"; _gaq.push(['_trackPageview']);(function() { var ga = document.createElement('script'); ga.type = 'text/javascript'; ga.async = true; ga.src = ('https:' == document.location.protocol ? 'https://ssl' : 'http://www') + '.google-analytics.com/ga.js'; var s = document.getElementsByTagName('script')[0]; s.parentNode.insertBefore(ga, s); })();

“ከአርቲስቶቹ” እና ከመለስ ውይይት ጠብቀን የነበረው ምንድን ነው?

ከሞላ ጎደል የሁሉንም ዘርፎች ባለሞያዎች የሚመለከቱ ጥያቄዎች ተጠቃለው በአንድ/ጥቂት ሰዎች ሊቀርቡ የሚችሉ ናቸው። ሲሆን በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ የታሰበባቸው አማራጭ ሐሳቦች ይዞ ቀርቦ ጠቅላይ ሚኒስትሩን “ወይ ይህን ሐሳብ ተቀበሉን አለዚያም ሌላ መፍትሔ ይስጡን” ብሎ ወግም ክብርም ያለው አካሔድ መከተል የሚቻል ነበር፤ ልብና ጭንቅላት የሚጠይቅ ትልቅ ነገር ሆነና ሳይሳካ ቀረ። ልብም ጭንቅላትም ያለው ጥቂት አርቲስት ጠፍቶ ይሆን? አይመስለኝም።…በሥራዎቻቸው እንደሚሆነው ሁሉ ከአቶ መለስ ጋራም ሲገናኙ የጥበባቸው ነፍስ የጠንጠለጠለበት ማኅበረሰባቸው/ሕዝባቸው ሕይወት ትዝም አላላቸው። “ሀብታችን” የሚሉት ሕዝብ ምላሳቸው ላይ እንጂ ልባቸው ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ ሳይኖርብን ይቀራል? የተጣሉትም እኮ በዚህ አይደለም። የኑሮ ውድነት፣ ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብት…እነርሱን ያገባቸዋል እንዴ? ምን ሲደረግ?! እነርሱ በቀጥታ “ዘፈን ማሳተም፣ ፊልም መሥራት፣ ግጥም ማንበብ…ተከልክሏል” ካልተባለ አይመለከታቸውም። ይመቻችሁ!…ይህን የምታነቡ አርቲስቶች ወቀሳ እነደበዛባችሁ ታስቡ ይሆናል። ተሳስታችኋል። ትንሽ ሠርታችሁ ብዙ የምናከብራችሁ፣ ቁም ነገር ባትናገሩም የምንሰማችሁ (ለዚያውም “የምታስተላልፉት መልእክት” እነዳለ እየተጠየቃችሁ)፣ ጥቂት ሰጥታችሁን ብዙ የምንመልስላችሁ ቂል ስለሆንን አይደለም፤ ስለምናስብና ተስፋ ልንቆርጥባችሁ ስለማንወድ ብቻ እንጂ። እናንተ ግን አልገባችሁም።

6a00d8341c586153ef00e54f3269778834-800wi

በቅርቡ ከ1500 በላይ ይሆናሉ የተባሉ በአዲስ አበባ የሚገኙ “አርቲስቶች” ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋራ ያደረጉት ውይይት የሰሞኑ አንዱ “መነጋገሪያ” ሆኗል። (“አርቲስቶች”ን በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ የከተትኩት በተደጋጋሚ እንደተባለው ነጋዴዎችም የድራማው አካል ስለነበሩ፣ በተጨማሪም እኛ አገር ቃሉን እንደ ማእረግ የስም አጫፋሪ አድርጎ የመጠቀምን አጉል ልማድ ላለመከተል ስል ነው።) ከአቶ መለስ ጋራ የተደረገውን ውይይት “የተሳካ ነበር” ሊል የሚችል ወገን የሚገኝ ከሆነ አቶ መለስ እና ሠራዊት/ሠራዊቱ ብቻ ሳይሆኑ አይቀሩም። እርግጥ አቶ መለስም ቢሆኑ “አርቲስቶቹ” በጉባኤው ስኬት ግምገማ ላይ መከፋፈላቸው ሳያሳዝናቸው አይቀርም፤ ሠራዊትም የደረሰበት ውርጅብኝ “ምነው በቀረብኝ” የሚያስብል ነው።

