. That in short is the end game of TPLF a sworn enemy of the Ethiopian state
gud yigermal!!!!!!!!!!!!!!! yihe yeferedebet deha hizib meche yihon yemiyalfilet???????????? egzerum bekachu lil alchalem, endew min yishal yihon????
@ Teshome:
You said: “I think it was last year few extreme Diaspora politicians protest against the idea of constructing Dam in front of Colombia University in Washington DC.” ( This was proved to be wrong, that idea was pretty dealt with the government)”
The European colonialists were constructing bridge and dams in Africa. The Italian constructed the major roads, dams and bridges in Ethiopia. The white racists in South Africa have also done constructed roads, bridges and skyscrapers. But this does not make them good or God. Racists remain racists. So, ወያኔ remains ወያኔ and this does not make ወያኔ and the white racists in South Africa or the British colonialist ቅዱስ. All these oppressors have one thing in common. They think they will rule remain in power for thousands of years: Remember Hitler, Ceausescu, Mussolini, Ben Ali, Mubarak, Ali Abdalla, and your petty dictator Zenawi. Don’t blame the Diaspora for extremism. TPLF and its commander-in-chief are personified tribal and primordial entities.
You said “Few months ago, you were saying that the government raised this issue because there was a cloud of fear of North Africans style of political uprising. (This was again proved to be wrong; Ethiopia is continuing as peaceful and the most stable East African countries)”
Your definition of peace is laughable. All indicators in Ethiopia contradict your assertion that the country is table. That was what Mubarak, Ben Ali, Ali Abdalla, Mengistu, Idi Amin, Mugabe, etc were telling their people. Did you see the 10,000 + Agazi killers beating people to evacuate the Palace-Bole Airport road whenever this petty dictator is coming and going? በኑሮ ውድነት የተጎሳቆለን ህዝብ ሰላም ሰፍኖለት በሰላም የኖራል ማለት በህዝብ ብሦት ላይ ማሾፍ ነው፡፡ The current ዝምታ of the people is not an indicator of what you call ወያኔዊ ሰላም rather it is the calm before the storm. Nether Africa political uprising not happening in Ethiopia does not mean that it will not happen. Absence of evidence of something happening now is NOT evidence of absence of something happening in the future.
You said “In the last month, you were saying the government raised this issue because it is only to rub the national feeling of the Ethiopian people and even this renaissance Dam was not there in the five years Growth and transformation plan. You were adamantly saying this is done for political decoration and consumption.” (This was again proved to be wrong that even the Egyptian government was much concerned and believed that the Ethiopian government is highly committed to construct this Historical Dam)”
Yes, the አባይን ልገድበላቸሁ is political decoration and consumption and it is one of the hundreds and thousands of ወያኔ ማጭበርበሪያ እና ማጨናፈሪያ:: The most important thing is to confuse cheat, lie, kill so long us it keeps Meles and his thugs in power even for one second. As Machiavelli said “the end justifies the means.” What TPLF is doing is ብሄራዊ ሰሜት ቀስቅሶ በዚያ በኩል የምትመጣን እንጥፍጣፊ ደጋፍ ለአንድ ሰኮንደም ቢሆን ሰልጣን ላይ ለመቆየት ለመጠቀም ነው፡፡ ለመሆኑ የአባይ ግደብ ለወላይታው ለአፋሩ ለከነባታው ምኑ ነው?
You said “In the last few weeks, when the Ethiopian people was involved and committed to be part and parcel of this historical Dam, you were saying the people was pressurized by the government to buy bonds. ( Again deadly wrong argument. Let alone bonds, people are donating money for free)”
Not only pressurized but also imprisoned. Those donating “free” are those TPLF benefited Mafia thugs. Do you know that in the many part of the county people are forced to donate almost three months salary for የወያኔ ተለጣፊ Party ልደት፡ የአካባቢ ልማት፤ የአባይ ግድብ, etc. When our salary was deducted by force during Mengistu time, there were many Teshomes who used to tell us that people were donating money free. During Mengistu this was called የወዴታ ግዴታ::በዚህ ኑሮ ወድነት My friend ራሱን መረጦ ሰልጣን ላይ ለተኮፈሰ የወያኔ ጭራቅ there is no rational being who can freely give money except those fatten by the TPLF policy. ለመሆኑ የአባይ ግደብ ለወላይታው ለአፋሩ ለከነባታው ምኑ ሆኖ ነው ገንዘብ የሚያዋጣው?
