Mesfin Negash

Posts by Mesfin [zeitgeist - የዘመኑ መንፈስ]

http://addisnegeronline.com

የአቶ መለስ ጸጉርና የሕገ መንግሥቱ ምሰሶዎች

መለስ ፖለቲካን የሚመለከቱት በጥቁርና ነጭ ቀለም ብቻ ነው። ይህም ንግግራቸውና አስተሳሰባቸው በጽንፋዊ አቋሞች እንዲሞላ ያደርገዋል። ሰውየው ሃይማኖተኛ ቢሆኑ ኖሮ አልሻባብን የመሰሉ ሴክቶችን በቀላሉ ሊቀላቀሉ ይችሉ እንደነበር እገምታለሁ። አሁንም ሕገ መንግሥቱን ስለማሻሻል ተጠይቀው የሰጡት መልስም እንዲሁ ያለ ነው፤ ቀላሉን አክርረው፣ ከባዱን አጥቁረው፣ በመጨረሻ የተሟላ ትርጉም የማይሰጥ የተምታታ ሐተታ አቅርበዋል። አቶ መለስ እርሳቸውና ፓርቲያቸው ሕገ መንግሥቱ “የሚሻሻል ምንም ነገር የለውም” ብለው እንደሚያምኑ፤ ነገር ግን “መለስተኛ ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ ቢደረግ ጽጉሬን እነጫለሁ ማለት አይደልም፤ የሚነጭ ካለ” ብለዋል። የአዲሱ ፓርላማቸው አባላትም በሳቅ አጅበዋቸዋል።
በመጨረሻ አቶ መለስ ይህን ተንኳሽ መልእክት በዚህ ወቅት ማስተላለፍ የፈለጉበትን ምክንያት መጠየቅ ያስፈልጋል። ዋናውና አስቸኳዩ የአቶ መለስ ግብ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይሁኑ ከዚያ ውጭ ያሉ ተቺዎቻቸው ነክሰው የሚጮኹበትን አዲስ አጥንት/አጀንዳ መስጠት ነው። ይህም በአገሪቱ የሰፈነውን አፈናና የኢኮኖሚ ችግር በመጠኑም ቢሆን ያስረሳ ይሆናል ብለው አስልተው ይሆናል። ሁለተኛው የማብራሪያው ግብ “የአውራ ፓርቲ” ትምህርትን በመከለስ እርሳቸውና ፓርቲያቸው የማይፈልጉት፣ “በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ” የሚል ፓርቲ እንኳን ቢሆን የሚኖረው በእርሳቸውና በሥርዓታቸው ቸርነትና ሆደ ሰፊነት እንጂ ሕጋዊ መሠረት ኖሮት እንዳልሆነ በድጋሚ ለማረጋገጥ ነው። ይህም ቢሆን የዋህ ተቃዋሚዎችን ለማነጫንጭና ‘ለማስቆጣት’ በቂ ይሆናል።

