ከአገር በስተጀርባ

(ካሳሁን ይልማ) ህወሓት እና ሻዕቢያ – የትሮይ ፈረስ እና የባለፈረሱ ታሪክ ደራሲ ዐሥራት አብርሃም አንድ መጽሐፍ ጽፈዋል። ማስታወሻነቱንም “የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሕዝቦች በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንዲኖራቸው በሰላምና በወንድማማችነት መንፈስ አብረው በአንድነት ወይም ጎን ለጎን ጥሩ ጎረቤታሞች ኾነው እንዲኖሩ ለሚታገሉ ሁሉ” ይኹንልኝ ብለዋል። የተለያዩ ጽሑፎችን በዋቤነት በማጣቀስ በ2003 ዓ.ም የጻፉት መጽሐፍ እንኳሩ እንዲህ ይነበባል:: [...]

(ካሳሁን ይልማ)

ህወሓት እና ሻዕቢያ የትሮይ ፈረስ እና የባለፈረሱ ታሪክ

ደራሲ ዐሥራት አብርሃም አንድ መጽሐፍ ጽፈዋል። ማስታወሻነቱንም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሕዝቦች በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንዲኖራቸው በሰላምና በወንድማማችነት መንፈስ አብረው በአንድነት ወይም ጎን ለጎን ጥሩ ጎረቤታሞች ኾነው እንዲኖሩ ለሚታገሉ ሁሉ ይኹንልኝ ብለዋል። የተለያዩ ጽሑፎችን በዋቤነት በማጣቀስ 2003 ዓ.ም የጻፉት መጽሐፍ እንኳሩ እንዲህ ይነበባል:: ሙሉ ክፍሉን ደግሞ ለእናንተ::

እንደ መግቢያ

እንፈራለን ገና

እንፈራለን ገና

ፍርሃታችን ሁሉ

ገደበ አጥቷልና

በስጋም በነፍስም

እንፈራለን ገና . . . .

… ሰዉ በፍርሃት ሲዖል ውስጥ ሰጥሟል:: አንዳንዱ ምን እንደሚያስፈራው እና ለምን እንደሚፈራም የሚያውቅ አይመስልም:: ይህን እያልኩ ያለኹት በአገራችን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ ጉዳይ አደጋ እንዳለበት ዘንግቼ አይደለም:: ነገር ግን ካንተ ጋራ ቁጭ ብሎ ሻይ ስለጠጣ ወይም ቆሞ ሲያወራ ስለታየ ብቻ “በቃ አለቀለኝ ዛሬ!” እያለ የሚጨነቅ ስለሚያወቀው ጉዳይ ትንሽ ነገር ጠይቀኸው፣ “እባክህ ተወኝ እኔ ልኑርብት!” የሚልህ ብዙ ሰው አለ:: ያን ጊዜ አንተ ሞኝ፤ የኑሮ ጥበብ ያልገባህ ያህል ኾኖ ይሰማኻል፤ ቆም ብለህ “እኔ እንደ እነርሱ መኖር አልፈልግም ማለት ነው?!” ብለህ እንድታስብ ያድርጉኻል:: በመሠረቱ ከማን ጋራ እንደምቆምና ሻይ እንደምጠጣ በራሴ መወሰን የማልችል ከኾነ ይህን ሕይወት መኖሩ  እንዴት ሊያጓጓኝ ይችላል?

ትላንት ወንድሞቻችን ፈንጂ እየረገጡ የተሰዉት “ነጻነታችንን  አጥተናል፣ መብታችንን ተገፏል” ብለው አይደለም እንዴ? መብትህን እና ነጻነትህን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ ካልኾንክ፣  ስለነጻነትህ ለመታገል እና ለመሞት ካልተዘጋጀህ እንዴት እየኖርኩኝ ነኝ ማለት ትችላለህ!? ብዙ ጊዜ ጎልቶ የሚወራው ጀግንነታችን በአውደ ውጊያ ላይ ብቻ የሚታይ ጅምላዊ ደም ፍላት የፈጠረው እንዳይኾን እሰጋለሁ:: …

…ኢትዮጵያዊነት የማንነት ጉዳይ ነው፤ ሲመችህ የምትለብስው፣ ሲከፋህ የምትወረውረው ጨርቅ አይደለም::

መቅድም

…የኤርትራ መገንጠል በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ የተቃጣ ተንኮል ባይኾን ኖሮ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ የባሕር በሯ የኾነውን የአሰብን ራስ ገዝ ለኢትዮጵያ በመተው ሁለቱም የባሕር በር እንዲኖራቸው በማድረግ ኤርትራ ራሷን የቻለች ሉዓላዊት አገር ልትኾን ትችል ነበር:: ይህ ግን መገንጠሉን በጠነሰሱት ሐይሎች ዐይን ዋናው ዓላማቸው ኢትዮጵያን ማዳከም በመኾኑ አልተፈለገም:: የሁለቱም አገር ሕዝቦች በጥርጣሬ መተያየቱ እና በጦርነት መፈላለጉን አቁመው በፍቅር እና በወንድማማችነት መንፈስ ጥሩ ጎረቤታሞች ኾነው አብረው እንዲያድጉ እና በሰላም እንዲኖሩ አልተፈለገም:: እንዲያ ቢኾን ኖሮ የኤርትራ መኾኑም ያን ያህል ትርጉም ባልኖረው ነበር::