You said “I think you guys are run out of steam for pseudo arguments, today you reappear from the very unusual place to say that the Ethiopian government is not honest enough to pay back the money for the purchased bond. I see inconsistency and loose association in the thought flow. When we see those ridiculous and pseudo arguments, is it not right to think the mental health concern of these individuals? What else less than this describe the situation?”
There are no independent judiciary and/or rule of law institution in TPLF Ethiopia,. Everything is the extension of ወያኔ. So, what is the guarantee that these “unelected thieves in power” cannot cheat and run daylight robbery? There is one thing they wanted to communicate to us: At least they intend to stay in power for the next 10 year by any means until they mature their bond.
You said “THE GRAND RENAISSANCE DAM WILL CONTINUE BEING ONE MAN’S FRUSTRATION, MANY ONES’ SALIVATION.”
On the contrary, THE GRAND THEFT, CHEATING AND LIES OF TPLF WILL CONTINUE BEING MILLIONS’ FRUSTRATION AND FEW THUGS SALIVATION.!!
Good arguments!!!!
Lubak
First I should appreciate your descent response and your language was pretty well mannered. That was a fascinating stuff and I liked it man.
But Your arguments were extraneous in all parameters and it appeared as if we were talking two different Ethiopia. It tells me what platform you and your like minds stand on.
However such an axis of evil thinking takes you no where but the very good thing is we, Ethiopians are extremely cautions of such people motives.
You can hate the government (ወያኔ as you wished to call it) for millions of reasons but I couldn’t understand at any instance why you people are flooding with eyes of the construction of this Grand renaissance Dam.
You know what I hate your two previous brutal government, Hailesselasie and Mengistu regimes but if they were the ones who initiated this noble idea, I wouldn’t for a second oppose this good thing – mind you keeping the political difference I had.
But the scenario you had is absolutely different and even I can assume you can go a great length to use every ammunition and Arsenals to explode the Dams constructed by ወያኔ ( like Tekeze, Gibe, Belese and now the planned Abbay).
This is the point why I raise the mental health concern of these people. You guys need a professional help. That is absolutely disheartening
ወንድሜ አባይ ቢገነባና ሕዝቤ የመብራት ተተቃሚ ቢሆን በማን እድሌ ግን እስካሁን በሀገሪቱ በመዋጮ የተሰራ ስራና ግድብ ባለመኖሩና ያን ሰርተው ያለፋት ያኮሩኛል ነገር ግን አሁን ይኸ ቦንድ በሚባለው ነገረ ትርጉሙም ሆነ ስሪቱ ስለማይገባኝ ጎመን በጤና በማለት የተሻለ እስከሚገኝ ያለችኝን በቤቴ ጓዳ ቋጥሬ ማስቀመጡን በራሴ በኩል እወዳለሁ ።
Teshome, if that is your real name. To me you sound like Lekim the tribalist squatter who refused to leave.
Your futile attempt to misrepresent the opposition’s position on the issue does not work here. No Ethiopian would object to Ethiopia’s aspiration for equitable use of the Nile water. This is true for individuals as well as groups whether they are inside or outside the country. Ethiopia’s attempt to redress the colonial time arrangement that gave disproportional power to Egypt & Sudan is not new. Actually that issue alongside the Assab issue was the battle cry of Ethiopian nationalists in the opposition arguing that International law supports Ethiopia’s position. When Ethiopian nationalists took such position, what did your beloved tyrant Legesse Zenawi do? -Sign MOUs with Egypt affirming Egypt’s and Sudan’s position
-Take every opportunity defending EPLF’s claim on Assab
etc..
This smart-aleck guy now steals our voice and claim to want construction of dam on Abay. By now it has come clear that Legesse Wedi-Banda Zenawi latest unveiled plan was not meant for real construction of the dam but was rather a self-aggrandizing political or diplomatic ploy and money making scheme for cash starved TPLF conglomerates. He knows if the dam will be built, it will only be built with World Bank money after Egypt and Sudan agree to renegotiate for a new treaty and perhaps on tributaries rather than on Abbay itself. Shame on those who take hard earned money from Ethiopian families under the guise of patriotic duty. After reading this article, those who are buying bonds willingly are going to have rude awakening as those Eritreans who trusted EPLF and bought its bond.