Read more
Ben Ali and Leila

ስጦታ ለአምባገነኖች፣ ከሚወዱት እና ከሚወዳቸው ሕዝባቸው

የነቱኒዚያም ንቅናቄ በተደራጁ የፖለቲካ ቡድኖች/ፓርቲዎች የተመሩ አይደሉም። በአገራቸው መንግስታት ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚዎችም ተስፋ የቆረጡት ዜጎች የለውጥ ፍላጎታቸውን በመግለጽ ለውጡን ለማስጀመር “መደራጀት” አላስፈለጋቸውም። ምክንያቱም የአሮጌውን ስርዓት መጨረሻ ለመጀመር ንቅናቄው የሚፈጥረው ድምጽ በቂ ስለሆነ ነው። የአምባገነኖቹን ግንብ በድምጽ/በጩኸት መናድ ይቻላል። ይህ ድምጽ በመደራጀት ቅርጽ ካልያዘ ግን ሙባረክን በሙባረክ፣ መንግሥቱን በመንግሥቱ፣ መለስን በመለስ የመተካቱ አደጋ ሰፊ ነው። አሁን ሁላችንም በማድነቅ ላይ የምንገኘው የመጨረሻውን መጀመሪያ ነው። የመጀመሪያው መጀመሪያስ ምን ይሆን ይሆን? አሳሳቢ ጥያቄ ነው።…
የ1966ቱን የኢትዮጵያ አብዮት የሚያስታውሰው የነቱኒዚያ ንቅናቄ በአገራችን ሊደገም ይችላል። ልዩ ሁኔታዎች ግን አሉን። ኢሕአዴግ የፈጠረው በብሔር ላይ የተመሠረተ ያለመተማመን ስሜት፣ የበለጠ በሚያስፈራ መልኩ ደግሞ ከመሪ እስከ ተራ ካድሬ ድረስ ሲነዛ የቆየው “የዘር ማጥፋት” መርዘኛ አስተሳሰብ ተግባራዊ መገለጫ ከኖረው ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያውቅ የለም። እነዚህ ሁለት ሁኔታዎች በሚፈጥሩት ስጋት መነሻነት የባሰ ችግር ለማስወገድ ሲሉ የግብጹን ሕዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያ እንዳይደገም የሚፈልጉ ሰዎች ቢኖር አልገረምም። አናንቀው የሚያልፉት ስጋት አይደለም። ኢሕአዴግ በተለይም ቁልፍ መሪዎቹ ይህንን ስሜት በማፋፋም ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ደግሞ የታወቀ ነው። ስለዚህም በኢትዮጵያ የሚፈጠር መሰል ሕዝባዊ ንቅናቄ ይህንን አደጋ አስወግዶ ተቃውሞውን በተነጣጠረ መልኩ በመንግሥት/አስተዳደሩ ላይ ማስተናገድ ካልቻለ ያልታሰበ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል።…
መለስ ከሚወዱትና ከሚወዳቸው ሕዝባቸው ተመሳሳይ የሥራ መልቀቂያ ይጠብቁ ይሆን?

Read more

የጠፋው ትውልድ [አንድ ለቅዳሜ]

“የጠፋው ትውልድ” የሽግግር ዘመኖች ትውልድ ነው፤ ለዚያውም የከሸፉ ሽግግሮች። ይህ ጠቃሚ ጎኖች ቢኖሩትም ጉዳቶችም አሉት። አንዱ ጉዳቱ ትውልዱ በፖለቲካው ውስጥ አሻራውን የሚተውበት እድልና ጊዜ ማጣቱ ነው። ሆኖም ይህ ትውልድ ደርግ እና ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ መኖር ያልነበረባቸው፣ ድጋሚም መምጣት የሌለባቸው የፖለቲካ ስርአቶችና አመራሮች መሆናቸውን ኖሮ አይቷቸዋል። ይህ ትውልድ ሁሉንም ፖለቲካዊ ጽንፎች በአያቶላዎቹ ሲተነተኑ ሰምቷል፤ በፊት አውራሪዎቹ ሲተገበሩ አይቷል፣ ኖሯቸዋልም። ይህ ትውልድ የፖለቲካ ሐላፊነቱን ካልተወጣ አገራችን አዳዲስ ደርጎች እና አዳዲስ ኢህአዴጎችን ማስተናገዷ እንደማይቀር እሰጋለሁ። ያን ጊዜ ብዙ መንግሥቱዎች ወይም ብዙ መለሶች ይወሩናል፤ አያርግብንና! “የጠፋው ትውልድ” ከዚህ ልምድ የሚቀስመው ትምህርት አገሪቱን ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚያሸጋገር ቀመር እና ፖለቲከኞች እንዲያፈራ ይረዳው ይሆን?
ይህ ትውልድ በመሠረቱ ስለ አገርም ይሁን ስለ ፖለቲካ ያለው አመለካከት በቅድሚያ የተቃኘው “እናት አገር” ወይም “ኢትዮጵያ” በሚለው ጽንሰ ሐሳብ ዙሪያ ነው። የ“እናት አገር” ገናና ታሪክ፣ ሉአላዊነት እና አንድነት የፖለቲካው እንብርት ነበር። ስለ እናት አገር ለተከታዩ “አዲሱ ትውልድ” የሚተርፍ አክብሮትና ፍቅር ያደረበትም ለዚህ ነው። የአክብሮቱና የፍቅሩ መገለጫ ሁሉ “ትክክል” መሆኑን ግን እጠራጠራለሁ። አብዛኛው በተለይም ከተማ ቀመሱ በ”እናት አገር” ርዕዮተ ዓለማዊና ባህላዊ መሠረት ቢቀረጽም፣ በሒደት “በብሔረሰብ መብት” አስተምህሮ መማረክ የጀመሩ ቁጥራቸው የማይናቅ የትውልዱ አባላት አሉ።

Read more
Wise Men Background Worship Slide

Politics “Genna” Version!