ይህ “ውይይት” ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሕዝብ ግንኙነት መድረኮች የሚለይበት አንድ ታሪካዊ ቁም ነገር ግን አለ። እርሱም የጥመቀቱ ተሳታፊዎች ሙሉ በሙሉ ሳያምኑ መውጣቸው ሳያንስ በአደባባይ “ውይይቱ ተጭበርብሯል” ማለታቸው ነው። በውጤቱ ከታየ ከዚህ ቀደም አቶ መለስ “የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን” ካነጋገሩባቸው “መድረኮች” የተለየ አይደለም፤ ሁልጊዜም መድረኩ በሆነ መንገድ ይጭበረበራል። ይህ ማለት ግን “አርቲስቶቹ” በመሠረታዊ ጉዳይ ላይ ተለያይተዋል ማለት ላይሆን ይችላል።

እስከ አሁን ስለዚህ የመከነ መድረክ በሚገባ ያልተዳሰሱ ተያያዥነት ያላቸው ሁለቱ ጥያቄዎች ያሉ ይመስለኛል። አንድ፤ አርቲስቶቹ በእርግጥ የተጣሉት በምንድን ነው? ሁለት፤ ከአርቲስቶቹና ከውይይቱ ጠብቀን የነበረው ምንድን ነው? እነዚህን ጥያቄዎች የመረጥኩት አንድም አንዳንድ ወዳጆቼ ሳይገባቸው ስለተበሳጩ፣ በተገቢ ምክንያት እንዳልተበሳጩ ወይም ጥፋቱ የእነርሱው የራሳችው ሊሆን እንደሚችል ለማስታወስ ነው። ወዲያውም አርቲስቶቻችን ቢያንስ የተወሰነው ተመልካች በውይይታቸው ያዘነው እነርሱ (አርቲስቶቹ) ባሰቡት ምክንያት አለመሆኑን ለመጠቆም ነው።

አርቲስቶቹ” በምን ተጣሉ?

በአርቲስቶቹ መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በተመለከተ (ካለሁበት የተሻለ መረጃ ለማግኘት የቻልኩት) “አዲስ ጉዳይ” መጽሔት ካቀረበው ዘገባ በመሆኑ ግምገማዬ በዚያ ላይ በእጅጉ የተመሠረተ ነው። ሌሎቹ ሪፖርቶች ያቀረቡልን በአብዛኛው ትችትና የዜና ዘገባ ነው። ወደ ክርክሬ ከመግባቴ በፊት ግን ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ ያቀረበው ቃለ መጠይቅ ሞጋችነት እንዳስደሰተኝ ሳልገልጽ ብቀር ውለታ ቢስ ያደርገኛል፤ ብዙ ወሳኝ ጥያቄዎችን ሳያነሳ ቢያልፍ። በዚህ ጽሑፍ የማቀርበው ወቀሳ በየሚዲያው ቃለ ምልልስ የሰጡትን አርቲስቶች ብቻ ሳይሆን ከተቀሩትም የሚበዙትን የሚመለከት እንደሆነ ማስታወስ ይኖርብኛል። “ይህ ወቀሳ አይመለከተኝም” የሚል እርሱ “በእነሠራዊት” ላይ የመጀመሪያውን “ድንጋይ” እንዲወረውር ይጋበዛል።

የአርቲስቶቹን የውዝግብ መነሻ በአራት ማጠቃለል ይቻላል።

ሀ.  የሙያና የሙያ ማኅበር ‘ፖለቲካ’

ለ.  “የማኅበሬ ችግር በማኅበሬ አባል ሳይነገር ቀረ” የሚል (በዋናነት በመድረክ/ውይይት አስተዳደር ብቻ

ሊፈታ የሚችል) የሰነፍ ቁጭት

ሐ.  ግለሰባዊ ሽኩቻ

መ.  ራስን የመሸጥ ንግዳዊ ውድድር

ሠራዊትና ሠራዊቱ። ይህን አገላለጽ እንዴት እንዳደነቅሁት መግለጽ ይቸግረኛል፤ ወደፊት የአንድ አባባል መነሻ ሳይሆን ይቀራል? ልክ “ከሠራዊትና ከሠራዊቱ ይጠብቅህ” እንደማለት። “ሠራዊትና ሠራዊቱን” ብዙዎቹ ተመልካቾች “መድረኩን ራስን የመሸጫ አጋጣሚ አደረጉት፤ ለራሳቸው ዘርፍና ለጓደኞቻቸው አዳልተው ሌላውን መድረክ ከለከሉ፤ ስለጥበብ ሳይሆን የጥበብ ውጫዊ መድረሻ በሆነው የገንዘብ አጀንዳ ጠለፉት…” እያሉ ወቅሰዋቸዋል። እውነት ያለበት ወቀሳ ነው። ለነገሩ ይህን ከሚሉት መካከል የኮሚቴው አባል ሁን ሲባል እምቢ ያለ አይጠፋም። አለዚያ ግን እነሠራዊት ለራሳቸው ሲቆርሱ አለማሳነሳቸውን አልካዱም፤ ይቅርታ ብጤም ጠይቀዋል (ይቺ ይቅርታ በየደረሰችበት እንዲህ መጫወቻ ትሁን?) በዚህ መድረክ “ራስን ለመሸጥ” (የዛሬን አያድርገውና ይህ አነጋገር ስድብ ነበር) የተደረገው ፍልሚያ በቅንነት ለሚመዝነው የሚያስገርም አይደለም፤ እንዲያውም አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ነጸብራቅ ነው። የመንግሥት ደጋፊ፣ ቢያንስ ደግሞ አል-ተቃዋሚ (ፍዝ ገለልተኛ) ሆኖ መታየት እውቀትንና ችሎታን ሸጦ ለማደር ወሳኝ መስፈርት በሆነበት አገር ይህን መሰሉ ውድድር የሚጠበቅ ነው። የተናገሩት ሁሉ ግን ለዚህ ብለው ተናግረዋል ለማለት አንችልም፤ ከልቡ ትልቅ ነገር የተናገረ አይጠፋምና።