The article is informative, at least for a person whose primary target is getting return for his/her investment. My heart tells me that this project will not be completed on time; there will be cost overrun; there will be other million problems including chnage of Government. But that will not prevent me from sacrifying 500 US dollars for my country. I do not expect to get any return for my money. If I get, GREAT. If not, this will be one sacrifice for a good cause. 500 US dollars will never make me rich. But if there are many other fellow with good heart, we may be able to make this dam possible! If the DEVIL builds the dam, that does not make it righteous. The DEVIl is still a DEVIL. But we will have our dam. You may say, what if they take the money? That is the RISK I will take to see my country take a step out of poverty!
@ Teshome
First, I do not understand why you want to call all people who oppose ወያኔ tribal and Lootocratic rule as “Axis of evil?” Rather they are “Axis of Resistance.”
Second, these days you repeatedly say those who oppose ወያኔ tribal and Lootocratic rule has “mental health” problem and I think you deserve a reply for this too to show you who really is suffering from a “mental health” problem.
I understand that your mental health patients are the people in the Diaspora and the home opposition. To characterize the Diaspora and home opposition is like “የምን አይነ ደረቅ መለሶ ልብ… እንደሚባለው ነው፡፡ ወይም ሌባው በገባያ ማሃል ሌባ ሌባ እያል እሮጠ እንደሚባለው ነው፡፡” There is no entity in Ethiopia that suffers all forms of mental health problem than ወያኔ and its associates.
Teshome:
It is rather Zenawi and his thugs that are suffering from what James Zumwalt appropriately called “Detached-Reality Syndrome (DRS)”. DRS is not a genetic disorder and is not found in the medical dictionary. But it is a disorder that seems to afflict dictators lake Mugabe, Mubarak, Zenawi, Ben Ali, etc. It is a product of the environment that is self-inflicted. It occurs when a brutal dictator purges his leadership circles of independent thinkers. James Zumwalt gives as an example from Saddam Hussein’s brutal rule:
“During Saddam’s reign of terror, he surrounds himself with “yes” men – people who told him only what he wanted to hear but never what he needed to hear to make an informed and rational decision. Those unfortunate enough to express their independent thought in his presence, such as the inner-circle member who suggested just before Saddam’s ouster that he consider seeking asylum in another country, soon discovered their leader had zero tolerance for such thinking. From the beginning of his regime, Saddam left no doubt he was judge and jury and, on some occasions, even executioner, ensuring everyone thought only as he thought. Few were willing to say anything to provoke Saddam’s wrath. Undoubtedly, in the days prior to Operation Iraqi Freedom, as was probably the case prior to the first Persian Gulf war, Saddam was assured by those around him that the Iraqi army would fight the good fight, extracting a heavy toll on the Americans and achieving victory in the end. Detached from reality, Saddam’s bravado prior to both wars probably was not false – for it may have reflected what he firmly believed based on what those around him had been saying. That such advice came from advisers predisposed not to object to their leader’s conditions had no rational bearing in Saddam’s mind.”
Suffering from this Saddam Hussein malady in Ethiopia is the ወያኔ leadership. Ethiopians for the past 20 years of ወያኔ rule have served TPLF leadership as a laboratory experiment in mind control forcing them to believe life during ወያኔ is utopia. Years of poverty, miss-rule, tribal favoritism, nepotism, looting, and የኑሮ ውድነት, etc have provided the Ethiopian people with a bitter dose of reality,. But the ወያኔ leadership and its ዘረኛ: ምርኮኛ እና ጥቅምኛ members remain detached from this reality. . In fact, at a time of devastating የኑሮ ውድነት where people are unable to eat once in a day, the ወያኔ leadership runs its propaganda machines to tell us that the country is peaceful and growing at double-digit, famine is “ history” and ብሄር ብሄረሰቦች ታይቶ በማይታውቅ ሁኔታ, በመፈቃቀድ (በመተቃቀፍ) አበረው እየኖሩ ነው:: የወያኔ ሳይንሳዊ እና ችግር ፈች አመራር. የብሄሮቸን ቅራኔ ብቻ ሳይሆን የፈታው አሁን በአገሪቱ ወስጥ አይጥና ድመት፤ ቀበሮና ፍየል፤ ጅብና አሀያ፡ አንበሳና በሬም በመፈቃቀድ (በመተቃቀፍ) አበረው እየኖሩ ነው: አይነት ነው የሚለን፡፡ The problem in the countei are the result of Kinjit, Andent, OLF, Shabiya, Ginbot 7, EPRP, etc. In other words, ወያኔ uses the Orwellian approach to find Ethiopian Snowballs as a scapegoat for its mismanagement of the country. In George Orwell’s dystopian allegorical novella- Animal Farm we read the following:
“Using a young pig named Squealer as a mouthpiece; Napoleon announces that Snowball stole the idea for the windmill from him. The animals work harder with the promise of easier lives with the windmill. After a violent storm, the animals find the windmill annihilated. Napoleon and Squealer convince the animals that Snowball destroyed the windmill, although the scorn of the neighboring farmers suggests the windmill’s walls were too thin. Once Snowball becomes a scapegoat, Napoleon begins purging the farm, killing animals he accuses of consorting with Snowball. Meanwhile, Boxer takes up a second maxim: “Napoleon is always right.” You can see clearly how Napoleon (Zenawi) uses the Squealers like Bereket and Kamal to run his ethnocentric experiment without a reality check.
