Tag Archives: Religious freedom
Recent Blog Posts
-
የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ እና አገራዊ ፋይዳው፤ አጭር ቁዘማ
6 Aug 2012
(ስደተኛው መስፍን ነጋሽ፤ ከአገረ ስዊድን)
ላለፉት ሰባት ወራት በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ምህዳር (public sphere) ሳይበርዱ ከሰነበቱት ርእሰ ጉዳዮች አንዱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሱት የመብት ጥያቄ እና መንግሥት ለጥያቄው የሰጠው ትርጉምና ምላሽ ይገኝበታል። ነገሩ ሰሞኑን ተካሮ ሰንብቷል። የመነጋገሪያ አጀንዳነቱም እንዲሁ በጣም ጨምሯል። በዚህ ንግግር ውስጥ በስሕተትም በእቅድም እየተምታቱ የሚቀርቡ ጉዳዮች መኖራቸውን ብዙዎች ያስተውሉታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ሆኖም ጉዳዮቹን ነቅሶ ማውጣቱ ለውይይት ብቻ ሳይሆን አቋምን ለመፈተሽም ይረዳል በሚል እምነት ነገሩን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ። ነገሩ ብዙ ጉዳዮችን የሚያሰናስል እንደመሆኑ ቁዘማዬም (reflection) ጥቂት ረዝሞ ልታገኙት ትችላላችሁ። ትእግስታችሁን እማጸናለሁ።
በዚህ ጽሑፍ የኢትዮጵያውን ሙስሊሞች ሕጋዊና ሰላማዊ ጥያቄዎች በሁለት ምክንያቶች በሌላውም ኢትዮጵያዊ መደገፍ አለባቸው እላለሁ። ሕጋዊ ጥያቄዎቹ ”ከአክራሪነት/ሽብርተኝነት” ጋራ ተደባልቀውና ተምታተው እየቀረቡ ችላ መባልም ሆነ መረገጥ አይገባቸውም ስል እከራከራለሁ።
I am at Awelia because injustice is there!
(No Comments)
-
The Ethiopian Gaze
27 Mar 2012
Derese Getachew/addisnegeronline.com
I always wonder if this ambivalent and pensive visual exchange, which never involves words, is an Ethiopian value in itself. Or is it ambivalence that Ethiopians find themselves in trying to reconcile their home grown norms of greeting everyone, including strangers with western values of greeting? Back home; people nod, wish you peace, or ask you how your evening has been when meeting you. In Ethiopia, passing by without greeting a bystander leaves a very eerie feel and a bad taste in the mouth of anyone.
(4 Comments)
-
ጥያቄው ከስኳር እና ከዋልድባ መምረጥ አይደለም
21 Mar 2012
ቁሳዊ ልማትን የማፋጠን እና ታሪካዊ/መንፈሳዊ እሴቶችን የመጠበቅ ጉዳይ ሁልጊዜም አብረውና ተስማምተው ላይሄዱ ይችላሉ። አንዱን ለማሳደግ ሌላውን ዋጋ ማስከፈል የሚያስፈልግበት አጋጣሚ የመስተጋብሩ ቋሚ መገለጫ ይመስላል። ጥያቄውን በአንድ ነጠላ የልማት ፕሮጀክት አንጻር መመልከት ይቻላል። “ፕሮጀክቱ እገሌ የተባለውን ታሪካዊና መንፈሳዊ እሴት ያለው ቦታ/ሕንጻ… ይነካዋል አይነካውም? ከነካው ምን ያህል? ወዘተ” በሚሉ ጥያቄዎች ዙሪያ መነጋገርም መደራደርም ተገቢ ነው። ከዚህ መሰሉ ዝርዝር ንግግር በፊት ግን በመጀመሪያ ስለ “ልማቱ” እና ሰለ “እሴቶቻችን” ምንነትና ፋይዳ ዘርዘር አድርጎ መነጋገር ይገባን ነበር። ይህ በተለያዩ ወገኖች የሚሰጠው የተለያየ ሚዛን ቢያንስ ለሚቀጥሉት 100 ዓመታት በሚካሔዱ የልማት ክንውኖች መላልሶ እንደሚገጥመን አልጠራጠርም። ለዚህም ነው በቅድሚያ በሐልዮት ደረጃ ጉዳዩን ማብላላት አስፈላጊ ነው የምለው። የቁሳዊ ልማታችን እና የባህል ልማታችን ምንና ምን ናቸው?
(No Comments)
-
የአድዋ ልጆች፤ ምኒልክ፣ መለስ እና እኔ
2 Mar 2012
የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ አድዋ ምኒልክን ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስንም ወልዳለች። ልጅነታቸው ግን ለየቅል ነው። ምኒልክ ለአድዋ የመንፈስ ልጅ ናቸው፤ መለስ የደምና የአጥንት ልጅ ናቸው። የደምና የአጥንት ልጆች የመንፈስ ልጅነትንም ደርበው የማግኘት እድል አላቸው፤ ሁልጊዜም ግን ላይሳካ ይችላል። ገብረ ሕይወት ባይከዳኝን አይቶ ድርብ ልጅነቱን ማድነቅ ነው፤ መለስን ተመልክቶ የደምና የአጥነት ሆኖ መቅረቱን መታዘብ ነው። መካ የተወልዶ ሁሉ በነብዩ መንፈስ እንደማይቃኝ፣ የቤተልሔሙ ልጅ ሁሉ በክርስቶስ መንገድ እንደማይሔድ መሆኑ ነው።
(No Comments)
-
ከቢቢሲ ጋራ
1 Mar 2012
የሬዲዮ ጋዜጠኝነት በድምጽ ማማር የሚገባበት ሳይሆን የእውቀትና የችሎታ ጉዳይ መሆኑን በነጻ ለማረጋገጥ ቢቢስ መስማት። ሬዲዮ ልክ እንደ ጋዜጣ ሁሉ ለሰፊው አድማጭ፣ ለፖለቲካ ልሒቁ፣ ለቢዝነስ ልሒቁ፣ ለባህል ልሒቁ…እየተባለ ሲሠራ፣ የአገር እውቀትና ምሁር በሬዲዮ እንዴት ሊቀርብ እንደሚችል ከቢቢስ የበለጠ ማሳያ መኖሩን እጠራጠራለሁ። የሬዲዮ ድራማ…እናቃለን ብላችሁ ለራሳችሁ እንዳትነግሩት፤ አደራ። በሸገር አንዳንድ ፕሮግራሞች ላይ ይህን ምርጥ ዘር አልፎ አልፎ አያዋለሁ፤ ለምሳሌ “ሸገር ካፌ” እንደነበር አስታውሳለሁ።
(No Comments)
Recent Comments