 

ከቻይናዊው አይ ዌይዌይ ሥራዎች አንዱ

 

 

 

የቴዎድሮስ ተክለአረጋይ ቃለምልልስ በማያዳግም መልኩ እንደገለጸልንና ቀድሞም እንደምናውቀው ግን “ዕድል ተነፈግን፤ ድራማ ተሰራብን” የሚሉት አርቲስቶችና ማኅበሮቻቸው እድል አግኝተው ከተናገሩት ሰዎች በተጨባጭ ይዘቱ (ሰብስታንቲቭሊ) የተለየ ጥያቄ አልነበራቸው። እንዲያውም አንዳንዶቹ “እንኳን እድል አልተሰጣቸው” የሚያስብሉ ናቸው። ይህ ማለት ጥያቄዎቹ መልስ አያስፈልጋቸውም፣ ሊፈቱ አይገባም፣ ለአርቲስቶቹ ሕይወትና ሞያ ምንም አስተዋጽኦ የላቸውም ማለት አይደለም። የደሞዝ እርከን፣ የጥበብ ማሳያና መሥሪያ ቦታ፣ ኮፒ ራይት፣ ከውጭ መሣሪያዎችን ስለማስገባት፣ የወረቀት ወይም የማባዣ ማሺን ቀረጥ የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ማለቴ ነው።

ነገር ግን እነዚህ ከሞላ ጎደል የሁሉንም ዘርፎች ባለሞያዎች የሚመለከቱ ጥያቄዎች ተጠቃለው በአንድ/ጥቂት ሰዎች ሊቀርቡ የሚችሉ ናቸው፤ “የግል/የዘርፍ ለቅሶዬን በራሴ ዜማ ሳለሰማ ቀረሁ” የሚያስበሉና ሌላ አዲስ የለቅሶ ነጠላ ዜማ የሚያስወጡ አልነበሩም። ሲሆን በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ የታሰበባቸው አማራጭ ሐሳቦች ይዞ ቀርቦ ጠቅላይ ሚኒስትሩን “ወይ ይህን ሐሳብ ተቀበሉን አለዚያም ሌላ መፍትሔ ይስጡን” ብሎ ወግም ክብርም ያለው አካሔድ መከተል የሚቻል ነበር፤ ልብና ጭንቅላት የሚጠይቅ ትልቅ ነገር ሆነና ሳይሳካ ቀረ። ልብም ጭንቅላትም ያለው ጥቂት አርቲስት ጠፍቶ ይሆን? አይመስለኝም። ችግሩ ልብና ጭንቅላት ያላቸው አርቲስቶች አንድም “ሠራዊት” የማደራጀት ጥበብ “አይገለጥላቸው”፣ አለዚያም በአካባቢው በአገሩ የሉም። በአንድ በኩል ሳየው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ሰዎች ሠራዊትንና ሠራዊቱን ማመስገን አለባቸው፤ ምክንያቱም እነሠራዊት ወቀሳውን ሁሉ ወስደውላቸዋል። (በነገራችን ላይ፣ በዚህ ስብሰባ ላይ ያልተገኙ አርቲስቶች ሪፖርት እንዲያደርጉ አልታዘዙም?)

