"; _gaq.push(['_trackPageview']);(function() { var ga = document.createElement('script'); ga.type = 'text/javascript'; ga.async = true; ga.src = ('https:' == document.location.protocol ? 'https://ssl' : 'http://www') + '.google-analytics.com/ga.js'; var s = document.getElementsByTagName('script')[0]; s.parentNode.insertBefore(ga, s); })();

የአቶ በረከት “የኢኮኖሚ ዕድገት እያጣጣመ ያለ” ሕዝብ እና አብዮት አዳባባይ

የመንግስት ጉዳዮች ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን ዛሬም እንደወትሮው ብልሀት እና መረጃ ያልጎበኘውን ዲስኩር ከማሰማት አልሰነፉም፡፡ በቱኒዚያ እና በግብፅ አደባባዮች የተስተዋለውን የሕዝብ አብዮት መነሾ ከኢትዮጵያ ኹኔታ ጋር በማነጻጸር የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሁለቱ አገሮች ሕዝቦች “በተሻለ የኢኮኖሚ እድገትና ሽግግርን እያጣጣመ ነገንም በተስፋ እየጠበቀ መኾኑን” ሲገልጹ የተለመደው የአቶ በረከት ማስተዋል የራቀው ድፍረት አብሯቸው ነበር፡፡ ለአቶ በረከት አሁን በሰሜን [...]

የመንግስት ጉዳዮች ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን ዛሬም እንደወትሮው ብልሀት እና መረጃ ያልጎበኘውን ዲስኩር ከማሰማት አልሰነፉም፡፡ በቱኒዚያ እና በግብፅ አደባባዮች የተስተዋለውን የሕዝብ አብዮት መነሾ ከኢትዮጵያ ኹኔታ ጋር በማነጻጸር የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሁለቱ አገሮች ሕዝቦች “በተሻለ የኢኮኖሚ እድገትና ሽግግርን እያጣጣመ ነገንም በተስፋ እየጠበቀ መኾኑን” ሲገልጹ የተለመደው የአቶ በረከት ማስተዋል የራቀው ድፍረት አብሯቸው ነበር፡፡
ለአቶ በረከት አሁን በሰሜን አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ አገራት እየተቀጣጠለ የመጣው የሕዝብ አመጽ የሚጠበቅ ነው፡፡ ነገር ግን የእርሳቸው ኢትዮጵያ “ተጨባጭ ዴሞክራሲን የተላበሰች፣ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የተከበረባት እንዲሁም ሕዝቡ በነጻ ምርጫ የፈለገውን የሚሾምባት” የምድር ተምሳሌት ናት፡፡ እናም የሕዝብ ቁጣ “ሲያልፍም አይነካንም” አይነት መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ንግግራቸውን ከቁም ነገር መውሰዱ ለምሁራዊ ወግ እንዲበቃ አያደርገውም፡፡ ይሁንና የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ኾነ ብለውም ይኹን በቸልተኝነት ለኻያ ዓመታት ለዘለቀው ጉዟቸው የሚሰጡት ግምት ከእውነት መራቁ የሚመሩትን ሕዝብ እና አመራራቸው ያመጣውን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ኹነቶች ለመመዘን ያላቸው አቅም እጅጉን ዝቅ ያለ መኾኑን አመላካች ነው፡፡
የምናውቃት የአቶ በረከት ኢትዮጵያ አንድ ነች፡፡ ከቱኒዚያ እና ከግብፅ ሕዝቦች ጋራ የሚያመሳስላት በአምባገነኖች መዳፍ ሥር ለዓመታት መዳከሯ እንጂ በኢኮኖሚ መሥፈርቶች ለማወዳደር የሚያስችል ቅርርብ እንደሌለም እናውቃለን፡፡ በቀላሉ እንኳን በቅርቡ ይፋ የኾነውን የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የፈርጀ ብዙ ድህነት መለኪያ ብንወስድ 90 በመቶ ያህሉ ዜጎቿ “ድኻ” የኾኑባት አገር ከአስር በመቶ ዝቅ ያለ የድኽነት ምጣኔ ካስመዘገቡት ሁለቱ አገራት ጋር ማወዳደሩ የሚያስኬድ አይደለም፡፡ አቶ በረከት “ተስፋ የቆረጠ” ያሉት ሕዝብ ከቱኒዚያ እና ከግብፅ ይልቅ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኝም ግልጽ ነው፡፡
በመካከለኛ የገቢ ሰንጠረዠ የሰፈሩት የሁለቱ አገሮች ሕዝቦች የኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ዛሬ አንድ ኢትዮጵያዊ ከሚጠይቀው የሕልውና ጉዳይ ጋር ሲነጻጸር የሰማይና የምድር ያህል ርቀት አለው፡፡ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ የእለት ጉርስን መሸፈን እንደ ስኬት የሚመለከት ነው፡፡ ከእለት እለት እየባሰበት የሚመጣ የኑሮ ውድነት፣ በአመት 20 በመቶ ምጣኔ የሚደርስ ሥራ አጥነት እና በነጻነት ተንቀሳቅሶ የመስራት መብት አለመኖር ዋነኛ የፖለቲካ ኢኮኖሚው መገለጫ ናቸው፡፡ ዜጎች በእኩል ተወዳድረው ሊያገኟቸው የሚገቡ የሥራ ዕድሎች ሙሉ ለሙሉ የተዘጉና የገዢው ፓርቲ ተዋናይ መኾን ብቻውን ዋነኛ መሥፈርት የኾነባት አገር ፤ ሌሎች አገራት ከሚያስፈልጋቸው አብዮት በብዙ እጅ የላቀ አብዮት እንደሚያስፈልጋት ደጋግሞ መናገር ይቻላል።