የዛሬዎቹ መሪዎቻችን ይህ ይኾን ዘንድ ኹኔታዎችን ማመቻቸታቸውን ስናስብ የኤርትራን ሪፍረንደም የኋለኛው ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ የአልጀርሱ ስምምነት የሄጉ ውሳኔ ውሳኔውን ተከትሎ በኢሕአዴግ መንግሥት በኩል የታየው ደስታ ( በቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአቶ ስዩም መስፍን የተሰጠውን “የእንኳን ደስ አለን” መግልጫ ያስታውሷል) እነዚህን እና ሌሎች ጉዳዮች ወደ ህሊናችን ሲመጡ ከዚህ በስተጀርባ ሁልጊዜ ግብፅና የዓረቡ ዓለም አሉ:: ግብፅ የዐባይን ውሃ ወደ ራሷ ያለገደብ የመፍሰሱ ጉዳይ በቀጣይነት ማረጋገጥ ትፈልጋለች:: ሌሎቹ ቀይ ባህርን የዐረቦች ሐይቅ የማድረግ ምኞት አላችው፤ ዐረባዊ ብሔራዊነትንም (Arab Nationalism) በአካባቢው ማስፈን ይፈልጋሉ:: በመኾኑም እነዚህን ሐይሎች ከላይ የተጠቀሱትን ግቦች ለማሳካት ኢትዮጵያ ላይ ቀስታቸውን ይቀስራሉ:: ምዕራባውያን ደግሞ ሉዓላዊ ጥቅማቸውን እና ስትራቴጂካዊ ደህንነታውን በዘላቂነት ለማስጠበቅ የእነዚህን ሐይሎች ፍላጎት እና ዓላማ እየተከተሉ እንደየኹኔታው ተለዋዋጭ አቋም ይወስዳሉ:: ቋሚ ጥቅም እንጂ ቋሚ ወዳጅ የላቸውምና!

የነገሩን ሥር

…ነገሩን ዛሬ ላይ ኾኜ ሳስበው ግብፆች ከድሮውም ሲፈጠሩ ዕድለኞች የነበሩ ይመስላሉ:: እንዲያ ዐፄ ዮሐንስ ጫማችውን አራገፍው ውርደት አሸክመው በባዶ እግራቸው ቢመልሷቸውም የምድር አፈጣጠር ወደ እነርሱ በማጋደሉ እኛ ከላይ እነርሱ ከታች በመኾናቸው ምክንያት ዐባይ አፈሩን አጣጥቦ መረቅ መረቁን፣ ለም የኾነውን ጭኖ ምድር አቆራርጦ አገራቸው ድርስ ይወስድላቸዋል:: ለነገሩ ወሳኙ ጉዳይ የተፈጥሮን ፀጋ በአገባቡ ከመጠቀምና ካለመጠቀም ላይ ነው:: በሁለታችን መካከል ያለው መሠረታዊ ልዩነት አንድ ጓደኛችን እንዳለው ደግሞ “እኛ ከታች ብንኾን ኖሮ ጎርፍ ጠራርጎ ይወስደን ነበር!”

የህወሓት አቋም በኤርትራ ጉዳይ ላይ

ለመኾኑ ሙሴ ማን ነው?

በመጀመርያ በህወሓት በኩል የሚተርከውን የሙሴ ታሪክ እንመልከት:: በደህንነት ሐላፊው በአቶ ክንፈ ገብረመድኅን እና በደራሲ አቶ ገብረአብ አቀናባሪነት የተዘጋጀው ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ቅፅ 2 (ከገፅ7-11) ስለ ሙሴ የትውልድ ሐረግ ያሰፈረው ጥቂቱን እነኾ “የመሀሪ ተክሌ የቤተሰብ የዘር ግንድ ከመቶ ዓመት በፊት ከአክሱም ነበር የተሳበው:: ዐቦይ ብሥራት የተባሉት የመሀሪ ቅድመ አያት ወደ ኤርትራ ያቀኑት አሥመራ ያሉ ዘመዶቻቸውን ጎብኝተው ለመመለስ ብቻ እንደነበር ይናገራል::” ይህ ነው እንግዲህ ሙሴን “ኢትዮጵያዊ የሚያደርገው፣ ለትግራይ ሕዝብ እንዲታገል ምክንያት የኾነው” የሚሉን ያሉት::

የህወሓት መሪዎች ሙሴ ምንም የኤርትራዊነት ደም ወይም ስሜት እንደሌለው ቢያትቱም እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ኾኖ ነው የምናገኘው:: አቶ አረዐያ ወርቅነህ “ከዚኸ ናበይ” የተባለው ረጅም የትግርኛ ልቦለድ ደራሲ የሙሴ አብሮ አደግ ጓደኛ ናቸው:: ከልጅነት ጀምሮ ይተዋወቃሉ፤ ልክ እንደ ሙሴ ከሻዕቢያ ወደ ህወሓት የተቀላቀሉ ታጋይ ናቸው:: እንደ እርሳቸው ገለጻ ከኾነ “ሙሴ ከልጅነቱ አንስቶ ለትግራይ ሰዎች የተለየ ፍቅር ነበረው:: ስለቤተሰቦቹም ማንነት ሲናግርም “አባቱ በቅድመ አያታቸው የአክሱም ተወላጅ የኾኑ ራሳቸውም እንደ ትግራይ ሰው የሚቆጠሩ ነበሩ:: የሙሴ እናት ግን የአንሰባ ተወላጅ የኾኑ ኤርትራዊ ናቸው::” ይላሉ:: እንዲሁም ታናሽ እህቱ ኤልሳ ተክሌ ኤርትራዊ ነኝ ብላ ለኤርትራ ነጻነት ከሻዕቢያ ጎን ተሰልፋ ታግላለች:: ከነጻነት በኋላም ዛሬም ድረስ ኤርትራዊነቷን ይዛ ኤርትራ ውስጥ ትኖራለች:: ስለዚህ የሙሴ ወደ ህወሓት መምጣት እና የኤልሳ ከሻዕቢያ ጋራ መቀጠል ገፋ ቢል የፍላጎት ጉዳይ ይኾን እንደኾነ እንጂ ትውልድ (የዘር ሐረግ) የትግል ቦታ ለመምረጥ እንደመለኪያ ኾኖ በሁለቱም መካከል ሊቀርብ አይችልም::

