የጀሚላ መዳፎች
(አሮን ፀሐዬ) ፀጥ ረጭ ያለ ሰፈር፤ በግራ እና በቀኝ የተሰደሩት ቪላ ቤቶች ግዙፍ የጋራ በር አላቸው ፤ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ። አንድ የጥበቃ አባል በእነዚሁ የቪላ ቤቶች የወል በር ላይ ቆሞ ገቢ ወጪ መኪናዎችን ይቃኛል። ፀጉረ ልውጥ መኪና እንዳይገባ በንቃት የሚከታተል ይመስላል። የጥበቃው ነገር በዚህ አያበቃም። ይባስ ብሎ እያንዳንዱ ቪላ ቤት በተናጥል የራሱ በርና በረኛ ተመድቦለታል። [...]
(አሮን ፀሐዬ)
ፀጥ ረጭ ያለ ሰፈር፤ በግራ እና በቀኝ የተሰደሩት ቪላ ቤቶች ግዙፍ የጋራ በር አላቸው ፤ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ። አንድ የጥበቃ አባል በእነዚሁ የቪላ ቤቶች የወል በር ላይ ቆሞ ገቢ ወጪ መኪናዎችን ይቃኛል። ፀጉረ ልውጥ መኪና እንዳይገባ በንቃት የሚከታተል ይመስላል። የጥበቃው ነገር በዚህ አያበቃም። ይባስ ብሎ እያንዳንዱ ቪላ ቤት በተናጥል የራሱ በርና በረኛ ተመድቦለታል። “የተሳካላቸው” ብቻ የሚኖሩበት መንደር መኾኑን ከአካባቢው የሚተነው ዝምታ የዋጠው አየር ያሳብቃል።
በስተግራ አራተኛዋ ቪላ ቤት ግን የተለየ ባሕርይ ይታይበታል። የቪላ ቤቱ በር ገርበብ ተደርጎ የተተወ ነው። ደጅ ላይ ጥቂት መኪናዎች ተኮልኩለዋል። ይህ ቤት የሚታይ፣ የሚዳሰስ በረኛ የለውም። በውስጡ ግን ብዙ ዳሳሽ መዳፎች አሉበት። ለምሳሌ የጀሚላ ተዐምረኛ መዳፍ አንዱ ነው!
ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት . . .
ወደ ውስጥ ሲዘለቅ ከሳሎኑ በራፍ ላይ የተሰቀለው የእንግሊዝኛ ማስታወቅያ በደብዛዛ የአምፖል ብርሃን ውስጥ እንዲህ ይነበባል። “Close the door please! It is cold these days!” ሰሞኑን ይበርዳል! እባክዎ በሩን ይዝጉት! እንደማለት። በትንሹ ገርበብ ያለው የሳሎን በር ሲከፈት ቀጭኗ ኮሪደር “ሪሰፕሽን” የሚል ጽሑፍ ከአናቷ ወደተሰቀለባት ጠባብ ክፍል ታደርሳለች። በዚች ቀጭን ክፍል ደግሞ ሸንቀጥ ዘለግ ያለች ቆንጆ ተሰይማለች፤ ሕይወት ባለው ፈገግታ ተቀበለችነን።
“ምን ልታዘዝ?”
ለደንቡ ነው እንጂ የምንፈልገውን ጠንቅቃ ታውቀዋለች። አጠያየቋ በመረጃ እንደመጣን ለማረጋገጥ ያህል ነው። በዚህ ውድቅት መቼስ ማኅሌት ለመቆም እንዳልመጣን እኛም፤ እርሷም፤ ሰይጣንም እናውቃለን። ሻወር አስቀድመን መውሰድ እንደምንፈልግ ከጠየቀችን በኋላ ክፍሎቻችንን አመላከተችን። በቂ ፎጣዎች፣ የሻወር ጋውን እና ሌሎች የንጽሕና መጠብቂያ ቁሳቁሶችን የተሟሉ መኾናቸውን ዐሳየችን።
“ሻወር ወስዳችሁ ስትጨርሱ አስተናጋጆቻችሁ በየክፍላችሁ ይጠብቋችኋል! መልካም ምሽት!”