Part of the lesson that the EPRDF took from the 2005 election was how to deal with religiously- affiliated individuals and groups. Its increasing control over the leadership of religious institutions is one aspect of the measures taken. The most obtrusive tactic employed in the last five years is infiltrating every inch of seemingly independent space within religious institutions and groups – recruiting all religiously active individuals or convincing them to stay away from politics altogether.

Rreligion remains an important factor in our politics, whether politicians recognize it or not. We should not ignore or avoid religion all together for political, social and national interests. Religious institutions and affiliated groups can play a positive role in supporting democracy and development. They can provide a grassroots level platform for deliberation and exercise of democracy. By the same token, they can be used to suppress people, as Marxists rightly argued. ‘Genna’, the birth of Jesus Christ, is about hope. Can our religions give us any hope about our politics?

Read more

ይቅር ባይ፣ ይቅር ተባይ፣ ይቅር አባባይ አሉ? ይቅርታና እርቅስ?

አንድ ጥፋተኛ የተባለ ወይም የሆነ ሰው “ይቅርታ” “ጠይቆ” ከእስር ወይም ከሌላ ዓይነት ቅጣት “ነጻ” መደረጉን በራሱ የሚቃወም ሰው ብዙ አይገኝም። ቁም ነገሩ ያለው ይቅር ባዩ “ስለጥፋቱ” ወይም አጠፋ ስለተባለው ነገር የደረሰበት ልባዊ ድምዳሜ፤ ይቅርታውን የሚጠይቅበት ምክንያት እና ፋይዳው ብቻ አይደለም። ይቅርታ ተጠያቂው እና አድራጊውም ወገን ደረሰብኝ ስለሚለው ጉዳት ብቻ ሳይሆን ስለጉዳቱ አድራሽ፣ ይቅርታውን ስለሚሰጥበት የሞራል እና የሕግ መሠረት እንዲሁም ስለይቅርታው ተናጠላዊና ሁለንተናዊ ፋይዳ የሚኖረው እምነትና ግብ የይቅርታውን ምንነት በተጨባጭ ይወስነዋል። ብዙውን ጊዜ ደግሞ በሁለቱ መካከል ይቅር አባባዮች አሉ። የእነርሱ ማንነት፣ የሞራል ተቀባይነት፣ በተግባር ለሕሊናዊ ዳኝነት የሚሰጡት ቦታ እና ከእርቁ ውጤት የሚፈልጉት ነገርም እንዲሁ እርቁን እርቅ የሚያደርግ፤ አለዚያም ድራማ የሚያሰኝ ሊሆን ይችላል።

አንድ ነጥብ በድጋሚ ላስረግጥ፤ እነዚህ በሦስቱም ወገኖች ዘንድ ሊፈተኑ የሚገባቸው ነገሮች ተሟሉም አልተሟሉም እንዲሁ “በሰብአዊነት” ብቻ የታሰረ “ከተጸጸተና ይቅርታ ከጠየቀ” መፈታቱን መደገፍ ከእርቅና ከይቅርታ ጥልቅ ሞራላዊና ስነልቦናዊ ትርጉምና ውጤት ጋራ ተፈጥሯዊ ግንኙነት ላይኖረው ይችላል። እንዲህ ሲሆን ይቅርታ ጠያቂውም፣ ሰጪውም ሆነ አሸማጋዩ ወገን (አንዱ ወይም ሁሉም) ድራማ እየሠሩ እንኳን ቢሆን እነርሱ ብዙዎቻችን በተግባር የማናውቀውንና የማናደርገውን የይቅርታ መንፈስ ተጋሪዎች ሊሆኑ አይችሉም።

Read more

[አንድ ለቅዳሜ] ስለ ፖለቲከኞቻችን ምን ይነበባል? እነርሱስ ምን ያነባሉ?

