"; _gaq.push(['_trackPageview']);(function() { var ga = document.createElement('script'); ga.type = 'text/javascript'; ga.async = true; ga.src = ('https:' == document.location.protocol ? 'https://ssl' : 'http://www') + '.google-analytics.com/ga.js'; var s = document.getElementsByTagName('script')[0]; s.parentNode.insertBefore(ga, s); })();

ጋዜጠኞች በ3 ተከፍለው ክትትል ይደረግባቸዋል

በኤሊያስ ክፍሌ ፋይል የኢሳት ኢንትርቪው በአቃቤ ሕግ ማስረጃነት ቀረበ

(ሙሉ ገ. እና ኤፍሬም ካሳ)
በአቶ በረከት ስምዖን የሚመራው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ በህትመት ሚዲያ ዘርፍ ፍቃድ አውጥተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የብዙኀን መገናኛ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞችን በሦስት ከፍሎ እንደሚከታተላቸው ታወቀ። ጋዜጠኞቹና ገዘባዎቻቸው “አዎንታዊ/ገንቢ”፣ “አሉታዊ/አፍራሽ” እና “አማካይ” በሚል መመደባቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ በዚህ የአቶ በረከት መደብ ውስጥ በዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ኢትዮጵያዊያንና በኢትዮጵያ የተመደቡ የሌሎች አገራት ጋዜጠኞችም ተካተዋል ብለዋል፡፡

(ሙሉ ገ.)
ቅዳሜ ሕዳር 1 ቀን 2004 ዓ.ም፡- በአቶ በረከት ስምዖን የሚመራው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በኢትዮጵያ ውስጥ በህትመት ሚዲያ ዘርፍ ፍቃድ አውጥተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የብዙኀን መገናኛ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞችን በሦስት ከፍሎ እንደሚከታተላቸው ታወቀ። ጋዜጠኞቹና ገዘባዎቻቸው “አዎንታዊ/ገንቢ”፣ “አሉታዊ/አፍራሽ” እና “አማካይ” በሚል መመደባቸውን ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡

በዚህ የአቶ በረከት መደብ ውስጥ በዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ኢትዮጵያዊያንና በኢትዮጵያ የተመደቡ የሌሎች አገራት ጋዜጠኞችም ተካተዋል ብለዋል፡፡

በኮሙዩኒክሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ውስጥ የሚሠሩ ምንጮቻችን እንደገለጹልን የአቶ በረከት ጽ/ቤት ከመጀመሪያው ሲቋቋም ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ አገራት የኢትዮጵያን ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ሕይወትን ዋቢ አድረገው የተሠሩ የጋዜጠኝነት ሥራዎችን የሚከታተል የሞኒተሪንግ ዴስክ አገልግሎት ነበረው። ከስድስት ወር በፊት በተሠራው የሥራ ማሻሻያ ጥናት ግን በሀገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ሚዲያ የኢትዮጵያንና የመንግሥቷን “መልካም ገጽታ የሚንዱ” የተባሉ የጋዜጠኝነት ሥራዎችን ተከታትሎ ሪከርድ በማድረግና ቀደም ሲል የነበሩ የህትመት ውጤቶችን ጨምሮ ደግሞ ክሊፕ በማድረግ በጽ/ቤቱ በሚገኘው የመገናኛ ብዙኀኑ እና የጋዜጠኞች የግል ፕሮፋይል ውስጥ ፋይል ተደርጎ ተቀምጧል ብለውናል፡፡

በመሆኑም በኢትዮጵያ ውስጥ ማን በምን ጉዳይ ላይ እንደሚጽፍና ምን ዓይነት አቋም እንዳለው፣ ማን በምን የብዕር ሥም እንደሚገለገል ጭምር ተፈርጆ በጽ/ቤቱ ተሰንዶ የሚገኝ ሲሆን “ጉዳቱ የከፋ ነው” ተብሎ ሲታሰብ የፖለቲካ ውሳኔ ተሰጥቶበት ፋይሉ ወደ ደኅንነትና መረጃ ክትትል ቢሮ ይላካል። ከዚያም ጋዜጠኛው ወይም ጸሐፊው የክትትል ቀለበት ውስጥ ይገባል፤ በዚህ ቀለበት ውስጥ ያሉ የሀገር ውስጥና በውጭ አገራት ያሉ ሚዲያዎች ላይ ግልጋሎት የሚሰጡ ጋዜጠኞች አሉ በማለት ምንጮቹ አብራርተዋል፡፡

የእነዚህ ጋዜጠኞች እንቅስቃሴ፣ የስልክ ልውውጥ፣ ኢሜል እና ሲዲኤምኤ ሁሉ በክትትል ቀለበት ሥር ይገባል፤ ለዐቃቤ ሕግ የሚረዱ ማስረጃዎች ከተሰባሰቡ በኋላ በድንገት በሽብርተኝነት ተከሶ ወደ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ይላካል። በዚህ መልክ የተያዘው ጋዜጠኛ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ ድራማውን እውነት ለማስመሰል ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም በሚል ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ይጠይቃል።

ከሰኔ ወር 2003 ዓ.ም ጀምሮ በመታሰር ላይ ያሉ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት በኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያለው የግል ፕሮፋይላቸው በሰሩት ዘገባ፣ በሰጡት ቃለ መጠይቅ እና በጻፉዋቸው ሌሎች ጽሑፎች ይዘትና በመንግሥት ላይ ሊያስከትል በሚችለው ኪሳራ ተሰልቶ “በቃቸው” የተባሉ መርዶ ነጋሪዎች‘ ናቸው ብለውናል፡፡