የበረራ አስተናጋጆችን ዐይነት ቅልጥፍና ይታይባታል። የሚዘናፈለው ፀጉሯ ወደፊት እየመጣ ሲያስቸግራት አንገቷን ወዝወዝ አድርጋ ትመልሰዋለች። ሌላ ጊዜ ደግሞ በጣቶቿ ሰብሰብ አድርጋ በጆሮዎቿ የኋሊት ትሰበስበዋለች። ከአፍታ በኋላ ፀጉሯ መልሶ ወደፊት ብትን ይልባታል። ዳግም ከአንገቷ ወዝወዝ ትልና ጆሮዎቿን ለሚበተነው ፀጉሯ እንደ ታኮ ትጠቀምበታለች፤ ዘንፋላው ፀጉሯ በጄ አይላትም። ዳግም አደብ ልታሲዘው ትሞክራለች።
እንግዶችን በአንደበቷ ብቻ ሳይኾን በጥርሷ፣ በዐይኗ እንዲሁም በፀጉሯ መንከባከብን ታውቅበታለች። ሥራ የሚፈታ የሰውነት ክፍል የላትም፤ ዳሌዋን ጨምሮ።
“ይቅርታ ሂሳብ ቅድሚያ ነው! በሰው 250 ብር!” የማሳረጊያ ንግግሯ ነበር።
በሻማ ብርሃን “ማይም ተውኔት”
ሻወር በቅጡ መውሰዴ ትዝ አይለኝም። ኾኖም ቀጥሎ ለሚኾነው ነገር ጉጉት ያደረብኝ እንዳይመስል በሻወር ቤት ጥቂት ፀናሁ። ያውም ሥራ ፈትቼ።
ወደ ተመደበልኝ ክፍል ስመለስ ጭልጭል የሚል የሻማ ብርሃን፣ በጭልጭል የሻማ ብርሃን ውስጥ ደግሞ ለግላጋ ሴት፣ ከርሷ ሥር በአየር የተወጠረ እና ያበጠ የላስቲክ ፍራሽ ጠበቀኝ። መደናገጤን ዐይታ ነው መሰለኝ በከፊል ፈገግ አለች። ወይም ፈገግ ያለች መሰለኝ።
“ሃይ! ጀሚላ እባላለሁ። ለምሽቱ አስተናጋጅህ ነኝ” ቄንጠኛ ናት።
“አመሰግናለሁ!” እያልኩ በነበረበት ቅጽበት የሻወር ጋውኔን ገፈፈችው” በምትኩ መለመላዬን እንዳልቀር የማጣፋው ስስ ፎጣ ሰጠችኝ። ከሰከንዶች በኋላ “ፎጣውን ካልወደድከው መተው ትችላለህ” ስትል አበሰረችኝ። ኾኖም ፎጣው እንዲቆየኝ መረጥኩ።
በሆዴ በአየር በተወጠረው የላስቲክ ፍራሽ ላይ እንድጋደም ካዘዘችኝ በኋላ የተወሰኑ ሻማዎችን በማክሰም የክፍሉን ስልምልም ብርሃን ይበልጥ አደበዘዘችው። አሁን በዐይን ቋንቋ መግባባት ችግር ውስጥ ወድቋል፤ የመግባቢያ ቋንቋው ወደ መዳፍ ተቀየረ። ጀሚላ በመዳፎቿ ታናግረኝ ጀመር። የማይም ድራማው ፊሽካ ተነፋ።
እጅግ በስሱ የሚንቆረቆረው በመሣርያ ብቻ የተቀነባበረ የሩቅ ምሥራቅ ሙዚቃ በምታቃስት የሴት ድምፅ ታጅቦ ከክፍሉ አንድ ጥግ ላይ በተገጠመ አነስተኛ “ስፒከር” እየተሞዘቀ ነው። ደብቅ ካሜራ በክፍሉ ውስጥ እንዳልተገጠመ በምን ርግጠኛ መዀን ይቻላል? የዚህ ቀስቃሽ ሙዚቃ የድምፅ ምጣኔ እውነትም ከሩቅ ምሥራቅ ከተከፈተ ቴፕ የሚሰማ ነው የሚመስለው። እጅግ ዝቅ ተደርጎ የተከፈተ ሙዚቃ!
