ከሐረር ጦር አካዳሚ እስከ ካባካ ቤተ መንግሥት

ካምፓላ ሜንጎ የሚገኘው የባጋንዳ ብሔር ንጉስ (ካባካ) ነጭ ቤተመንግስት በተለምዶ የሚያረብብት ጸጥታ ዛሬ የለም። ንጉሳቸውን የወንዶች ሁሉ የበላይ (ሳባሳጃ) ብለው ለሚጠሩት ባጋንዳዎች ዛሬ የሀዘን ቀን ነው። ሜይ 24። በዚህ ቀን ነበር የቀድሞው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሚልተን ኦቦቴ በባጋንዳ ታሪክ መዝገብ ላይ በሀዘን የሰፈረ ጭፍጨፋ ያከናወኑት። ከልጅ ልጅ ለሚወራረሰው የባጋንዳ ንጉሳዊ ስርዓት ወደ ሃይማኖታዊ አምልኮ የሚጠጋ [...]

ካምፓላ ሜንጎ የሚገኘው የባጋንዳ ብሔር ንጉስ (ካባካ) ነጭ ቤተመንግስት በተለምዶ የሚያረብብት ጸጥታ ዛሬ የለም። ንጉሳቸውን የወንዶች ሁሉ የበላይ (ሳባሳጃ) ብለው ለሚጠሩት ባጋንዳዎች ዛሬ የሀዘን ቀን ነው። ሜይ 24። በዚህ ቀን ነበር የቀድሞው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሚልተን ኦቦቴ በባጋንዳ ታሪክ መዝገብ ላይ በሀዘን የሰፈረ ጭፍጨፋ ያከናወኑት። ከልጅ ልጅ ለሚወራረሰው የባጋንዳ ንጉሳዊ ስርዓት ወደ ሃይማኖታዊ አምልኮ የሚጠጋ አመለካከት ያላቸው ባጋንዳውያን ከ45 ዓመት በፊት ያኔ ዙፋን ላይ የነበሩትን የአሁኑን ካባካ አባት ከሞት ለማዳን መስዋዕትነት የከፈሉበት ቀን ነው።

አንድ ሺህ የሚጠጉ ባጋንዳውያን የተገደሉበትን ያን ቀን ለማሰብ የባጋንዳ ብሔር አባላት በባለ ግርማ ሞገሱ ነጭ ቤተመንግስት ተሰባስበዋል። በሀዘን ጊዜ እንደሚያደርጉት ሁሉ ከዛፍ ቅርፊት የተሰራ (ባርክ ክሎዝ) ልብስ ለብሰዋል። ቀኑን ለመዘከር በቤተመንግሥቱ ደጃፍ የተሰባሰቡት ሰልፈኞች የኀዘን ሙዚቃ በሚያሰሙ አዳጊዎች አጃቢነት በካምፓላ ጎዳናዎች ለመዘዋወር እስኪነሱ ድረስ ወደ ቤተመንግሥቱ ለመግባት የማይሞከር ነበር። ባጋንዳዎች “ኦሉቢሪ ዋካባካ” እያሉ የሚጠሩት ቤተመንግስት በር በሰዎች ታጥሯል።

ከቤተመንግስቱ ቀጠሮ አለኝ። ቀጠሮዬ ጭፍጨፋው ሲካሄድ በቦታው ከነበሩ እና ካባካውን በህይወት ከአገር እንዲሸሹ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱ ሰው ጋር ነው። ሻለቃ አብርሃም ሳንኮማ ይባላሉ። የካባካው የክብር ዘብ አባል እንደነበሩ ተነግሮኛል። ታሪክ ለመስማት ጓጉቼያለሁ። በስተመጨረሻ ወደባለግርማው ግቢ ዘለቅሁ። ሻለቃ አብርሃም ወዳሉበት ክፍል ጠቆሙኝ። ከውጭ ቆሜ በር ስቆረቁር በባሕላችን እንግዳን ወደ ቤታችን እንዲገባ የምንጋብዝበት አስደሳች ቃል ወደ እኔ ሲወረወር ሰማሁ። “ይግቡ! እንኳን ደኅና መጣህ”። ‘የሰማሁት የአማርኛ አረፍተ ነገር ነው አይደል?’ ራሴን ጠየቅሁ።

