ጥያቄው ከስኳር እና ከዋልድባ መምረጥ አይደለም
ቁሳዊ ልማትን የማፋጠን እና ታሪካዊ/መንፈሳዊ እሴቶችን የመጠበቅ ጉዳይ ሁልጊዜም አብረውና ተስማምተው ላይሄዱ ይችላሉ። አንዱን ለማሳደግ ሌላውን ዋጋ ማስከፈል የሚያስፈልግበት አጋጣሚ የመስተጋብሩ ቋሚ መገለጫ ይመስላል። ጥያቄውን በአንድ ነጠላ የልማት ፕሮጀክት አንጻር መመልከት ይቻላል። “ፕሮጀክቱ እገሌ የተባለውን ታሪካዊና መንፈሳዊ እሴት ያለው ቦታ/ሕንጻ… ይነካዋል አይነካውም? ከነካው ምን ያህል? ወዘተ” በሚሉ ጥያቄዎች ዙሪያ መነጋገርም መደራደርም ተገቢ ነው። ከዚህ መሰሉ ዝርዝር ንግግር በፊት ግን በመጀመሪያ ስለ “ልማቱ” እና ሰለ “እሴቶቻችን” ምንነትና ፋይዳ ዘርዘር አድርጎ መነጋገር ይገባን ነበር። ይህ በተለያዩ ወገኖች የሚሰጠው የተለያየ ሚዛን ቢያንስ ለሚቀጥሉት 100 ዓመታት በሚካሔዱ የልማት ክንውኖች መላልሶ እንደሚገጥመን አልጠራጠርም። ለዚህም ነው በቅድሚያ በሐልዮት ደረጃ ጉዳዩን ማብላላት አስፈላጊ ነው የምለው። የቁሳዊ ልማታችን እና የባህል ልማታችን ምንና ምን ናቸው?
Read more


Recent Comments