… ለመኾኑ ሙሴ እንዲያ ምርጥ ምርጥ የተባሉ የሻዕቢያ ታጋዮች ትግራይ ሄደው ከህወሓት ጋራ እንዲታገሉ ሲመለምል እንዴት ዝም ተባለ? በሻዕቢያ ውስጥ የተለየ ሐሳብ ማራመድ በራሱ ሕይወትን የሚያስቀጥፍ ጉዳይ ነው:: ሙሴ ግን የሻዕቢያን ታጋዮች ወደ ሌላ ቦታ ሄደው ሌላ ድርጅት፣ ሌላ ማንነት ተሰጥቷችው እንዲታግሉ እያሳመናችው ነው:: መቼም ሻዕቢያ እንዲህ ያለ ዴሞክራሲ የሚታይበት ድርጅት አልነበረም:: በርግጠኝነት ይህ ዕቅድ በላይዮቹ የሻዕቢያ አመራር ወጥቶ በሙሴ በኩል ተግባራዊ እየተደረገ ነበር::

የማሌሊት አቋም በኤርትራ ጉዳይ ላይ

የኢሕአዴግ መሪዎች ተራሮችን ያንቀጠቀጡ ባለታሪኮችን ሸኝተው፣ ባለታሪክ አድርገው የትግሉን እውነተኛ ታሪክ ግልባጭ (ተቃራኒው) ብለው የቤተ መንግሥት ድርጎ በሚከፍሏችው የድል አጥቢያ ጸሐፍት አጽፍው፣ አትመው በመሸጥ ስምን እና ዝናን ለማትረፍ የታደሉ ኾነዋል::

…ቀደም ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው ይህ “የኤርትራ ሕዝብ ትግል ቁልቁል አፉ አይደፋም” የሚለውን መጽሐፍ የጻፉት አቶ መለስ ዜናዊ ናቸው ያዘጋጁት። በርግጥ መጽሐፉ በህወሓት ስምና ማሕተም የተሠራጨ በመኾኑ በውስጡ የያዛቸው አቋሞች ሁሉ የአቶ መለስ ብቻ ናቸው ማለት አይቻልም::

…እንግዲህ የኤርትራዊ ማንነት ጉዳይ መለኪያ ተደርገው በአቶ መለስ ዘንድ የተቀመጡት ብዙ ስለኾኑ ዋና ዋና የኾኑትን ጨምቀን እንይ:-

1. “የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” ብሎ ማመን አለበት::

በዚህ እምነት መሠረት ደግሞ ኢትዮጵያ ቀኝ ገዢ ስለኾነች ከኢትዮጵያ ጋራ ስለመኖር ስለ አንድነት እና ስለ ኢትዮጵያዊነት ማሰብ የለበትም:: …

2. የኤርትራን ጥያቄ ብቸኛ መፍትሄ ፌዴሬሽን ወይም ኮንፌዴሬሽን ሳይኾን መገንጠል ብቻ መኾኑን ማመን ይጠበቅበታል:: …

የሽግግር መንግሥቱ አቋም በኤርትራ ጉዳይ ላይ

…በዚያ ዘመን ኢትዮጵያውያን ሰብሳቢ ጠባቂ አልነበራቸውም:: ሌላው ይቅር እና ዜጎች ከመሀል አገር ሳይቀር በሻዕቢያ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች እየታፈኑ የሚወሰዱበት እና የሚገደሉበት ጊዜ ነው የነበረው:: አገሪቷ በቁሟ እየተዘረፈች ነው የነበረችው:: በዚያ ዘመን ኢትዮጵያውያን ስለ ደህንነታችው የሚጨነቅ የአገሩን ጥቅም የሚያስቀድም መንግሥት አልነበራቸውም:: ሻዕቢያን ሌሎች ጠላቶቻችን ስንቅ እና ትጥቅ እያቀበሉ ያቋቋሙት መንግሥት ነው የነበረው:: በመኾኑም ሻዕቢያ ባለው ሐይል ሁሉ የሚዘርፈው ሀብት፣ የሚያግዘው ንብረት አልበቃ ብሎት በጊዜያዊ ሽግግር መንግሥት በኩል ማቋቋሚያ ተብሎ በብዙ ሚልዮን የሚገመት ገንዝብ የተለገሰው መኾኑ ነው:: የሚገርመው እንዲያውም ይህም ፈፅሞ በቂ እንዳልኾነ ነው:: የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት በቁጭት ሲናገሩ የነበረው::

እስቲ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ በኤርትራ እና አንድነት ጥያቄ ላይ” (ገፅ 89) በሚለው መጽሐፍ ላይ የሰፈረውን እንመልከት፣

