"; _gaq.push(['_trackPageview']);(function() { var ga = document.createElement('script'); ga.type = 'text/javascript'; ga.async = true; ga.src = ('https:' == document.location.protocol ? 'https://ssl' : 'http://www') + '.google-analytics.com/ga.js'; var s = document.getElementsByTagName('script')[0]; s.parentNode.insertBefore(ga, s); })();

የሃና እና የቻይና ግንኙነት፣ በናዝሬት ፔንስዮን

ሃናን ከሌሎች የ“ናዝሬት ፔንስዮን” ኮማሪቶች ልዩ የሚያደርጋት ከቻይናውያን እና ከፊሊፒንስ አገር ሰዎች ጋራ ያላት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ነው። ሃና ለሀበሻ ወንድ ጊዜ እና ግድ የላትም። ሁልጊዜ በቁመት ከሚያንሷት የሩቅ ምሥራቅ ኮበሌዎች ክበብ ሥር ናት፤ ትኾናለች፤ ይወዷታል። በጊዜ መጥተው እርሷን የእነርሱ ለማድረግ ይሟሟታሉ። ቋንቋ በማይመስል ቋንቋ የኾነ ነገር እያሏት ከት ብለው ይስቃሉ። እርሷም በቻይንኛ ከት ብላ ትስቃለች። ሳቃቸው ቤጂንግ እና ማኒላ ይሰማል።

(ገዛኸኝ ይርጋ)

ሃና አገር አይደለችም፤ ኢትዮጵያዊት የቡና ቤት ሠራተኛ/ ዝሙት አዳሪ እንጂ። ገላዋን ለቻይናውያን እና ለእነርሱው መሰል ዜጎች በማከራየት የምትተዳደር የሌት ለፍቶ አዳሪ። የሃና እና የቻይናውያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት “ናዝሬት ፔንስዮን” ባለጌ ወንበር ላይ ተጀምሮ ጓሮ 150 ብር በሚከፈልበት አልጋ ላይ ፍጻሜውን ያገኛል። ሁል ጊዜ፤ ማታ ማታ።

“ናዝሬት ፔንስዮን” ኮሜርስ አካባቢ ከቴሌ ባር ገባ ብሎ የሚገኝ ሰፊ የአስረሽ ምቺው ቤት ነው። መካከለኛ ገቢ ያላቸው አዲስ አበቤዎች አማርጠው ዝሙት መግዛት ሲሹ ሦስት ቤቶችን ያዘወትራሉ። የፒያሳውን “በአካል. ፀ”፣ የኻያ ሁለት ማዞርያውን “ሰገን”ን  እና የኮሜርሱን “ናዝሬት ፔንስዮን”ን። ሦስቱም ተመሳሳይ የአስተዳደር፣ የአሠራር እና የአመራር ስልትን ይከተላሉ። በእነዚህ ሦስት ቤቶች ምን የመሰሉ ዲጄዎች ምን የመሳሰሉ ሙዚቃዎችን ያጫውታሉ፡፡ ደንበኞችን በሁሉም መልኩ የሚያጫውቱ ብዙ የቡና ቤት ሴቶች ያሉትም በእነዚህ ሦስት የአዲ’ሳባ ዝነኛ መሸታ ቤቶች ውስጥ ነው። ነጭ ጋውን የለበሱ ተቆጣጣሪዎች፣ ደረታቸውን ያሳበጡ ቦዲጋርዶች፣ ቢራ የሚያቀርቡ ወንድ አስተናጋጆች በሦስቱም መሸታ ቤቶች ተመሳሳይ በሚባል መልኩ ይገኛሉ።

ናዝሬት ፔንስዮን ይህ ጽሑፍ በሚጻፍበት ወቅት 27 ኮማሪቶችን ያስተዳድር ነበር። ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ ወደ ሥራ የሚገቡት የናዝሬት የምሽት ኮማሪቶች ልክ እንደ መደበኛ የመንግሥት መሥርያ ቤት የሚተዳደሩበት ያልተጻፈ ሕግ እና ደንብ አላቸው። ለምሳሌ ሁሉም ሴቶች ወደ ሥራ ሲገቡ በረንዳው ላይ በተቀመጠ መዝገብ ላይ ፊርማቸውን እና የገቡበትን ሰዓት ያኖራሉ። ባልተጻፈው ሕግ መሠረት ማንኛዋም ሴተኛ አዳሪ ደንበኛን ማንጓጠጥ በፍፁም አይፈቀድላትም። ለዳንስ ከተዘጋጀው ስፍራ ውጭ በጠረጴዛ ዙርያ ከደንበኛ ጋራ መላፋትም ኾነ መደነስ አይቻልም። ደንበኛ ለአጭሬ /ሾርት/ መስተናገድ ካሻው ሴቷ ለሚመለከተው አለቃዋ በቃል ወይም በጥቅሻ ማሳወቅ ግዴታዋ ነው። ለአዳር ከኾነ ደግሞ የመውጫ ግብር ብር 30 መክፈል ይጠበቅባታል።