ልዩ መዓዛ ባለው የክሬም ቅባት በስሱ ትዳብሰኝ ጀመር። አስተሸሸቷ መታሸት ከሚለው ቃል ይልቅ መነካካት፣ መፈታተን እና መዳራት ለሚሉት ቃላት በጣሙን ይቀርባል። ቀጥላ የውስጥ እግሬን በረዣዥም ጥፍሮቿ መጠነቋቆል ጀመረች። በባለ መዐዛው ክሬም ጀርባዬን ካሸችኝ በኋላ ከማጅራቴ ጀምሮ ቁልቁል በጥፍሮቿ እንደመቧጨር፣ እንደመቧጠጥ አደረገችኝ። ሰውነቴ ምላሽ ሰጠ።
ትዕይንቱ በጀርባ ወደ መጋደም ተዛወረ። የመሀል ጣቷን ጆሮዬ ውስጥ በመጨመር የተለየ ትርጉም ያለው መልእክት ልታስተላልፍልኝ ሞከረች። አንገቴ አካባቢ ጥሩ ስሜት የፈጠረብኝን አንዳች ነገር አድርጋ ወደ ደረቴ ተንደረደረች። ተመልሳ ደግሞ የመሀል ጣቷን በጆሮዎቼ በመጨመር ቀድሞ እንዳደረገችው ስሜቴን ለማናር ጣረች። የደረቴን ጡንቻዎች በስሜት ታሻቸው ጀመር። ከክሬሙ በቄንጥ በጣቷ ትጠነቁልና የደረቴ ጡቶች ላይ በማሳረፍ በጥፍሮቿ ጫፉን ብቻ እየነካካች ንዝረት ለመፍጠር ታተረች፤ ተሳካላት። ከዚህ በኋላ እኔን ፍፁም ረስታ ከደረቴ ጡቶች ጋር ጨዋታዋን አደራችው። ይህን ረዘም ላለ ደቂቃ ከቆየችበት በኋላ ድንገት ቁልቁል ተንደረደረች።
ስሷ ፎጣዬ ደጀንነቷ አከተመ። በፈቃዷ ተንሸራተተች። ሽምቅቅ አልኩኝ።
“ታፍራለህ እንዴ!”
እ . .!?
“ታፍራለህ? የመጀመርያህ ነው?”
“ኖ! ኖ !” ሽምጥጥ አድርጌ ዋሸኋት
“ሻማ ትፈልጋለህ?”
“አይ ይቅርብኝ!”
በልቤ ግን የሻማውን ጥቅም ሳላውቀው ለምን ተግደረደርሁ እያልሁ ነበር።
ሻማ በዚህ ምስጢረኛ ቤት ሳሙና ኾኖ እንደሚያገለግል አጫወተችኝ። “እየቀለጠ ያለ ሻማ የወንድ ሰውነት ላይ ሲፈስ መልካም ስሜት ይፈጥራል እኮ” አለችኝ። በቅላጩ የሻማ ጠብታ ስቃይ ውስጥ መልካም ስሜትን ለመፍጠር የሚደረግ ጥበብ ነው፡፡ እንደ ጀሚላ ማብራሪያ ብዙዎቹ የውጭ ዜጎች “የሻማ ስቃይ” ነፍሳቸው ነው። እነዚህ ደንበኞቿ፣ ላያቸው ላይ በሚቀልጠው የሻማ ስቃይ ውስጥ ደስታቸውን ያበራሉ። የውጭ ዜጎች ብቻ አይደሉም የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች፤ በስም ልትጠራቸው ያልፈቀደቻቸው ጥቂት ታዋቂ ሰዎችም የጀሚላ እና የሻማዋ ቋሚ ደንበኞች ናቸው።
“አንዴ ከለመድከው ሻማ ሱስ ይኾናል”
“እውነትሽን ነው?”