“መለስኖሚክስ” እና “የፍቅር አዲስ ኢኮኖሚ”

በግልጥ በሚታይ መልኩ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከ97 ምርጫ በኋላ “ልማታዊ መንግስት” የሚል ጽንሰ ሐሳብ ወደ ፖለቲካቸው ሲያስገቡ ኢኮኖሚውን ለማገዝ አዲስ መላ አስከትለው ነበር፡፡ ኢኮኖሚውን ለማገዝ ያመጡት መላ ከምርታማነት ጋር በቀጥታ የተያያዘ አልነበረም፡፡ ይልቁንም ምርታማነት ያልነካቸውን “የምርታማነት ወሬ” በብዛት እና እስኪያሰለች ለሕዝቡ ማድረስ፡፡ ከምንም ተነስቶ የሚያሰግር የኢኮኖሚ መረጃ ይበተናል፡፡ በየትኛውም ጊዜ ቢኾን ከመንግስት የሚወጡ መረጃዎች ታሽተውና ለፖለቲካ ፍጆታ በሚውል መልኩ ተሰልተው ይለቀቃሉ፡፡ ስለዚህም ባለፉት ስድስት አመታት ኑሮ አሽቆለቆለም፤ ተመነደገ የቁጥር መረጃዎች እንዳሰገሩ አሉ፡፡
ይህ የአቶ መለስ “ብልሃት” ማለትም የተሳሳተ የኢኮኖሚ ፖሊሲን በሚፈበረኩ አዎንታዊ መረጃዎች “ማከም” ግን የዓለም አቀፍ ተቋማትን የሚደናግረውን ያህል ከመረጃዎቹ ይልቅ ኢኮኖሚውን ለሚኖረው ማኀበረሰብ የሚያደናግሩ አልነበሩም፡፡ ኑሮን ሲኖረው መረጃዎቹን ሳይሆን ምርቱን የሚናፍቀው ሕዝብ የመለስ ኢኮኖሚን ፉርሽ መኾኑን ይናገራል፡፡
ከወራት በፊት ድምጻዊት ፍቅር አዲስ ነቃዓጥበብ የብር ዶላርን የመመንዘር አቅም መውደቅን ተከትሎ የአንድ ብር ቄጤማ ገበያው ለማዘጋጀት ፍቃደኛ አለመኾኑን ተገንዝባ የሰነዘረችው ጥያቄ በሚያሰግሩ ምትሃት ቁጥሮች “ሐልዮት” የቆመውን “የመለስ ኢኮኖሚ” ገመና የሚገልጥ ነበር፡፡ በወቅቱ ፍቅር አዲስ “ዶላር እና ቄጤማ ምን አገናኛቸው?” ስትል ነበር የጠየቀችው፡፡ ይህ “የፍቅር አዲስ ኢኮኖሚ” የተንዛዛ እና የሚያምታታ ሕልዮት የለውም፤ ነገር ግን በተምታቱ የኢኮኖሚ መረጃዎች የተውሸለሸለው ኢኮኖሚ አቶ መለስ እና አቶ በረከት ከሚያስቡት በላቀ መልኩ ምን ያህል ማህበረሰቡ እየተገነዘበው እንዳለ ነው የሚያሳየው፡፡
ሰሞነኛውም የአቶ በረከት “የኢኮኖሚ ዕድገትን እያጣጣመ ያለ” የተባለ ሕዝብ የአቶ መለስንም ኾነ የፍቅር አዲስ ኢኮኖሚ ያውቃቸዋል፡፡ የመለስ ኢኮኖሚ “በምትሃት ቁጥሮች” ነገር ግን የፍቅር አዲስ ኢኮኖሚ ደግሞ በሚጨበጥ የገበያ መስተጋብር እንደሚገለጥ ያውቀዋል፡፡ ይህም ስሌት ነው ከአብዮት አደባባይ እና ከጣህሪር አደባባይ የትኛው እንደሚርቅ በግልጽ የሚያሳየው፡፡