ናዝሬት ፔንስዮን በሚያስተዳድራቸው ሴተኛ አዳሪዎቹ ብዛት ብቻም ሳይኾን ጥራትም ጭምር ይታወቃል። ብዙም ጉስቁልና ያልደረሰባቸው፣ ሰውነታቸው ያልሟሸሸ እና የጨዋ የሚመስል፣ የዕድሜ ኪሎ ሜትራቸው ከሰላሳ ያልዘለለ፣ ብዙ ያልተጎበኙ የሚመስሉ ሴቶች ለወንዶች ዐይን ማረፍያ የኾኑበት ቤት መኾኑ ተመራጭ ያደርገዋል ይላሉ የረዥም ጊዜ ደንበኞቹ።

ይህ ቤት ሁለት ዐይነት የዝሙት ዋጋ ሜኑ የሚያቀርብ ነው። ለዜጋ እና ለሀበሻ። በዚህ ቤት አጠራር ዜጋ የሚባሉት ከኢትዮጵያውያን ውጭ ዜግነት ያላቸውን ሲኾን በተለይም የቻይና እና የፊሊፒንስ ዜጎች ላይ ያተኮረ ዐይነት ነው። አንዲት የቤቱ ኮማሪት አንድ የቻይና ዜጋ ለማውጣት መውጫ ግብር 50 ብር መክፈል ሲጠበቅባት ከሀበሾች ጋራ ሲኾን ግን 30 ብር ብቻ በቂዋ ነው። በናዝሬት ፔኔሲዮን ለሾርት/quickie/ አንድ አልጋ ለዜጋ (ቻይና እና ቻይና መሰል ደንበኞች ማለት ነው)150 ብር ሲወሰንባቸው ሀበሾቹ 100 ብር ብቻ ይከፍላሉ።

ሃና ወደዚህ ቤት በከፍተኛ ዝውውር ከመጣች ሁለት ዓመት ለመድፈን ጥቂት ሌሊቶች ይቀሯታል። የሕዋ ርቀት በብርሃን ይለካል፣ ኀይሌ ገብረ ሥላሴ በማይክሮ ሰከንድ ይቆጥራል፣ ሃና በሌሊቶች ብዛት ዕድሜዋን ታሰላለች። የኻያ አራት ወራት ሌሊቶችን ከሞላ ጎደል በናዝሬት ፔንስዮን አልጋዎች ላይ አሳልፋለች። ከዜጎች ጋር።

ሃናን ከሌሎች የ“ናዝሬት ፔንስዮን” ኮማሪቶች ልዩ የሚያደርጋት ከቻይናውያን እና ከፊሊፒንስ አገር ሰዎች ጋራ ያላት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ነው። ሃና ለሀበሻ ወንድ ጊዜ እና ግድ የላትም። ሁልጊዜ በቁመት ከሚያንሷት የሩቅ ምሥራቅ ኮበሌዎች ክበብ ሥር ናት፤ ትኾናለች፤  ይወዷታል። በጊዜ መጥተው እርሷን የእነርሱ ለማድረግ ይሟሟታሉ። ቋንቋ በማይመስል ቋንቋ የኾነ ነገር እያሏት ከት ብለው ይስቃሉ። እርሷም በቻይንኛ ከት ብላ ትስቃለች። ሳቃቸው ቤጂንግ እና ማኒላ ይሰማል።

ኾኖም በአንድ ሌሊት ከአንድ አልያም ከሁለት ቻይናውያን ጋራ ብታድር ነው። ሌሎች ቤቱን የሚሞሉት ቻይና መሰል ዜጎች ግን ሃናን በቢራ አታለው፣ ጭኗን ደባብሰው ሹልክ ይላሉ። ተንጠራርተው አንገቷ ሥር ሳስመው ይሰናበቷታል።

ሃና ገላዋን ለመጋራት ለሚሹ ዋጋዋ የሚያደራድር አይደለም። ለአጭሬ ብር 350፣ እንዲሁም ለአዳር ብር ከ500-650 ትጠይቃለች። ከሀበሾች ይልቅ “ዜጋዎች” ይንከባከቡኛል ትላለች። በተለይ ፊሊፒኖች።

