Posts by admin admin

mercato2

መርካቶ የዘይት ወረፋው አይሏል; ሰልፍ ሀምሳ ብር እየተሸጠ ነው

ዛሬ ረፋዱ ላይ በአቶ ጌቱ ገለቴና በወንድማቸው አቶ አስራት የሚመራው ጌት-አስ ኢንተርናሽናል እንደ ‹‹አልሳም›› ሁሉ ከሳምንት በፊት የተመዘገቡ ደንበኞቼን ሳላስተናግድ አገልግሎት አልሰጥም በማለቱ ጥቂት ነጋዴዎች በብስጭት ሰልፉን ጥለው ሲሄዱ ብዙዎቹ ግን ሁኔታው ሊለወጥ ይችላል በሚል ሰልፋቸው ባለበት ቦታ ድንጋይ እያመጡ በመቀመጥ የሚኾነውን ሲጠባበቁ ነበር፡፡

Read more
n51658023525_1517284_8889

Ababa Tesfaye to Host New Show

The well-liked and honored children’s program host, Tesfaye Sahilu – known as “Ababa Tesfaye” – is hosting a new show to be shown at Panoramic Theater, the new theater in the Martyr’s building.
* * *
From Our Archive: Ababa Tesfaye’s Great Journey (Interview)

A couple of months before we started Addis Neger newspaper, the same team launched a website called Ethiomirror. It was a short-lived project. Most of the articles were read only by a very small number of people. Here we publish an Interview with the great Ababa Tesfaye. He had been the background sound for Ethiopian children for the past forty years. Fired from his work, he makes a living by selling his books.

Read more

የኤደን ፣ የቤቲ እና የሜላት አማርኛ

ለግል ት/ቤቶች የፈረንጅ ምስል የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ በጉልህ የሚታየው የደሞዝ ልዩነትም ለዚህ ጥሩ ማስረጃ ነው፡፡ አንድ በግል ት/ቤት የሚገኝ ምንም አይነት ዲፕሎማም ሆነ ዲግሪ የሌለው ፈረንጅ የቆዳ ቀለሙ ነጭ በመሆኑ ብቻ ማስተርስ ካለው ኢትዮጵያዊ በአምስት እጥፍ የበለጠ ደሞዝ ያገኛል፡፡ የአንድ ፈረንጅ አማካይ ደሞዝ ከ 5-11 ሺ የኢትዮጵያ ብር ይደርሳል፡፡ በአንጻሩ ሁለተኛ ዲግሪና ረዥም የስራ ልምድ ያለው ኢትየጵያዊ መምህር 3 ሺ ብር የክፍያ ጣርያው ነው፡፡

በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ከፈረንጆች ቀጥሎ ጥሩ ክፍያ የሚያገኙት ህንዶች፣ ጃማይካዎችና ሌሎች የአፍሪካ ዜግነት ያላቸው መምህራን ናቸው፡፡ ሆኖም በስደት ወደ ሶስተኛ አገር ለመሄድ አዲስ አበባ የሚኖሩ አፍሪካውያን በ‹‹ሀበሻ›› ደሞዝ ሊቀጠሩ ይችላሉ፡፡

Read more

ዲቪ እና CV

ነገሩ ስላስደነቀኝ ተጨማሪ ነገር ለማግኘት በዩኒቨርስቲው ግቢ መዘዋወር ጀመርኩ፡፡ የዲቪ ማስታወቂያዎች በተማሪዎች ካፌ፣ በመማርያ ክፍሎች ደጅ ባሉ የማስታወቂያ ሰሌዳዎች፣ በቤተ መጻሕፍቱ በር ላይ ወዘተ ተለጣጥፎ አየሁ፡፡ የማስታወቂያው ይዘት ተማሪዎች ዕድሉ እንዳያመልጣቸው እና እንዲጠቀሙበት የሚያባብል ነው፡፡ የተማሪዎች ካውንስል ነው ይህንን የሚስተባብረው፡፡ በኔ ጊዜ የነበረው የተማሪዎች ካውንስል የመንግሥት ለውጥ እንዲመጣ ያስተባብር እንደነበር ትዝ አለኝ፡፡

Read more

ጓሳ – ያልተዘመረለት ተፈጥሮ

(በመሀመድ ሰልማን) …አቶ መለስ “መሀል ሜዳ” የመጡ ጊዜ ታድያ ሰውየው ያረፉበት ስፍራ “ሕይወት ሆቴል” በሚባል አነስተኛ የገጠር መዝናኛ መሆኑ ተነግሮኝ ይህንኑ ለማረጋገጥ ሄድኩኝ፡፡ ሆቴሏ በከተማዋ መሀል ትገኛለች፡፡ ሙሉ በሙሉ የጭቃ ቤት ስትሆን ጥግ ጥጉን የተሰሩ ወደ ጎን ያዘመሙ መኝታ ክፍሎችና አንድ ምግብ ቤት በውስጧ ይዛለች፡፡ የሆቴሉ እመቤት የሀበሻ ቀሚስ አድርገው፣ ግዙፍ መነፅራቸውን ደቅነው ለምሳ ቤታቸው የተገኘውን ሰው ለማብላት ተፍ ተፍ ሲሉ አገኘኋቸው፡፡…