አቶ በረከት የዘነጉት ነገር . . .?

አቶ በረከት ያነሷቸውን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ወደ ጎን ብንላቸው ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ብቻቸውን አብዮት አደባባይን የበለጠ ቅርብ እና የሚናፈቅ ያደርጉታል፡፡ ዋጋ እየተተመነለት ለኪሳራ የሚዳረገው ነጋዴ፣ ክፍያው እና ድካሙ የማይመጣጠንለት ምንደኛ፣ በምርጥ ዘር እና በማዳበሪ እዳ ኑሮው የተጎሳቆለበት አርሶ አደር፣ ነገ የስራ ዋስትና የሌለው ተማሪ እና ሌሎች የማህበረሰቡ አካላት የግብጽ ዜጎች ጣህሪርን ለነጻነት ከሚናፈቁት በላይ አብዮት አደባባይን ይናፍቃሉ፡፡
አቶ በረከት ግን ይህ የነጻነት ናፍቆት አልገባቸውም ወይም እንዲገባቸው አልፈልጉም፡፡ ማህበረሰቡም እርሳቸው ከሚያስቡት በላቀ የኢኮኖሚውን መረጃ ከኑሮው ምዕራፍ እየገለጠ እንደሚያነብ ዘንግተውታል፡፡ የእርሳቸው መዘንጋት ግን አብዮት አደባባይን ሩቅ፣ ጣህሪርን ግን ቅርብ አያደርግም፡፡

21 Responses to “የአቶ በረከት “የኢኮኖሚ ዕድገት እያጣጣመ ያለ” ሕዝብ እና አብዮት አዳባባይ”

  1. “……የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሁለቱ አገሮች ሕዝቦች “በተሻለ የኢኮኖሚ እድገትና ሽግግርን እያጣጣመ ነገንም በተስፋ እየጠበቀ መኾኑን” Bereket is mocking the plight of the Ethiopian people as usual.

    We must understand that the Woyanes know the reality more than we do. Some of the economic crisis being experience by the populace are well planned strategies. They simply utter empty words to make appearances. They are counting only on their brute force to squash any dissent.

  2. Very timely,simple,understandable and impressive comment.
    Cheers!!!

  3. አብዮት አደባባይ የሚለው ስም ለካ ትንቢት ኖሯል…ትንቢቱን እናቅርበው ወገኖቼ!!