ናዝሬት ፔንስዮን ቀኑ ገና ለዐይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር ይከፈታል። የመጀመርያዎቹ ተስተናጋጆች ግን ቻይናውያን ፊሊፒንሶች ናቸው። አንዳንዴ የሥራ ሽርጣቸውን እንኳ ሳያወልቁ ናዝሬት ተንደርድረው ይገባሉ። ጊዮን አካባቢ አላልቅ ያለውን የኢትዮጵያ ሰማይ ጠቀሱን ናኒ ሕንፃ የሚገነቡ ናቸው ብዙዎቹ። ቀሪዎቹ ደግሞ ቀለበት መንገድን ለማገናኘት የሚተጉ ናቸው። ሃና እና ጓደኞቿ እስኪመጡ ቢራ እየቀማመሱ ፑል በመጫወት ጊዜ ይገድላሉ።

“ናዝሬት ፔንስዮን” ዕድሜ ጠገብ መሸታ ቤት ቢኾንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እድሳት አድርጎ በአዲስ የሥራ መንፈስ ነው ገበያውን የተቀላቀለው። የሰከረ ሰው ራሱን እያየ የሚደንስበት ስፍራን አዘጋጅቷል። በባለጌ ወንበሮች ላይ ቂብ ብሎ መጠጣት ያማረው በቤቱ የግራ ማእዘን አካባቢ መሰየም ይችላል። ኳስ እያየ የጀበና ቡና ከቢራ ጋራ እያጣጣመ ከቤቱ ሴቶች ጋራ ድርድር ማድረግ የፈለገ በረንዳ ላይ በተዘረጋ ሰፊ አዳራሽ ውስጥ ባሉ ሶፋዎች ላይ መንጋለል ይችላል። ቤቱ ውስጥ ቆሞ፣ ቁጭ ብሎ፣ ተንጋሎ ለመጠጣት የሚያስችሉ ምቹ ስፍራዎች ተሰናድተዋል። ሲጋራ፣ ማስቲካ፣ ሶፍት፣ ኮንዶም እና የመሳሰሉትን ለመግዛት ወደ ውጭ መውጣት አይጠበቅም። “አማረ” የሚባል ልጅ እግር የሚያስተዳድራት ትንሽዬ ኪዮስክ ግቢው ውስጥ ተቋቁማለች። እነ ሃና አሁንም አሁንም እየሄዱ አንድ ጊዜ ሲጋራ፣ አንድ ጊዜ ኮንዶም፣ ሌላ ጊዜ ሞባይል ካርድ ይሸምታሉ፡፡

“አማረ ቆንጆ፣ እስኪ የሞባይል ካርድ ስጠኝ፤”

“የቅድም የሲጋራ አልከፈልሽኝም እኮ…፤”

“ብር ጨርሻለኹ አንድ “ዜጋ” ላውጣና አሰጥኻለኹ …”

“ትናንት ለሜሪ 10 ብር ስጣት ብለሽኝ ሰጥቻታለሁ፣ እሱም አለብሽ።”

“አውቂያለኹ! እሰጥኻለሁ አልኩህ እኮ፣ ያንን ዜጋ እያዳከምኩት ነው፣”

“አሁን ካርድ ባለ ስንት ልስጥሽ፣”

“የ‘ተሾመ ቶጋን’ አርግልኝ፤ አዲሱን፣”

ለረዥም ጊዜ በገበያ ላይ ያሉት የሞባይል ካርዶች ባለ 100፣ ባለ 50 እና 25 ብር ብቻ ነበሩ። በቅርቡ ቴሌ ባለ 15 ብር ካርድ ገበያ ላይ እንዲኖር አድርጓል። ‘ተሾመ ቶጋ’ የሚል ስም የወጣለት ይኸው በቅርቡ ቴሌ ያስተዋወቀው ባለ 15 ብር የሞባይል ካርድ ነው። ሃናን ለምን የካርዱ ስም እንደዚያ እንደተባለ ጠየቅኋት። “ሐሳብ አያስጨርስም አለችኝ።” ስቄ ለማባራት ጊዜ ወሰደብኝ። ባለፈው አምስት ዓመት የፓርላማው አፈ ጉባዔ ሲያሳዩት የነበረው ጠባይ እና ሐሳብ የማያስጨርሱ ናቸው ለማለት ይኼ ካርድ ገበያ ላይ መምጣት ነበረበት ለካ።

“ናዝሬት ፔንስዮን” ኪዮስክ ብቻ አይደለም ያለው። አይበለውና ተጠናቀው ሲወጡ ፓንትዎ ቢበላሽ ደጅ ሳይወጡ እዚያው ይሸምታሉ። አይበለውና ለሾርት ሊገቡ ሲሉ የእግርዎ ጠረን አሳሰበዎ። አዲስ ካልሲ እዚያው ይሸጣል። ያውም የቻይና። ለሴቶች ጡት መያዣ እና ንጽሕና መጠበቅያም በግቢው ይሸጣል።