Detached-reality syndrome is so firmly entrenched within the ወያኔ mindset that it tries to hide any truth even when it is too obvious to hide. This deception is openly evidenced by the official line put forth by the ወያኔ ETV, ውሸት Information Centre (WIC), Fana./Fara Radio, Reporter, Ethio-Channel, etc like the Communists used to do it in USSR. After the overthrow of Czar Nicholas II by the February Revolution of 1917, Soviet Russia had two main newspapers, Pravda, shown here above, and Izvestia, shown below. Pravda, which means “Truth”, was the official voice of the Communist Party and Izvestia, which means “News”, was the Official voice of the Soviet Government. One of the running jokes throughout most of the Soviet dominion over Russia was this assessment of the two newspapers by the non-Communist citizenry: “There is no Pravda in Izvestia, and there is no Izvestia in Pravda” or in English “There is no truth in News, and there is no news in Truth.”
Teshome:
Finally: የወያኔ አመራርና የወያኔ ዘረኛ: ምርኮኛ እና ጥቅምኛ አባሎች ሌላው የdetached-reality syndrome manifestation is that “በደርግ ጊዜ ያለሞተ ሰው በሙሉ ደርግ መስሎ ነው የሚታያቸው::”
Cheers
Dear ANOL,
Why it is not possible to past pictures?
@ Teshome
First, I do not understand why you want to call all people who oppose ወያኔ tribal and Lootocratic rule as “Axis of evil?” Rather they are “Axis of Resistance.”
Second, these days you repeatedly say those who oppose ወያኔ tribal and Lootocratic rule has “mental health” problem and I think you deserve a reply for this too to show you who really is suffering from a “mental health” problem.
I understand that your mental health patients are the people in the Diaspora and the home opposition. To characterize the Diaspora and home opposition is like “የምን አይነ ደረቅ መለሶ ልብ… እንደሚባለው ነው፡፡ ወይም ሌባው በገባያ ማሃል ሌባ ሌባ እያል እሮጠ እንደሚባለው ነው፡፡” There is no entity in Ethiopia that suffers all forms of mental health problem than ወያኔ and its associates.
Teshome:
It is rather Zenawi and his thugs that are suffering from what James Zumwalt appropriately called “Detached-Reality Syndrome (DRS)”. DRS is not a genetic disorder and is not found in the medical dictionary. But it is a disorder that seems to afflict dictators like Mugabe, Mubarak, Zenawi, Ben Ali, etc. It is a product of the environment that is self-inflicted. It occurs when a brutal dictator purges his leadership circles of independent thinkers. James Zumwalt gives as an example from Saddam Hussein’s brutal rule:
“During Saddam’s reign of terror, he surrounds himself with “yes” men – people who told him only what he wanted to hear but never what he needed to hear to make an informed and rational decision. Those unfortunate enough to express their independent thought in his presence, such as the inner-circle member who suggested just before Saddam’s ouster that he consider seeking asylum in another country, soon discovered their leader had zero tolerance for such thinking. From the beginning of his regime, Saddam left no doubt he was judge and jury and, on some occasions, even executioner, ensuring everyone thought only as he thought. Few were willing to say anything to provoke Saddam’s wrath. Undoubtedly, in the days prior to Operation Iraqi Freedom, as was probably the case prior to the first Persian Gulf war, Saddam was assured by those around him that the Iraqi army would fight the good fight, extracting a heavy toll on the Americans and achieving victory in the end. Detached from reality, Saddam’s bravado prior to both wars probably was not false – for it may have reflected what he firmly believed based on what those around him had been saying. That such advice came from advisers predisposed not to object to their leader’s conditions had no rational bearing in Saddam’s mind.”