ሌላው በጣም የሚያስቀው ነገር የአንዱ ዘርፍ ባለሞያ ለሌላው ያለው ንቀት ነው። ቀደም ሲል እንዳልኩት መድረኩ የገለጠው አንዱ ገመና አብዛኞቹ አርቲስቶቻችን ልክ እንደፖለቲከኞቻችን እርስ በርስ መረዳዳት ቀርቶ መከባበር እንኳን እንደማይችሉ ነው። ስለመቻቻልና መከባበር መግጠም፣ መዝፈን፣ ዜማ ማቀናበር… ሌላ፤ የሚሉትን መኖር ሌላ። ለማንኛውም አደባባይ የወጣ በሽታ የተሻለ የመዳን እድል ስላለው ነገሩ የሚያስቆጭ አይደለም። አርቲስቶቻችን ቁም ነገር ቢኖራቸውና “ከትንንሽ” የሞያ ዘርፍ ክበባቸው ወጥተው ማሰብ ቢችሉ ኖሮ ቁጭታቸው “ለእንትን ሞያ ሰዎች 3 እድል ተሰጠ፣ የእኛ ሞያ ሰው ሳይናገር ቀረ” የሚል ሳይሆን መሠረታዊ ጥያቄ ቀርቧል አልቀረበም፣ ለጥያቄው ያቀረብነው ሙግት አቶ መለስን የሚከነክንና የሆነ ለውጥ የሚያመጣ ሆኗል አልሆነም፣ አገራዊና ማኅበረሰባዊ ፋይዳ ያላቸውን ጥያቄዎች አንስተናል አላነሳነም ሊሆን በቻለ ነበር።

አሁን ወደኋላ ተመልሶ እውነታውን ለማረጋገጥ አይቻልም እንጂ ለሁሉም እድል ቢሰጥ ምን ይጠይቁ እንደነበር ብናውቅ በወደድን ነበር። የ “አዲስ ጉዳይ” ዘገባ እንዳስነበን ከሆነ ግን የሚያስቆጭ ጥያቄ አልቀረም። የሚያስቆጭ ጥያቄ ነበረኝ የሚል አርቲስት ካለ “ሳይቀርብ የቀረበው ጥያቄ” በሚል በቅርብ እንደሚያሳውቀን ተስፋ እናድርግ።

 

የእኛ ይባስ!

የአርቲስቶቹን እና የአቶ መለስን “ውይይት” ተመልክቶ ያደነቀ ሰው አልገጠመኝም። እንዲያውም አንድ የአዲስ አበባ ጓደኛዬ “በአንድ በኩል መለስ በሌላ በኩል እነእንትና (እሱ ስም ጠርቷል) ተቀምጠው ሌላ ምን ትጠብቃለህ?” ሲል ነገሩን አጠቃሎታል። ሆኖም ውይይቱ የብዙ የዋሃንን ቀልብ መሳቡ አያጠራጥርም። ሌላው ቢቀር “ዝነኛ ሰዎቻችን” ተሰባስበው ሰውየውን ሲያናግሩ “የሆነ ነገር” ማንሳታቸው አይቀርም ከሚል ምኞት ሊሆን ይችላል፤ ቀሪው ደግሞ “እስቲ ደሞ የእነዚህ ጉድ እንስማ” የሚል ይሆናል። ውይይቱ በቀጥታ በቴሌቪዥን መተላለፉ በራሱ ለአርቲስቶቻችን ትልቅ መልእክት ነበረው፤ ቢገባቸው ኖሮ።

በአርቲስቶቻችን “ልማታዊነት” እና ….(ለመጻፍ ያልተፈቀደ) መሆናቸውን በማስመስከራቸው የተደሰተ ሰው ቢኖር መብቱን አከብራለሁ። ቀሪዎቹ ወዳጆቼ በአርቲስቶቻችን ያዘኑት፣ የተሳቀቁት ለምንድን ነው? ምን ጠብቀው ነበር? ጥቂት ነጥቦችን ላንሣ።

1. ካነጋገር ይፈረዳል

ቀደም ሲል እንደጠቆምኩት አርቲስቶቹ አለን የሚሉትን ጥያቄ፣ ረባም አልረባም፣ ተስማሙበትም አልተስማሙበትም፣ በተሻለና በተደራጀ መንገድ ማቅረብ ይገባቸው ነበር። ከውይይቱ በኋላ የወጣው ገመና የጥቂት ሰዎችና ማኅበራት ብቻ ሳይሆን የሁሉም አርቲስቶች ተደርጎ የሚቆጠር ነው። አዝነንባችኋል። አዝነንላችኋል።

2. ጥበብ ያለ ነጻነት

ውይይቱን ከተከታተሉ ሰዎች መካከል አርቲስቶቻችን የነጻነትን ጥያቄ በሆነ መንገድ ያነሳሉ ብለው የጠበቁ ነበሩ። እርግጥ “ፖለቲካ አልወድም” ብሎ መናገርን እንደሐፍረት የማይቆጥር፣ በድንቁርናው መኩራራት የሚያመረው አርቲስት ስለነጻነት መልከ ብዙነትና ሕልውናዊ አስፈላጊነት በመጥቀስ ንግግሩን እንዲጀምር አንጠብቅም። ሌላው ቢቀር ግን ጥበብን በቀጥታና ወዲያው ስለሚመለከተው ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት በሆነ መንገድ ጥያቄ እንዲያቀርብ መጠበቅ የተገባ ነው፤ ከኢትዮጵያ በቀር። ለነገሩ ብዙዎቹ (“ሁሉም” እንዳልል በመቶ ዓመት አንድ ጊዜ ብቅ እያሉ የሚያሳጡን አሉ!) የኢትዮጵያ አርቲስቶች የሐሳብ እንጂ የነጻነት እጥረት የለባቸውም ብሎ ማሰብ ከእውነታው ብዙ አያርቀን ይሆናል። ስለዚህ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ጉዳያቸው ባይሆን ልንወቅሳቸው አይገባም።