“ናዝሬት” ጥሎበት በቻይና እና ቻይና በሚመስሉ ዜጎች ይወደዳል። የቤቱ 60 በመቶ ደንበኞች እነዚህ ዐይናቸው ጠበብ ያሉ ዜጎች ናቸው። ለምን ይህን ቤት መረጡ ሲባል ግን መልስ የሚሰጥ የለም። በየዕለቱ የእነዚህ ቻይና መሰል ፍጡሮች ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም። የገዥው ፓርቲን የዲፕሎማሲ አዝማምያ ተከትሎ የሚሠራ ቤት ይመስላል። የቤቱ ዲጄዎችም ይህንኑ በመረዳት አንድ መላልሰው የሚያጫውቱት የቻይና ዜማ እንዳለም ተነግሮኛል።

ሁሉም አስተናጋጆች ዐይኑ የጠበበን ሁሉ ቻይና እያሉ ይጠራሉ። ሃና ግን ማን ምን እንደኾነ ጠንቅቃ ከማወቋም በላይ ቋንቋቸውን ትሞካክራለች። ከሁሉም ዜጎች ሃና በፊሊፒንሶች ፍቅር የወደቀች ይመስላል። እርሷ እንደምትለው ፊሊፒኖች ለሴት ልጅ ክብር ይሰጣሉ፣ ጥሩ ይከፍላሉ። ጥሩ ይጋብዛሉ፣ ርኅራሄ አላቸው። ፍቅር ይሰጣሉ። ሃና ከእኔ ጋራ በነበረችበት ወቅት በተደጋጋሚ ከፊሊፒኖች ስልክ ሲደወልላት ሰምቻለኹ። እንግሊዝኛ እና ፊሊፒኖ እየቀላቀለች ታወራቸዋለች።

ብዙዎቹ ፊሊፒኖች ሜድሮክ ውስጥ ሠራተኞች እንደኾኑ ሃና ነግራኛለች። የማያልቀውን ናኒ ሕንፃ የሚሠሩትም እነርሱ ናቸው። ገብርዔል አካባቢ የሚገኘው ዳግም ሚሌኒየም ሆቴል ውስጥ ነው የሚኖሩት። የተወሰኑት ደግሞ “ራስ ሆቴል” ያድራሉ። ሃና በተደጋጋሚ እዚያ ይዘዋት እንደሚሄዱ ትናገራለች። “አንድም ጉዳት አድርሰውብኝ አያውቁም። አብረን አድረን፣ ጋብዘውኝ፣ ሸኝተውኝ እንለያያለን” ትላለች። የተወሰኑት ቋሚ ደንበኞቿን ስም እየጠራች በእርግጠኝነት አግብተው እንደሚወስዷትም ትናገራለች። “ጃክ በጣም ነው የሚወደኝ፣ እኔም እወደዋለሁ፣ የሚስቴን ፍቺ እንደጨረስኩ ይዤሽ እሄዳለኹ ብሎኛል” ትላለች ለእርግጠኝነት ሩብ በጎደለው ተስፋ።

ሃና ከፊሊፒኖ ቋንቋ ወሳኝ የምትላቸውን ቃላት ነግራኛለች። ልክ ትሁን አትሁን ግን የማውቀው ነገር የለም። “ቻካ ቻካ” /ጨዋ ያልኾነ ስድብ/፣ “ኢቃው”/ አንተ፣ አንቺ ማለት ነው/፣ “ሲራዉሉ”/ እብድ፣ “መሃላ ማልጊታ” /እወድኻለሁ/ ፣ “አዲባባህ” /አንተ የኔ ነህ/። የሃና የፊሊፒኖ መዝገበ ቃላት ታድያ ከስድብ እና ከፍቅር ቃላት ዘሎ አያውቅም።

ሃና ከቻይኖች ጋራ ያላት አግባብም እንደፊሊፒኖዎቹ አይሁን እንጂ መልካም ነው። እንደ ቡና ስኒ ተመሳሳይ የኾኑ ቻይናዊያንን አንዱን ከሌላው ለመለየት አፍንጫና ፀጉራቸውን አተኩራ ታያለች። ከዚያም በስማቸው ትጠራቸዋለች። ቻይኖች ጠንካራ ሠራተኞች ናቸው። ጥንካሬያቸው ግን ምሽት ላይ አይደገምም።