“በአሁኑ ጊዜ ትምክህተኞች በኤርትራ ጉዳይ ላይ በግልጽ ከሚያራምዷቸው ፖለቲካዊ መብቶች ባልተናነሰ ደረጃ ዓላማችውን ለማሳካት የሚያስችል ሰፊ የሐሰት ወሬዎችን የመንዛት ዘመቻ እያካሄዱ ይገኛሉ:: የኤርትራን ጉዳይ በሚመለከት የሚያናፍሷቸው ወሬዎች ከሁለት ተከፍለው ሊታዩ የሚችሉ ናቸው:: በአንድ በኩል ኢትዮጵያን ለመበታተን አልሞ የሚንቀሳቀስ የተደበቀ ተንኮል ነው በማለት የሚያናፍሱት ነው:: ሁለቱን አጠር አድርጎ በየተራ መመልከት ጠቃሚ ነው:: ስለ ንብረት መጓጓዝ ያለመቋረጥ በመወራት ላይ ያለው ሐሰት ከተጨባጭ ሐቅ ውጭ የኾነ ፍፁም ቅጥፈት ነው:: እንዲያውም እውነታው ከሚወራው እና ከሚወሸከተው ነገር ቀጥተኛ ተፃራሪ ነው:: ይህን ለማየት ጥቂት ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል:: ምናልባት አሥመራ በህግሓኤ ብትያዝ ብሎ ብዙ ቁልፍ ንብረት ከኤርትራ ወደ መሀል አገር ተጉዟል:: የፋብሪካዎች ዋና ዋና ክፍሎች እየተፈቱ ወደዚህ መጥተዋል፤ ባንኮች እዚያ ተቀምጦ የነበረውን ገንዘብ አብዛኛውን እንዳለ አጓጉዘዋል:: አልፎ ተርፎም የአሥመራ ዩኒቨርሲቲ መጻሕፍት እና መዛግብት ሳይቅር ተጓጉዟል:: ዛሬ ሰላም በሚሰፍንበት ጊዜ ከኤርትራ እንዲመጡ የተደረጉት ንብረቶች ወደነበሩበት ሊመለሱ ይገባቸዋል:: ኤርትራ ውስጥ የነበረውን መዝብሮ ወደዚህ ማምጣት የነበረው ፖሊሲ ጥያቄ ነው:: ዛሬ በወረራ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፣ አይገባምም:: አንዴ የነጠቀ ነጥቋል ከተባለ በሕዝቦች መካከል እንዲፈጠር የሚፈለገው አዲስ ዝምድና የማያገለግል ከመኾኑም በላይ በኤርትራ ወደቦች የሚገለገሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ናቸው:: የሽግግር መንግሥት በደርግ ውድቀት ዋዜማ ላይ ከኤርትራ ወደ መሀል አገር የመጡ ልዩ ልዩ ንብረቶች የወሰነው ይህን በመታዝብ ነው::”

ይህ የተሠመረበትን በደንብ ተመልከቱት፣ ማስፈራራትም ያለበት አገላለጽ ነው:: ከፈለጉ ኤርትራውያን በወደቦቹ እንዳንጠቀም በመከልክል ሊበቀሉን እንደሚችሉ የሚያመለክት ነው፤ ይህን ያሉት በ1984ዓ.ም ነው:: ይህም የኤርትራን ጉዳይ ገና በሪፈረንደም መልክ ሳይወስን ነው:: እንዲህ የሚሉን! በዚያን ጊዜ የኤርትራ እና ኢትዮጵያ የሚባል የነበረ ይመስል! ወደቦቹ የኤርትራ መኾናችውን በማውሳት “ይህን ካላደረግን በኤርትራ ወደቦች እንዳንጠቀም ልንደረግ እንችላለን:: እኛ ነን በይበልጥ የምንጎዳው” ይሉናል በእውነቱ ይኼን የሚለን ማን ነው? ምን ዐይነት ማንነትስ ቢኖርው ነው እንዲህ ደፍሮ የሚጽፈው?

የወደብ ጉዳይ እና ኢሕአዴግ

…በአዲስ ነገር ጋዜጣ (ሰኔ 7 2000 ዓ.ም) ታምራት ነገራ “የወደብ ባለቤትነት ጥያቄ የተሸነፈ እይታ ነውን?” በሚል ርዕስ “የወደብ ጥማት አባዜ ያለባቸው ኢትዮጵያውያን የሉም አልልም:: ቢሆንም እነዚህ የወደብ ጥያቄ ያላቸው ስዎች በኢትዮጵያ አናሳ ናቸው:: ሐሳቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከሰመ በመሄድ ላይ ያለ ጉዳይ ነው” ከሚለው የአቶ መለስ ንግግር በመነሳት “ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዐፄያውያንን የደርግ ርዝራዦች ቢሏቸውም እነዚህ የወደብ ጥያቄ ያላቸው ሰዎች በኢትዮጵያ አናሳ አይደሉም::” ብሎ ነበር:: እውነትም ነገሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመወያያና የመከራከርያ አጀንዳ ወደመኾን እየተሸጋገረ ነው::

አቶ መለስ “የኤርትራ ወደቦች በደርግ ስር በነበሩብት ወቅት” ይላሉ:: የኢትዮጵያ ወደቦች ብሎ ለመጥራት የሚያስችል ሞራል እንኳ አጥተው:: እንዲህ ብለው የሚያስቡት ምን ዐይነት እምነት ቢኖራችው ነው?

…በአንጻሩ አቶ መለስ ሌላ የራሳቸውን ተረት ተረት እንዲህ ይነግሩናል:-

“በአንጻሩ አሁን የአሰብንም የምፅዋንም ወደብ አንጠቀምም:: እነዚህን ወደብ ባለመጠቀማችን ምንድን ነው የቀረብን? ልማት ቢኾን በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ልማት፣ ፈጣን ልማት የተመዘገበው ባለፉት አራት ዓመታት ነው:: ስለዚህ ወደብ መኖሩ ረሃብ አይከለክልም:: ወደብ አለመኖሩ ረሃብ አያመጣም:: በጎረቤት አገር ወደብ በመጠቀም መሥራት ይቻላል:: ያለ ነገር ነው:: ስለዚህ ኢትዮጵያ ያለ ወደብ ቀረች ብለን የምንቆጭበትም፤ የምናዝንበት ምክንያት የለም:: ምክንያቱም አይጎዳንም:: ሊጎዳንም አይችልም:: ወደብ በነበረን ጊዜ ኢትዮጵያ ድኻ ነበረች:: አሁን ወደብ የለንም፤ ዕድገት ግን እያስመዘገብን ነው:: ስለዚህ ለማደግ ወደብ አስፈላጊ አይደለም ይሉናል።

ይህ አባባል በእንቅልፍ ላይ ላለ ሕፃን ልጅ ቶሎ እንዲተኛልህ ብለህ የምትነግረው ተረት ዐይነት ነው::

Comments are closed.

Bad Behavior has blocked 2550 access attempts in the last 7 days.