Suffering from this Saddam Hussein malady in Ethiopia is the ወያኔ leadership. Ethiopians for the past 20 years of ወያኔ rule have served TPLF leadership as a laboratory experiment in mind control forcing them to believe life during ወያኔ is utopia. Years of poverty, miss-rule, tribal favoritism, nepotism, looting, and የኑሮ ውድነት, etc have provided the Ethiopian people with a bitter dose of reality,. But the ወያኔ leadership and its ዘረኛ: ምርኮኛ እና ጥቅምኛ members remain detached from this reality. . In fact, at a time of devastating የኑሮ ውድነት where people are unable to eat once in a day, the ወያኔ leadership runs its propaganda machines to tell us that the country is peaceful and growing at double-digit, famine is “ history” and ብሄር ብሄረሰቦች ታይቶ በማይታውቅ ሁኔታ, በመፈቃቀድ (በመተቃቀፍ) አበረው እየኖሩ ነው:: የወያኔ ሳይንሳዊ እና ችግር ፈች አመራር. የብሄሮቸን ቅራኔ ብቻ ሳይሆን የፈታው አሁን በአገሪቱ ወስጥ አይጥና ድመት፤ ቀበሮና ፍየል፤ ጅብና አሀያ፡ አንበሳና በሬም በመፈቃቀድ (በመተቃቀፍ) አበረው እየኖሩ ነው: አይነት ነው የሚለን፡፡ The problem in the countei are the result of Kinjit, Andent, OLF, Shabiya, Ginbot 7, EPRP, etc. In other words, ወያኔ uses the Orwellian approach to find Ethiopian Snowballs as a scapegoat for its mismanagement of the country. In George Orwell’s dystopian allegorical novella- Animal Farm we read the following:
“Using a young pig named Squealer as a mouthpiece; Napoleon announces that Snowball stole the idea for the windmill from him. The animals work harder with the promise of easier lives with the windmill. After a violent storm, the animals find the windmill annihilated. Napoleon and Squealer convince the animals that Snowball destroyed the windmill, although the scorn of the neighboring farmers suggests the windmill’s walls were too thin. Once Snowball becomes a scapegoat, Napoleon begins purging the farm, killing animals he accuses of consorting with Snowball. Meanwhile, Boxer takes up a second maxim: “Napoleon is always right.” You can see clearly how Napoleon (Zenawi) uses the Squealers like Bereket and Kamal to run his ethnocentric experiment without a reality check.
Detached-reality syndrome is so firmly entrenched within the ወያኔ mindset that it tries to hide any truth even when it is too obvious to hide. This deception is openly evidenced by the official line put forth by the ወያኔ ETV, ውሸት Information Centre (WIC), Fana./Fara Radio, Reporter, Ethio-Channel, etc like the Communists used to do it in USSR. After the overthrow of Czar Nicholas II by the February Revolution of 1917, Soviet Russia had two main newspapers, Pravda and Izvestia. Pravda, which means “Truth”, was the official voice of the Communist Party and Izvestia, which means “News”, was the Official voice of the Soviet Government. One of the running jokes throughout most of the Soviet dominion over Russia was this assessment of the two newspapers by the non-Communist citizenry: “There is no Pravda in Izvestia, and there is no Izvestia in Pravda” or in English “There is no truth in News, and there is no news in Truth.”
Teshome:
Finally: የወያኔ አመራርና የወያኔ ዘረኛ: ምርኮኛ እና ጥቅምኛ አባሎች ሌላው የdetached-reality syndrome manifestation is that “በደርግ ጊዜ ያለሞተ ሰው በሙሉ ደርግ መስሎ ነው የሚታያቸው::”
Teshome;
I bet you are a retard;period!
Some Questions to Teshome, I hope you will have answers to the following basic questions.
In Ethiopia most security and financial institutions are occupied by members of one tribe(note that am not referring to the whole tribe like what u would like me to do so. only few members like it was during the last Ethiopian rulers). What is your idea?
Do u think institutions like election board, police and military are neutral in Ethiopia?
What is your idea about the corruption going on in Ethiopia?
Do u think it is best for ethiopia to have ethenic federalism system?
Meles promised that we will eat three times before 20 years. still ppl are starving. Dont u think there is some problem? Do u think it is healthy to for one person to rule us for 20 years? Compare the democracy in Ghana and in Ethiopia, How do u compare it? Do u think there is freedom of speech,freedom of writting etc in ethiopia?
How do u see meles’s stand on Assab port and on eritrea generally?
If you give me satisfactory answers to the above questions and few more, I will change to EPRDF supporter because that would mean i was wrong. Hopefuly u would not twist my qusestions. I believe we have difference and we need to share ideas coz there might be chances to atleast narrow our difference as citizens of one country.
