Tag Archives: terrorism
Recent Blog Posts
-
የሽብርተኝነት ፖለቲካ እና የአቶ መለስ ቁማር
8 Jan 2012
(ይህ ጽሑፍ አገር ቤት ለሚታተመው “ፍትሕ” ጋዜጣ የተጻፈና የወጣ ነው። የጋዜጣው አዘጋጆችካደረጓቸው አነስተኛ ማስተካከያዎች በቀር በጋዜጣው የወጣው ጽሑፍ ይኼው ነው። ጽሑፉን ለጋዜጣው ከላኩ በኋላ ያገኘኋቸውን መረጃዎችና ማስተካከያዎች እዚህ ተካተዋል።)
ከአንድ የሴናተሮች ቡድን ጋር የተገናኙ አንድ ምንጭ እንደሚሉት አሜሪካ የሁለቱን ጋዜጠኞችም ሆነ የሌሎቹን ኢትዮጵያውያን አቻዎቻቸውን መፈታት የምትፈልገው በኢትዮጵያ ያለው ሥርአት ዴሞክራሲያዊ ይሆናል በሚል እምነት አይደለም። የራሳቸውን ቃል ለመጠቀም “ጋዜጠኞቹ እንዲፈቱ የምንፈልገው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት ውስጥ እንዳትገባ ለመከላከል ነው።” አራት ነጥብ። መለስ ከዚህ በተቃራኒው የዓለም አቀፉን ትኩረት በጨቋኝ ገጽታቸው መሳብ ይፈልጉ ይሆን? ካልፈለጉ ከነአሜሪካ ጋራ ይስማማሉ። ቀሪው የተለመደውን የማርያም መንገድ ፈልጎ ስዊድናውያኑን መፍታት ይሆናል። ኢትዮጵያውያኑ ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬስ? ጥያቄ ነው።
በኦብነግ በኩል ግን ዜናው “በረከተ መርገም” ነው። እዚህ ያነጋገርኳቸው የኦብነግ አባላት ፊት ለፊት ባይናገሩትም በጋዜጠኞቹ መያዝ ድርጅታቸው እንዳልከሰረ ይምናሉ። “በሁሉቱም መንገድ ማትረፋችን አይቀርም ነበር” ነው ሒሳቡ። ጋዜጠኞቹ ተሳክቶላቸው ዘገባቸውን ይዘው ቢወጡ በሆነ መንገድ መለስን የሚያጋልጥ እንደሚሆን ጥርጥር እንዳልነበረው አንድ የኦብነግ የወጣቶች ማኅበር መሪ አጫውቶኛል። ብዙ ተመልካቾች ኦብነግ ጋዜጠኞችን ለመርዳት የሚያነሳሳ ጠንካራና ምክንያታዊ (ሌጂቲሜት) ፍላጎት እንዳለው ይምናሉ። አሁን ጋዜጠኞቹ መያዛቸውም ቢሆን በተዘዋዋሪ የሚናገረው ኦጋዴን ውስጥ “ዓለም ሊሰማው የማይገባ” ነገር መኖሩን ይመስላል።(No Comments)
-
“አሸባሪሪነት!” የነጻነት እዳችን፤ የገዢነት እዳቸው
19 Dec 2011
በመጨረሻው መጨረሻ የነጻነት ፈላጊዎች ጥያቄ ግፍን በማብዛት፣ አዲስ ስም በመለጠፍ፣ በማሰር፣ በመግደል፣ በማሰደድ ተሸንፎ እንደማያውቅ የተረጋገጠ ነው። እነአቶ መለስ ዛሬ ለማስፈራሪያ ጥቂቶቻችንን መረጡ እንጂ የአሸባሪሪነት “ወንጀሉ” ኢትዮጵያ የነጻነት አገር ሆና ለማየት የሚመኙና ባመኑበት መንገድ የሚሠሩት ዜጎች ሁሉ ነው። በዚህ ቀልደኛ ክስ መካታት የነአቶ መለስን ትኩረት የመሳብ ማረጋገጫ ከመሆን አልፎ ተከሳሾቹ ከሌሎች የበለጠ ለኢትዮጵያ የሚያስቡ/የምናስብ ወይም የታገልን ተደርጎ የሚያስቆጥር አይደለም። ወይም እንደዚያ አይነት ስሜት አይሰማኝም። ብዙ ሠርተው በክሱ የተካተቱ እንዳሉ ሁሉ፣ ምንም የሠራን (ያሸበርርን) ሳይመስለን የተካተተንም አለን። እርግጥ ማሸበርር መቻሌን ማወቄ አልከፋኝም። የእነአቶ መለስ ውቃቢ ተከሳሾቹን ከሌሎቹ “ወንጀለኞች” እንዴት አድርጎ እንደሚመርጥ ለማወቅ አልሞከርኩም፤ ትርጉም ስለሌለው። በክሱ ስማችን የተጠቀስነውም ሆንን ያልተጠቀሳችሁት ሚልዮኖች ነጻነትና ዴሞክራሲን በመጠየቁ “ወንጀል”ሁላችንም አንድ ነን፤ “እስክንድር ነጋ ነኝ! አንዱዓለም አራጌ ነኝ (I am Eskinder Nega, I am Andualem Arage. . .) እንደማለት! ለአቶ መለስ “ወንጀል” የሆነው የነጻነት፣ የፍትሕ፣ የእኩልነት ጥያቄ ቀዳሚ መተሳሰሪያችን ነው። በዚያው ምትሐታዊ ባለቅኔ ዮሐንስ ስንኝ ላሳርግ፤
ዘመን ቢያርቃችሁ፣
ስፍራ ቢለያችሁ፣
ዕንባ አጋጠማችሁ።(No Comments)
-
The ‘T’ Word: Terrorists’ of Ethiopia unite!