በእርግጥም አማርኛ ነበር። የሻለቃ አብርሃም ጥርት ያለ አማርኛ ከቤተመንግሥቱ ላይ አልነቀል ላለው ቀልቤ ጥሩ ማባነኛ ነበር። ወደቢሯቸው ስገባ አንድ ሙዚቃ ይሰማኝ ነበር። ግን በቅጡ አላደመጥኩትም ነበር። ሻለቃ አብርሃም በመቀመጫቸው ላይ ራሳቸው ካመቻቹ በኋላ ወደሚወዘውዙበት ሙዚቃ አመላከቱኝ። “ምነው ፊትህን አዙረህ ተቀመጥክ?” አሉኝ። ወይ ጉዴ! ለካንስ የሚያስደንቁ ነገሮች አላለቁም።

የሻለቃ አብርሃም ኮምፒውተር የሚያጫውተውን ሙዚቃ አውቀዋለሁ። አረ! ማወቅም ብቻ አይደል። ስሰማው ተብረከረኩ። “አለምዬ ሶራ፤ ሶራ ሶራ!”። ‘የት ነው ያለሁት?’ ጥያቄዬ ቀጥሏል። ምንም አስገራሚ ነገር እንዳልተፈጠረ ሁላ ሻለቃ አብርሃም ያናግሩኝ ይዘዋል። አማርኛቸውን ስላላመኑት ይመስላል እንግሊዝኛ ጀምረዋል። የኮምፒዩተሩን ስክሪን የሞሉት ትከሻቸው እስክስታ የሚመታ ሳይሆን የሚርገብገብ የሚመስል ሰዎች በጣታቸው እያሳዩኝ “Look at this! This takes me back to Addis!” አሉኝ። አንገቴን በመስማማት ነቀነቅኩ። በስንቱ ተደንቄ እችላለሁ!

ስለ ባጋንዳ ንጉስ የነበሩኝን ጥያቄዎች ለጊዜው ወደ ጎን አድርጌ ሻለቃ አብርሃም አንዴት እንዲህ ከኢትዮጵያ ጋር እንደተቆራኙ እንዲያጫውቱኝ ጠየቅኋቸው። ፊታቸው ላይ ደስታ እየተነበበ አመታት ወደ ኋላ ተመለሱ። ወደ ወጣትነታቸው ዘመን። ነገርን ከስሩ…..

ታሰርኩ እንዴ!”

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው ወጣቱ አብርሃም በሁለት ምርጫዎች መካከል ልቡ ተከፍሏል። በአንድ በኩል እንደማንኛውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ወጣት ማኬሬሬ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ትምህርቱን መቀጠል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የንክሩማህን የአንዲት አፍሪካ (pan Africa) ሐሳብ በመቀበል አፍሪካን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት በሚደረገው ትግል ውስጥ መሳተፍ እንደምርጫ ቀርበውለታል። አብርሃም የወጣትነት ልቡ ወደ ሁለተኛው አማራጭ አዘነበለ። የተባበረች አንዲት አፍሪካን እውን ለማድረግ እንደሚያስችል ባመነበት ትግል ለመሳተፍ ወሰነ።

እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደረገው ደግሞ ናይሮቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የወጣ ማስታወቂያ ነበር። እ.ኤ.አ በ1959 የተላለፈው ይህ ማስታወቂያ በመላው አፍሪካ ለሚገኙ ወጣቶች የተሰጠ “የቀዳማዊ “ኃይለሥላሴ ስኮላርሺፕ” እድል ነበር። ከዚህ በፊት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው የተነሱትን ፎቶግራፍ ያየው አብርሃም ይህን የመሰለ እድል በቅኝ አገዛዝ በተያዙት ሌሎች የአፍሪካ አገሮች እንደማይሞከር ያውቅ ነበር። አንድ ጥቁር ወታደራዊ የማዕረግ ልብስ መልበስ እንኳ የሚችልባት ብቸኛዋ የአፍሪካ አገር ኢትዮጵያ ነበረች። ልቡ ተሸነፈ።

