
ያልተዳሰሱ የሐውልቱ ወጎች
ቀራጺው አቶ ብዙነህ ተስፋ ሐውልቱን እንዲሠራ ሲነገረው የተሰማው ደስታ ልክ አልነበረውም። ሐውልቱ የሚሠራላቸው ግለሰብ በሕዝብ ዘንድ ያላቸው ስምም ይኹን ሐውልቱ ሊያመጣው የሚችለው ውዝግብ ለእርሱ አልተከሰተለትም። “ሰውየውን በጣም ነው የማደንቃቸው” የሚለው አቶ ብዙነህ የእኚህ ሰው የተማረ ሰብእናና በእርሱ አገላለጽ “ማቹርድ አስተሳሰብ” ይማርከዋል። የሐውልቱንም ዕድሜ በተመለከተ ሲነገር የነበረውን አምስት መቶ ዓመት አቶ ብዙነህ አያውቀውም። “እኔ እንዲህ ዐይነት ዋስትና አልሰጥም” ሲል ጫን ባለ አነጋገር የሐውልቱ ዕድሜ ያን ያህል ሊኾን አንደማይችል አስቀምጧል። ከዚህ በተጨማሪ ሐውልቱ የተሠራው ከናስ ነው የሚለውንም አስተያየት ያስተባብላል፤ ሐውልቱ የተሠራው ፋይበር ግላስ ከተባለ ግብአት ነው በማለት። ከዚህ ዐይነቱ ቁስ የሚሠራው ሐውልት ደግሞ ዕድሜው ከስድሳ እና ከሰባ አይበልጥም የሚለውን ግምቱንም ያስቀምጣል።
Read more
Recent Comments