@Ewnet
You have all the right to do whatever you think is right.
We are discussing principles not whether our contribution would make us rich or poor. As you know one of the strategies ወያኔ uses to stay in power is through systematic and periodic “RATIONINIG” of political, social and economic agenda. They have many of these agendas in their available stock and use them depending on the type of fear they sense to change public opinion. እነሱ እየመጠኑ በሚወረውሩት አጀንዳ እኛ ሰንባላ እነሱ ስልጣን ላይ ያቆየናል ብለው የሚያስቡትን ሌላ አጀንዳ እያቦኩ ይጋገራሉ፡፡ For example:
• ብሶት የውለደውን ሰዉየ ሰመተን ሳንጨረስ፤ዲሞከራቲክ የሚግ ተዋጊ አውሮፕላን አብራሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተመረቁ የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• በወረወሩልን አንቅጽ 39 ተባለተን ሳናበቃ፤ የተከራይ አከራይ የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• በተከራይ አከራይ አጀንዳ ተባለተን ሳናበቃ፤የባድመ ወረራ የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• በባድመ ወረራ አጀንዳ ተባለተን ሳናበቃ: የአልጀርስ ሰምምነት የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• በአልጀርስ ሰምምነት አጀንዳ ተባለተን ሳናበቃ: የሄግ የድንበር ኮሚሽን የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• በሄግ የድንበር ኮሚሽን አጀንዳ ተባለተን ሳናበቃ:እንከን የሌለው ምርጫ የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• በእንከን የሌለው ምርጫ ጉንጫችነን ሰናለፋ;የጎዳና ነውጠኞች የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• በጎዳና ነውጠኞች ስንራኮት በአገር ክህደትና ዘር ማጥፋት የተከሰሱ የቅንጅት አመራሮች የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• በአገር ክህደትና ዘር ማጥፋት የተከሰሱ የቅንጅት አመራሮች በሚለው አጀንዳ ሰንተራመስ የተማሪዎች ጉባኤ; የገበሬዎች ጉባኤ; የወጣቶች ጉባኤ: የሴቶች ጉባኤ: የነጋዴዎች ጉባኤ; የተለጣፊ ፓርቲዎች ጉባኤ: የክልሎች ጉባኤ; የሴተኛ ጉዳሪዎች ጉባኤ: የኢንቨስተሮች ጉባኤ:የወዛደሮች ጉባኤ etc የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• እነዚህን ሳንጨርስ; የባንዲራ ቀን የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• የባንዲራ ቀን የሚል አጀንዳ ስናንጎራጉር; የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የሚል አጀንዳ ስንወቅጥ አልሸባብ የሚል አጀንዳ ይዘው ሞቃዲሾ ይውርዳሉ::
• አልሸባብ የሚል አጀንዳ ስናማሰል; የኦጋዴን እና የኦንግ ሽብርተኞች የሚል መዝሙር ይዘምራሉ::
• የኦጋዴን እና የኦንግ ሽብርተኞች የሚል መዝሙር ዘምረን ሳንጨረስ: ልማታዊ መንግሰት፡ ልማታዊ ጋዜጠኛ: ልማታዊ ካድሬ: ልማታዊ ተማሪ; ልማታዊ ስጋ ቤት:ልማታዊ ጫት ቤት:ልማታዊ ዳንስ ቤት: ልማታዊ ጠላ ቤት; etc የሚል ከበሮ ይጎስማሉ:
• በልማታዊዎቹ ሰንተራመስ; የተከዜ፤ ግልገል ጊቤ፤ ሸበሌ ሃይል ማመንጫ: የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• በተከዜ፤ ግልገል ጊቤ፤ ሸበሌ ሃይል ማመንጫ አጀንዳ ስንመላለስ የኢትዮጵያ ህዳሴ የሚል ነጠላ ዜማ ይለቃሉ፡፡
• የኢትዮጵያ ህዳሴ የሚለውን ነጠላ ዜማ ለማሳመር የህዳሴው ድልድይ አባይ ላይ ተገነባ የሚል ከበሮ ይጎስማሉ:
• የህዳሴው ድልድይ አባይ ላይ ተገነባ የሚል ከበሮ ሲቀደድ: የዋጋ ቁጥጥር የሚል አጀንዳ ይዘው ሻጭና ሸማችን ያቧቅሳሉ:
• በዋጋ ቁጥጥር የሚል አጀንዳ ሰንረጋገም: ቤት በመፍረስ አና ሰዎችን ከመኖሪያቸ ማፈናቀል አካባቢን መልሶ ማልማት በሚል ካባ ተሸፍኖ በቅ ይላል፡፡
• በአካባቢን መልሶ ማልማት ጉድይ ሰንተራመስ: የኤርትራን መንግስት በሃይል ማስወግድ እና ስግብግብ የመሬት ሌባ ኢንቨስተሮች ተያዙ የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• የኤርትራን መንግስት በሃይል ማስወግድ የሚለውን አጀንዳ ስናቦካ: የአባይ ግደብ እና የአባይ ቦንድ የሚል አጀንዳ ይዘው ብቅ ይላሉ፡፡