ናይሮቢ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አቀና። በወቅቱ በናይሮቢ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን አቶ ጌታቸው መካሻን አግኝቶ ያለውን ፍላጎት ገለጸ። በተመሳሳይ ኹኔታ ጥሪውን ተቀብለው የመጡ አፍሪካውያን ወጣቶች በዚያ ነበሩ። ወጣቶቹ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከጋና፣ ከናይጄሪያ እና ከኡጋንዳ የተውጣጡ ነበሩ። የመግቢያ ፈተና ወስደው ካለፉ በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንዲሔዱ ተነገራቸው።

እ.ኤ.አ ጥር 1960 አዲስ አበባ እንደደረሱም በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በአቶ ከተማ ይፍሩ የሚመራ አንድ ቡድን ቃለመጠይቅ አደረገላቸው። በኢትዮጵያ ሊያገኟቸው የሚችሏቸውንም የትምህርት እድሎች ጨምረው ነገሯቸው። “ምን መማር ትፈልጋለህ?” የሚለው ጥያቄ አንዱ ነበር። አብረዋቸው የነበሩትን ወጣቶች ምኞት እውን ያደረገችው ኢትዮጵያ አብርሃምንም ምኞቱን አልነገችውም። ከሁሉ በላይ ወጣቱን አብርሃም ያስደነቀው የምላሹ ፍጥነት ነበር።

አብረዋቸው ከነበሩት የእድሉ አሸናፊዎች መካከል አንዱ ሕክምና አንዱ አውሮፕላን አብራሪነት እንደመረጡ ወዲያው ወደሚመለከታቸው ትምህርት ቤቶች ተላኩ። “እኔ ወታደራዊ ሳይንስ መማር እንደምፈልግ ስናገር ይህን ትምህርት ለምን እንደመረጥኩ ተጠይቄ ነበር” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም ለጥያቄው የሰጡትንም ምላሽ ያስታውሳሉ። “አፍሪካን ነፃ ለማውጣት!” ነበረ ምላሻቸው። “ብዙም ሳይቆይ ያለንበት ድረስ በወታደራዊ አለባበስ የተንቆጠቆጡት ጄኔራል ገብረሥላሴ ያሉበት የወታደር ጂፕ መኪና መጣ” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም መጀመሪያ የተፈጠረባቸውን ስሜትም ያስታውሳሉ። “ምን ተፈጠረ ታሰርኩ እንዴ!” የሚል ድንጋጤ እንደተሰማቸውም ሲያስታውሱ ፈገግ ይላሉ።

እነኛ የአደሬ ሴቶች…

ሻለቃ አብርሃም እንደ እርሳቸው ሁሉ ከተመለመሉ 49 ተማሪዎች ጋር በመኾን ወደ ሐረር ለመጓዝ የ60 የኢትዮጵያ ዶላር ተቀበሉ። ያኔ የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዳሁኑ ብር ሳይሆን ዶላር ነበር። ወደ ሐረር አብረዋቸው ይጓዙ የነበሩት ተማሪዎች ምን ሲሉዋቸው እንደነበረም ያስታውሳሉ። “ከየት ነው ደግሞ አንተ የመጣኸው? ለምን አገርህ አትማርም ነበር? እዚህ አገር ወታደር ኾነህ መሞት ትፈልጋለህ?” ከየአቅጣጫው የሚወረወሩ ጥያቄዎች ነበሩ። የአብርሃም ኹኔታ ለሌሎቹ የሐረር የጦር አካዳሚ ምልምሎችም ጥያቄ የፈጠረ ነበር። በጦር አካዳሚ ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ከሚሄዱ ምልምሎች መካከል ከእናቶቻቸው ተላቅሰው የተለያዩ ነበሩ። ይህ ሁኔታ አሁንም ድረስ ለሻለቃ አብርሃም ግርምትን እንደፈጠረባቸው አለ።