በኤሊያስ ክፍሌ ፋይል የኢሳት ኢንትርቪው በአቃቤ ሕግ ማስረጃነት ቀረበ

(ኤፍሬም ካሳ)
በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢብዴፓ) ሊቀ መንበር አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚያብሔር፣ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ፣ ሂሩት ክፍሌ፣ የ“ፍትሕ” ጋዜጣ ዓምደኛ ርእዮት ዓለሙ ላይ ዐቃቤ ሕግ ዐርብ ህዳር 1 ቀን አቀርበዋለሁ ያለው ኦዲዮ ቪዲዮ ማስረጃ ባለመሟላቱ ፍርድ ቤቱ ማስረጃውን ለመመልከት ለህዳር 6 ቀን 2004 ዓ.ም ቀጥሯል፡፡
በዕለቱ ተሲያት በኋላ በዋለው ችሎት ዐቃቤ ሕግ የሲዲውን ጭብጥ ለፍርድ ቤት እንዳስረዳው አንደኛው ተከሳሽ በአሜሪካን አገር የሚኖረው ኤሊያስ ክፍሌ የሚያከናውነውን አጠቃላይ “የሽብር ድርጊት” የሚገልጽና በተለያዩ ጊዜያት ይሄን ሥርዓት ለመጣል ያለውን ፍላጎት የሰጠው ቃለ መጠይቅ ያስረዳልኛል ብሏል፡፡
ለእይታ የቀረበው ሲዲ የኢሳት ቴሌቪዥን የውይይት ፕሮግራም ሲሆን በቴሌቭዥን ፕሮግራሙ ላይ ጋዜጠኛ ኤሊያስ ክፍሌ በእንግድነት ቀርቦ ከጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ጋራ በሰሜን አፍሪካና በአረቡ ዓለም ሕዝባዊ ንቅናቄ ላይ ያላቸውን የግል አስተያየትና ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ሲተነትኑ የሚያሳይ ቃለ መጠይቅ ነበር፡፡
10፡30 ሰዓት ሲሆን ዐቃቤ- ሕግ ሲዲው ረጅም ስለሆነ እና ይዘቱም ተመሳሳይ በመሆኑ ሊበቃን ይችላል ብሎ ሌላ ሲዲ በማቅረብ ”ይሄ የድምጽ ሲዲ ደግሞ አራቱ ተከሳሾች ከቁጥር አንድ ተከሳሽ ኤሊያስ ክፍሌ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያሳይ እና ቀደም ብሎ “ፍርድ ቤቱ በሰጠው ፍቃድ መሠረት የመረጃና የደኅንነት ጽ/ቤት ባደረገው ክትትል የተጠለፈ የስልክ ልውውወጣቸው ነው” በማለት ለፍርድ ቤቱ አብራራ፡፡
ፍርድ ቤቱ ወደ ጽሑፍ የተገለበጠው የድምጽ ማስረጃ ካለ ቢቀርብ ጊዜ ለመቆጠብ መልካም ነው ያለ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ “እኛ ድምጻቸው እንዲቀርብ ነው እንጂ ወደ ጽሑፍ የተቀየረው 110 ገጽ አለን” ብሏል፡፡
የ5ተኛ ተከሳሽ የርእዮት ጠበቃ ሞላ ዘገየ “ደንበኛዬ የተከሰሰችው በግብረ አበርነት ነው፤ በመሆኑ ዋና ክሱ የሚለው ደግሞ በዋና ወንጀል አድራጊነትና በተባባሪነት ስለሆነ መጀመሪያ የሰማነው ቪዲዮ መቆረጥ የለበትም፤ ለፍትህ አሰጣጥ ሲባል ዐቃቤ- ሕግ የሚፈልገው ብቻ ሳይሆን ለፍርድ ቤቱ የሚጠቅመውን ሁሉ መታየት አለበት” በማለት ተቃውሟቸውን አሰሙ፡፡
ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ እነዚህ ጠበቆች የቆሙት ለኤሊያስ ክፍሌ ሳይሆን እዚህ ላሉት ተከሳሾች ነውና ስለ እርሱ ጉዳይ ስለማይመለከታቸው መታየት መቀጠሉ ውድቅ ተደርጎ በደኅንነትና መረጃ ክፍል በጠለፋ የተያዘ የድምጽ ማስረጃ እንዲታይልኝ ሲል ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ክሱ የቀረበው በጋራ በመሆኑ መነጣጠል ለፍትሕ አሰጣጡ ስለሚያስቸግር አንደኛው ተከሳሽ ኤሊያስ ክፍሌን የሚመለከቱት ማስረጃዎች ብቻ ቀርበው ያልተከሰሱት ሲሳይ አጌናን የሚመለከተው ግን እንዳይቀርብ ወስኖ ተቋርጦ የነበረው ሲዲ መታየት ቢጀምርም ተከታታይ ክፍሉን ዐቃቤ ሕግ ለማቅረብ ባለመቻሉ (በዘዴ ባለ መፍቀዱ) ማስረጃ የማየቱ ሂደት ሊቀጥል አልቻለም፡፡
ፍርድ ቤቱ የሰውን ማጉረምረም ተመልክቶ ዐቃቤ ሕግ ማስረጃው የሚታይበትን ሁኔታ ያመቻቻችሁ አትመስሉም በማለት ወቀሳ አቅርቦ የድምጽና የምስል ማስረጃዎችን ለማየት እንደገና ለህዳር 6 ቀን 2004 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት እንዲቀጥል ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

No comments yet... Be the first to leave a reply!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

Bad Behavior has blocked 886 access attempts in the last 7 days.