ስጦታ ለአምባገነኖች፣ ከሚወዱት እና ከሚወዳቸው ሕዝባቸው
የነቱኒዚያም ንቅናቄ በተደራጁ የፖለቲካ ቡድኖች/ፓርቲዎች የተመሩ አይደሉም። በአገራቸው መንግስታት ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚዎችም ተስፋ የቆረጡት ዜጎች የለውጥ ፍላጎታቸውን በመግለጽ ለውጡን ለማስጀመር “መደራጀት” አላስፈለጋቸውም። ምክንያቱም የአሮጌውን ስርዓት መጨረሻ ለመጀመር ንቅናቄው የሚፈጥረው ድምጽ በቂ ስለሆነ ነው። የአምባገነኖቹን ግንብ በድምጽ/በጩኸት መናድ ይቻላል። ይህ ድምጽ በመደራጀት ቅርጽ ካልያዘ ግን ሙባረክን በሙባረክ፣ መንግሥቱን በመንግሥቱ፣ መለስን በመለስ የመተካቱ አደጋ ሰፊ ነው። አሁን ሁላችንም በማድነቅ ላይ የምንገኘው የመጨረሻውን መጀመሪያ ነው። የመጀመሪያው መጀመሪያስ ምን ይሆን ይሆን? አሳሳቢ ጥያቄ ነው።…
የ1966ቱን የኢትዮጵያ አብዮት የሚያስታውሰው የነቱኒዚያ ንቅናቄ በአገራችን ሊደገም ይችላል። ልዩ ሁኔታዎች ግን አሉን። ኢሕአዴግ የፈጠረው በብሔር ላይ የተመሠረተ ያለመተማመን ስሜት፣ የበለጠ በሚያስፈራ መልኩ ደግሞ ከመሪ እስከ ተራ ካድሬ ድረስ ሲነዛ የቆየው “የዘር ማጥፋት” መርዘኛ አስተሳሰብ ተግባራዊ መገለጫ ከኖረው ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያውቅ የለም። እነዚህ ሁለት ሁኔታዎች በሚፈጥሩት ስጋት መነሻነት የባሰ ችግር ለማስወገድ ሲሉ የግብጹን ሕዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያ እንዳይደገም የሚፈልጉ ሰዎች ቢኖር አልገረምም። አናንቀው የሚያልፉት ስጋት አይደለም። ኢሕአዴግ በተለይም ቁልፍ መሪዎቹ ይህንን ስሜት በማፋፋም ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ደግሞ የታወቀ ነው። ስለዚህም በኢትዮጵያ የሚፈጠር መሰል ሕዝባዊ ንቅናቄ ይህንን አደጋ አስወግዶ ተቃውሞውን በተነጣጠረ መልኩ በመንግሥት/አስተዳደሩ ላይ ማስተናገድ ካልቻለ ያልታሰበ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል።…
መለስ ከሚወዱትና ከሚወዳቸው ሕዝባቸው ተመሳሳይ የሥራ መልቀቂያ ይጠብቁ ይሆን?