ደብረብርሃን፣ ባኬሎ፣ ጣርማ በር፣ መዘዞ፣ ማዞርያ፣ ጓሳ፣ መሀል ሜዳ፡፡ እነዚህ ወዳልተዘመረለት የጓሳ ምድር የሚያደርሱ የኢትዮጵያ ትንንሽ ከተሞች ናቸው፡፡ አዲስ አበባን መነሻ ካደረግን 260 ኪሎ ሜትር መራቅ ይኖርብናል፡፡ ይህ ድንቅ ስፍራ እንደ አክሱም ሽቅብ የተቀሰረ ሀውልት የለውም፤ እንደ ላሊበላ በፍልፍል ድንጋይ አልታነፀም፤ እንደ ኤርታሌ የሚንተከተክ ላቫ አልፈጠረበትም፡፡ እንዲያው ዝም ብሎ የተዘረጋ የፕላቶ ሸንተረር ነው፡፡ ግን ልብን ወከክ የሚያደርግ፣ ቢያዩት ቢያዩት የማይጠገብ እንዲሁም የማያልቅ፣ እንዲሁም የማይደክም ግን ደግሞ ሩቅና ሰ…ፊ!
ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ወይም ወደ የአማርኛውን ክፍል ይጎብኙ።

Read more

ብሔራዊ ባንክ የብርን የመመንዘር አቅም ዝቅ ሊያደረግ ነው

ባለፈው የካቲት ወር 2001 ዓ.ም የብር የምንዛሬ ምጣኔን በ22 በመቶ ዝቅ እንዲል መመሪያ አስተላልፎ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡም ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ምንጮች ገለጹ፡፡ በአዲሱ የምንዛሬ ማስተካከያም በሕጋዊው የምንዛሬ ገበያ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ14 ብር ሊመነዘር ይችላል፡፡
እንደምንጮች ገለጻ ከኾነ የዶላር እጥረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት በመደበኛው እና በኢመደበኛው (Parallel Exchange Market) ገበያዎች መካከል ያለው የምንዛሬ ምጣኔ ልዩነት እየሰፋ ሄዷል፡፡ በሣምንቱ የምንዛሬ ገበያ አንድ ዶላር በመደበኛው ገበያ በአማካይ በ13.40 ብር የሚመነዘር ሲኾን በድብቅ በሚካሄደው ኢመደበኛ ገበያ ግን አስከ 14 ብር ድረስ ይመነዘራል፡፡ ይህም በሁለቱ የምንዛሬ ገበያዎች ያለውን ልዩነት (premium) እንዲሰፋ አድርጎታለ፡፡ በውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ምክንያት ንግድ ባንኮች በወጪ እና ገቢ ንግድ የተሰማሩ ደንበኞቻቸውን በአግባቡ ማስተናገድ እየተሳናቸው እንደኾነም መረጃዎቹ ይገለጻሉ፡፡ ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ወይም ወደ አማርኛው ክፍል ይሂዱ።

Read more

የሙስሊሞች ተቃውሞ አገራ አቀፍ እየሆነ ነው፤ ኢሕአዴግ ሙስሊም አባላቱን “ለምክክር” ለነገ ቅዳሜ ጠርቷል

(ሩቂያ ሰ./ አዲስ ነገር ኦንላይን)

* በአዲስ አበባ በተከሰተ ግጭት ሰዎች ተጎድተዋል
* “[መጅሊሶች] ራሳችሁንም መንግሥትንም ከዚህ አጣብቂኝ አውጡ” የመንግሥት ተወካይ

በአዲስ አበባ የአሊያ ትምህርት ቤት እና መስጂድ የተጀመረው የሙስልሞች የአደባባይ ተቃውሞ ስምንተኛ ሳምንቱን ባስቆጠረበት በዚህ ሳምንት አገር አቀፍ መልክ እየያዘ መሆኑን ምንጮች ለአዲስ ነገር ያደረሱዋቸው መረጃዎች ጠቆሙ። ሰሞኑን ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰበውን 300 ሺህ ፊርማ ጨምሮ በድምሩ ከ500 ሺህ በላይ የአቤቱታና የተቃውሞ ፊርማ ተሰብስቦ በሕዝብ ለተመረጠው ኮሚቴ መድረሱ ተዘግቧል። ሁኔታው እጅግ እያሳሰበው የመጣው መንግሥት የተወካዮቹን ቁጥርና አይነት በመጨመር ነገሩን ለማብረድ እየሞከረ ነው።