እርሳቸው የገቡበት ኮርስ ሶስተኛው ዙር ቢሆንም ሐረር የጦር አካዳሚ በነበሩ ጊዜ ግን ቀድመዋቸው ከገቡት የአንደኛ እና የሁለተኛ ኮርስ ተማሪዎች ጋር አብሮ የመቆየት እድል ገጥሟቸው ነበር። በወቅቱ አስተማሪ የነበሩት ደግሞ ህንዳውያን እና የሆለታ ገነት ምሩቅ ኢትዮጵያውያን መኮንኖች ነበሩ። “ስልጠናው እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነበር” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም ትምህርቱ በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች ይሰጥ ስለነበር አስቸጋሪ እንዳልነበረባቸው ያስረዳሉ።

ምንም እንኳን አብረዋቸው የቆዩት ስድስት ወር ብቻ ቢኾንም ከመካከላቸው ጄኔራል አበበን እና ጄኔራል ሙሉጌታን ያስታውሳሉ። በሁለተኛው ምድብ ከገቡት እጩ መኮንኖች መካከል በኋላ በመንግሥት ሥልጣን ላይ ከነበሩት መካከል፤ ጎሹ ወልዴን፣ ፍሰሐ ደስታን ከነበራቸው ቅርርብ ጭምር ያስታውሷቸዋል። “ጎሹ የቅርብ ጓደኛዬ ነበር፣ ፍሰሐን የማስታውሰው ባስተማረኝ ጥቂት የትግርኛ ቃላት ነው” ይሉና ቃላቱን ያስታውሳሉ “ከመይለኻ፣ ጽቡቅ…”። ብርሃኑ ባየህንም “በመጠኑ ኩሩ ጎንደሬ ነበረ” እያሉ ትዝታቸውን ያካፍላሉ።

ሻለቃ አብርሃም የተማሩባትን ሐረርን በጣም እንደወደዷት ይናገራሉ። ሐረርን ለምን እንደወደዷት ሲናገሩ የድምፃቸው ከፍታ ይጨምራል። “አየሩ ተስማሚ ነው፣ የሴቶቹ ውበት!። እነኛ የአደሬ ሴቶች በጣም ውብ ነበሩ። ቋንቋ ባያግደኝ ኖሮ እንዴት ጥሩ ነበር! በዚያ ላይ ጥሩ የፍራፍሬ አገር ነበር” እያሉ ምክንያቶችን ይደረድራሉ።

ኡጋንዳዊው በጎጃም
ስልጠናቸውን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ያጠናቀቁት ሻለቃ አብርሃም ከምረቃው በኋላ ፈተና ገጠማቸው። በወቅቱ ኡጋንዳ ገና ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ያልወጣች በመኾኗ ወደ አገራቸው መመለስ እንደማይችሉ ታወቃቸው። ይህንን የሚያውቁት ብዙዎቹ ጓደኞቻቸውም እዚያው በኢትዮጵያ እንዲቀሩ መከሯቸው። “ዩጋንዳ በቅርቡ ነፃ ትወጣለች። እስከዚያው ድረስ እዚህ ቆይ” የወዳጆቻቸው ምክር ነበር። ምክሩን ሰምተው ኢትዮጵያ ቀሩ። እንደሌሎቹ ምሩቃን ሁሉ እርሳቸውም ምድብ ክፍል እና ደሞዝ ተቆረጠላቸው። ያስተማረቻቸውን ኢትዮጵያን በውትድርና ለማገልገል ጎጃም ሁለተኛ ክፍለ ጦር ውስጥ በአሰልጣኝ መኮንንነት ተመደቡ።