እንኳን ሐሳብን ስለመግለጽ ነጻነት ቀርቶ የአዲስ አበባ መስተዳድር ቴአትሮች “ልማታዊ” እንዲሆኑ ያወጣውን መመሪያና አዝማሚያውን (በአዲስ ነገር ጋዜጣ ሰፊ ዘገባ ቀርቦበታል)  እንኳን ያስታወሰ አርቲስት እንዴት ጠፋ? ወይስ ትክክል ነው ብለው ያምናሉ? እንደዚያም ከሆነ “መመሪያው ለሁላችንም በየዘርፋችን ይዘጋጅ፣ መንግሥት አፈጻጸሙን በቅርብ ይከታተል” ብለው ጥያቄ ማቅረብ ነበረባቸው። ለመተዛዘቡ ያህል ይህ ጥያቄ ትዝ ያለው ነበር ይሆን? እንደማይጠፋ ተስፋ አደርጋለሁ። ተስፋ የማደርገው ግን ለራሴ ስለማዝንለትም ጭምር ነው።

አርቲስቶቻችን ስለነጻነትና ስለጥበብ ያላቸው ግንዛቤ የሚዘረጋው ከአካላዊ ሰቀቀን (ምግብ፣ ልብስ…) መላቀቅ ድረስ ብቻ ይሆን? እንደዚያማ ባይሆን “ለነጻ” ውይይት ተጋብዘሃል የተባለ አርቲስት “ጥያቄህን አጥና፤ ስላላጠናህ አታቀርብም…” ሲባል እንዴት ይቀበላል? ልብ በሉ ስለ ጥያቄው ይዘት እያነሳሁ አይደለም፤ ጥያቄውን ለማቅረብ ስላላቸው ነጻነት እንጂ። “ጥያቄዬን እዚያው ነው የማቀርበው፣ በነጻነቴ አልደራደርም፣ አለዚያ መናገሩ ይቅርብኝ” ያለ አርቲስት ካለ እንድናውቀው እማጸናለሁ። የአንዱ ማኅበር ሰብሳቢ “ጥያቄያቸውን ባለማጥናታቸው” (አያስቅም?) እንዳይጠይቁ ተከልክለዋል፤ እርሳቸው ግን ያላጠኑት “ነገሩን በሚገባ ስለሚያውቁት” እንጂ የፈለጉትን ጥያቄ በመረጡት ቅርጽ የማቅረብ ነጻነታቸውን አላስነካም ብለው አይደለም። ለመሆኑ ከመድረክ ጀርባ የተሠራው ቴአትር ነጻነትን የሚጋፋ መሆኑን በተለያየ መንገድ መግለጻ አይቻልም ነበር? እርግጥ የኢትዮጵያውያን ዋናው የተቃውሞ መግለጫ “ዝምታ ነው” ሲባል ሰምቻለሁ። እንኳን ዝም አላችሁ!

ይህን ግዜ “የደሞዝ ጭማሪውም ሆነ የቀረጥ ጥያቄው እኮ የአርቲስቱን ነጻነት በተዘዋዋሪ ለማስጠበቅ የሚያስፈልጉ ናቸው” የሚል መልስ እንደሚዘጋጅ አውቃለሁ። ተመልሶ ተሞቷል። እዚህ ላይ አቶ መለስን ላድንቅ፤ ምክንያቱም የሚፈልጉትን ያውቃሉ፤ አለቀ። “እኛ ጥበብን የምንፈልገው ለሰው ኀይል ልማት ነው” ብለው እቅጩን አስቀምጠዋል። ይህ ማለት ምን ማለት ነው ብሎ መነጋገር ሌላ ርእሰ ጉዳይ ነው፤ ግን ተግባብተናል።