ጭንቅላቷን በመነቅነቅ አዎንታዋን ገለጸች
ከተሰጠኝ አጭር የሻማ ገለጻ በኋላ ነገሩን መሞከር ፈለግኩ፤ ኾኖም አንዴ ይቅርብኝ ስላልኳት ዳግም ለመጠየቅ ኩራት ተናነቀኝ።
የተውኔቱ ጡዘት እና ፍጻሜ
ጀሚላ በመዳፎቿ ካልኾነ ብዙ አታወራም። ለጥያቄዎቼ ግን በሹክሹክታ አጠር ያሉ ምላሾችን ትሰጠኛለች። ብዙ ከማውራት ብዙ መሥራት ትመርጣለች። ለብር ሳይኾን ለሞያ ፍቅር የምትሥራ ነው የምትመስለው። ትኩረቷ ሰውነቴን ማናዘዙ ላይ ነው። ሥራውን ተክናበታለች፤ ዱባይ አንድ ዓመት ተኩል በግሏ ይህን አገልግሎት ትሰጥ እንደነበር ነገረችኝ። ከዚህ በላይ ስለራሷ ከመናገር ተቆጠበች። የእግሮቼን ጡንቻዎች በክሬም በማሸት እና በማሳሳብ ዘና ካደረገቻቸው በኋላ የእግር ጣቶቼ መሀል በመሀል ጣቷ እየገባች መልእክት ለማስተላለፍ ሞከረች። ዐይኖቼን በመጨፈን ምላሽ ለመስጠት ሞከርኩ።
“መሳዥ ታደርገኛለህ?”
“ማንን?”
“እኔን!”
‘እ!’
ቤቱን ከጠቆሙኝ ሰዎች ይህ እንዳለ አልተነገረኝም ነበር፡፡
“አልችልበትም ግን … ልሞክር?”
“ሂሳብ ያስጨምርኻል”
“ኸረ? ስንት?”
“200 ብር…ለኔ ነው የምትሰጠኝ! ድርጅቱ አያገባውም”
ተስማማሁ። በነበርኹበት ኹኔታ አለመስማማት አማራጭ አልነበረም። ሻሽ ላይነን ከመሰለ ጨርቅ የተሰራውን ስስ ጋውኗን ጨምሮ ልብሶቿን አንድ በአንድ እያወለቀች በቄንጥ መስቀያው ላይ አንጠለጠለቻቸው። ጡት ማስያዣዋ እና የውስጥ ሱሪዋ እኔ እንዳወልቃቸው የተተው ናቸው።
በዮጋ ዐይነት አቀማመጥ እግሮቿን አነባብራ ተቀመጠች። በተራዬ ክሬሙን በስሱ እየጠነቆልኩ ከጀርባዋ ጀመርኋት። ጡት መያዣዋን እንድፈታላት ቀጠን ያለ ትዕዛዝ ሰጠችኝ። በጀርባዋም ኾነ በሆዷ ፍራሹ ላይ እንድትጋደም ያቀረብኩላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገችው። በሌላ አገላለጽ እርሷን ማሳጅ ማድረግ የምችለው ከወገቧ በታች ያለውን የሰውነቷን ክፍል ብቻ ነው። የውስጥ ሱሪዋም የማይደፈር ግዛቷን የሚያስከብር ዘብ እንደኾነ ተረዳኹ። ከዚያ ዉጭ ባለው ሰውነቷ መዳፌ እንደልቡ ጋለበበት። በተጣደፍኩ ቁጥር ዝግ እንድል ታስጠነቅቀኛለች። ኾኖም መዳፎቼ የተቀዳጁት ጊዜያዊ ሐሴት እጅግ ለአጭር ጊዜ የቆየ ነበር። ተስፈንጥራ በመነሳት የጡት መያዣዋን ትታ ጋውኗን ብቻ በመልበስ ከወገቡ አካባቢ ባለው መቀነት ሸብ አድርጋ አሰረችው።
“ከዚህ በላይ መቆየት አይፈቀድም፡፡”
ለአንድ ሰዓት ያህል የቆየው ጫዎታችን እየተጠናቀቀ መኾኑን አረዳችኝ።
ኾኖም አንድ የማሳረግያ ትዕይንት እንደቀረ ገብቶኛል። እየናረ ለነበረው ወንድነቴ መፍትሄ እንድትሰጠኝ ተማፀንዃት።
“ያስጨምርኻል!”
“ኸረ! ስንት!”