የቱኒዚያው ፕሬዚደንት ቤን አሊ እና ዝነኛ ሚስታቸው ከአገር የወጡት እንዴት ነው? ያልተቀባቸው ንግሥት፣ የቤን አሊ ሚስት ላይላ ትራቤልሲ 45 ሚልዮን ዩሮ ያወጣል የተባለውን ወርቅ እርግጥ ይዛው ወጥታለች? እነዚህ ጥያቄዎች ለታሪክ ካልሆነ ፋይዳቸውን ድንገት የተነጠቁ ይመስል ዳናቸው የጠፋው በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው። ከዚያ ይልቅ የቤን አሊን አገዛዝ የገረሰሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ የአዲስ አብዮት ጅማሬነት የዓለምን ትኩረት ስቧል። በአምባገነኖች አገዛዝ ስር ያሉ ሕዝቦችም ቱኒዚያውያኑን ገና አድንቀው አልወጣላቸውም። ሶሪያንና ሞሮኮን በመሳሰሉት አገሮች የቱኒዚያው መነቃቃት የፈጠራቸውን የተቃውሞ ሰልፎች አስተናግደዋል። ግብጻውያን ግን መነቃቃቱን የምር ወስደውታል። ይህን ጽሑፍ በምከትብበት ወቅት ሙባረክ “የመጨረሻቸው ይሆናል” የተባለውን ንግግራቸውን በቴሌቪዥን ያቀርባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ቀርተዋል። ሒላሪ ክሊንተንን ጨምሮ ስንት ወዳጆቻቸው አስተያየት ሲሰጡ ሙባረክ ራሳቸው ግን ድምጻቸውን አጥፍተዋል።፡ምናልባትም ጽሑፉን ስጨርስ ሙባረክ ከስልጣን ወርደው ይሆናል። አገሪቱን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲገዙ ኖረው ልጃቸውን ተክተው ለመሰናበት ሲዘጋጁ የነበሩት የ83 ዓመት አዛውንት አጭር የስንብት አማራጭ ቀርቦላቸዋል፤ ከሚወዳቸውና ከሚወዱት ሕዝባቸው።
የዛሬን አያድርገውና በግብጽ ለ30 ዓመታት የቆየው የሙባረክ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተቃውሞ ሰልፍን የሚታገስ አልነበረም። እርሱም አልበቃ ብሏቸው ትናንት የሰዓት እላፊ አውጀው ነበር። ኢንተርኔት እና ሞባይል ስልክም አዘግተዋል። ቁም ነገር ግን በሕግ ከለላ፣ በጉልበት አፈና ሁሉንም ነገር ሰጥ ማረግ የማይቻልበት ጊዜና ሁኔታ ሳያስቡት ደርሷል። እስከ ትናንት ድረስ ሙባረክ ይህ ሰዓታቸው መድረሱን አልተረዱም። አሁን የቀረ ነገረ ቢኖር ወታደሩ የት እንደሚቆም በግልጽ አለመታወቁ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ረጅም ጊዜ የሚፈጅ አይደለም። ወታደሩ ከሙባረክ ጋር መቆምን ቢመርጥ እንኳን ግን አዲሱ የግብጽ አብዮት አይቆምም፤ ልዩነቱ የለውጡ ፍጥነትና ይዘት ብቻ ነው።
በቱኒዚያ እና በግብጽ የሆነው በአገራቸው እንዲደገም የሚመኙ ብዙ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ለማረጋገጥ ጥናት ማካሄድ አያስፈልግም። ባለፉት ሁለት ቀናት የአዲስ አበባ ወዳጆቼ ቢቢሲና አልጀራ ላይ ተተክለው እንደሚያመሹ ሲያጫውቱኝ ነበር፤ የፌስቡኩ ልውውጥም ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው። ነገር ግን ይህን መሰል ሕዝባዊ ንቅናቄዎች የተፈጠሩበትን ምክንያት ከውጤታቸው ለይቶ ማየት ምኞታችንን ትርጉም ያለው ያደርግልናል።
የመጨረሻው መጀመሪያ- የመጀመሪያው መጀመሪያ
የቱኒዚያና የግብጽ ሕዝባዊ አመጾች የመንግሥት ለውጥ ማምጣታቸው የሚያጠራጥር አይመስልም። አንዳች አይነት የመንግሥት ወይም የአመራር ለውጥ ይኖራል። የሕዝባዊ ተቃውሞው አባላት የየራሳቸው የግልም የጋራም ሕጋዊ ጥያቄዎች አሏቸው፤ ይኖሯቸዋል። መንግሥታቱና መሪዎቻቸውን መቃወማቸውም ተገቢ ነው። ይህ ማለት ግን ለተቃውሞ የወጣው እያንዳንዱ ሰው ከመፈክር አልፎ ተቃውሞው ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ይፈጥራል ማለት አይደለም። ይህ ደግሞ መሰል አብዮቶችን ተከትለው በመጡ ታሪኮች የታየ ነው።
የነቱኒዚያም ንቅናቄ በተደራጁ የፖለቲካ ቡድኖች/ፓርቲዎች የተመሩ አይደሉም። በአገራቸው መንግስታት ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚዎችም ተስፋ የቆረጡት ዜጎች የለውጥ ፍላጎታቸውን በመግለጽ ለውጡን ለማስጀመር “መደራጀት” አላስፈለጋቸውም። ምክንያቱም የአሮጌውን ስርዓት መጨረሻ ለመጀመር ንቅናቄው የሚፈጥረው ድምጽ በቂ ስለሆነ ነው። የአምባገነኖቹን ግንብ በድምጽ/በጩኸት መናድ ይቻላል። ይህ ድምጽ በመደራጀት ቅርጽ ካልያዘ ግን ሙባረክን በሙባረክ፣ መንግሥቱን በመንግሥቱ፣ መለስን በመለስ የመተካቱ አደጋ ሰፊ ነው። አሁን ሁላችንም በማድነቅ ላይ የምንገኘው የመጨረሻውን መጀመሪያ ነው። የመጀመሪያው መጀመሪያስ ምን ይሆን ይሆን? አሳሳቢ ጥያቄ ነው።
ቱኒዚያ-ግብጽ-ኢትዮጵያ?