ለመሆኑ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የመሪነት ሚና የመጫወት ፍላጎት ያለው ሰው እንዲያነባቸው የሚመከሩ መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው? አንዳንድ ጊዜ የምንረዳበት መንገድና መጠን ቢለያይ እንኳን ስለ አገራችንም ይሁል ስለሌላ ስለሚጠቅመን ጉዳይ ተቀራራቢ መረጃ (ትርጉም አላልኩም) እንዲኖረን ሊነበቡ ይገባቸዋል የምንላቸው መጻሕፍት (ግምታዊ) ዝርዝር ቢኖረን የሚጠላ አይደለም። “የተሳሳቱ መረጃዎች የተሳሳተ ሕግ ይወልዳሉ” የሚባለው እንዳይደርስብን ፖለቲከኞቻችን ቢያውቁት፣ ቢገነዘቡት የምንላቸውን መሠረታዊ ጉዳዮች እንዲረዱልን ልናግዛቸው ይገባል፤ በአንድ በኩል ፖለቲከኞች የእኛው ስራ ውጤቶች ናቸውና።

ነገሩ ሰፊ ክርክር የማጫር እድል ቢኖረውም አንባብያን የአገራችን ፖለቲከኞች ሊያነቧቸው ይገባል ወይም ቢያነቧቸው ጥሩ ነው የምትሏቸውን መጻሕፍት ዝርዝር እንድታካፍሉኝ ልጋብዝ። በመጨረሻ የመጻሕፍቱን ዝርዝር እዚሁ መልሰን እናትማቸዋለን። መጻሕፍቱ በየትኛውም ቋንቋ የተጻፉ፤ ኢልቦለድም ልቦለድም ሊሆኑ ይችላሉ። ታሪክ፣ ፖለቲካ፣ የሕዝብ አስተዳደር፣ ኢኮኖሚ፣ ሕግ ወዘተ እያሉ ማሰቡ ያግዝ ይሆናል። የመጽሐፍ ርእስ ከጠፋ በርእሰ ጉዳይ ለምሳሌም “ሐሳብን ስለመግለጽ ነጻነት፤ ስለ ሕግ ልእልና ወዘተ ቢያነቡ” ብሎ ሐሳብ መስጠት አይከፋም።

Read more

[አንድ ለቅዳሜ] የአዲስ ርእዮተ ዓለማዊ ትንተና ጅማሮ

እዚህ ላይ “አማካይ” ርእዮተ ዓለማዊ አማራጫ መቅረብ/መገኘት እንዳለበት በተደጋጋሚ ይነገራል። ተገቢም ነው። እኔም ይህን እደግፋለሁ፤ ፖለቲካ በአንድ በኩል ሙከራ ስለሆነም ጭምር። ነገር ግን ሁሉም በአማካይ ፍለጋ ብቻ መጠመድ የለበትም፤ ምክንያቱም ትክክለኛው ወይም የተሻለው አማራጭ አማካዩ ላይሆን ይችላልና። ለዚህም ነው በሌኒናዊ ግራ አመለካከት ታፍኖ የቆየው ፖለቲካ በመሠረቱ የተለየ የሆነውን የቀኝ/ሊበራል አመለካከት ለማስተናገድ ረጅም ጊዜና ትግል ያልጠየቀው። ከትምህርት እና ከከተሜነት መስፋፋት ጋራ የሚወለዱ አዳዲስ ፍላጎቶች ተፈጥረዋል፣ ይፈጠራሉም። ስለዚህም እነርሱን ርእዮተ ዓለማዊ ቅርጽ እየሰጡ የሚተነትኑ አማራጮች ያስፈልጋሉ።

Read more

[አንድ ለቅዳሜ] የአደባባይ ምሑራኑ የት ገቡ?

