የ“አኬልዳማ” “ተዋንያን” በእነአንዷለም አራጌ ላይ ሊመሰክሩ ነው?
Individuals appeared on the infamous Stalin style confession TV ‘documentary’ “Akeldama” to incriminate themselves are reportedly to testify against defendants accused of “terrorist, treason and espionage.” More than 30 individuals are listed as witnesses against the defendants. The list includes names such as Debebe Eshetu, Zemenu Mola and others who appeared on “Akeldama”, sources in the Federal Hight Court told Addis Neger. Among the defendants in the same file are Andualem Arage (Vice president of UDJ), Birhanu Nega (leader of Gibot 7), Eskinder Nega and five other journalists. 16 of the 24 defendants are in exile.
(ሙሉ ገ.)
ሐሙስ ታህሳስ 5 ቀን 2004 ዓ.ም፡- የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት ከይፋዊ ጊዜ ቀጠሮ ውጪ በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ ላይ ተሰይሟል፡፡ ፍርድ ቤቱ ነገ ታህሳስ 6 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ቀርበው እንዲሰሙ ብይን ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ዛሬ ጠዋት ከይፋዊ የጊዜ ቀጠሮው ውጭ የእነአንዷለምን የክስ መዝገብ ለማየት የተሰየመው የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በ25/03/04 ጊዜው እንዲያጥርለትና ምስክሮቹን ለማሰማት እንዲችል ፍትሕ ሚንስቴርን በደብዳቤ በመጠየቁና ፍርድ ቤቱም “ታሳሪዎች በማረሚያ ቤት ቆይታ ላይ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ ነው” ተብሏል።
የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው “ይህ ችሎት ተቀጥሮ የነበረው ለታህሳስ 16 በመሆኑ በያዝነው የጊዜ አጀንዳ መሠረት ደንበኞቻችንን ለማነጋገር በምንዘጋጅበት ጊዜ ቀጠሮው ተሰርዞ ወደ ዛሬ እንዲመጣ በመደረጉ እንዳቀድንወ ሳናናግራቸው ቀርተናል፤ ስለዚህ ዛሬ ይሄን ችሎት ለመከታተል ዝግጁ አይደለንም” ቢሉም ፍርድ ቤቱ ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎ ዐቃቤ ሕግ ነገ የሰው ምስክሮችን እንዲያቀርብ ብይን ሰጥቷል፡፡
እንደ ፍርድ ቤት የዜና ምንጮቻችን በቅርቡ ከመንግሥት ጋር በመደራደር እና በግዴታ “አኪልዳማ‘ በተሰኘው የኢቲቪ የፕሮፓጋንዳ ዝግጅት ላይ ራሳቸውን፣ ሌሎች ሰዎችን እና ፓርቲዎችን በመውቀስ ለመንግሥት የድጋፍ ቃላቸውን የሰጡ (“ግለ ሂስ ያደረጉ”) እና ከእሥር የተፈቱት የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ) ዋና ጸሐፊ አቶ ዘመኑ ሞላ፣ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ አባል አሳምነው ብርሃኑ፣ አርቲስት ደበበ እሸቱ እና ሌሎች ከ 30 በላይ ሰዎች የዓቃቤ ሕግ ምሥክር ሆነው ሊቀርቡ ነው፡፡
የዐቃቤ ሕግ ምሥክሮች ናቸው የተባሉት ከእሥር የተፈቱትና ሌሎች ከሰላሳ በላይ ሰዎች ቀደም ሲል በናዝሬት ከተማ አንድ ሆቴል ውስጥ አርፈው በዐቃቤ ሕግ፡- ብርሃኑ ወንድማገኝ፣ አንተነህ ጌታቸው፣ ቴዎድሮስ ባህሩ እና ዘረሰናይ ምስግና የምሥክርነት ቃል አሰጣጥ ልምምድ ሲያደርጉ ነበር ያሉን አንድ የፍርድ ቤት የዜና ምንጫችን ትላንትና ከትናንት ወዲያ ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰው ልምምዳቸውን በመቀጠል አጠናቀዋል ብለውናል፡፡
አንድ ሌላ ምንጭ በበኩላቸው አቶ ዘመኑ ሞላ እና ሌሎችም ጥቂት ሰዎች ወደእስር ቤት ባይላኩም በቁም እስር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሰዎቹ ከተለቀቁበት ጊዜ ጀምሮ በየቀኑ ለፖሊስ ሪፖርት እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል።
የተከሳሽ ጠበቆች ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እስረኞች በቤተሰቦቻቸው፣ በጠበቆቻቸው፣ በሃይማኖት አባቶቻቸውና በሥራ ባልደረቦቻቸው የመጠየቅ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን አላከበረም፣ የፌዴራል ፖሊስ ደግሞ ታሳሪዎችን በቁጥጥር ሥር ሲያውል የወሰደባቸውን የግል ንብረቶች አልመለሰም፣ ኢቲቪ በሕግ ሂደት ላይ የሚገኝ ሁኔታን አኪልዳማ በሚል ዶኩመንተሪ ፕሮግራም የታሳሪዎችን ስብዕና የሚነካ ከፍርድ በፊት ውሳኔ የሰጠ ፕሮግራም በማቅረቡ የፕሮግራሙ አዘጋጅና የኢቲቪ ሥራ አስኪያጅ ይጠየቁልን ሲሉ አቤቱታቸውን በድጋሚ በማቅረብ ፍርድ ቤቱን ተማጽነዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የማረሚያ ቤት ተወካይን በመጥራት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ቀርቦ ሁኔታውን እንዲያስረዳ ለሁለት ጊዜ ያህል በደብዳቤ መጥራቱን ገልጾ፣ እስከ አሁን የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ያልተፈጸመበትን ምክንያት ቢጠይቅም ተወካይዋ እኔ ደብዳቤውን አድርሻለሁ ለምን እንዳልቀረቡ አላውቅም በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ለሦስተኛ ጊዜ የማረሚያ ቤቱን አስተዳደር “አዝዛለሁ” ብሏል፡፡
የተከሰሽ ጠበቆች ዐቃቤ ሕግ ነገ ዓርብ ታህሳስ 6 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በምስክርነት የሚያቀርባቸውን 35 ሰዎች ዝርዝር መረጃ እና ስማቸውን ገልጾ እንዳላሳወቃቸው ፍርድ ቤቱን ቢጠይቁም ለምስክሮች ደኅንነት ሲባል የተደረገ ነው በሚል ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ የነገው የፍርድ ቤት ድራማ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።
No comments yet... Be the first to leave a reply!