3. ጥበብ ያለ ሰው/ሕዝብ

የጥበብ ማዕከል ሰው ነው፤ ኅብረተሰብ ነው። ጥበብ የቱንም ያህል ወደሸቀጥነት ብትቀየር ይህን ውሏን አትስትም። ሕይወት ወደ ሸቀጥነት ተለወጠ በሚባልበት የምእራቡ ዓለም እንኳን ዛሬም፣ አሁንም ስለ ሰው ልእልና፣ ስለ ነጻነት…ይጻፋል፣ ይዘፈናል፣ ይሳላል፣ ይቀረጻል። ይህ ማለት ለሕዝብ በተለያየ መንገድ ይቀርባል። ነጻነት በለሌባቸው አገሮች ሳይቀር አርቲስቶች ይህን ያደርጋሉ፤ የሰውን ልጅ በአጠቃላይ፣ በተለይም ደግሞ የራሳቸውን ማኅበረሰብ እውነታና ምኞች፣ መከራና ደስታ፣ እሪታና እልልታ ይጽፋሉ፣ ይዘፍናሉ…። ብዙዎቹ የእኛ አርቲስቶች ግን ለዚህ አልታደሉም፤ እኛም አልታደልንም።

ብዙዎቹ የእኛ አርቲስቶች  መዝፈን፣ መግጠም (በአደባባይ ማንበቡን ጭምር)፣ ጽፎ ማሳተም…የሚፈልጉት ስለ ደስታው፣ ስለ እልልታው እና አልፎ አልፎ ሲሳሳቱ ስለ ምኞቱ ነው። መከራውን፣ ረሃቡን፣ እሪታውን፣ ብሶቱን እና እውነታውን አያዩትም ወይም ያላዩ መስለው ያልፉታል፤ አይሰሙትም፣ አይዳስሱትም። ስለኑሮ ውድነት፣ ስለ ረሃብ፣ ስለ ነጻነት እጦት፣ ስለሙስና፣ ስለሚሰደደው ሕዝብ ወዘተ ትንፍሽ የማይሉት ሰዎች “እልልታ አለ” ሲባሉ የሚቀድማቸው የለምና በቀደም እለት “አባይን ካለየን አይነጋልንም” ብለው ወንዝ ለወንዝ ተንከራተቱ። (የአባይ ጉብኝታችሁን መቃወሜ አይደለም፤ ግን ግማሽ ውሸት ነው፤ እናንተም ውሸታችሁን ነው። ግማሽ ሕይወት ነው።) ውይ እረስቼው! ለካስ ስለ ኤድስ ብዙ ዘፈን፣ ቴአትር/ድራማ፣ ፊልም፣ ግጥም፣ መጽሐፍ…ጽፈዋል። እርግጥ…(ለመጻፍ ያልተፈለገ) መሆኑ አይካድም። ቢሆንም በዚህ በኩል ባለውለታዎቻችን ናችሁ።

በሥራዎቻቸው እንደሚሆነው ሁሉ ከአቶ መለስ ጋራም ሲገናኙ የጥበባቸው ነፍስ የጠንጠለጠለበት ማኅበረሰባቸው/ሕዝባቸው ሕይወት ትዝም አላላቸው። “ሀብታችን” የሚሉት ሕዝብ ምላሳቸው ላይ እንጂ ልባቸው ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ ሳይኖርብን ይቀራል? የተጣሉትም እኮ በዚህ አይደለም። የኑሮ ውድነት፣ ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብት…እነርሱን ያገባቸዋል እንዴ? ምን ሲደረግ?! እነርሱ በቀጥታ “ዘፈን ማሳተም፣ ፊልም መሥራት፣ ግጥም ማንበብ…ተከልክሏል” ካልተባለ አይመለከታቸውም። ይመቻችሁ!

4. ጥበብ ያለ እውነት/ፍትሕ

ጥበብ እና ጥበበኛ እውነትና ፍትሕን ይወዳሉ ይባላል። ጥበብና ጥበበኛ እውነትን ይገልጻታል፣ ያኖራታል፤ አልፎም ዋጋ ይከፍልላታል። ይባል ነበር ድሮ። በግማሽ እውነታ ላይ ተንጠልጥለው መኖርን የሕይወት ዘይቤ ያደረጉት ብዙዎቹ አርቲስቶቻችን እውነትን ለገዢዎች እነዲናገሩ ሳይሆን በመጀመሪያ እውነትና ፍትሕን እንዲያውቁ መመኘት አለብን።

በብዙ አምባገነን አገሮች መሪዎች አርቲስቶችን እንደ አንድ ንኡስ መደብ ለመቆጣጠር መሞከር የተለመደ ነው። አብዛኛው ምናቡን አብዝቶ የሚጠቀመው ፍርሀቱን ለማፋፋት ስለሆነ ተጨማሪ ጫና አያስፈልገውም፤ ጥቂቶቹ ደፋር አማጽያን ደግሞ እንደየጉዳያቸው ጥልቀት በተናጠል ይስተናገዳሉ። ይሄ የእኛም አገር እውነታ ይመስላል። በተናጠል የተስተናገዱ አሉ (ነጠላና ብዙ እያምታታሁ ተቸገርኩ)፤ የፈጠራ ችሎታቸውን ውስጣዊ ፍራሃታቸውን ለማግዘፍና ለሌውም ለመትረፍ የሚጠቀሙበት ብዙዎቹ ደግሞ ጥበብን ተሰናብተው በየአቅጣጫው ወደ “ከተፋ” ከገቡ ዓመታት ተቆጥረዋል።