ከፖለቲካ አቋሞች ወይም ከኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች የሚመነጩ ፍላጎቶችን ወደ ጎን ብለን፣ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ብንመረምር ለአቶ መለስና ጓዶቻቸው ከሚወዱትና ከሚወዳቸው ሕዛባቸው የሥራ መለቅቀቂያ የሚላክበት ዕድል ሰፊ መሆኑን መናገር ይቻላል። በመሠረቱ በቤን አሊ፣ በሆስኒ ሙባረክ እና በመለስ ዜናዊ መካከል የዘይቤ እንጂ የግብ እና የስልት ልዩነት የለም። ሦስቱም ዴሞክራሲያዊ ነን ይላሉ፣ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገባቸውን ይለፍፋሉ፣ ተቃዋሚዎቻቸውን ያስራሉ ይገድላሉ፣ በምእራብ ወዳጆቻቸው የመረጋጋት ምንጭ ተደርገው ይቆጠራሉ፣ ቤተሰቦቻቸው፣ ዘመዶቻቸውና የቅርብ ተላላኪዎቻቸው ኢኮኖሚውንና ፖለቲካውን የመዘወር ልዩ መብት ያገኛሉ፣ የስለላ እና የወታደሩን ቁልፍ ቦታዎች በራሳቸው ሰዎች ያስይዛሉ።
ኢትዮጵያውያን የሚጋፈጡት ጭቆናም ይሁን የኑሮ ሸክም ከቱኒዚያም ይሁን ከግብጻውያን የባሰ ነው። ስለዚህም ተመሳሳይ የሕዝባዊ ተቃውሞ በኢትዮጵያ ቢፈጠር የሚገርም አይደለም። ይህን በመፍራት መንግሥት በየአቅጣቸው እየወሰደው የሚገኘው እርምጃም ከማያገግመው የኢኮኖሚ ቁስል ጋራ ተዳምሮ ብሶቱን እንደሚያብሰው ለመረዳት የማይፈቅዱት የስርአቱ ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው። (አሁን ሙባረክ በቴሌቪዥን ቀርበው እየተናገሩ ነው፤ በግብጽ ሰዓት አቆጣጠር እኩለ ሌሊት አልፏል። ለመሆኑ ምን ይላሉ? “ብሶታችሁን እየተከታተልኩ ነው፤ ነገ ጠዋት አዲስ መንግሥት እመሰርታለሁ፤ ከዚያም ችግሮቹ ሁሉ ይወገዳሉ።” ድንገት በፈጣሪ ተልከው የወረዱ መልአክ አይመስሉም? ቤን አሊም እንዲህ ብለው ነበር፤ መንግሥቱም እንዲህ ብለው ነበር። ሙባረክ ሂድ፣ ሙባረክ ውረድ!)