እንደ ሃና መረጃ ከኾነ ቻይናውያን እንደሚሠሩት ቀለበት መንገድ ዘለግ ያለ የፆታ ባንዲራ/ብልት/ የላቸውም። ሃና መጠኑን የምትገልጸው ትንሿን የእጅ ጣቷን ለብቻዋ አውጥታ በማሳየት ነው። ይህ መልካም ነገር ነው ለሃና። ለእርሷ ከዚያ ይልቅ ጠረናቸው ምቾት አይሰጣትም። “በጡት ፋንታ ሲጋራ ነው እንዴ እያጠቡ ያሳደጓቸው”  ስትል ትሳለቃለች። ይህን እያወራች “እስኪ ሲጋራ ስጠኝ” ትላለች አስተናጋጁን በጥቅሻ እየጠራች። ሲጋራው ሲመጣላት ግን አስተናጋጁ እንዲለኩስላት አትፈቅድም። በአቅራቢያዋ እየተዝናና ካለ ቻይናዊ ጋራ ሄዳ ለኩስልኝ ትለዋለች። በቻይንኛ ይሽኮረመማል። የሃና እና የቻይናውያን ግንኙነትም ለቀጣዩ ደረጃ ሰዓቱን ይጠብቃል።

6 Responses to “የሃና እና የቻይና ግንኙነት፣ በናዝሬት ፔንስዮን”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

[አንድ ለቅዳሜ!] አጀንዳ ነጠቃ ከባንዲራው ጀርባ?

የባንዲራው ቀን አከባበር እና ዙሪያውን የሚከተሉትን ንግግሮች ለሚተነትን ታዛቢ ኢሕአዴግ ቢያንስ በዚህ ጉዳይ “የቀኞቹን” አጀንዳ ማንሳቱ መሠረታዊ ሽግሽግ መሆኑ የሚያሻማ አይደለም። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት አቀንቃኙን አንድ “ትልቅ” አጀንዳ የሚያሳጣው ነው። እርግጥ ቀደም ሲል እንዳልኩት የባንዲራን ጉዳይ ሁሉም ወገን የሚስማማበት ቢሆን አገረዊ ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ የሚደገፍ ነው። በፓርቲ ፖለቲካ ግን “የአጀንዳው አቀንቃኝ እኔ ነኝ፤ ኢሕአዴግ ደግሞ ተቃዋሚ ነው” በማለት ጉዳዩን አጀንዳ አድርጎ ለቆየው ጎራ ፖለቲካዊ ዋጋ የሚያስከፍለው ነው።
ጥያቄዬ ይህ ጎራ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ተረድቷል ወይ የሚል ነው። ሌላው ቢቀር ኢሕአዴግ አጀንዳውን መጋራቱን ሳይነቅፍ ፖለቲካዊ ነጥብ ለማስቆጠር እንደሚችል ወይም ይችል እንደነበር ያውቃል ወይ? ወይስ ኢሕአዴግ አሁን ቢሆን “ባንዲራው ይወክለዋል ለሚባለው ነገር ተግባራዊ ታማኝነት የለውም” ብሎ የሚከራከርበት አጀንዳ አለው? በአርማው ላይ ሕዝበ ውሳኔ ይካሔድ ብሎ መጠየቅ ለዚህ የተሰጠ የታሰበበት መልስ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል?…

በነገራችን ላይ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲት ንግግር እንዲያቀርቡ የቀረበላቸው ግብዣ እንዳሰቡት አልተሰካም። ጭራሹንም ያልታሰበ ትኩረት ስቦ አሳጣቸው እንጂ። ከንግግሩ በኋላ ወደ መኪናቸው ሲያመሩ አንድ የሚያጽናና ንግግር ለራሳቸው ማድረግ አለባቸው፤ ብቻቸውን….(ለምሳሌ እንዲህ የሚል) ….

የባንዲራው ቀን አከባበር እና ዙሪያውን የሚከተሉትን ንግግሮች ለሚተነትን ታዛቢ ኢሕአዴግ ቢያንስ በዚህ ጉዳይ “የቀኞቹን” አጀንዳ ማንሳቱ መሠረታዊ ሽግሽግ መሆኑ የሚያሻማ አይደለም። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት አቀንቃኙን አንድ “ትልቅ” አጀንዳ የሚያሳጣው ነው። እርግጥ ቀደም ሲል እንዳልኩት የባንዲራን ጉዳይ ሁሉም ወገን የሚስማማበት ቢሆን አገረዊ ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ የሚደገፍ ነው። በፓርቲ ፖለቲካ ግን “የአጀንዳው አቀንቃኝ እኔ ነኝ፤ ኢሕአዴግ ደግሞ ተቃዋሚ ነው” በማለት ጉዳዩን አጀንዳ አድርጎ ለቆየው ጎራ ፖለቲካዊ ዋጋ የሚያስከፍለው ነው።
ጥያቄዬ ይህ ጎራ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ተረድቷል ወይ የሚል ነው። ሌላው ቢቀር ኢሕአዴግ አጀንዳውን መጋራቱን ሳይነቅፍ ፖለቲካዊ ነጥብ ለማስቆጠር እንደሚችል ወይም ይችል እንደነበር ያውቃል ወይ? ወይስ ኢሕአዴግ አሁን ቢሆን “ባንዲራው ይወክለዋል ለሚባለው ነገር ተግባራዊ ታማኝነት የለውም” ብሎ የሚከራከርበት አጀንዳ አለው? በአርማው ላይ ሕዝበ ውሳኔ ይካሔድ ብሎ መጠየቅ ለዚህ የተሰጠ የታሰበበት መልስ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል?…