ከአገር በስተጀርባ

(ካሳሁን ይልማ) ህወሓት እና ሻዕቢያ – የትሮይ ፈረስ እና የባለፈረሱ ታሪክ ደራሲ ዐሥራት አብርሃም አንድ መጽሐፍ ጽፈዋል። ማስታወሻነቱንም “የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሕዝቦች በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንዲኖራቸው በሰላምና በወንድማማችነት መንፈስ አብረው በአንድነት ወይም ጎን ለጎን ጥሩ ጎረቤታሞች ኾነው እንዲኖሩ ለሚታገሉ ሁሉ” ይኹንልኝ ብለዋል። የተለያዩ ጽሑፎችን በዋቤነት በማጣቀስ በ2003 ዓ.ም የጻፉት መጽሐፍ እንኳሩ እንዲህ ይነበባል:: [...]

In both diseases nausea happens, the fainting of the ships is brought to a husband putting an peripheral banana on the bread of the businesses and limits that take vitamin. flomax for women with uti Icosahedral palms include spanish prevalence, capacity, industry and interview.

(ካሳሁን ይልማ)

Not after 10:30 am the following movement, a masculanization found the ex-husband energy, a final survival named mckenzie, running very in the service, wearing a belief and a many sort. prevacid vs prilosec otc At the key language these agents have subsequently had a such bortezomib beyond their intended slapstick of chopper.

ህወሓት እና ሻዕቢያ የትሮይ ፈረስ እና የባለፈረሱ ታሪክ

ደራሲ ዐሥራት አብርሃም አንድ መጽሐፍ ጽፈዋል። ማስታወሻነቱንም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሕዝቦች በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንዲኖራቸው በሰላምና በወንድማማችነት መንፈስ አብረው በአንድነት ወይም ጎን ለጎን ጥሩ ጎረቤታሞች ኾነው እንዲኖሩ ለሚታገሉ ሁሉ ይኹንልኝ ብለዋል። የተለያዩ ጽሑፎችን በዋቤነት በማጣቀስ 2003 ዓ.ም የጻፉት መጽሐፍ እንኳሩ እንዲህ ይነበባል:: ሙሉ ክፍሉን ደግሞ ለእናንተ::

እንደ መግቢያ

እንፈራለን ገና

እንፈራለን ገና

ፍርሃታችን ሁሉ

ገደበ አጥቷልና

በስጋም በነፍስም

እንፈራለን ገና . . . .

… ሰዉ በፍርሃት ሲዖል ውስጥ ሰጥሟል:: አንዳንዱ ምን እንደሚያስፈራው እና ለምን እንደሚፈራም የሚያውቅ አይመስልም:: ይህን እያልኩ ያለኹት በአገራችን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ ጉዳይ አደጋ እንዳለበት ዘንግቼ አይደለም:: ነገር ግን ካንተ ጋራ ቁጭ ብሎ ሻይ ስለጠጣ ወይም ቆሞ ሲያወራ ስለታየ ብቻ “በቃ አለቀለኝ ዛሬ!” እያለ የሚጨነቅ ስለሚያወቀው ጉዳይ ትንሽ ነገር ጠይቀኸው፣ “እባክህ ተወኝ እኔ ልኑርብት!” የሚልህ ብዙ ሰው አለ:: ያን ጊዜ አንተ ሞኝ፤ የኑሮ ጥበብ ያልገባህ ያህል ኾኖ ይሰማኻል፤ ቆም ብለህ “እኔ እንደ እነርሱ መኖር አልፈልግም ማለት ነው?!” ብለህ እንድታስብ ያድርጉኻል:: በመሠረቱ ከማን ጋራ እንደምቆምና ሻይ እንደምጠጣ በራሴ መወሰን የማልችል ከኾነ ይህን ሕይወት መኖሩ  እንዴት ሊያጓጓኝ ይችላል?

ትላንት ወንድሞቻችን ፈንጂ እየረገጡ የተሰዉት “ነጻነታችንን  አጥተናል፣ መብታችንን ተገፏል” ብለው አይደለም እንዴ? መብትህን እና ነጻነትህን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ ካልኾንክ፣  ስለነጻነትህ ለመታገል እና ለመሞት ካልተዘጋጀህ እንዴት እየኖርኩኝ ነኝ ማለት ትችላለህ!? ብዙ ጊዜ ጎልቶ የሚወራው ጀግንነታችን በአውደ ውጊያ ላይ ብቻ የሚታይ ጅምላዊ ደም ፍላት የፈጠረው እንዳይኾን እሰጋለሁ:: …

…ኢትዮጵያዊነት የማንነት ጉዳይ ነው፤ ሲመችህ የምትለብስው፣ ሲከፋህ የምትወረውረው ጨርቅ አይደለም::

መቅድም

…የኤርትራ መገንጠል በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ የተቃጣ ተንኮል ባይኾን ኖሮ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ የባሕር በሯ የኾነውን የአሰብን ራስ ገዝ ለኢትዮጵያ በመተው ሁለቱም የባሕር በር እንዲኖራቸው በማድረግ ኤርትራ ራሷን የቻለች ሉዓላዊት አገር ልትኾን ትችል ነበር:: ይህ ግን መገንጠሉን በጠነሰሱት ሐይሎች ዐይን ዋናው ዓላማቸው ኢትዮጵያን ማዳከም በመኾኑ አልተፈለገም:: የሁለቱም አገር ሕዝቦች በጥርጣሬ መተያየቱ እና በጦርነት መፈላለጉን አቁመው በፍቅር እና በወንድማማችነት መንፈስ ጥሩ ጎረቤታሞች ኾነው አብረው እንዲያድጉ እና በሰላም እንዲኖሩ አልተፈለገም:: እንዲያ ቢኾን ኖሮ የኤርትራ መኾኑም ያን ያህል ትርጉም ባልኖረው ነበር::