“ብዙም አማርኛ ስለማልችል የማሰለጥነው ሰልፍ ነበር” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም። “ለሰልፍ እና ለስፖርት ስልጠና የሚኾኑትን የአማርኛ ቃላት በደምብ ስለማውቃቸው በቀላሉ ነበር ሥራውን የለመድኩት” ይላሉ። አሁንም እነዚህኑ የትእዛዝ ቃላት ከነቅላፄያቸው በደምብ ያስታውሷቸዋል። “አሳርፍ! ተጠንቀቅ! ወደፊት ሒድ!”። እዚያው ጎጃም እያሉ ነበር የህይወታቸውን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስን መልዕክት የደረሳቸው።

“በዚሁ ምድብ ሥራዬ ላይ እንዳለሁ አንድ ቀን በሄሊኮፕተር የመጡ ክቡር ዘበኞች በአስቸኳይ አስጠሩኝ” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም፤ በአስቸኳይ ጃንሆይ ቤተ መንግሥት እንዲደርሱ የተጠሩበትን ሁኔታ ይተርካሉ። “የማእረግ ልብሴን እንደለበስኩ ወደ ሄሊኮፕተር ስጣደፍ አንዳንዶቹ ጓደኞቼ ለሹመት ልጠራ ለፍርድ ስላልገባቸው በጥያቄ ያጣድፉኝ ጀመር። አንዳንዶቹ ‘ምን አድርገህ ነው?’ ሲሉኝ ሌሎቹ ደግሞ ‘ከተሾምክ እንዳትረሳን’ ይሉኝ ነበር።” አራት ኪሎ ቤተመንግሥት ሲደርሱ ያልጠረጠሩት ነገር ገጠማቸው።

ጃንሆይ ብቻቸውን አልነበሩም። የባጋንዳው ሥርወ መንግሥት የወቅቱ ንጉሥ ካባካ ሙቴሳም አብረዋቸው ተቀምጠው ነበር። “ካባካው በሉጋንዳ ስሜን እና ጎሳዬን ጠየቁኝ” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም። በኋላ እንደሰሙት የእርሳቸውን እዚያ መኖር አንድ ሰው ተናግሮ ስለነበረ ይህን ለማጣራት ነበር የተጠሩት። “ካባካው ከመደነቃቸው በላይ ጥርጣሬም የነበራቸው ይመስላል” ይላሉ ሻለቃ። “ምክንያቱም ካባካው እኔ በእንግሊዝ የተላኩ ሰላይ አለመኾኔንም ለማጣራት ጥያቄዎች ይጠየቁኝ ነበር።”
ካባካው ሻለቃ አብርሃምን ጥቂት የፈተነ ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር። ጥያቄው “ተመልሰህ አገርህን ለማገልገል ፈቃደኛ ነህ ወይ?” የሚል ነበር። “ደሞዝ ሳልቀበል፣ እንዲያው ሳልዘጋጅ ይዘውኝ ሊሄዱ ነው?” ብለው ሀሳብ ቢገባቸውም ያለማቅማማት መልስ ሰጡ። “እንዴታ ካባካ ምን ገዶኝ!”። የውስጣቸውን በውስጣቸው እንደያዙ የሰጡት መልስ ነበር።

የያኔው የመቶ አለቃ የአሁኑ ሻለቃ አብርሃም እንደፈሩት ያኔውኑ ወደ ኡጋንዳ አልተመለሱም። በአንድ ቀጭን ትእዛዝ ወደመጡበት ክፍላቸው እንዲመለሱ ተደረገ። “የመቶ አለቃ አብርሃምን ወደክፍላቸው መልሷቸው!”። ነገር ግን አንድ ተስፋ ከካባካው ተሰጥቷቸው ነበር። “ከነፃነት በኋላ እንጠራህና ወደአገርህ ትመጣለህ”። የማይታጠፈው የካባካ ሙቴሳ ቃል ነበር፤ ከባለ ግርማው የአራት ኪሎው ቤተ መንግሥት።