እነሆም በጥበብ እና በእውነት እየከሱ፣ እየጫጩ እናያቸዋለን፤ በአካላዊ ቁመና እያማሩ፣ በገንዘብም ከአምና ዘንድሮ እየተሻላቸው እንታዘባቸዋለን። ከዚህ አኳያ በዚህ ታሪካዊ ውይይት ላይ “እውነት” (ጥበበኞች እውነት ምንድን ነው የሚለው ጥያቄ እጅግ ያብሰለስላቸው ነበር) የሚናገር ሰው ይኖራል ብሎ የጠበቀ ሰው ብሶቱን በምስኪን አርቲስቶቻችንና “ቤተሰቦቻቸው” ላይ ማላከክ የለበትም። አርቲስቶቹ ስለ ሰብአዊ መብት፣ ስለ ኑሮ ውድነት፣ ስለ ሙስና፣ ስለ ፍትሕ እጦት፣ ስለ ሕዝቡ ብሶት… ወዘተ በቀጥታም ይሁን በቅኔ እንዲናገሩ የሚጠብቅ ሰው ራሱን ለብስጭት በመዳረጉ የተሰማንን ልባዊ ሐዘን በአርቲስቶቻችንና በሠራዊታቸው ስም እገልጻለሁ።

ይህን የምታነቡ አርቲስቶች ወቀሳ እነደበዛባችሁ ታስቡ ይሆናል። ተሳስታችኋል። ትንሽ ሠርታችሁ ብዙ የምናከብራችሁ፣ ቁም ነገር ባትናገሩም የምንሰማችሁ (ለዚያውም “የምታስተላልፉት መልእክት” እነዳለ እየተጠየቃችሁ)፣ ጥቂት ሰጥታችሁን ብዙ የምንመልስላችሁ ቂል ስለሆንን አይደለም፤ ስለምናስብና ተስፋ ልንቆርጥባችሁ ስለማንወድ ብቻ እንጂ። እናንተ ግን አልገባችሁም።

ወቀሳዬን ሁላችሁም “ፖለቲከኛ” እንድትሆኑ የማስገደድ ወይም የመጠየቅ አድርጎ የሚመለከተው እንደማይጠፋ አውቃለሁ። ግን አይደለም። ወቀሳዬ ከባሕራችሁ የወጣችሁ አሳዎች ሆናችሁ ነው። ይህ ማለት ፖለቲካ ከሆነ እርግጥም “ፖለቲከኛ” ሁኑ እያልኩ ነው። “ፖለቲካኛ” ሳትሆኑ አየናችሁ፤ አልተሳካላችሁም። እስቲ ደሞ “ፖለቲከኛ” ሆናችሁ ሞክሩት። ወደባሕራችሁ ተመለሱ።

ከውስጥም ከውጭም ታሪክና ፍልስፍና እየጠቀሱ መነጋገሩ አይረባንም ብዬ ወደዚያ አልገባሁም። እንዲያ ባይሆን ኖሮ በተለይ ስለቻይናዊ አይ ዌይዌይ ጥቂት በተጫወትን በወደድኩ ነበር፤ ባይሆን ጥቂት ሥራዎቹን እዚህ አያይዣቸዋለሁ።

በመጨረሻ፤ እዚህ ካሰፈርኩት ወቀሳ መካከል የተወሰነው የማይመለከታቸው ሰዎች እነዳሉ በድጋሚ ላስታውስ። እናንተን ያኑራችሁ። ድምጻችሁን ባንሰማም ውስጥ ውስጡን የምትብሰለሰሉም ትኖሩ ይሆናል፤ ቢያንስ ከእኛ እንደ አንዱ ሆናችኋልና እንረዳችኋለን። ወትሮም ቢሆን ጥበብን መገልገያ (ብቻ) ሳይሆን ማገልገያም ጭምር የሚያደርጓት ጥቂቶች እንደሆኑ አንዘነጋም። ጸሎታችንም “ብዙኀኑ ለምን በዙ?” የሚል አደለም፤ “ጥቂቶቹ ለምን ‘ጠፉ?’” የሚል እንጂ።  በሌላ ስብሰባ እንገናኝ።

7 Responses to ““ከአርቲስቶቹ” እና ከመለስ ውይይት ጠብቀን የነበረው ምንድን ነው?”

  1. Mesfinne

    I get on my nerves after reading this brash and unapologetic commentary which put all Ethiopian artists in one basket. I just laughed at the way you tried backing your claim.