በነገራችን ላይ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲት ንግግር እንዲያቀርቡ የቀረበላቸው ግብዣ እንዳሰቡት አልተሰካም። ጭራሹንም ያልታሰበ ትኩረት ስቦ አሳጣቸው እንጂ። ከንግግሩ በኋላ ወደ መኪናቸው ሲያመሩ አንድ የሚያጽናና ንግግር ለራሳቸው ማድረግ አለባቸው፤ ብቻቸውን….(ለምሳሌ እንዲህ የሚል) ….
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

No Responses to “[አንድ ለቅዳሜ!] አጀንዳ ነጠቃ ከባንዲራው ጀርባ?”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

[አንድ ለቅዳሜ!] አጀንዳ ነጠቃ ከባንዲራው ጀርባ?

የባንዲራው ቀን አከባበር እና ዙሪያውን የሚከተሉትን ንግግሮች ለሚተነትን ታዛቢ ኢሕአዴግ ቢያንስ በዚህ ጉዳይ “የቀኞቹን” አጀንዳ ማንሳቱ መሠረታዊ ሽግሽግ መሆኑ የሚያሻማ አይደለም። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት አቀንቃኙን አንድ “ትልቅ” አጀንዳ የሚያሳጣው ነው። እርግጥ ቀደም ሲል እንዳልኩት የባንዲራን ጉዳይ ሁሉም ወገን የሚስማማበት ቢሆን አገረዊ ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ የሚደገፍ ነው። በፓርቲ ፖለቲካ ግን “የአጀንዳው አቀንቃኝ እኔ ነኝ፤ ኢሕአዴግ ደግሞ ተቃዋሚ ነው” በማለት ጉዳዩን አጀንዳ አድርጎ ለቆየው ጎራ ፖለቲካዊ ዋጋ የሚያስከፍለው ነው።

ጥያቄዬ ይህ ጎራ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ተረድቷል ወይ የሚል ነው። ሌላው ቢቀር ኢሕአዴግ አጀንዳውን መጋራቱን ሳይነቅፍ ፖለቲካዊ ነጥብ ለማስቆጠር እንደሚችል ወይም ይችል እንደነበር ያውቃል ወይ? ወይስ ኢሕአዴግ አሁን ቢሆን “ባንዲራው ይወክለዋል ለሚባለው ነገር ተግባራዊ ታማኝነት የለውም” ብሎ የሚከራከርበት አጀንዳ አለው? በአርማው ላይ ሕዝበ ውሳኔ ይካሔድ ብሎ መጠየቅ ለዚህ የተሰጠ የታሰበበት መልስ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል?…

በነገራችን ላይ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲት ንግግር እንዲያቀርቡ የቀረበላቸው ግብዣ እንዳሰቡት አልተሰካም። ጭራሹንም ያልታሰበ ትኩረት ስቦ አሳጣቸው እንጂ። ከንግግሩ በኋላ ወደ መኪናቸው ሲያመሩ አንድ የሚያጽናና ንግግር ለራሳቸው ማድረግ አለባቸው፤ ብቻቸውን….(ለምሳሌ እንዲህ የሚል) ….

መስከረም 10 ቀን “የባንዲራ ቀን” ተከብሯል። ብዙ ጊዜ እንደሚሆነው በዘንድሮውም በዓል ቢሆን የቆዩት ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀርም። አቶ መለስ “ባንዲራውን ጨርቅ ብለዋል፤ ስለዚህም እርሳቸውና ፓርቲያቸው ስለባንዲራው ክብር የመናገር የሞራል መሠረት የላቸውም” ከሚለው ዘላለማዊ መርገም ከሚያላብሳቸው ክርክር ጀምሮ በዓሉን ተራ ፖለቲካዊ ድራማ አድርገው እስከሚመለከቱት ዜጎች ድረስ ሐሳቡ ይንሸራሸራል። በኢሕአዴግ “ርእዮተ ዓለም” እና ፖሊሲዎች ተስማሙም አልተስማሙም የባንዲራ ቀን መከበሩን እንደ ክፉ የማያዩ ብቻ ሳይሆን የሚደግፉም ጭምር ብዙ ሰዎች እንደሚኖሩም እርግጥ ነው።