የ1966ቱን የኢትዮጵያ አብዮት የሚያስታውሰው የነቱኒዚያ ንቅናቄ በአገራችን ሊደገም ይችላል። ልዩ ሁኔታዎች ግን አሉን። ኢሕአዴግ የፈጠረው በብሔር ላይ የተመሠረተ ያለመተማመን ስሜት፣ የበለጠ በሚያስፈራ መልኩ ደግሞ ከመሪ እስከ ተራ ካድሬ ድረስ ሲነዛ የቆየው “የዘር ማጥፋት” መርዘኛ አስተሳሰብ ተግባራዊ መገለጫ ከኖረው ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያውቅ የለም። እነዚህ ሁለት ሁኔታዎች በሚፈጥሩት ስጋት መነሻነት የባሰ ችግር ለማስወገድ ሲሉ የግብጹን ሕዝባዊ አመጽ በኢትዮጵያ እንዳይደገም የሚፈልጉ ሰዎች ቢኖር አልገረምም። አናንቀው የሚያልፉት ስጋት አይደለም። ኢሕአዴግ በተለይም ቁልፍ መሪዎቹ ይህንን ስሜት በማፋፋም ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ደግሞ የታወቀ ነው። ስለዚህም በኢትዮጵያ የሚፈጠር መሰል ሕዝባዊ ንቅናቄ ይህንን አደጋ አስወግዶ ተቃውሞውን በተነጣጠረ መልኩ በመንግሥት/አስተዳደሩ ላይ ማስተናገድ ካልቻለ ያልታሰበ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል።
የቱኒዚያና የግብጽ አብዮቶች በምእራባውያን እገዛ የተካሄዱ አይደሉም። ውስጣዊ ሁኔታ የፈጠራቸውና ያፈነዳቸው ናቸው። ስለዚህም ለክስም የሚያመቹ አልሆኑም፤ “የውጭ ኀይሎች፣ ጸረ ኢትዮጵያ ኀይሎች፣ ጸረ…” የሚል ማጭበርበሪያ ሙሾ ለማውረድ እንኳን የሚመቹ አልሆኑም። ሌላው አስተዛዛቢ ልዩነት በሰልፈኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ ነው። በግብጽ ዛሬ የነበረው ሁኔታ መጀመሪያ ፍጽም ሰላማዊ ቢሆንም እየቆየ ግን ከፖሊስ ጋራ በተፈጠረ ግጭት ግርግርና ውድመትን ያስከተለ ጭምር ሆኗል። ፖሊስ የወሰደው እርምጃ ግን የእኛ መንግስት በ1997/98 ከወሰደው ጋራ ፈጽሞ የሚነጻጸር አይደለም። ሆኖም በዚህ መሰሉ ንቅናቄ የሚከፈለው ዋጋ በአንዱ ወገን ቁጥጥር ስር ያለ አይደለም።
በኢሕአዴግ አያያዝ ኢትዮጵያ ከዚህ የተለየ የለውጥና የመሻሻል አማራጭ አታገኝ ይሆናል። አለዚያም ከራሱ ከኢሕአዴግ ውስጥ የሚመጣ የለውጥ ንቅናቄ (ሪፎርም) መጠበቅን ይጠይቃል። ይህ ደግሞ ከሃይማኖት ያልተናነሰ እምነትንና ተስፈኝነትን የግድ ይላል።
ተራህን ተቆጣ
የሰሞኑ የሰሜን አፍሪካ አብዮት ተራ፣ ያልተደራጁ ነገር ግን የሕይወታቸው ባለቤት መሆን የሚፈልጉ ዜጎች አምባገነኖችን ሲያንቀጠቅጡ አሳይቶናል። ሐሳብን የመግለጽ፣ የመደራጀት፣ የመሥራት፣ የተረጋጋ ሕይወት የመምራት ወዘተ መብቶቹን የተነጠቀ ሕዝብ ለጊዜው በእለት ሕይወቱ የተጠመደ ይመስላል፤ ቁጣው እየተጠራቀመ መሆኑን የሚረዱት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው። የሰሞኑ አብዮት አንድ ውብ ነገርም ይህ ቁጣ ነው።
ቁጣው ግን የተሟላ ሆኖ አላገኘሁትም። ማኅበረሰቦቻችንን አፍነው የያዙት መንግሥታት ብቻ አይደሉም፤ በብዙ መልኩ አፋኝ የሆነ ባህል ሰለባዎችም ነን። ለአምባገነኖች የሚመቹ ተገዢዎች ከሚያደርጉን ምክንያቶች የተወሰኑት ከባህሎቻችን የሚቀዱ ናቸው። ጊዜው ሲደርስ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የባህል ለውጥም እንደሚያስፈልግ የሰሞኑ የተቃውሞ እንቅስቃሴ አላስታወሰም። ወይም በመንግሥት ለውጥ ሁሉም ነገር እንደሚፈታ ተስፋ አድርጎ ይሆናል፤ ተሳስቷል።
ሳምንቱን ለግብጽና ለቱኒዚያ ወገኖችችን መታሰቢያ አድርገነዋል! መለስ ከሚወዱትና ከሚወዳቸው ሕዝባቸው ተመሳሳይ የሥራ መልቀቂያ ይጠብቁ ይሆን? ማን ጠብቆ ያውቃል!