Read more

የማይዋጠው “ቦጅ ቦጅ”

(አበበች በላቸው) መቸም “ቦጅ በጅን” የማያውቅ ተጋዳይ አለ ማለት ያስቸግራል። ቦጅ ቦጅ የእንግሊዝኛው (HOTCH POTCH) በአርሶ አደር አማርኛ ሲነገር ነው። ቦጅ ቦጅ ለአንድ ምግብ የተሰጠ ስያሜ ሲሆን በትግሉ ጊዜ ተጋዳይ ያገኘውን ሁሉ ሰብስቦ እንጀራውንም፣ ድርቆሹንም፣ ወጥ የነካካውንም አንድ ላይ አድርጎ የሞቀ ውሃ/የተፈላ ውሃ ተቸልሶበት ፍርፍር አይሉት ፍትፍት ብቻ ያን ተተራምሶ የተሠራውን ምግብ ነበር ቦጅ ቦጅ [...]

Read more

ፍርድ ቤቱ በእነኤልያስ ክፍሌ ክስ ከ14 ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እስራት በየነ

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን አሰምቶ እንደጨረሰ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ “አጠቃላይ ሁኔታው የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ነው። ከጥርጣሬ ባሻገር ምንም ዓይነት ማስረጃ ባልቀረበበት ሁኔታ ነው የፈረዳችሁብን” በማለት ቅሬታውን ገልጿል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ሊቀ መንበር አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚያብሔር በበኩላቸው “እኔ ጥፋተኛ አይደለሁም፣ ለሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በተቃዋሚ ፓርቲ በመሰለፌ ነው ይሄ ቅጣት የተወሰነብኝ” በማለት ለፍርድ ቤቱ ቅሬታቸውን ያሰሙ ሲሆን የቀኝ ዳኛው ሙሉጌታ ኪዳኔ ቆጣ ብለው አሁን ዝም በሉ ቅሬታ ካላችሁ ይግባኝ መጠየቅ ትችላላችሁ ብለዋል፡፡

Read more

በእነአንዷለም መዝገብ 24ቱ ተከሳሾች ተከላከሉ ተባሉ

(ሙሉ ገ./ኢዲስነገር ኦንላይን)
ዛሬ ከሰአት በኋላ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ በዋለው ሦስተኛ ወንጀል ችሎት የመሐል ዳኛ እንዳሻው አዳነ የፍርድ ቤቱን ብይን በንባብ አሰምተዋል። የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾች ላይ ካቀረባቸው ስድስት ክሶች ውስጥ በ1ኛው ክስ ሁሉም የተከሰሱ ሲሆን አንዷለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ ዮሐንስ ተረፈ፣ ሻምበል የሸዋስ ይሁንአለም፣ ክንፈሚካኤል ደበበ፣ ምትኩ ዳምጤ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አያሌው፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ውቤ ሮቤ፣ መስፍን አማን፣ ዘለሌ ጸጋ ስላሴ፣ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም፣ አበበ በለው፣ ኦባንግ ሜቶ የተባሉት ተከሳሾች ወንጀሉን ስላለመፈጸማቸው እንዲከላከሉና እንዲያስረዱ፤ በአንፃሩ በኤፍሬም ማዴቦ፣ አበበ ገላው፣ ንአምን ዘለቀ፣ ኤልያስ ሞላ፣ ደሳለኝ አራጌ ዋለ፣ ኮ/ል አለበል አማረ በተባሉት ተከሳሾች ላይ ግን ዐቃቤ ሕግ ክሱን የሚያስረዳ በቂ ማስረጃ ባለማቅረቡ መከላከል ሳያስፈልጋቸው ነጻ ወጥተዋል ብሏል- ፍርድ ቤቱ፡፡ ክሱ በጸረ ሽብር ሕጉን አንቀጽ 3/1-4፣ አንቀጽ 4 እና 6 የተደነገገውን በመተላለፍ በሚል የቀረበ ነው። በክስ ቻርጁ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በዚህ ክስ ቢካተቱም በኋላ ዐቃቤ ሕግ 23ኛ እና 24ኛ ተከሳሾች “በታይፕ ስሕተት” መግባታቸውን በመጥቀስ ከዝርዝሩ ወጥተዋል። የክሱ ጭብጥ በጥቅሉ የሽብር ድርጊት መፈጸም ወይም ለዚሁ መዘጋጀትንና ማሴርን፣ እንዲሁም ሽብርተኝነትን ማበረታታን የሚመለከት ነው።

Read more

A Joint Statement: ‘Commission must stand up for human rights in Ethiopia’

In a joint statement issued today, December 20, 2010, Europe and Sweden based organizations and groups called the European Commission to take action against the Ethiopian Government. Among the signatories of this statement are European Federation of Journalists and Reporters Without Borders. The parties called that “Europe must also stand up for the role of the media as the watchdog of democracy by stating that what is happening now in Ethiopia is an issue larger than the case of the two Swedish journalists. The trial currently going on in Addis Ababa, where all parties are acting as expected, is in fact emblematic of the injustice done to the Ethiopian people by its own government.”