አንድ የተማረ ሰው ከምንም ተነስቶ ወደ መጨረሻው ደረጃ ለመድረስ የሚያስችለው ውጫዊ ሁኔታ ከጊዜ ጊዜ፣ ከቦታ ቦታ ይለያያል። ይሁንና እጅግ ወሳኙ ግብአት የግለሰቦቹ ውስጣዊና ግላዊ እምነት፣ ፍላጎት እና ግብ ነው። ቀድሞውኑ የምሁራኑ መገለጫ ነባራዊውን/ያለውን እያጸደቁና እያደነደኑ መኖር ሳይሆን ለሰው ልጅ የተሻለ ሕይወት ለማምጣት ያለውን መለወጥ/መረበሽ ነውና ውጫዊ ሁኔታው ከጅምሩ አጋዣቸው እንዲሆን አይጠበቅም። ይህም ሸክሙን ከውጭ ወደ ውስጥ ይመልሰዋል።

የእኛ የሕዝባዊ ምሁራን እነማን ናቸው? በእኔ ዕድሜ (የላይትማንን ደረጃ ልጠቀምና) ወደ ሦስተኛው ደረጃ መድረስ ችለው የነበሩ የአደባባይ ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ብቻ ናቸው። አሁን ደግሞ ጊዜው አጭር ቢሆንም ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ናቸው። የፕሮፌሰር መስፍን ወደ ፓርቲ ፖለቲካ መግባት (በተለይም የቅርብ ጊዜው የውዝግብ ድራማ) የሚያስነሳው ጥያቄ ቢኖርም ሰውየው ከአደባባይ ምሁርነታቸው የወረዱ አይመስለኝም። ምናልባትም አጋጣሚው የአደባባይ ምሁራንን በፓርቲ ፖለቲካ የሚኖራቸውን ተሳትፎ እንድንቃኝ የሚጠይቅ ነው። ነጻነት ባለበት የምእራቡ ዓለም ያሉና የአደባባይ ምሁር (public intellectual) መባል የሚገባቸው ጸሐፊዎች፣ ተናጋሪዎችም አሉ፣ ቁጥራቸው የእድሉን ያህል አይደለም እንጂ።

Read more

[አንድ ለቅዳሜ] የፖለቲካ ተሐድሶን ፍለጋ

ጥያቄውን በአቋራጭ ለመመለስ ቀላሉ መፍትሔ “አንድ ብቸኛ የተሐድሶ አነሳሽ ሊኖር አይችልም” ብሎ ውይይቱን በአጭሩ መቅጨት ነው። አለዚያም ፖለቲካችን ዞሮ ዞሮ የአፍሪካ ፖለቲካ ስለሆነ አለዚያም “ያልተጠበቀ ነገር” ወይም “ተአምር” ሊፈጠር እንደሚችል በማመን መልሱን ለጊዜ መተው አማራጭ መልስ ይመስል ይሆናል። ሁለቱም የአጭር መልስ አማራጮች ፖለቲካችን የገባበትን ድቅድቅ ከማሳየታቸውም ባለፈ ቀላል መከራከሪያዎች ተደርገው የሚታዩ አይደሉም። እነዚህን ለጊዜው ትተን ግን አሁን በማኅበረሰባችን ውስጥ ካሉ ኀይሎች/ክፍሎች መካከል ቀጣዩን የፖለቲካ ተሐድሶ በመቀስቀስ የትኛው ምን አይነት አቅም እና ዕድል እንዳለው መገምሙ ጠቃሚ ይሆናል።

1. አገር ውስጥ የሚገኙ ተቃዋሚዎች?
2. የተማረው ኀይል (ተማሪዎችን ጨምሮ)
3. የተደራጁ አካላት (ሲቪል ማኅበራት፣ የሞያ ማኅበራት ወዘተ)?
4. በሥልጣን ላይ በሚገኘው ቡድን ውስጥ የሚገኙ/የሚፈጠሩ ንዑስ ቡድኖች?
5. የታጠቁ ተቃዋሚ ኀይሎች
6. በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን (ዳያስፖራ)
7. ክፍለ አህጉራዊ ሁኔታዎች
8. የውጭ ተጽእኖ (በተለይ የምዕራቡ ዓለም እና ቻይና)
9. ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች

(እዚህ ያልተቀሰ ቢኖር እየጨመርን እንደምንቀጥል ታሳቢ በማድረግ) ከእነዚህ መካከል ቀጣዩን የፖለቲካ ተሐድሶ በማስጀመርና በመምራት በተናጠልም ሆነ በጋራ ወሳኝ ድርሻ የሚኖራቸውን ሦስት አካሎች በቅደም ተከተል ምረጡ ብንባል መልሳችን ምን ይሆናል?