  4. Dogbert: “Reality is always controlled by the people who are most insane.”
    Bereket is Insane !

  5. The stupid and racist woyane will have no shame in preaching Ethiopians to the extent that we are the richest of the richest. why not? they have good tirgian supporters like aiga who spread the propaganda.

  6. Miskin Addisneger simun yemaiwokil
    there is not any new thing you say
    this has been said by tomar seifenebelbal, urji abay and nation newspapers
    EPRDF goes with VICTORY as usual while you will remain whining

  7. እብሪት በራሱ መጥፎ ጠባይ ነው አለማወቅ(አንዳንዶች ድንቁርና የበለጠ ገላጭ ነው ይላሉ) ሲታክልበት ግን አደገኛነቱ የከፋ ይሆናል። አቶ በረከትን የተጠናወተው ይሄ ለመሆኑ በየጊዜው
    የሚሰጣቸውን መግለጫዎች ዋቢ ማድረግ ይቻላል። የቱኒሲያንና የግብፅን ሁኔታ አስመልክቶ
    የሰጠው አስተያየት ከዚህ ቀደም ከሰጣቸው ቀፎ አስተያየቶች የተለየ አለመሆኑ የሚያሳየው ቢኖር ‘ሰው ተስህተቱ ይማራል’ የሚለው አባባል ለሁሉ ሰው እንደማየሰራ ይመስለኛል።

  8. አይ አቶ በረከት፥

    በድርቅ የተሰቃየነው ያለፉት 40ዓመታት አልበቃ ብሎን ይኸው ደግሞ በኢሕአዴግ ድርቅና ለመሰቃየት ተፈርዶብን ድፍን 20ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ እናንተ ጀለሳሞቹ ገና ከመፈጠራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ሦስት ጊዜ ይበላል ብላችሁን ነበር፡፡ ጽድቁ በቀረ ሆነና ነገሩ ረሃቡን የለመድነው ቢሆንም ሥራ አጥነቱን፣ የገንዘብ ዋጋ ማሽቆልቆልን፣ ዘረኝነተን፣ በሥልጣን ፈረስ ላይ ሙጭጭ ማለትን ግን መታገስ አቃተን፡፡ 97 ላይ ለዚሁ መልስ ለመስጠት የሚችል የሕዝብ አቋም መኖሩ የተረጋገጠ ቢሆንም ረግጦ መግዛትና የአፈና ተቋማትን አገልግሎት እንደ ድር አወሳስቦ የሚጠቀመው መንግሥት በግፍ አጨንግፎታል፡፡

    ከአረብ አገራት በፊት ኢትዮጵያውያን ይህንኑ ፍላጎት አሳይተው ነበር ተዘነጋ መሰለኝ፡፡

    ለማንኛውም አቶ በረከት አሁን ጊዜው የምጥ ሆኗልና፤ አብዮታዊ ዲሞክራሲ በቀደደው …. አትናገር ዝም በል፡፡

  9. በርግጥ የኢኮኖሚ እድገት በ4ኪሎና በቢተዘመዱማሕበር አባላት መታየቱ እሙን ነው ። የዚህ አይነቱ የኢኮኖሚ እድገት ለቱኒዝያ ፣ ለግብፅና የነጻነት ጥይቂ በተፋፋመባቸ ሀገሮች እንዳልበጀ የነ በረከት ዲሽ ይህን አይነት ዚና እንደማያስገባ በ20አመት ልምድ አውቀናል ።
    የእትዮጵያ ህዝብ ግን ጊዚውን እንደሊሎቹ ሀገሮች ይጠብቃል ።
    ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

  10. Ato Berket, try to make good impression.
    As a key EPRDF leader you better have a clear look inwards at the Ethiopian people and also outwards at what others have been doing including our neighbor in North Africa.

    I am not at your wavelength to deny the scale of security threat and danger of any unexpected uprising at any moment at any condition and any where in Ethiopia. You better swallow this gross fact and look for its solution in advance

  11. I don’t think Bereket is mocking or joking. These guys, Bereket and his boss, are ignorant and arrogant beyond belief. They live among their own likes and there is no way to test or evaluate their ‘wisdom’. No body challenge them because they do not allow it.

