ከአቤ ቶኪቻው ጋራ የተደረገ አጭር ቃለ ምልልስ፤ ከስደት
አዲስ ነገር፡- ከመንግሥት ጋር በምን መልኩ እንድትተባበር ነበር ደኅንነቱ ይወተውቱህ የነበረው ?
አበበ ፡- ግልጽ የሆነ ነገር የለም ነገር ግን “Double agent ሆነህ ከእኛ ጋር” ስራ ይልኝ ነበር፡፡
“በአውራምባ ታይምስ” እና “በፍትሕ” ሣምንታዊ ጋዜጦች ላይ በሚያቀርባቸው የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ሽሙጦቹ የሚታወቀው አበበ ቶላ (አቤ ቶኪቻው) ከአገር መውጣቱን ከአዲስ ነገር ኦንላይን ጋር ባደረገው አጭር ቃለ-ምልልስ ገለጸ፡፡ ለደኅንነቱ በመስጋት አሁን የሚገኝበትን አገር ለመግለጽ ያልፈለገው አበበ፣ በመንግስት የደኅንነት ሰዎች ደረሰብኝ በሚለው ክትትል እና ማስፈራራት ምክንያት ቤተሰቡን ለመሰናበት ሳይችል አገር ለቆ ለመውጣት መገደዱን ተናግርል፡፡ “ፍትሕ መጫዎቻ ስትኾን መመልከቱ የየእለት ክስተት ኾናል” የሚለው አበበ “ከምገባ ወጣሁ” ሲል ይሳለቃል፡፡ ከአገር ከወጣ በኋላ የሰጠውን የመጀመሪያ አጭር ቃለ ምልልስ ይመልከቱ።
አዲስ ነገር፡- በድንገት አገርህን ለቀህ ለመውጣት ምክንያትህ ምንድን ነው?
አበበ ፡- ባለፉት ስድስት ወራት በይፋ ከመንግስት ጋር እንድተባበር ሲወተውተኝ እና ሲከታተለኝ የነበረው የደኅንነት ሰው በእኔ ተስፋ መቁረጡንና እኔን እስር ቤት ለመወርወር መወሰኑን ነገረኝ፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተሰቤን ሳልሰናበት በድንገት አገሬን ለመልቀቅ ተገድጃለሁ፡፡ ያው “ከመግባት መውጣት” ይሻላል ብዬ ነው
አዲስ ነገር፡- ከመንግሥት ጋር በምን መልኩ እንድትተባበር ነበር ደኅንነቱ ይወተውቱህ የነበረው ?
አበበ ፡- ግልጽ የሆነ ነገር የለም ነገር ግን “Double agent ሆነህ ከእኛ ጋር” ስራ ይልኝ ነበር፡፡
አዲስ ነገር ፡- አቤ እዚህ ላይ ግልፅ አድርገው፤ ለሌላ አካል የደኅንነት ስራ ትሰራለህ ብለው ይጠረጥሩህ ነበር
አበበ ፡- መጠርጠር ብቻ ሳይሆን መረጃም አለን ብለውኛል፡፡ ይሁንና እኔ ከጸሐፊነት ውጪ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ የለኝም፡፡ ስሰራ የነበረውም ለመንግሥት የሚጠቅም እንደነበር ነው የማምነው፡፡ እጽፋልሁ፡፡ በጽሑፌም የታችኛውን ኅብረተሰብ ሮሮ አሰማለሁ፡፡ ይህንንም ነው ለመንግሥት ይጠቅማል የምልህ እንጂ የማንም ኤጀንት አይደለሁም፤ የመሆን ፍላጎትም የለኝም፡፡
አዲስ ነገር ፡- በቅርቡ በአሸባሪነት ከተፈረጁት ሰዎች ጋር ካለህ የስራ ግንኙነትና ቅርርብ አንፃር የደረሰብህ ተፅእኖ አለ?
አበበ ፡- በአሽባሪነት ከተፈረጁት ጋዜጠኞች ጋር መገናኘት ቀርቶ ቤተስቦቻቸውን መጠየቅ ፈታኝ ነው፡፡ ይሁንና የሚደርስብኝን የመፈረጅ አደጋ ችላ በማለት በተደጋጋሚ ታሳሪዎቹንም ሆነ ቤተሰቦቻቸውን እጠይቅ ነበር፡፡
አዲስ ነገር፦ የስደትን የመጀመሪያ ቀኖች ከባድነት ስለምንረዳ ከዚህ በላይ አንጠይቅህም። እንኳን ደኅና መጣህ፤ ሥራህን ከስደት እንድትቀጥል እንመኛለን። የሚፈልጉት ዝምታህን ነው፤ ዝምታህን አትስጣቸው።
No comments yet... Be the first to leave a reply!