Read more

[አንድ ለቅዳሜ ] ሥልጣን እንጂ ተጠያቂነት የሌለበት “የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ”

ኢሕአዴግ የምርጫ 2002 እፍረቱን ለማረሳሳት (ሊረሳ የሚችል ከሆነ) ብዙ ሙከራዎችን ማድረግ ነበረበት። የመጀመሪያው እና ትልቁም “የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ” ተብሎ የቀረበው ሰነድ ነው። ዕቅዱ በይዘቱም ሆነ በቅርጹ ሰፊ የሐሳብ ልውውጥን የሚጋብዝ ነው። እስካሁን በብዛት ትኩረት የተሰጠው ግን ዕቅዱ ሊሳካ የሚችል በመሆኑና ባለመሆኑ ላይ ነው። ዕቅዱ የሚሳካም ይሁን አለዚያም የማይፈጸም፣ የሰነዱ ፖለቲካዊ ፋይዳ ተገቢውን ትኩረት ያገኘ [...]

Read more

[አንድ ለቅዳሜ!] ከብርቱካን እስር ወደ ብርቱካን ጥያቄዎች

ክርክሩ “ለምን ይቅርታ ጠየቀች” ሳይሆን በዋናነት ይቅርታ ለመጠየቅ ተጠቀመችበት የተባለው አገላለጽ ነው። በእውነትም አገላለጹ እርሷን ለማዋረድ፣ ደጋፊዎቿን ለማሳፈር ሆን ተብሎ የተቀመረ እንደሆነ የሚያከራክር አይደለም። በዚህ ጉዳይ ላይ የብርቱካንን ምስክርነት ሳንሰማ “ይህኛውን ቃል፣ ያኛው አረፍተ ነገር” ብሎ መከራከር ትርጉም ካለው መደምደሚያ ላይ ማድረስ አይችልም። ብርቱካን ይቅርታ በጠየቀችበት ደብዳቤ ውስጥ በጣም ያስገረመኝን አንድ አረፍተ ነገር ልጥቀስ። “…ወደዚህ ስህተት ልገባ የቻልኩት መንግሥት የውጭ ኀይሎችን ተጽእኖ በመፍራት ሊያስረኝ አይችልም፤ ካሰረኝም ተገዶ በአጭር ጊዜ ይፈታኛል በሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ነው።” ቃላት ለአንድ ቀን እግር አውጥተው ወደየመጣችሁበት ተመለሱ ቢባሉ እነዚህ ቃላት የነብርቱካንን ሰፈር (ፈረንሳይ ለጋሲዮን) ዳገት ችለው ይወጡታል? ብርቱካን ይቅርታው ስለጠየቀችበት ከባቢያዊ፣ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ሁኔታ የራሷን ቃል ሳንሰማ “ቢሆንም…ምንም ቢሆን…” ማለት ብዙዎችን ከወዲሁ የሚያሳጣ አመለካከት ይመስለኛል። ጊዜ ሰጥቶን ዝርዝሩን እንሰማለን።

ሁለተኛው የአመለካከት ዘርፍ “ዋናው መፈታቷ” ብሎ የሚቆመው ነው። ይህ ምልከታ ለብርቱካን ሰብአዊነት የበለጠ ቦታ ይሰጣል፤ ለከፈለችው ዋጋ ከፍተኛ ዋጋ በመስጠትም “እርሷ የበኩሏን አድርጋለች” ብሎ ሊያምንም ይችላል። ከዚያም ባለፈ ስል ልጇ እና እናቷ ወዘተ በማሰብ መፈታቷን የራሱ ግብ አድርጎ ያስቀምጠቃል።

Read more
[አንድ ለቅዳሜ!] ይቅርታ ለብርቱካን ወይስ ይቅርታ ከብርቱካን? ይቅር ባዩ ማነው?

[አንድ ለቅዳሜ!] ይቅርታ ለብርቱካን ወይስ ይቅርታ ከብርቱካን? ይቅር ባዩ ማነው?