In ethiopian context,the situation is unprecented but the internal tension and the anger within the people have been soared more than any time.
The same question was being risen during 2005 election regarding the peoples unity and the people have shown same although the current situation is a bit different than 2005.
It should be well calculated before such a move gets implemented.
It needs leader in the opposition camp or public figures and commitment for change until the end irrespective of blood sheds or related problems to come.
This tyranny government used to use ethnic as a jocker to the end game.
The people should be aware and speculate all the possible challenges and I dont think it is not possible.
It is better to die fighting for freedom and remove this mafia group than living with the current scenario.
‘KEFREHAT KOFEN KALEWETAN there wil not be change and this is in the hands of our generation.
Thanks for sharing
Good topic, well structured sentences, congratulations!!
But what is the point?
Is it our culture is not conducive for democratic change and
the danger of the ethnic division and rivalry is great, and
our hopes might not be realized
so we should not demand our god given rights?
so my friend you are still trying to be a by stander who will be satisfied in your critic of the status quo and the opposition.
Do you consider yourself part of the democratic movement? To me you should be part of the movement but not a member of any organization. I think you are hanging on to your initial objective of being in the middle.
Dear Tufa,
Thank you for commenting. However, it looks you are in some kind of imaginary dialogue. In case you want to provoke further discussion, you missed the point or have a serious problem of understanding Amharic. Did I say that we shouldn’t demand our rights for any reason?
You put yourself in a high moral ground to ask me where do I stand. Are you actually demonstrating in front of Meles’ office when you write this comment? I don’t have to get your blessing and advice to be part of “the democratic movement.” You also lack an elementary understanding of middle ground politics for which you try to accuse me. What I sometimes called for in ideological debates is “middle ground”, not “being in the middle.” FYI, it doesn’t mean that I don’t have positions, ideological or otherwise, but want to avoid divisive interpretations in the face of imminent disaster. Democracy is about understanding, not blind positions and impositions. For the record, does your “democratic movement” allow a person to be a by standard? If not, it is inherently dictatorial movement but by name. Get off your high horse.
yadergeln
The article is good. especially i love the last sentence.
To express my view, Ethiopia and ethiopians are not ready for such kind of uprising. It is not that we dont have reason to do so. also not that the people are not patriotic but our situations wont allow us to come up with better results. In a country where there are groups like OLF who have only negative plans to the country and people, there is no way. Tunisians dont have groups like OLF to worry. Neither egyptians did. They have only one purpose which is a regime change with in their country. What was OLF people saying during the last ethiopian uprising? They were saying this is a fight between tigrians and amhara, it dont belong to us. Imagine, they will do it any time because these special group of people can not change.
Dear Mesfin,
Your tirade as a response to my input reflects to your thin skin not to mE. As a person in public space I would have thought you would take criticism, fair or unfair, well . Alas, you are not there but I know you can get there.
I must admit I do not understand what you call “middle ground politics” in the current Ethiopian politics. I suspect you are not talking about Lidetu’s thrid way or is it some other political philosophy? I for sure will benefit if you can explain what you mean by middle ground politics.
For me the question in Ethiopia is about liberty, democracy, and equality. I do not see a middle ground on these questions. You either support these universal values or you don’t.
I read your piece because I like your and Abiye’s (I hope abiye is well. it has been awhile since he wrote a piece) pieces. So I still think your contributions are useful and sometimes misguided as far as I am concerned.
I think your call for change in our culture, which I agree with, is timely and you might benefit from it.
Ayizoh!!!!
@Tufa
I think you made a very good point and I totally failed to see why Mesfin reacted so angrily. There is definitely no middle ground on liberty, democracy, and equality. You are either a democrat or you are not. I think its as simple as that. In any case I think Mesfin’s article is very timely although Ethiopia is not yet ready for change. The question should have been what could be done to fast forward the change in Ethiopia which is already long overdue.