  12. ባብዛኛው፣ በልመናና፣ የሀያል መንግስት መልካም ሎሌ በመሆን በሚመጣ የውጭ ድጎማ የሚንቀሳቀስ ኢኮኖሚን የተሸከመ መንግስት፣ አንዴ አምስት ሚሊዮን ሌላ ጊዜ ሶስት ሚሊዮን ዜጎቼ ተራቡ ኡኡ! ድረሱልኝ እያለ ላለፉት ሀያ አመታት ያለም ለጋሾችን መከራ ያበላ መንግስት፣ ባለስልጣን እንዲህ “የተሻለ ኢኮኖሚ…” እያለ ሲቀላምድ ማድመጥ በጣም አሳዛኝ ነው፤ የግለሰቡንም ማንነት በቅጡ ያሳየናል።
    እብሪት በራሱ መጥፎ ጠባይ ነው፣ አለማወቅ(አንዳንዶች ድንቁርና የበለጠ ገላጭ ነው ይላሉ) ሲታክልበት ግን አደገኛነቱ የከፋ ይሆናል። አቶ በረከትን የተጠናወተው ይሄ ለመሆኑ በየጊዜው
    የሚሰጣቸውን መግለጫዎች ዋቢ ማድረግ ይቻላል። የቱኒሲያንና የግብፅን ሁኔታ አስመልክቶ
    የሰጠው አስተያየት ከዚህ ቀደም ከሰጣቸው ቀፎ አስተያየቶች የተለየ አለመሆኑ የሚያሳየው ቢኖር ‘ሰው ተስህተቱ ይማራል’ የሚለው አባባል ለሁሉ ሰው እንደማይሰራ ነው።

  13. hi dere addis neger.basalfnaw worat ymetakerbut merja betam kewnat yerk new.bahwenu seat b agerachen tyto ymyetwek edget eysmezagben balenbet sat edndzh yal wora bdtakerbu betam arif naw.

  14. Berket is one of the idiot person I have ever known, he was trying to mock in Ethiopian people, we all know better that he was trying to save his stink government, i believe it is to late to give a bragging speech. You will face ICC or Ethiopian court for the crime you committed.

  15. the more you engage in name calling, the more I love Bereket and the Ethiopian government. Long live EPRDF and Meles!!

    • Who cares if you love TPLF. That is your choice. It also shows who you are. It is your right to love racist ignorant idiots like Bereket and Melese. You think we care. That is your problem

    • dinkem digaf ete!

  16. I can understand why people in this blog have distaste to Bereket. Because he is so capable to dismantel any sabotage they have been looking for. His message is so powerful and coherent. Rather I would have been surprised if Addis Neger posted any positive thing about Bereket.

    • Yonas
      It takes one to know one. Bereket and the group he represents do not have any argument except brute force. Bereket and his masters will come down. It is a matter of time.

  17. what in the world do you expect from the propaganda minister of an authoritarian state.Remember what the info ministry in Iraq was saying when the Americans were on the door steps of Baghdad. He was saying that the Iraqi army is in control. Also Mengistu’s information ministry was saying the army is holding strong, while rebel forces were surrounding Addis. If there is anything we’ve learned so far it is that informations ministries are a place where lies are generated. Bereket is just doing his job, which is to lei. That is what you have to do to be in that position. doesn’t just make you wanna raise kids in this world.

  18. dibaba regasa 3 March 2011 at 4:34 am

    You guys keep writing about revolution and the eprdf keeps building the country that you ruined for decades.adis neger,almariam,eskindir nega,birhanu nega and shabia are just crack heads and the eprdf is so lucky that he has egg head enemies everywhere.So far the color revolutionaries have written strategies on how to topple the eprdf from their comfortable villas in the US.WOW!You want to fight with big macs?You should be awarded a grammy in the best comedians of the year catagory award.The dogs bark but the caravan passes.In five years time i bet you will still cry while ethiopia develops.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

Bad Behavior has blocked 433 access attempts in the last 7 days.