የጃንሆይ “አጃቢ”
እ.ኤ.አ በጥቅምት 1962 ዩጋንዳም ቀን ወጣላት። በገዛ ልጇ በካባካ ሙቴሳ ፕሬዚዳንትነት እንድትመራ ተደርጋ ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ወጣች። በንጉሡም በዓለ ሲመት ላይ እንዲገኙ በክብር እንግድነት የተጠሩት ቀዳማዊ ኀይለሥላሴም በባለሥልጣኖቻቸው አጃቢነት ወደ ኡጋንዳ ሊሄዱ ተነሱ። ጃንሆይ ወደ ኡጋንዳ ሲመጡ የመቶ አለቃ አብርሃንም አልረሷቸውም።

“ከንጉሡ ባለሥልጣኖች ጋር በአንድ አውሮፕላን በርረን ኡጋንዳ ደረስን” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም በኩራት። የዚያን ጊዜው ደስታቸው ከፊታቸው ላይ ይታያል። ኃይለሥላሴን አጅበው መምጣታቸውን እስካሁንም በኩራት ይናገሩታል። “እንደመጣን ያረፍነው አሁን ፓርክ ሆቴል ተብሎ በሚታወቀው የያኔው ሮያል ሆቴል ነበር” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም እንዴት ቤተሰቦቻቸውን እንዳገኙ ሲተርኩም በተመስጦ ነው።

“ቀዳማዊ ኀይለሥላሴን አጅቤ በበዓለ ሲመቱ ላይ ስገኝ የብዙ ኡጋንዳውያን ቀልብ በእኔ ላይ አርፎ ነበር” ይላሉ አብርሃም። በቦታው ከነበሩት ሰዎች መካከልም አንድ ሰው ወደ እርሳቸው መጥቶ “አንተ ሳንኮማ አይደለህም እንዴ?” ሲል እንዳስታወሳቸው ይገልጽላቸዋል። “ያም ሰው የእኔን መምጣት ለመንደሬ ሰዎች ሁሉ አዳረሰው” ይላሉ ሻለቃ። ብዙም ሳይቆዩ ከካባካው ፈቃድ ተቀብለው ለረጅም ጊዜ የተለዩዋቸውን ቤተሰቦቻቸውን የማየት እድል አገኙ:፡ “ካባካው ቀድመው የጠየቁኝን ጥያቄ በድጋሚ ያቀረቡልኝም ከዚያ በኋላ ነበር” ሲሉ የእናት አገራቸው ጥሪ እንዴት እንደደረሳቸው ያስታውሳሉ።

ካባካው “እኛ አሁን የምታገኘውን ያህል ደሞዝ ልንከፍልህ አንችልም። መጥተህ ግን አገርህን እንድታገለግል እንፈልጋለን” ይሏቸዋል። አብርሃም በካባካው ንግግር ስሜታቸው ተነካ። እምቢ ሊሉት የማይችሉት ጥያቄ ነበር። ነገር ግን አንድ ቅድመ ሁኔታ አቀረቡ። “አሁን ድንገት ነው ተጠርቼ የመጣሁት። ተመልሼ እንድሄድ እና ተዘጋጅቼ እንድመጣ ይፈቀድልኝ” አሉ። ተፈቀደላቸው። የመልስ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ፤ ለማይቀረው የእናት አገር ጥሪ ዝግጅት!

የቁርጥ ቀን
ኢትዮጵያን ተሰናብተው ወደ ኡጋንዳ የመጡት ሻለቃ አብርሃም በካባካው የክብር ዘብ ውስጥ ተመደቡ። ለአራት ዓመት ካባካውን በታማኝነት እንዳገለገሉ ፈታኙ የቁርጥ ቀን መጣ። የካባካውን እውነተኛ ሰው ማንነት የሚፈትነው ችግር! አብርሃም ሳንኮማም ፈተናውን በቆራጥነት ለማለፍ ወደ ኋላ አላሉም። ህይወታቸውን እስከ መሥዋዕትነት በመሥጠት ፕሬዚዳንታቸው እና ንጉሣቸው የጣሉባቸው እምነት ትክክለኛ መኾኑን አስመሰከሩ።

