አንድ ዶላር በኻያ ብር ሊመነዘር ነው
የአዲስ ነገር ኦንላይን ምንጮች በዚህ ሳምንት እንደገለጹት ብሔራዊ ባንክ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት የብርን የአሜሪካ ዶላር የመግዛት አቅም በ15 በመቶ ያህል ለመቀነስ ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህም በሰሞኑ መደበኛ የምንዛሬ ገበያ በአማካይ በብር 17.35 ሲገዛ የነበረው የአሜሪካን ዶላር በብር 20 ሊመነዘር ይችላል፡፡
የኢትዮጰያ መንግሥት በተለይ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ እየተባባሰ የመጣውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቅረፍ አልተቻለውም፡፡ ስለዚህም በዓለም አቀፉ ገበያ የዋጋ ተወዳዳሪነትን ይጨምራል፤ በዚህም የውጭ ምንዛሬ ክምችት ተያይዞ ያድጋል በሚል በተደጋጋሚ የብርን የመግዛት አቅም ማሽመድመድን ብቸኛው አማራጭ አድርጓል፡፡ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ በወሰደው እርምጃ የብርን የምንዛሬ ዋጋ በ20 በመቶ አውርዶት ነበር፡፡ ይኹንና የታሰበው የገቢ ንግድ ሳይጨምር የዋጋ ግሽበት ከነበረበት ከፍተኛ ምጣኔ እየገሰገሰ የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፡፡
Recent Comments