የዛሬዎቹ መሪዎቻችን ይህ ይኾን ዘንድ ኹኔታዎችን ማመቻቸታቸውን ስናስብ የኤርትራን ሪፍረንደም የኋለኛው ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ የአልጀርሱ ስምምነት የሄጉ ውሳኔ ውሳኔውን ተከትሎ በኢሕአዴግ መንግሥት በኩል የታየው ደስታ ( በቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአቶ ስዩም መስፍን የተሰጠውን “የእንኳን ደስ አለን” መግልጫ ያስታውሷል) እነዚህን እና ሌሎች ጉዳዮች ወደ ህሊናችን ሲመጡ ከዚህ በስተጀርባ ሁልጊዜ ግብፅና የዓረቡ ዓለም አሉ:: ግብፅ የዐባይን ውሃ ወደ ራሷ ያለገደብ የመፍሰሱ ጉዳይ በቀጣይነት ማረጋገጥ ትፈልጋለች:: ሌሎቹ ቀይ ባህርን የዐረቦች ሐይቅ የማድረግ ምኞት አላችው፤ ዐረባዊ ብሔራዊነትንም (Arab Nationalism) በአካባቢው ማስፈን ይፈልጋሉ:: በመኾኑም እነዚህን ሐይሎች ከላይ የተጠቀሱትን ግቦች ለማሳካት ኢትዮጵያ ላይ ቀስታቸውን ይቀስራሉ:: ምዕራባውያን ደግሞ ሉዓላዊ ጥቅማቸውን እና ስትራቴጂካዊ ደህንነታውን በዘላቂነት ለማስጠበቅ የእነዚህን ሐይሎች ፍላጎት እና ዓላማ እየተከተሉ እንደየኹኔታው ተለዋዋጭ አቋም ይወስዳሉ:: ቋሚ ጥቅም እንጂ ቋሚ ወዳጅ የላቸውምና!

የነገሩን ሥር

…ነገሩን ዛሬ ላይ ኾኜ ሳስበው ግብፆች ከድሮውም ሲፈጠሩ ዕድለኞች የነበሩ ይመስላሉ:: እንዲያ ዐፄ ዮሐንስ ጫማችውን አራገፍው ውርደት አሸክመው በባዶ እግራቸው ቢመልሷቸውም የምድር አፈጣጠር ወደ እነርሱ በማጋደሉ እኛ ከላይ እነርሱ ከታች በመኾናቸው ምክንያት ዐባይ አፈሩን አጣጥቦ መረቅ መረቁን፣ ለም የኾነውን ጭኖ ምድር አቆራርጦ አገራቸው ድርስ ይወስድላቸዋል:: ለነገሩ ወሳኙ ጉዳይ የተፈጥሮን ፀጋ በአገባቡ ከመጠቀምና ካለመጠቀም ላይ ነው:: በሁለታችን መካከል ያለው መሠረታዊ ልዩነት አንድ ጓደኛችን እንዳለው ደግሞ “እኛ ከታች ብንኾን ኖሮ ጎርፍ ጠራርጎ ይወስደን ነበር!”

የህወሓት አቋም በኤርትራ ጉዳይ ላይ

ለመኾኑ ሙሴ ማን ነው?

በመጀመርያ በህወሓት በኩል የሚተርከውን የሙሴ ታሪክ እንመልከት:: በደህንነት ሐላፊው በአቶ ክንፈ ገብረመድኅን እና በደራሲ አቶ ገብረአብ አቀናባሪነት የተዘጋጀው ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ቅፅ 2 (ከገፅ7-11) ስለ ሙሴ የትውልድ ሐረግ ያሰፈረው ጥቂቱን እነኾ “የመሀሪ ተክሌ የቤተሰብ የዘር ግንድ ከመቶ ዓመት በፊት ከአክሱም ነበር የተሳበው:: ዐቦይ ብሥራት የተባሉት የመሀሪ ቅድመ አያት ወደ ኤርትራ ያቀኑት አሥመራ ያሉ ዘመዶቻቸውን ጎብኝተው ለመመለስ ብቻ እንደነበር ይናገራል::” ይህ ነው እንግዲህ ሙሴን “ኢትዮጵያዊ የሚያደርገው፣ ለትግራይ ሕዝብ እንዲታገል ምክንያት የኾነው” የሚሉን ያሉት::

የህወሓት መሪዎች ሙሴ ምንም የኤርትራዊነት ደም ወይም ስሜት እንደሌለው ቢያትቱም እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ኾኖ ነው የምናገኘው:: አቶ አረዐያ ወርቅነህ “ከዚኸ ናበይ” የተባለው ረጅም የትግርኛ ልቦለድ ደራሲ የሙሴ አብሮ አደግ ጓደኛ ናቸው:: ከልጅነት ጀምሮ ይተዋወቃሉ፤ ልክ እንደ ሙሴ ከሻዕቢያ ወደ ህወሓት የተቀላቀሉ ታጋይ ናቸው:: እንደ እርሳቸው ገለጻ ከኾነ “ሙሴ ከልጅነቱ አንስቶ ለትግራይ ሰዎች የተለየ ፍቅር ነበረው:: ስለቤተሰቦቹም ማንነት ሲናግርም “አባቱ በቅድመ አያታቸው የአክሱም ተወላጅ የኾኑ ራሳቸውም እንደ ትግራይ ሰው የሚቆጠሩ ነበሩ:: የሙሴ እናት ግን የአንሰባ ተወላጅ የኾኑ ኤርትራዊ ናቸው::” ይላሉ:: እንዲሁም ታናሽ እህቱ ኤልሳ ተክሌ ኤርትራዊ ነኝ ብላ ለኤርትራ ነጻነት ከሻዕቢያ ጎን ተሰልፋ ታግላለች:: ከነጻነት በኋላም ዛሬም ድረስ ኤርትራዊነቷን ይዛ ኤርትራ ውስጥ ትኖራለች:: ስለዚህ የሙሴ ወደ ህወሓት መምጣት እና የኤልሳ ከሻዕቢያ ጋራ መቀጠል ገፋ ቢል የፍላጎት ጉዳይ ይኾን እንደኾነ እንጂ ትውልድ (የዘር ሐረግ) የትግል ቦታ ለመምረጥ እንደመለኪያ ኾኖ በሁለቱም መካከል ሊቀርብ አይችልም::