• ወዘተ: ወዘተ; ወዘተ; ወዘተ:ወዘተ;ወዘተ …………………………………………
So, for ወያኔ and its propaganda architects የአባይ ድልድይ ጠቀሜታ የሚታየው ለኢትዮጵያ ባለው የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ሳይሆን : ወያኔ እንደልቡ ለሚሞቀው የስልጣን እሳት በማገዶነት ማገልገሉ እና ወያኔ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ክኒንነቱ ነው፡፡መቻሉ ነው::
Let me share with you what I got from Wikipedia:
“Nazi propaganda promoted Nazi ideology by demonizing the enemies of the Nazi Party, especially Jews and communists, but also capitalists and intellectuals. It promoted the values asserted by the Nazis, including heroic death, Führerprinzip (leader principle), Volksgemeinschaft (people’s community), Blut und Boden (blood and soil) and pride in the German race. Propaganda was also used to maintain the cult of personality around Nazi leader Adolf Hitler.
Nazi propaganda uses the total media portfolio for this purpose. Newspapers, Speaker, Posters, Films, Books, Text books, Comics, Magazines, Radio (Internal broadcasts and External broadcasts), and Fine art were fully controlled to run only the nazi version of reality.
Ewnet: Do you smell something similar in ወያኔ Ethiopia?
Cheers
andand gize risk wesdo hagerin megenbat teru new. ye Ethiopia hezb risk wesdo keshabya gar kebur hiywetun keflual, gin heyweten kemestet yemaytekawen birr seto tewleden makoyet yeshalal, poleticaw mechem yetebelashe new hulum yawkewal,gin esty ehadig lepoletica belo new gin yezot ayhedem ye abayen gedeb, shy amet kemerab biyanes sera lay enetebaber, bezy ehadigem gain yareg esty, egna mogne enehun.
ርቢው አታስቀን እባክህ ወንድሜ ደግሞ አታፍርም እንዴ ተማሪው የህግ ታራሚው ሌላውም ሌላውም በፍላጎት ለግድቡ አዋጣ ስትል ምነው ጃል እረ ትንሽ እፈር ወንድም አለም ለመሆኑ ለዚህ ነዋ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ቦንድ ካልገዛችሁ ተብለው ፈተና የተከለከሉት ግዴታ ማለት ላንተ ዉዴታ ከሆነ የስነ አእምሮ ሀኪም እንድትጎበኝ ወንድማዊ ምክር እለግስሃለሁ በል ወንድሜ አንድዬ ይማርህ.
Weret
Sir, Thank you for questioning the unpopular but just for the moment Please stay focus on the issue raised. We can’t discuss anything and everything at once. Keep this questions in your mind and you will raise them later on to the place they fit well. But that doesn’t mean I am less sympathetic.
Thank you
Lubak
I was so amazed, you proved yourself that you are indissociable from’Derge thinking’. At times you forgot that your government, I mean…some would like to call it “Nefetagnawe zemen” is dead for ever.
The statements does not make sense and is full of holes. Because I see in many of the arguments you gave us, your memory about ‘Derge’ may be slipping but YOUR BILE ISN’T.
What merit could one have in hiding himself in what happened in the last 20 years?
Please stay focus on the issue the writer raised…
Didn’t you hear… I am sorry I din’t have Amharic font but….