በአጭሩ አቶ መለስ ብርቱካን “ድጋሚ ይቅርታ ትጠይቅና እንለቃታለን” እያሉን ነው። መለስ “ካለፈው ታሪኳ አንጻር ድጋሚ ይቅርታ ብትጠይቅ አይገርመኝም፤ መንግሥትም ከልምዱ አኳያ ይቅርታ ቢያደርግላት አይደኝቀንም” ብለዋል። ትርጉም ግልጽ መሰለኝ።እንዲያውም አይጋ ፎረም ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ እርሷ ብቻ ሳትሆን ቤተሰብም፣ ጠበቃም…ስለእርሷ ተገብቶ ይቅርታ ሊጠይቅላት እንደሚችል አንቀጽ ተጠቅሶ “አቅጣጫው” ተብራርቷል። በአጭሩ ጥሪው “እርሷ እምቢ ማለቷ ስለማይቀር እባካችሁ አንዳችሁ ይቅርታ ጠይቁላትና እንገላገል” ይመስላል። በቀዳሚው የቅንጅት አመራሮች እስር ወቅት ፕሮፌሰር መንስፍ ወልደ ማርያም “ለኢሕአዴግ የማርያም መንገድ እንስጠው” በማለት ታሳሪዎቹ እንዲፈርሙ ሐሳብ አቅርበው ነበር ይባላል። ይህም ሌላ “የማርያም መንገድ” ጥያቄ ይሆን?

ሞራል በፖለቲካ ውስጥ ያለውን ቦታ ባስታወስኩ ቁጥር የዛሬዎቹ ይቅርታ ጠያቂ እና ሰጪዎች ልዩነት አብሮ ይመጣብኛል። ብርቱካ እና መለስ የሁለት ትውልድ ብቻ ሳይሆን የሁለት ዓለምም ሰዎች ናቸው (“መለስ” ስል አቶ መለስን ብቻ ማለቴ አይደለም፤ “ብርቱካን” ስል የእርሷን ሐሳብ የሚጋሩ በተለይም የትውልድ አቻዎቿን ማለቴ እንደሆነ ሁሉ)። በዚህ ጉዳይ ላይ በሌላ ጽሑፍ እመለስበት ይሆናል፤ መለስ፣ ብርቱካንን እና ቴዲን ሊረዷቸው ያልቻሉበትን ምክንያት ፍለጋ። ለመሆኑ አሁን ይቅርታ ጠያቂው ማነው? ይቅርታ ሰጪውስ? ብርቱካን የእነአቶ መለስን ይቅርታ ትፈልጋለች ወይስ እነአቶ መለስ የእርሷ ይቅርታ ይገባቸዋል? ዓለም ይህን አትፈቅድ ይሆናል እንጂ ለነገሩስ በአደባባይ ብርቱካንንም ሆነ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ የነበረባቸው አሳሪዎቿ ነበሩ።

Read more

[አንድ ለቅዳሜ!] መለስ ኮሎምቢያ ፖፕ ቤኔዲክት እንግሊዝ

በነገራችን ላይ

የሰሞኑ የኢሕአዴግ ጉባኤ ምን ማለቱ ነው? እኛ እኮ ቻይና ሞዴላችን ናት ሲባል በኢኮኖሚ ብቻ መስሎን ነበር። ውይ በፓርቲ ልብስም ጭምር ሆነ እንዴ? ኮፍያው አልቀረ፤ ምንጣፉ አልቀረ። አይ እንዲህ ከሆነ አንድ ፊቱን አጠራርም ይቀየርልና። ሊቀ መንበር መሌ ይባልልን፤ ልክ ሊቀ መንበር ማኦ ወይም ሊቀ መንበር መንጌ እንዲል። ጉባኤው በኢቲቪ የተዘገበበት መንገድ ደግሞ በልጅነታችንን ያየነውን የኢሰፓ ጉባኤ የሚያስታውስ ነው። “አውራ ፓርቲ” በደንብ እየገባችን ነው።

