“አንድነት” የታሰሩ አመራሮቹን መፈታት በመጠየቅ የሻማ ማብራት ምሽት አካሔደ
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት) ትናትን እሑድ በእስር ላይ የሚገኙት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ አንዷለም አራጌ እና ሌላው አመራር ናትናኤል መኮንን ከእስር እንዲፈቱ በመጠየቅ የሻማ ማብራት ምሽት አካሔዷል። ስነ ሥርዓቱ የተካሔደው ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ የፓርቲው ሐላፊዎች ባደረጉት የሁለት ቀናት ስልጠና ማጠናቀቂያ ላይ መሆኑ ቃውቋል።
ፓርቲው በየክልሉ ያሉ አመራሮችን፣ አዲስ አበባ ቀበና አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽ/ቤቱ በማሰባሰብ ከዓርብ ጀምሮ ለሁለት ቀናትና ሌሊት ስልጠና መስጠቱንና የተሳካ የፖለቲካ ትግል የልምድ ልውውጥ ማድረጉን ገልጿል።
(ሙሉ ገ./አዲስ ነገር ኦንላይን)
ሰኞ የካቲት 5 ቀን 2004 ዓ.ም፡- አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት) ትናትን እሑድ በእስር ላይ የሚገኙት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ አንዷለም አራጌ እና ሌላው አመራር ናትናኤል መኮንን ከእስር እንዲፈቱ በመጠየቅ የሻማ ማብራት ምሽት አካሔዷል። ስነ ሥርዓቱ የተካሔደው ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ የፓርቲው ሐላፊዎች ባደረጉት የሁለት ቀናት ስልጠና ማጠናቀቂያ ላይ መሆኑ ቃውቋል።
ፓርቲው በየክልሉ ያሉ አመራሮችን፣ አዲስ አበባ ቀበና አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽ/ቤቱ በማሰባሰብ ከዓርብ ጀምሮ ለሁለት ቀናትና ሌሊት ስልጠና መስጠቱንና የተሳካ የፖለቲካ ትግል የልምድ ልውውጥ ማድረጉን ገልጿል።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴ “የቁርጠኝነት፣ የእውቀት እና የኢኮኖሚ ችግሮች” ጎልተው እንደሚገኙ የገለጸው አንድነት ፓርቲ “በተለያዩ ሥልጠናዎች በመታገዝ የገዢውን ፓርቲ የማዳከም ስልቶች አስቀድሞ ማመላከትና መፍትሄ ማበጀትና መማማር” አስፈላጊ እንደሆነ ገልጿል፡፡
የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ባዘጋጀው ከሶማሌ ክልል ተወካይ በቀር ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ 58 ተወካዮች በተገኙበት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት በተካሄደው የአባላት ሥልጠና እና የልምድ ልውውጥ የፓርቲው የፖለቲካ ተግባሮች፤ የሕዝብ ግንኙነትና የኤዲቶሪያል ቦርድ ተግባሮች፤ ማኅበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊና የፋይናንስ ጉዳዮች፤ የፓርቲው ሕግና ሰብዓዊ መብት ጉዳይ ተግባሮች፣ ስለ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት እና ስለ ፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ተግባሮች መወያየታቸውን ሪፖርተራችን የፓርቲውን አመራሮች ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ “ይህ ሥልጠና በፓርቲው ፕሮግራም፣ ደንብ፣ ስትራቴጂና የአምስት ዓመት ዕቅድ ላይ ተመስርቶ የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም በአዲሱ የከተማ ቦታ ሊዝ አዋጅ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፣ የጋራ መግባባት ላይም ተደርሷል፤ ሥልጠናውም በክልሎች ጭምር በስፋት ይቀጥላል” ብለዋል፡፡
በስልጠናና የልምድ ልውውጡ መጨረሻ በተካሔደው የሻማ ማብራት ዝግጅት ፓርቲው በአቶ አንዷለም አራጌንና በአቶ ናትናኤል መኮንን ላይ በእስር ቤት የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተደጋጋሚ እየተካሄደባቸው ነው ሲል መንግሥት ከሷል፤ እንዲፈቱም ጠይቋል። የሻማ ማብራት ዝግጅቱ ታሳሪዎቹ እስከፈቱ ድረስ ቀጣይነት እንደሚኖረውም አስታውቋል፡፡
No comments yet... Be the first to leave a reply!