…Diro begorade zendero bebonde tebelule
@ TESHOME
Your way of arguing remains similar.”S. GIRMA” put his fears and doubts in understandable reasons and well mannered language.Respecting your opposing rights,you didn’t confront his reasons with reasons that could convince us against him. instead,u chose to mention “ነገሬን ለማጠቃለል እንደ ኢሕአዴግ የመሳሰሉ በሕዝብ ውክልና የሌላቸው መንግሥታት ዕድሜ መተንበይ አዳጋች በሆነበት በዚህ ወቅት ለታማኝነት ብዙም ዝና ከሌለው መንግሥት ጋር የገንዘብም ሆነ ሌላ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል ውል መዋዋል የኢኮኖሚ አስተዋይነት (Economically prudent) አድርጌ አልወስደውም::” and made your argument personal…these is the way of argument that “MELES” has been using for the last 20 years in parliament it’s called “circular argument” it’s defined as “when you can not confront the truth and reasons of your opponent just take out one phrase that he used and try to make fun of it”. So…
This guy called ‘Teshome’ is doing his job successfuly. These Woyane cadres are trained to act as ‘anchorman’ in pro-democracy blogs. Their main task is targeting good articles posted on the blogs and diverting the partcipants from the essence of the matter. Currently, the woyanes are trying to keep people focused on Abay Dam issue. In the middle of the argument they bring divisive topics such as ‘Derg’, ‘Nefitegna’, ‘nationalities’,'Diaspora’ etc. The main objective is to stifle questions of demoracy, rights, and freedom from being openly discussed among Ethiopians. I am not surprised most of the heated debate is still on the untimely topic of Abay Dam.
@ Teshome
Thank you for reply to my post.
I very well know (as you do) that Dergue was one of the worst regimes we had in our long History. Our problem is that we moved from Mengistu’s Dergue-I to Meles’s Dergue-II which is more primordial, primitive and backward in its content. By this, I want to tell you (once and for all) is that “የደርግ እርኩስነት ወያኔን ቅዱስ ስለማያደርገው” please stop comparing the two.
I do not know why የደርግ ሙት መንፈስ ከ20 አመት በህዋላ ከመቃበር አፍትለኮ ወያኔነና አባሎቹን ለምን እንደሚያተራምሳቸው? I brought my memory from Dergue time not because I was a member of Dergue or a beneficiary of its policy or admire that regime. Rather it was meant to counter your credulous assertion that “people are contributing free”. I said this was also exactly what we were told by many የደርግ ተሾመዎች፡፡
Finally, please የወያኔ አመራርና የወያኔ አባሎች “በደርግ ጊዜ ያለሞተ ሰው በሙሉ ደርግ መስሎ አይታያቸሁ ነው ለማለት የምፈለገው፡፡
Cheers Teshe!!
@ Ewnet
” Its a risk I am willing to take to see my country get out of poverty” REALLY? In a country where majority of a capital is wasted by corruption, do u believe its a risk worth taking?
I dont understand such people who turn blind eye to the facts and fall victims of woyane propaganda. 500$ wont make u richer?? dude it will make u 500$ richer and now u made one woyane thug 500$ richer. No u made woynae i AK 47 richer… did u ever got that for a fact?
@Teshome
I dont agree with your comments made at the top. I believe the writer explained what bond is, and how it is implmeneted, and judged from political facts that is is not a risk worth taking with the current government… Where do u see the fault? Mixin economy and politics?? Wake up Teshe, economy policy is one of he biggest issues in politics ever since the introduction of communism dude. Didnt expect this much inanity from the only outspoken supporter of the government.
On second thoughts proves me again and again that there is no intellect from the other camp. Always denying facts and living in false reality. A good response will be “so far the government has completed these project successfully and with this much budget so we can trust the government”. Dont know if u can post an article here but would luv to hear ur side of the story and challenge u there.
Power to the people!!
“አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል”
correction; new one
“አባይ ማደሪያ የለው ደሞዛችንን ይዞ ይዞራል”
Gifti
For the comment I forward as “I can assume you can go a great length to use every ammunition and Arsenals to explode the Dams constructed by ወያኔ ( like Tekeze, Gibe, Belese and now the planned Abbay).
You responded as…..
“Your futile attempt to misrepresent the opposition’s position on the issue does not work here.”
Who do you think speak close to the reality we know? Here you have the link from your favorite propagandist blog. I preferred to call it ‘Eritrean review’
http://www.ethiopianreview.com
‘Opposition group cut power in western Ethiopia’
I know sometimes desperation urge you to go through the walls of fear. ( fear of reality).
But what do you think the single biggest reason of such desperate action?
AddisNeger Editors,
This is one article that needs to get into the hands of every Ethiopian. I hope you understand the urgency of the matter to make this possible. Ultimately, the question is this: Is the current government putting pressure on citizens to a point where saying NO to buying bonds results in punitive measures of one type or another? Similar to joining the ruling party resulted in employment!?