    Suppose that meeting was a hypothetical one what type of expectation are were demanding from these innocent artists OR what are they functionally expect to deliver in the meeting.

    Who has the right to design this serious home work for them which the opposition parties failed to do it by them selves?

    was there a hidden Agenda to make these artists an instrument for POLITICAL ZOO OF THE FUNCTIONALLY FAILED DIASPORA POLITICIANS?

    I guess lairs are politicians, there is a away actually a peaceful way to believe and live with out politics. Who knows, these artists may have this in their mind. It is needlessly harsh to say they are ignorant

  2. Thanks Mesfin. I am glad that you brought the Chinese artist Ai Weiwei for a contrast.

    Although I appreciate the well articulated and reasoned argument, you are too kind in criticizing the artists. I always have a feeling that most of the current Ethiopian artists are more of professional entertainers. They do whatever seems popular and commercially viable. I don’t see the passionate, principled, compassionate, and dedicated personalities we see in respected artists (of course there are some few exceptions such as Tilahun (RIP), Teddy Afro,,,). Their acts and performances don’t impart the usual power and force an art should possess and exert on a society. They don’t inspire, enlighten, energize, don’t give hope to people’s hearts, don’t heal the wounded souls of a desperate and miserable society.

  3. I hasten to add that the government main interest is to drive a wedge between people and the artists. The role of artists in people’s movements, for example in the Egypt and Tunisian uprising, is monumental. I believe the woyanes are tipped by their Western advisers to perform such stunts and thus killing two birds with a stone. First, they pretend that they have the full support and backing of the elites of the society (in this case artists). Second, they create a discord between the people and the artists and hence preventing the people its voice and means of communication (the art).

    Some of them such as Serawit Fikire are fledgling artists who trying to discover themselves in new domains (such as film director), perhaps they could one day be cultural heroes. The Woyanes are nipping this in the bud and killing them before they grow. Creating a conflict between an artist and the people is an effective way of killing the art.

  4. Belay

    You said
    “I don’t see the passionate, principled, compassionate, and dedicated personalities we see in respected artists (of course there are some few exceptions such as Tilahun (RIP), Teddy Afro,,,)”

    Dear Let’s be honest here, Tilahun and Tedi Afero are good vocalists; that’s all, what and where are these adjectives coming from. Should we trust you that the nature and the out come of the meeting would have been totally changed if these two artists had participated. This is an odd claim.

    I found many of the people who oppose the Ethiopian artists in the meeting ( imagine they were 1500 in number)are facing a lot of slippery slope. Before pointing a finger on someone, ask yourself that what do you do on your part? This a very serious question one shouldn’t turn his face away from.

    You said

    “….Woyane Creating a conflict between an artist and the people and this is an effective way of killing the art”

    What a prejudice? This is in fact incurable. Man, You are gonna get troubled

  5. “There is no reply to the ignorant like keeping silence”

  6. WELCOME BACK MISFIN ..we miss u!!!!!!
    NICE OBSERVATION KEEP IT !!!

  7. Thank you Mesfin.

    This is very nice analysis/argument regarding the meeting between the “Crime-in-Chief” and “ሠራዊትና ሠራዊቱ::” The so called “Artists” are direct and indirect beneficiaries of the Cannibalistic and Lootocratic regime of Meles Zenawi. History is full of examples of such artists serving inhuman regime.

    Richard Grenier, Hitlers’ Filmmaker, raises a very interesting question: Can artists loyal to cannibalistic regimes like Nazi Germany or Communist Russia produce great work? His primary example is Leni Riefenstahl, but Mr. Grenier also refers to the movies of Russian film directors loyal to the Soviet regime like Aleksandr Dovzhenko and Sergei Eisenstein. It is impossible for a truly honest and talented artist to thrive while working in the service of an inhuman regime.

    After his first successful film, Dovzhenko never amounted to anything; his life was an exercise in futility. Eisenstein was the most talented film director of those years. He produced his first truly great film, The Battleship Potemkin, in 1925, not long before Stalin succeeded in driving all independent creativity in art deep underground. Devoted to exposing the cruelty of czarism in the 1905 revolution, the film would have suited the needs of any anti-czarist movement, democratic or totalitarian. Eisenstein’s other truly great work is Ivan the Terrible, which Stalin ordered him to produce.

    There is no much qualitative difference between those served brutal dictators in the past and ሠራዊትና ሠራዊቱ serving the beastocracy of ወያኔ thugs.

Bad Behavior has blocked 3455 access attempts in the last 7 days.