… ለመኾኑ ሙሴ እንዲያ ምርጥ ምርጥ የተባሉ የሻዕቢያ ታጋዮች ትግራይ ሄደው ከህወሓት ጋራ እንዲታገሉ ሲመለምል እንዴት ዝም ተባለ? በሻዕቢያ ውስጥ የተለየ ሐሳብ ማራመድ በራሱ ሕይወትን የሚያስቀጥፍ ጉዳይ ነው:: ሙሴ ግን የሻዕቢያን ታጋዮች ወደ ሌላ ቦታ ሄደው ሌላ ድርጅት፣ ሌላ ማንነት ተሰጥቷችው እንዲታግሉ እያሳመናችው ነው:: መቼም ሻዕቢያ እንዲህ ያለ ዴሞክራሲ የሚታይበት ድርጅት አልነበረም:: በርግጠኝነት ይህ ዕቅድ በላይዮቹ የሻዕቢያ አመራር ወጥቶ በሙሴ በኩል ተግባራዊ እየተደረገ ነበር::

የማሌሊት አቋም በኤርትራ ጉዳይ ላይ

የኢሕአዴግ መሪዎች ተራሮችን ያንቀጠቀጡ ባለታሪኮችን ሸኝተው፣ ባለታሪክ አድርገው የትግሉን እውነተኛ ታሪክ ግልባጭ (ተቃራኒው) ብለው የቤተ መንግሥት ድርጎ በሚከፍሏችው የድል አጥቢያ ጸሐፍት አጽፍው፣ አትመው በመሸጥ ስምን እና ዝናን ለማትረፍ የታደሉ ኾነዋል::

…ቀደም ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው ይህ “የኤርትራ ሕዝብ ትግል ቁልቁል አፉ አይደፋም” የሚለውን መጽሐፍ የጻፉት አቶ መለስ ዜናዊ ናቸው ያዘጋጁት። በርግጥ መጽሐፉ በህወሓት ስምና ማሕተም የተሠራጨ በመኾኑ በውስጡ የያዛቸው አቋሞች ሁሉ የአቶ መለስ ብቻ ናቸው ማለት አይቻልም::

…እንግዲህ የኤርትራዊ ማንነት ጉዳይ መለኪያ ተደርገው በአቶ መለስ ዘንድ የተቀመጡት ብዙ ስለኾኑ ዋና ዋና የኾኑትን ጨምቀን እንይ:-

1. “የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው” ብሎ ማመን አለበት::

በዚህ እምነት መሠረት ደግሞ ኢትዮጵያ ቀኝ ገዢ ስለኾነች ከኢትዮጵያ ጋራ ስለመኖር ስለ አንድነት እና ስለ ኢትዮጵያዊነት ማሰብ የለበትም:: …

2. የኤርትራን ጥያቄ ብቸኛ መፍትሄ ፌዴሬሽን ወይም ኮንፌዴሬሽን ሳይኾን መገንጠል ብቻ መኾኑን ማመን ይጠበቅበታል:: …

የሽግግር መንግሥቱ አቋም በኤርትራ ጉዳይ ላይ

…በዚያ ዘመን ኢትዮጵያውያን ሰብሳቢ ጠባቂ አልነበራቸውም:: ሌላው ይቅር እና ዜጎች ከመሀል አገር ሳይቀር በሻዕቢያ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች እየታፈኑ የሚወሰዱበት እና የሚገደሉበት ጊዜ ነው የነበረው:: አገሪቷ በቁሟ እየተዘረፈች ነው የነበረችው:: በዚያ ዘመን ኢትዮጵያውያን ስለ ደህንነታችው የሚጨነቅ የአገሩን ጥቅም የሚያስቀድም መንግሥት አልነበራቸውም:: ሻዕቢያን ሌሎች ጠላቶቻችን ስንቅ እና ትጥቅ እያቀበሉ ያቋቋሙት መንግሥት ነው የነበረው:: በመኾኑም ሻዕቢያ ባለው ሐይል ሁሉ የሚዘርፈው ሀብት፣ የሚያግዘው ንብረት አልበቃ ብሎት በጊዜያዊ ሽግግር መንግሥት በኩል ማቋቋሚያ ተብሎ በብዙ ሚልዮን የሚገመት ገንዝብ የተለገሰው መኾኑ ነው:: የሚገርመው እንዲያውም ይህም ፈፅሞ በቂ እንዳልኾነ ነው:: የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት በቁጭት ሲናገሩ የነበረው::

እስቲ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ በኤርትራ እና አንድነት ጥያቄ ላይ” (ገፅ 89) በሚለው መጽሐፍ ላይ የሰፈረውን እንመልከት፣