Read more

በነአንዷለም ላይ ምስክሮች መሰማት ጀመሩ

የመኢዴፓ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ ዘመኑ ሞላ፣ የአንድነት ፓርቲ አባል አቶ አሳምነው ብርሃኑ እና አርቲስት ደበበ እሸቱ (አልመሰክርም ብሎ እያቅማማ ነው የሚል መረጃ አለ) የተካተቱበት 14 ምስክሮች ደግሞ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 9 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት እንዲያቀርብ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በሰኞው ችሎት ላይ “ከሰው ምሥክር ባሻገር የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃ አለኝ” ሲል የገለጸ ሲሆን የቪዲዮው ማስረጃ በእሥር ላይ የነበሩትና ከመንግሥት ጋር በመደራደር በቁም እስር ላይ የሚገኙት ሰዎች ንግግር እና “የደኅንነት ሰዎች ከዚህ ቀደም በሌሎች ላይ የሰሩት አይነት የጀርባ ክትትል ድረማ ቀረጻ ነው” ሲሉ አንድ የፍትሕ ሚንስትር ሠራተኛ ለሪፖርተራችን ተናግረዋል፡፡
በሌላ ዜና “የሙስሊሞች ጉዳይ” መጽሔት አዘጋጆች ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ “ምርመራዬን አላጠናቀኩም” በማለቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቶባቸዋል።

Read more

Atrocities in Ethiopia? No problem! Just close your eyes and send more money!

In July 2011, two Swedish journalists entered the Ethiopian province Ogaden embedded with the ONLF guerrilla movement. The trial against the journalists and other abuses seem to surprise donor agencies, politicians and others outside of Ethiopia. But in fact, it is nothing new. On the contrary, abuses and crimes against human rights have been ongoing [...]

Read more

የአገር ቤት ጋዜጠኞች ምን ጻፉ ( ከጥቅምት 27 እስከ ሕዳር 2/2004 ዓ.ም)

  ማስፈራራትን እንደ ማበረታታት አድረገው በፍርኀት የተለወሰ ምክር የሚያቀርቡላችሁን አትስሙዋችው   ተመስገን፤ የፍትሁ ተመስገን፤ ሲጽፍ ብዕሩ የማያወላዳው ተመስገን፤ ምሬቱን መደበቅ የማይችለው ተመስገን፤ በዚህ ሳምንት “አንድ በሉ” በሚለው ዐምዱ ሥር ማስፈራራትን እንደ ማበረታታት አድረገው በፍርኀት የተለወሰ ምክር የሚያቀርቡላችሁን አትስሙዋችው፤ ከእነርሱም ራቁ፤ እነርሱን በመስማት የሚመጣ አንዳች ለውጥ የለም የሚል መልእክት ያለው አንድ ጽሑፍ አቅርቧል፡፡ ተመስገን መሮታል፡፡ ከባልደረቦቹ [...]

Read more

ጋዜጠኞች በ3 ተከፍለው ክትትል ይደረግባቸዋል

በኤሊያስ ክፍሌ ፋይል የኢሳት ኢንትርቪው በአቃቤ ሕግ ማስረጃነት ቀረበ

(ሙሉ ገ. እና ኤፍሬም ካሳ)
በአቶ በረከት ስምዖን የሚመራው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ በህትመት ሚዲያ ዘርፍ ፍቃድ አውጥተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የብዙኀን መገናኛ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞችን በሦስት ከፍሎ እንደሚከታተላቸው ታወቀ። ጋዜጠኞቹና ገዘባዎቻቸው “አዎንታዊ/ገንቢ”፣ “አሉታዊ/አፍራሽ” እና “አማካይ” በሚል መመደባቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ በዚህ የአቶ በረከት መደብ ውስጥ በዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ኢትዮጵያዊያንና በኢትዮጵያ የተመደቡ የሌሎች አገራት ጋዜጠኞችም ተካተዋል ብለዋል፡፡

Read more

Bad Behavior has blocked 2470 access attempts in the last 7 days.