12 Nov 2011
If you are one of those human beings concerned about matters of freedom, justice or democratic transition in Ethiopia: Beware, terrorism is lurking around your doors! It would come and turn you into a hobgoblin bent on societal destruction. Do you need advice? Stop thinking, then rest assured you will not be a suspect for terrorism.
(No Comments)
-
የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች እሰሩ!
16 Sep 2011
የኦነግ እና የግንቦት 7፣ አልፎም የኦብነግ ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄ ነው። ድርጅቶቹን አሁን በተያዘው ፋሽን “ማዳከም ይቻላል” ተብሎ ታስቦ ይሆናል፤ ጥያቄዎቹን ማጥፋት ግን አይቻልም። የኢሕአዴግን ዘመቻ በተቃራኒው ካየነው ለእነዚህ ድርጅቶች የማያገኙት ድጋፍ እየሰጣቸው እንደሆነ መረዳት አይከብድም። በዚህም ልክ ኢሕአዴግ እንደደርግ በራሱ አንገት ላይ ገመድ እየጠመጠመ ይገኛል። የእነአቶ መለስ ትንቢትና ፍርሐት የሮበርት መርቶንን “ራሱን የሚፈጽም ትንቢት” (self-fulfilling prophesies) ያስታውሰኛል። መርተን እንደሚለው እነዚህ ትንቢቶች የሚደርሱት ዋናዎቹ ባለቤቶች “እውነት ናቸው፤ ይደርሳሉ” ብለው ስለሚያምኑ፤ በዚሁ እምነታቸው ላይ በመመሥረትም ተግባራዊ ምላሽ ስለሚሰጡ ነው። ለኢሕአዴግም በአጠቃላይ ተቃዋሚዎቹ በተለይ ደግሞ እነግንቦት 7 እና እነኦነግ በራሳቸው የሚፈጸሙ ትንቢቶች ሆነውበታል። ኢሕአዴግ እነዚህና ሌሎቹም ቡድኖች የሚያነሱትን የፖለቲካ ጥያቄ በፖለቲካዊ መንገድ ቢፈታ ቡድኖቹ/ጥያቄዎቹ እውነት ሆነው እንደሚያከስሩት፣ የጭቆና ስርአቱ ከስሩ እንደሚናድ ያውቃል። እነአቶ መለስ የዘነጉት ነገር እነዚህ ቡድኖች “በሕገ ወጥ” መንገድ ሊገለብጡዋቸው እንደሚችሉ መተንበይና ለትንቢቱም ምላሽ መስጠት በመጀመራቸው ከኪሳራው ሊያመልጡ የሚችሉበት እድል መዘጋቱን ነው። በሁለቱም በኩል ኢትዮጵያ አምባገነንነትን ከትከሻዋ አሽቀንጥራ ትጥላለች። ትንቢቱ ይደርሳል፤ ቀርቶም አያውቅም። እስከዚያው “የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች” አሸብሩ፣ ክበቡ፣ እሰሩ፣ ግደሉ።
(3 Comments)
-
Melotica: Terrorism Ethiopian Style (አሸባሪ ያልሆናችሁ እጃችሁን አውጡ? መሎቲካ!)
31 Aug 2011
ምን ሆንን? አንድም ማኅበረሰቡ ትልቅ ቀውስ ውስጥ ነው፤ አለዚያም ለወንጀል የተሰጠው የሕግና የፖለቲካ ትርጉም ከመሠረታዊ የሰውል ልጅ መብት፣ ፍላጎትና ባሕርይ ጋራ የሚቃረን ነው። የኢትዮጵያው ቀውስ ምክንያት ወንጀል በዘፈቀደ የሚተረጎም ከመሆኑ የሚመነጭ ነው። ጋዜጠኛ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ የሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አባል፣ የ“ሕገ” ወጥ ፓርቲ አባል፣ ከገዢው ቡድን ጋራ ጥቂት እንኳን የሐሳብ ልዩነት ያለውና ይህ “ወንጀሉ” የተደረሰበት፣ የኢሕአዴግ አባል አልሆንም ያለ፣ አዋጣ የተባለውን ገንዘብ ያላዋጣ፣ ውጭ ሆኖ በተቃውሞ የሚጽፍ ወይም የሚናገር ወዘተ. ሁሉ እንደወንጀል የሚያስከስስ ሆኗል፤ ወይም ብዙዎች እንደዚያ እንዲያምኑ የሚያስገድድ ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህ ምን አይነት ፖለቲካ ነው? ምን አይነት ዴሞክራሲ ነው? ምን አይነት አገር ነው? ፖለቲካው “መሎቲካ” ይባላል (መልቲ ፖለቲከ ወይም የመለስ ፖለቲካ)፤ ዴሞክራሲው “አብዮታዊ ዴሞክራሲ”።
(2 Comments)
Recent Comments