በዚሁ ሰሞን መኢአድ በባንዲራው ላይ የሰፈረው አዲሱ ዓርማ/ምልክት በሕዝበ ውሳኔ እንዲጸድቅ ወይም እንዲለወጥ ጥያቄ አቅርቧል። በባንዲራ ላይ የሚውለውን ዓርማ ምንነት ለመወሰን ሕዝበ ውሳኔ ማካሄድ እንደ ኢትዮጵያ ላለ አገር ቅንጦት ቢመስልም አንድ መሠረታዊ የፖለቲካ ልዩነት መኖሩን ግን ይጠቁመናል። ይህም ልዩነት በኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት (Ethiopian Nationalism) አቀንቃኞች እና የብሔር ተኮር ብሔረተኝነትን (Ethnic Nationalism) እስከ መጨረሻው ጥግ የመጎተት ፍላጎት ባላቸው “ግራ ጠርዘኞች” መካከል ያለ ነው። (አንዳርጋቸው ጽጌ “ብሔር/ብሔረሰብ” የሚለው ጽንሰ ሐሳብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተሰጠውን ትርጉም እና ቦታ በተመለከተ ያቀረበውን አዲስ ሙግታዊ ምልከታ እዚህ ባናነሰውም ለውይይቱ ጠቃሚ መሆኑ አይካድም።)

የሁለቱ ጎራዎች ልዩነት ርእዮተ ዓለማዊ አድማስ ሰፊ ቢሆንም ይህ የብሔረተኝነት ጥያቄ ግን ቁልፍ ከሚባሉት አንዱ ነው። ይህን አጀንዳ ከሌሎቹ ልዩነቶች የተለየ የሚያረገው ነገር ቢኖር ከሁለቱ አንዱን መምረጥ የግድ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን አንዱን ወይም ሌላውን መምረጥ የሚያስከትለው ፖለቲካዊ ትርጉም ለሁሉም ዜጋ ሊባል በሚችል መልኩ ግልጽና ቀጥተኛ መምሰሉም ነው። የብሔረተኝነት ጥያቄው አንዱ መገለጫ ደግሞ ባንዲራ ሆኗል።
ኢሕአዴግ መራሹ የግራ ጠርዘኛ ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነትን ከመሠረቱ ለመናድ ይዞት የተነሳውን ዓላማ ከግቡ ለማድረስ የመጀመሪያ ኢላማው ያደረገው ባንዲራን ነበር፤ በሁለት መንገድ። በአንድ በኩል ረጅም ታሪክ አለው የሚባለውን የኢትዮጵያ ባንዲራ ከነታሪኩ ሲያጣጥል፤ ይህ ዋጋ የሚያስከፍል ሲመስለው ደግሞ ባንዲራው አጀንዳ እንዳይሆን፣ እንዲዘነጋ ለማድረግ ሲጥር ከርሟል።

በሁለተኛው ተመጋጋቢ አካሄዱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነትን የብሔር ተኮር ብሔረተኝነት ዋነኛ ጠላት አድርጎ እያቀረበ፣ ብሔር ተኮሩ ብሔረተኝነት ከአዲስ ተቀናቃኝ ክልላዊ ባንዲራ ጋራ እንዲያያዝ ለማድረግ ሞክሯል። በትምህርት ቤቶችም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎችም ሁለቱ ብሔረተኝነቶች ፈጽሞ አብረው እንደማይሄዱ፤ ቀዳሚው (ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት) በመሠረታዊ የማይቀየር ተፈጥሮው የሁለተኛው ዓይነት ብሔረተኝነት ቋሚ ጠላት እንደሆነ ሲሰብክ ቆይቷል። አካሄዱም የማጥቃት ነበር። (በየክልሎቹ ክልላዊ መዝሙሮች የተንፀባረቁትን ሐሳቦች በሌላ አጋጣሚ መቃኘቱ ይሻላል። እስከዚያው ግን የክልላዊ መዝሙሮቹን ግጥሞች የሚያካፍለን ብናገኝ አንጠላም።)

ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነትን አራምዳለሁ የሚለው ጎራ ራሱን በተከላካይነት ባገኘበት የድኅረ 83 ፖሊተካ፣ ርእዮተ ዓለማዊ ተገቢነቱንም ሆነ የእርሱ ቀዳሚ ምልክት ነው በመባሉ ኢላማ የሆነውን ባንዲራ በሚገባ የመከላከል አቅም ሳያገኝ ቆይቷል። ይህን ታሪካዊ የኀይል ሚዛን ልዩነት ያስከተለውን ፖለቲካዊ ድሉን በዘላቂነት በሚያዘክር መልኩ መቅረጽ የፈለገው ኢሕአዴግ (የግራ ጠርዘኛው ፊት አውራሪ) ይህንኑ አሻራውን በባንዲራው ላይ ለመተው ወሰነ፤ ሁሉ ይቻለዋልና አደረገውም። አሁን በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ የሚታየው የኮከብ ምልክትም በሕግ የባንዲራው አካል ተደረገ። ምልክቱ “አምባሻ” በሚል “የክርስትና ስም” መጠራቱ ግን ነገሩ ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን ክልላዊ ትርጉም እንደተሰጠውም የሚያስታውስ ነው። ለማስታወስ ያህል በግሌ ክልሎች ወይም ብሔረሰቦች የራሳቸው ባንዲራ እንዲኖራቸው መደረጉን አልቃወምም፤ ይህ ባንዲራ እና ምልክትነቱ ግን ከኢትዮጵያ ባንዲራ ጋራ በተቃርኖ የሚተረጎም የነበረበትን አፍላ የኢሕአዴግ የድል ስካር ዘመናት በሐዘን አስታውሳቸዋለሁ።