“በአሁኑ ጊዜ ትምክህተኞች በኤርትራ ጉዳይ ላይ በግልጽ ከሚያራምዷቸው ፖለቲካዊ መብቶች ባልተናነሰ ደረጃ ዓላማችውን ለማሳካት የሚያስችል ሰፊ የሐሰት ወሬዎችን የመንዛት ዘመቻ እያካሄዱ ይገኛሉ:: የኤርትራን ጉዳይ በሚመለከት የሚያናፍሷቸው ወሬዎች ከሁለት ተከፍለው ሊታዩ የሚችሉ ናቸው:: በአንድ በኩል ኢትዮጵያን ለመበታተን አልሞ የሚንቀሳቀስ የተደበቀ ተንኮል ነው በማለት የሚያናፍሱት ነው:: ሁለቱን አጠር አድርጎ በየተራ መመልከት ጠቃሚ ነው:: ስለ ንብረት መጓጓዝ ያለመቋረጥ በመወራት ላይ ያለው ሐሰት ከተጨባጭ ሐቅ ውጭ የኾነ ፍፁም ቅጥፈት ነው:: እንዲያውም እውነታው ከሚወራው እና ከሚወሸከተው ነገር ቀጥተኛ ተፃራሪ ነው:: ይህን ለማየት ጥቂት ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል:: ምናልባት አሥመራ በህግሓኤ ብትያዝ ብሎ ብዙ ቁልፍ ንብረት ከኤርትራ ወደ መሀል አገር ተጉዟል:: የፋብሪካዎች ዋና ዋና ክፍሎች እየተፈቱ ወደዚህ መጥተዋል፤ ባንኮች እዚያ ተቀምጦ የነበረውን ገንዘብ አብዛኛውን እንዳለ አጓጉዘዋል:: አልፎ ተርፎም የአሥመራ ዩኒቨርሲቲ መጻሕፍት እና መዛግብት ሳይቅር ተጓጉዟል:: ዛሬ ሰላም በሚሰፍንበት ጊዜ ከኤርትራ እንዲመጡ የተደረጉት ንብረቶች ወደነበሩበት ሊመለሱ ይገባቸዋል:: ኤርትራ ውስጥ የነበረውን መዝብሮ ወደዚህ ማምጣት የነበረው ፖሊሲ ጥያቄ ነው:: ዛሬ በወረራ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፣ አይገባምም:: አንዴ የነጠቀ ነጥቋል ከተባለ በሕዝቦች መካከል እንዲፈጠር የሚፈለገው አዲስ ዝምድና የማያገለግል ከመኾኑም በላይ በኤርትራ ወደቦች የሚገለገሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ናቸው:: የሽግግር መንግሥት በደርግ ውድቀት ዋዜማ ላይ ከኤርትራ ወደ መሀል አገር የመጡ ልዩ ልዩ ንብረቶች የወሰነው ይህን በመታዝብ ነው::”

ይህ የተሠመረበትን በደንብ ተመልከቱት፣ ማስፈራራትም ያለበት አገላለጽ ነው:: ከፈለጉ ኤርትራውያን በወደቦቹ እንዳንጠቀም በመከልክል ሊበቀሉን እንደሚችሉ የሚያመለክት ነው፤ ይህን ያሉት በ1984ዓ.ም ነው:: ይህም የኤርትራን ጉዳይ ገና በሪፈረንደም መልክ ሳይወስን ነው:: እንዲህ የሚሉን! በዚያን ጊዜ የኤርትራ እና ኢትዮጵያ የሚባል የነበረ ይመስል! ወደቦቹ የኤርትራ መኾናችውን በማውሳት “ይህን ካላደረግን በኤርትራ ወደቦች እንዳንጠቀም ልንደረግ እንችላለን:: እኛ ነን በይበልጥ የምንጎዳው” ይሉናል በእውነቱ ይኼን የሚለን ማን ነው? ምን ዐይነት ማንነትስ ቢኖርው ነው እንዲህ ደፍሮ የሚጽፈው?

የወደብ ጉዳይ እና ኢሕአዴግ

…በአዲስ ነገር ጋዜጣ (ሰኔ 7 2000 ዓ.ም) ታምራት ነገራ “የወደብ ባለቤትነት ጥያቄ የተሸነፈ እይታ ነውን?” በሚል ርዕስ “የወደብ ጥማት አባዜ ያለባቸው ኢትዮጵያውያን የሉም አልልም:: ቢሆንም እነዚህ የወደብ ጥያቄ ያላቸው ስዎች በኢትዮጵያ አናሳ ናቸው:: ሐሳቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከሰመ በመሄድ ላይ ያለ ጉዳይ ነው” ከሚለው የአቶ መለስ ንግግር በመነሳት “ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዐፄያውያንን የደርግ ርዝራዦች ቢሏቸውም እነዚህ የወደብ ጥያቄ ያላቸው ሰዎች በኢትዮጵያ አናሳ አይደሉም::” ብሎ ነበር:: እውነትም ነገሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመወያያና የመከራከርያ አጀንዳ ወደመኾን እየተሸጋገረ ነው::

አቶ መለስ “የኤርትራ ወደቦች በደርግ ስር በነበሩብት ወቅት” ይላሉ:: የኢትዮጵያ ወደቦች ብሎ ለመጥራት የሚያስችል ሞራል እንኳ አጥተው:: እንዲህ ብለው የሚያስቡት ምን ዐይነት እምነት ቢኖራችው ነው?

…በአንጻሩ አቶ መለስ ሌላ የራሳቸውን ተረት ተረት እንዲህ ይነግሩናል:-

“በአንጻሩ አሁን የአሰብንም የምፅዋንም ወደብ አንጠቀምም:: እነዚህን ወደብ ባለመጠቀማችን ምንድን ነው የቀረብን? ልማት ቢኾን በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ልማት፣ ፈጣን ልማት የተመዘገበው ባለፉት አራት ዓመታት ነው:: ስለዚህ ወደብ መኖሩ ረሃብ አይከለክልም:: ወደብ አለመኖሩ ረሃብ አያመጣም:: በጎረቤት አገር ወደብ በመጠቀም መሥራት ይቻላል:: ያለ ነገር ነው:: ስለዚህ ኢትዮጵያ ያለ ወደብ ቀረች ብለን የምንቆጭበትም፤ የምናዝንበት ምክንያት የለም:: ምክንያቱም አይጎዳንም:: ሊጎዳንም አይችልም:: ወደብ በነበረን ጊዜ ኢትዮጵያ ድኻ ነበረች:: አሁን ወደብ የለንም፤ ዕድገት ግን እያስመዘገብን ነው:: ስለዚህ ለማደግ ወደብ አስፈላጊ አይደለም ይሉናል።

ይህ አባባል በእንቅልፍ ላይ ላለ ሕፃን ልጅ ቶሎ እንዲተኛልህ ብለህ የምትነግረው ተረት ዐይነት ነው::

Comments are closed.

Bad Behavior has blocked 3683 access attempts in the last 7 days.