ነገሩ እንዲህ ነው። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሚልተን ኦቦቴ ከፕሬዚዳንቱ ካባካ ሙቴሳ ጋር የነበራቸው አለመግባባት ጦዞ ወደ መበጠሱ ደረሰ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን በኃይል ለመፍታት ሞከሩ። እ.ኤ.አ ሜይ 24 ቀን 1966ም ወታደሮችን ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት በመላክ ድንገተኛ ጥቃት ከፈቱ። የንጉሡ የክብር ዘቦች ጥቃቱን በመከላከል ንጉሡን ለማትረፍ የተቻላቸውን ሁሉ አደረጉ። ሻለቃ አብርሃም ከእነዚህ መካከል አንዱ ነበሩ።

ሻለቃ አብርሃም በወቅቱ የነበራቸው ሚና ንጉሡን በስውር በር በማስወጣት በ“ናሚሬምቤ” የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መደበቅ ድረስ ይሄዳል። በኋላም በጀልባ ወደ ሞምባሳ እንዲያመልጡ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ይህ ጀብዱ በህይወታቸው ከሚኮሩባቸው ተልዕኮዎች ቁንጮው ሳይሆን አይቀርም። ሆኖም ጀብዷቸው እስርን አተረፈላቸው። ካባካውን ካስመለጡበት ኬንያ ታስረው በኡጋንዳውያን ፖሊሶች ተመረመሩ። ለካባካው ታማኝ የነበሩት ሻለቃ አብርሃም ግን ምንም ትንፍሽ አላሉም።

“ጆሮ ጠቢ ኾንኩ!”
ከእስር እንደተፈቱ በወቅቱ ለደህንነታቸው አስጊ ከነበረችው ከአገራቸው ከኡጋንዳ ይልቅ ወደ ሁለተኛ ቤታቸው ወደ ኢትዮጵያ ፊታቸውን አዞሩ። “ወደጃንሆይም ቀርቤ ወደ እናት ክፍሌ እንዲመልሱኝ ጥያቄ አቀረብኩ” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም። ጥያቄአቸው ግን አዎንታዊ ምላሽ አላገኘም። ምክንያቱም ከሻለቃ አብርሃም የተሰወረ አልነበረም። “ፋይሌ ተዘግቶ አልተሰናበትኩም” እያሉ መከራከሪያ ቢያቀርቡም ጉዳዩ ለጃንሆይ ቀላል አልነበረም።

“ጃንሆይ በእኔ ምክንያት ከኡጋንዳ መንግሥት ጋር መቃረን አልፈለጉም ነበር” ይላሉ አብርሃም። ግን ጃንሆይ ጥለው አልጣሏቸውም። “ይህ የእኛ ሰው ነው በማለት በተባበሩት መንግስታት ጽሕፈት ቤት ውስጥ በደህንነት ሰራተኝነት እንድቀጠር አደረጉኝ” ሲሉ የጃንሆይን ገለታ ያወሳሉ። “በእርግጥም አማርኛ ማወቄ ሥራውን በቀላሉ እንድሰራው ረድቶኛል” ይላሉ አብርሃም አስቂኙን የአማርኛ የደህንነት ስም እያስታወሱ። “ጆሮ ጠቢ ኾንኩ!”።

በዚህ ዙር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ቤት ንብረት እንዲያፈሩ አድርጋቸዋለች። ከዚያም ከፍ ባለ ኢትዮጵያዊት ሚስትም አግኝተዋል። የሻለቃ አብርሃም ባለቤት ወይዘሮ መሠረት ገብረጻድቅ ይባላሉ። እ.ኤ.አ ከ1978 ጀምሮ ተጋብተው እስካሁንም በትዳር ዓለም አብረው አሉ። ይህም ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ያጠናከሩበት ሌላው ማሰሪያ ነበር።