ግን ግን ይሄ “አውራ ፓርቲ” የሚለው ስያሜ በድርጅቱ ሊቀ መንበር ታምኖበት የጸደቀ ነው? ትርጉሙ እኮ ያምታታል። ለምሳሌ “አውራ” የሚለው ዋና፣ ታላቅ፣ መሪ፣ የጫጩቶቹ ፓርቲዎች ሁሉ አባት የሚል በጎ ትርጉም ይሰጣል። እናቲቱን ዶሮ መፈለግ የሕዝብ ጉዳይ ነው።
ጸረ ልማትና ጸረ ሕዝብ ኀይሎች ግን “አውራ” የሚለውን “እንደልማድህ ለፍልፍ፣ ተናገር፣ ወሬ እንደሆን አያልቅብህም፣ አንተን ከማዳመጥ ሌላ ምን ምርጫ አለን አውራብን፣ ደሞ ጀመረህ በል አውራብን ልባችንንም አውልቀው” እያሉ የተሳሳተ ትርጉም ሊሰጡት ይችላሉ። እስቲ አሁን አንዱ ተንኮለኛ “አውራ ፓርቲያችን” ሲል ምን ማለቱ ነው? ደግሞስ ይህ ስያሜ አጋር የምንላቸውን ፓርቲዎች ጸረ ሕዝቦች “ጫጩት ፓርቲዎች” እንዲሏቸው በር አይከፍትም ወይ? በሒደት “አውራ ፓርቲ” ምስጋና መሆኑ ቀርቶ ስላቅ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ወይ ይህንን ቃል አለአግባባ አጥብቆ ወይም አላልቶ ማንበብን፤ እንዲሁም ለራስም ሆነ ለሌላ ሰው ከተፈቀደው ውጭ የሆነ ትርጉም ሊሰጥ በሚችል ወይም ሊሰጥ ይችላል ተብሎ በሚያስጠረጥር ቃናና ድምጽ መናገርን የሚከለክል ሕግ ማውጣት የአዲሱ ፓርላማ የመጀመሪያ ስራ ይሁን አለዚያም ሳይለመድ ይቀየር። አማራጭ መጠሪያዎችን እንቀበላለን። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Read more
DancingAnimals

So You Think You Can Dance? Try Politics!

The most daunting task is measuring how much the New Generation is ready to invest in order to set the country on the right track. Is the New generation politically matured and courageous enough to learn from history? What is the root cause of this generational obsession in our politics, anyway? Is it uninterrupted generation-wide dissatisfaction, or lack of intentional collaboration among generations?

There will not be any clear-cut, single-generation politics. Finding the right mix of generations, both at the party and national level, is the cardinal question of political succession. Anyone who “thinks s/he can dance” can join politics. So you think you can dance? Play politics.

Read more
ሐውልቱ፤ ባለሐውልቱ እና ሐውልተኞቹ- የድቀቱ ምስክሮች

ሐውልቱ፤ ባለሐውልቱ እና ሐውልተኞቹ- የድቀቱ ምስክሮች

ቤተ ክርስቲያኒቱ ካለችበት ቀውስ አንጻር አሁን የሚያስፈልጋት ጥልቅ ራስን የምር የመፈተን ቁርጠኝነት ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረታዊ አስተምህሮዎች፣ ትውፊት እና ታሪክ ግምት ውስጥ ያስገባ የመንፈሳዊ እና ተቋማዊ ለውጥ አብዮት/ተሐድሶ ሊያመጣ የሚችል ራስን የመፈተሽ ተጋድሎ ይጠብቃታል። ሐውልት የሚቆምለት ተጋድሎም እርሱ ይሆናል። ይህ የለውጥ አብዮት ከየት ይነሣል፣ እነማን ያሥነሱታል፣ እንዴትና እንደ ምን ተጀምሮ በምን ይጠቃለል ይሆን? የሚሉት ጥያቄዎች ቀላል መልስ የላቸውም።

እስከዚያው ግን ቢያንስ ለድቀቱ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ ለአባ ጳውሎስ የቆመው ሐውልት ባለበት ይቆይ። ባይሆን ከግርጌው የሰፈረውን ጽሑፍ መቀየር ይሻላል። “ወደ መንበሩ ከመጡ ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የገባችበት መንፈሳዊ እና ተቋማዊ ድቀት በየዓመቱ 99.6 በመቶ እንዲያድግ ስላደረጉት መንፈሳዊና ስጋዊ ተጋድሎ ምስክር ይሆን ዘንድ ልጆቻቸው ይህንን ሐውልት አቆሙላቸው።” ሐውልቱን አታፍርሱት።

Read more

Bad Behavior has blocked 2472 access attempts in the last 7 days.