"; _gaq.push(['_trackPageview']);(function() { var ga = document.createElement('script'); ga.type = 'text/javascript'; ga.async = true; ga.src = ('https:' == document.location.protocol ? 'https://ssl' : 'http://www') + '.google-analytics.com/ga.js'; var s = document.getElementsByTagName('script')[0]; s.parentNode.insertBefore(ga, s); })();

በነአንዷለም ላይ ምስክሮች መሰማት ጀመሩ

የመኢዴፓ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ ዘመኑ ሞላ፣ የአንድነት ፓርቲ አባል አቶ አሳምነው ብርሃኑ እና አርቲስት ደበበ እሸቱ (አልመሰክርም ብሎ እያቅማማ ነው የሚል መረጃ አለ) የተካተቱበት 14 ምስክሮች ደግሞ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 9 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት እንዲያቀርብ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በሰኞው ችሎት ላይ “ከሰው ምሥክር ባሻገር የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃ አለኝ” ሲል የገለጸ ሲሆን የቪዲዮው ማስረጃ በእሥር ላይ የነበሩትና ከመንግሥት ጋር በመደራደር በቁም እስር ላይ የሚገኙት ሰዎች ንግግር እና “የደኅንነት ሰዎች ከዚህ ቀደም በሌሎች ላይ የሰሩት አይነት የጀርባ ክትትል ድረማ ቀረጻ ነው” ሲሉ አንድ የፍትሕ ሚንስትር ሠራተኛ ለሪፖርተራችን ተናግረዋል፡፡
በሌላ ዜና “የሙስሊሞች ጉዳይ” መጽሔት አዘጋጆች ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ “ምርመራዬን አላጠናቀኩም” በማለቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቶባቸዋል።

(ሙሉ ገ.፤ አዲስነገር ኦንላይን)

ሰኞ ታህሳስ 9 ቀን 2004 ዓ.ም፡- የፌዴራል ዐቃቤ- ሕግ በሀገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ በሚገኙ 24 የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት እና ጋዜጠኞች ላይ ለፈጠረው የ”ሽብርተኝነት‘ ወንጀል ክሥ ያስረዱልኛል ያላቸውን 21 የሰው ምሥክሮች አርብ ዕለት ለሙሉ ቀን አሰማ፡፡

የመኢዴፓ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ ዘመኑ ሞላ፣ የአንድነት ፓርቲ አባል አቶ አሳምነው ብርሃኑ እና አርቲስት ደበበ እሸቱ (አልመሰክርም ብሎ እያቅማማ ነው የሚል መረጃ አለ) የተካተቱበት 14 ምስክሮች ደግሞ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 9 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት እንዲያቀርብ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ በሰኞው ችሎት ላይ “ከሰው ምሥክር ባሻገር የሰነድና የቪዲዮ ማስረጃ አለኝ” ሲል የገለጸ ሲሆን የቪዲዮው ማስረጃ በእሥር ላይ የነበሩትና ከመንግሥት ጋር በመደራደር በቁም እስር ላይ የሚገኙት ሰዎች ንግግር እና “የደኅንነት ሰዎች ከዚህ ቀደም በሌሎች ላይ የሰሩት አይነት የጀርባ ክትትል ድረማ ቀረጻ ነው” ሲሉ አንድ የፍትሕ ሚንስትር ሠራተኛ ለሪፖርተራችን ተናግረዋል፡፡

ዓርብ ታህሳስ 6 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዐቃቤ ሕግ የሰው ምስክሮቹን በሦስት ከፍሎ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበ ሲሆን የታሳሪዎችን ቤት ንብረት ሲፈትሽና ኢሜል ሲበረብር የነበሩ ታዛቢዎች እና በወንጀል ድርጊቱ ላይ ባለማወቅ በተዘዋዋሪ መንገድ ተካፍለዋል ያላቸውን 21 ሰዎች፣ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ 5 ታዛቢ ምስክሮች፤ በአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አንዷለም አራጌ ላይ 3 ታዛቢ ምሥክሮች፤ በአንድነት ፓርቲ አመራር አባል ናትናኤል መኮንን ላይ 2 ታዛቢ ምስክሮች፤ በአንዷለም አያሌው ላይ 2 ምስክሮች፣ የተቀሩት 8 ምሥክሮች ደግሞ በክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ላይ መሥክረዋል፡፡

በሌላ ዜና “የሙስሊሞች ጉዳይ” መጽሔት አዘጋጆች ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ “ምርመራዬን አላጠናቀኩም” በማለቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቶባቸዋል። ጋዜጠኞቹ አክመል ነጋሽ ፣ ኢስሀቅ እሸቱና አህመዲን ጀበል ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ የደረሰባቸውን እንግልት ለፍርድ ቤቱ መናገራቸውን የአንደኛቸው ወንድም በፌስቡክ ገጹ ላያ ባሰፈረው እማኝነት ገልጿል። ማስረጃ ሳይዝ መክሰስን ዋና ስራው ያደረገው አቃቤ ሕግ ጋዜጠኞቹ “በተለያዩ በራሪ ወረቀቶች አመፅን የሚቀሰቅሱ ጽሑፎችን በመበተን ጠርጥረናቸዋል” ቢልም ለፍርድ ቤቱ የሚያቀርበው ማስረጃ ግን አልነበረውም። ታሳሪዎቹ በቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኙ፣ ቅዱስ ቁርአንን ጨምሮ መጻሕፍት እንዲገቡላቸው እንዳልተፈቀደላቸው ለችሎቱ አመልክተዋል።

ጋዜጠኛ አክመል ነጋሽ የኮምፒውተርና የፌስ ቡክ ፓስወርዳቸውን አስገድደዉ እንደተቀበሏቸው፣ አሸባሪና አክራሪ በሚል እንደሚሰድቧቸው ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ ሌላው ጋዜጠኛ ኢስሀቅ እሸቱ በበኩሉ የተከሰሰበትን ወንጀል ምንነት የሰማነው በቸሎቱ ላይ መሆኑን ተናግሯል። አህመዲን ጀመል ፖሊስ ብዙ መረጃዎችን ከታሳሪዎች ቤትና የሥራ ቦታ መውሰዱን ጠቅሶ በቀጣዩ ቀጠሮም ሌላ ቀጠሮ እንዳይጠይቅ አሳስቦ የዋስ መብት ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ሆኖም ዐቃቤ ሕግ ምርመራውን ሳያጠናቅቅ የዋስ መብት አይሰጥም ያሉት ዳኛ ለመጪው አርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል። ጋዜጠኞቹ የአቶ መለስ መንግሥት በሙስሊሞች የሃይማኖት ነጻነት በመዳፈር “ይህኛውን አስተምህሮ ተከተሉ፣ ያኛውን ተዉ” በማለት የጀመረውን አምባገነናዊ ጣልቃ ገብነት በመቃወም፣ እንዲሁም የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤቱ ከፖሊቲካ ጥገኝነት ነጻ እንዲሆን ወዘተ በመንግሥት ላይ በሚያቀርቡት ሒስ እንደሌሎቹ የአገራችን ጋዜጠኞች ሁሉ ተደጋጋሚ ወከባ ሲፈጸምባቸው እንደነበረ የሚታወስ ነው። የአሁኑ ክስም የዚሁ የዚሁ ወከባ እና አገር አቀፍ መልክ ያለው የአፈና ዘመቻ አካል እንደሆነ ይታመናል።

No comments yet... Be the first to leave a reply!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

Bad Behavior has blocked 4049 access attempts in the last 7 days.