ከባለቤታቸውም ሁለት ልጆች የወለዱ ሲኾን የመጀመሪያ ልጃቸው የዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ ነች። ልጆቻቸው አማርኛን አቀላጥፈው እንደሚናገሩ የሚገልጹት ሻለቃ አብርሃም በዚህም ምክንአት አንዳንድ ጊዜ ሚስጥር እንደሚያልፋቸው ይናገራሉ። “ ‘እናንተ ቅድም ምንድነው ለእናታችሁ የነገራችኋት’ እያልኩ ስቆጣ ሁሉም ይስቁብኛል” እያሉ እርሳቸውም ይስቃሉ።

ሻለቃ አብርሃም አዲስ አበባ ገርጂ አካባቢ ቤት እንዳላቸው ይናገራሉ። “አቤት አሁንኮ ሰፈሩ ሁሉ ተቀይሯል!” እያሉ ያፏጫሉ የትውልድ ቀዬአቸውን እንደሚያስታውሱ ሁሉ። ቤት የሰሩበትን ቦታ የገዙበትን ገንዘብ ትንሽነት ያደንቃሉ። “45 ሺህ ብር! አሁን በዚህ ዋጋ መሬት ማግኘት የማይታሰብ ነው።”
ሻለቃ አብርሃም የሁለተኛ አገራቸው ትዝታ የሚወዘውዛቸው ዓይነት ናቸው። “አብረውኝ የሰለጠኑት ጓደኞቼም አዛዦቼም ወደ ኡጋንዳ ስመጣ ደጋግመው የነገሩኝ አንድ ነገር ነበር ‘ኢትዮጵያ አገርህ ናት። ኢትዮጵያን እንዳትረሳ‘ ብለውኝ ነበር” ይላሉ። ሻለቃ አብርሃም ምላሻቸው ጥያቄም መልስም ነበር። “ኢትዮጵያን እንዴት እረሳታለሁ?!”።

በእርግጥም አልረሷትም። ከሶስት ዓመት በፊት ገበያ ላይ የዋለው የገጠሪቱ ኢትዮጵያን ዘፈን እያደመጡ በሀሳብ ይነጉዳሉ። ሻለቃውን ተሰናብቼያቸው ወጣሁ። “አለምዬ ሶራ!” እየሸኘኝ ነበር። በ“ባሲማ ኡጌንዜ” ፋንታ “አለምየ ሶራ”! ለዚያውም በካባካው ቤተ መንግሥት!

{ይህ ጽሑፍ የተወሰደው ከሐበሻዊ ቃና ጋዜጣ ቁጥር 3 ላይ ነው}

Comments are closed.

Bad Behavior has blocked 2550 access attempts in the last 7 days.

ከሐረር ጦር አካዳሚ እስከ ካባካ ቤተ መንግሥት

ካምፓላ ሜንጎ የሚገኘው የባጋንዳ ብሔር ንጉስ (ካባካ) ነጭ ቤተመንግስት በተለምዶ የሚያረብብት ጸጥታ ዛሬ የለም። ንጉሳቸውን የወንዶች ሁሉ የበላይ (ሳባሳጃ) ብለው ለሚጠሩት ባጋንዳዎች ዛሬ የሀዘን ቀን ነው። ሜይ 24። በዚህ ቀን ነበር የቀድሞው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሚልተን ኦቦቴ በባጋንዳ ታሪክ መዝገብ ላይ በሀዘን የሰፈረ ጭፍጨፋ ያከናወኑት። ከልጅ ልጅ ለሚወራረሰው የባጋንዳ ንጉሳዊ ስርዓት ወደ ሃይማኖታዊ አምልኮ የሚጠጋ [...]

Long says he chose the subdivision humanity' diagnosis to suggest, however, as co-workers of a armed diving protection suspended in the disease of mad counterinsurgency, people especially however live in inner series. accutane results how long Radio insugente transmits lessons in worthwhile and in the hot differences drug, substance, cell and tojolabal.

Bad Behavior has blocked 3761 access attempts in the last 7 days.