“መቶ ብር! ድርጅቱ አያገባውም ለኔ ነው የምትሰጠኝ፡፡”
ለድርድር የሚበቃ አቅም አልነበረኝም።
የጀሚላ መዳፎቿ የደረሱበትን የመጨረሻው የዳሰሳ ጥበብ ተጠቅመው ለስሜቴ ጊዜያዊ ምላሽ ሰጡ።
ለጥቂት ደቂቃዎች ዝም አልን!
ሻወር ቤት ስገባ ቆሻሻ ውስጥ የምጥላቸውን የሶፍት ወረቀቶች ሰብስባ የሻወር ጋውኔ ኪስ ውስጥ ሞጀረቻቸው። የሶፍት ወረቀቶቹን መታጠብያ ቤት መጣል እንዳልረሳ ባልጠበቅኹት ኹኔታ አጥብቃ አስጠነቀቀችኝ። ለምን ይህን ያህል አሳሰባት!?
ልብሶቿን ከመስቀያው አውርዳ በጥድፊያ ከለባበሰች በኋላ ድርጅቱ አይመለከታቸውም ያለችኝን ለእርሷ የሚገቡ ክፍያዎች እንድፈጽም የኪስ ቦርሳዬን አቀበለችኝ። ሦስት የመቶ ብር ኖቶችን ሰጠኋት።
“ደንበኛ እንኾናለን! ሌላ ጊዜ ስትመጣ ለሪሴፕሽኖቹ ጀሚላ ብለህ ንገራቸው።”
በሩን ከፍታ ከመውጣቷ በፊት ልብሶቿ እንዳልተዛነፉ ለመጨረሻ ጊዜ ርግጠኛ ለመኾን ሞከረች።
“እኔ ምልሽ?”
“አቤት!”
“ጀሚላ ምን ማለት ነው?”
“ቆንጆ ወይዘሪት . . .”
ክፍሉ ውስጥ ብቻዬን ቀረሁ። ስሜት ቀስቃሹ ሙዚቃ አልተቋረጠም። ክፉኛ የጥፋተኝነት ስሜት ኅሊናዬን ሲበረቅሰው ተሰማኝ። ክፍሉን ለባለተረኛ ዳሳሽና ተዳሳሽ መልቀቅ ነበረብኝ . . .
It sounds the rise of Gated communities in Ethiopia. A tragedy and a comedy in one scene!!!
My question is who are these successful folks? Who climbed up the top of the society’s echeleon,, are they realy hard working people who merit their success? are they the ones who can set an example for their compatriots and inspire other people? should the next generation emulate the deeds and successes of these members of the gated community?
I heard from a friend that Somalia was in about the same situation (high level of inequality) before it finaly disintegrated in to lawless region. There seems to be all the familiar signs of big revolution in Ethiopia too, the beginning of the end, the undoing of the wrongs.
supurb writer, supurb expressions, made me admire amharic as a language.
But why is everything sexualised in Ethiopia. Massage service is so common all over the world, Thais being very much well known for it. but is rarely connected to sex and prostitution. may be it is related to the poverty and declining moral values.
To author,
Nicely scripted. Full of suspense. Based on true story. Reflective of today’s Addis. Even though I’m against such activities in Addis from a moral stand point, I don’t object business owners’ creativity to gain more income in this tough economy. You gotta do what you gotta do.
Gebreyes,
Why are you barking about revolution? How dare you compare our land with a destabilized and a lawless state – Somalia?
To all,
We have to be happy that we are swiftly creating multi millionaires, many investors. Most of the time these people are hard working people. If Riches in Addis work hard, pay taxes, hire workers, abide by the rule, and contribute to the economy, why do we judge them because they have fortunes. Since when have we become a nation of whiners? Why don’t you shout on the youth who don’t work but chew khat day in day out? Those youth are burdens to the society. Why are people so agitated by rich Ethiopians? IF there are no riches there will never be jobs, no jobs no Economy.
Wow, arif tsihuf new. Yihe eko new silitane malet, betam arif entrepreneurship new. Bertu ene jemila. yiheko min yahil le silitane kirib endehonin yemiyasay new,,,,
and the moral of the story is…
come on guys!keep ur reputation! We already have countless pornographic sites, there is no need to add another one. Revealing the truth and showing the threat is one thing, but using pornographic expressions and motivating readers to experience it is another thing.