"; _gaq.push(['_trackPageview']);(function() { var ga = document.createElement('script'); ga.type = 'text/javascript'; ga.async = true; ga.src = ('https:' == document.location.protocol ? 'https://ssl' : 'http://www') + '.google-analytics.com/ga.js'; var s = document.getElementsByTagName('script')[0]; s.parentNode.insertBefore(ga, s); })();

“የጸረ ሽብር ሕጉ የፈጠረው ቀውስ በጋዜጠኞች ስልጠና ሊታከም ነው”

ይሄን ሥልጠና ለማዘጋጀት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሥልጠናውን ማንዋል ያዘጋጀ ሲሆን ጋዜጠኞቹን የማስተባበር ሥራ በአቶ አንተነህ አብርሃም ለሚመራው “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት” (ኢብጋሕ ) የተሰጠ ኃላፊነት ሲሆን የሠልጣኝና የአሰልጣኞችን አበል ጨምሮ አጠቃላይ የዝግጅቱ የገንዘብ ወጪ ደግሞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የተሰጠ ኃላፊነት ነው ተብሏል፡፡ የዚህ ኮሚሽን መሪ በቅርቡ ከአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ተከሰው መታሰራቸውን እንደማያውቁ መናገራቸው ይታወሳል።

በአቶ በረከት ስምዖን የሚመራው የመንግሥት ኮሙኑኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በአቶ አንተነህ አብርሃም ከሚመራው “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት” (ኢብጋሕ) እና ከጸረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር በቅርቡ በኢህአዴግ መንግሥት ተግባራዊ እየተደረገ በሚገኘውና አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ እያሸበረ በሚገኘው በጸረ ሽብር ሕግ ላይ ጋዜጠኞችን ሊያሰለጥን ነው፡፡ በቅርቡ የበርካታ ጋዜጠኞችን ያለአግባብ መታሰር ተከትሎ በጋዜጠኞች ዘንድ የተፈጠረውን መደናገጥ ለማርገብ ይሞከራል ተብሏል።

በዚህ “የጸረ ሽብር ሕግ ዋስትናና አተገባበር” በሚል በመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስተባባሪነት በተዘጋጀው የጋዜጠኞች ሥልጠና ላይ የመንግሥትና የግል መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በሥልጠና ወቅት የሚገበዩትን እውቀት ለአድማጭ ተመልካቾቻቸውና ለአንባቢዎቻቸው ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የጽ/ቤቱ የዜና ምንጮቻችን አሳውቀውናል፡፡

ዓርብ ጥቅምት 3 ቀን እና ቅዳሜ ጥቅምት 4 ቀን 2004 በአዳማ- ናዝሬት በሚካሄደው ሥልጠና ላይ “የአቶ በረከት ስምዖን መገኘትን እስከ አሁን ያልተረጋገጠ ነው” ያሉን ምንጮቻችን ምክትላቸው አቶ ሽመልስ ከማል ግን ሥልጠናውን ከሚሰጡት የሕግና የጋዜጠኝነት ባለሙያዎች ዝርዝር ውስጥ መካተቱን ገልጸዋል፡፡

ከአንድ ሣምንት በፊት የመንግሥት ጋዜጠኞች በደብዳቤ የተጠሩ ሲሆን ለግል ሚዲያ ጋዜጠኞች ግን በስልክ የአንድ ሠልጣኝ ጋዜጠኛ ሥም ዝርዝር እንዲልኩ ብቻ እንድናስፈጽም ነበር የታዘዝነው በማለት አብራርተዋል፡፡ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ የጸረሽብር ሕግ ዋስትናና አተገባበር ሥልጠና እንደተጠናቀቅ የመንግሥትና የግል ሚዲያ አባላት በአንድ ላይ መንግሥት ከጀርባ ሆኖ የሚመራው የአቋም መግለጫ እንዲያወጡ የሚጠበቅ ሲሆን በጋራም በአዳማ ናዝሬት ልዩ ልዩ ሆቴሎች የመዝናኛ ፕሮግራም ተይዞላቸዋል በማለት ምንጮቻችን አሳውቀዋል፡፡

ይሄን ሥልጠና ለማዘጋጀት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የሥልጠናውን ማንዋል ያዘጋጀ ሲሆን ጋዜጠኞቹን የማስተባበር ሥራ በአቶ አንተነህ አብርሃም ለሚመራው “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት” (ኢብጋሕ ) የተሰጠ ኃላፊነት ሲሆን የሠልጣኝና የአሰልጣኞችን አበል ጨምሮ አጠቃላይ የዝግጅቱ የገንዘብ ወጪ ደግሞ ለጸረ ሙስና ኮሚሽን የተሰጠ ኃላፊነት ነው ተብሏል፡፡ የዚህ ኮሚሽን መሪ በቅርቡ ከአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ጋራ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት ተከሰው መታሰራቸውን እንደማያውቁ መናገራቸው ይታወሳል።

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ጋዜጠኞች ስልጠናው “ድራማ ነው” ብለውናል። አንድ በመንግሥት ሚዲያ የሚሰራና በስልጠናው እንዲካፈል የታዘዘ ጋዜጠኛ “ትእዛዝ ስለሆነ መሳተፍ ግዴታዬ ነው፤ አለበለዚያ ባለመሳተፍ ሽብርተኝነትን አበረታተሃል ከማለት አይመለሱም” ሲል በስራ ቦታው ያለውን ውጥረት ገልጡዋል። ከግሉ ሚዲያ የሚገኙ ጋዜጠኞችም የመሳተፍ ፍላጎት ባይኖራቸውም ለጋዜጦቻቸው ሕልውና ሲሉ ሊሳተፉ እንደሚችሉ ተናግረዋል። አንድ ጋዜጠኛ “የጸረ ሽብር ሕጉ የፈጠረው ቀውስ በጋዜጠኞች ስልጠና ሊታከም ነው” በማለት ተሳልቋል።

No comments yet... Be the first to leave a reply!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

Bad Behavior has blocked 4066 access attempts in the last 7 days.