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከብዙ መርገሙ በቀር ባንዲራን በተመለከተ በረከት ነበረው፤ ግራ ጠርዘኞቹ ከብዙ ታሪካዊ ጠባሳዎቹ ጋራ ኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት ከፍተኛ የማስተሳሰር የተፈተነ ኀይል እንዳለው የሚረዱበት አጋጣሚ ሆነ። የኢትዮጵያ ባንዲራም አዲስ የተፈጠረ እስኪመስል ድረስ አስፈላጊነቱ ተገለጠላቸው። ግራ ጠርዘኞች በተለይም ኢሐአዴግን መሰሎቹ ለተግባራዊ ፖለቲካ ትኩረት የመስጠት ኅልውናዊ ግዴታ ያለባቸው ወይም ይህን የማገናዘብ ፖለቲካዊ ብስለት ያዳበሩት ወደ መካከል (ሚድል ገራውንድ ፖለቲክስ) መምጣት እንዳለባቸው የወሰኑበት ትልቁ ታሪካዊ አጋጣሚ ይህ ጦርነት ይመስለኛል።

አሁን ኢህአዴግ እና አጋሮቹ ለኢትዮጵያ ባንዲራ የሚሰጡት ክብርም የዚህ ርእዮተ ዓለማዊ ሽግሽግ መገለጫ ተደርጎ ሊቆጠር የሚገባው ነው። አሁን የኢትዮጵያን ባንዲራ በማንኛውም መልኩ በአደባባይ የሚያጥላላ የኢሕአዴግ ፖለቲከኛ አይገኝም፤ እንዲያውም ባንዲራው ደም የፈሰሰበት፣ አጥንት የተከሰከሰለት፣ በጋራ ያስከበርነው ነጻነታችን ተምሳሌት መሆኑን እንደ አዲስ ለመንገር የሚዳዳቸው ካድሬዎች ይበዛሉ። በበኩሌ እንኳን ደኅና መጣችሁ ከማለት በቀር የቀደመ ክህደታቸውን አንስቶ ማውገዝን አልመርጥም።

ኢሕአዴግ የባንዲራ ሕግ በማውጣት፣ የባንዲራ ቀንን በአገር አቀፍ ደረጃ በማክበርና በመሳሰለው ድርጊት የተወሰኑ የኢትዮጵያዊ ብሔረተኞች ብቻ ተደርገው ይቆጠሩ የነበሩ አጀንዳዎችን መጋራት ብቻ ሳይሆን መንጠቅም መጀመሩን የማያስተውል ፖለቲከኛ ካለ አዲስ ስም ልናወጣለት ሳይገባ አይቀርም። በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ስለባንዲራው የሚነገረውም የተደራጀ አመለካከት መኖሩን የሚጠቁም ነው። ይህ መጥፎ ነው እያልኩ አይደለም። ግን እውነት ከተቃዋሚው ጎራ መካከል የኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት አቀንቃኝ ነኝ የሚለው ክፍል ይህን ሽግሽግና የአጀንዳ መጋራት/መንጠቅ ሒደት በሁለንተናዊ ትርጉሙ ለመረዳት እየሞከረ ይሆን? በእርግጠም በፖለቲካ ዓለም የሐሳብ ሞኖፖሊ የለም፤ “የእኔ ነው አትንካብኝ” አይባልም። ባይሆን አጀንዳውን እያጠሩ፣ እየተረጎሙ ይጓዛሉ። ርእዮተ ዓለማዊ ሽግሽጉም ሆነ የአጀንዳ ቅርርቡ እውነተኛ እና አገራዊ መግባባትን የሚፈጥር ሆኖ ሲገኝ ደግሞ በሁሉም ጉዳይ መለያየት የግድ ስላልሆነ በደስታ የሚጋሩት ሊሆን ይችላል።

ኢሕአዴግ ርእዮተ ዓለማዊ ሽግሽግ እና የአጀንዳ መጋራት ወይም ማስጣል ስራውን የጀመረው በራሱ በግራ ጠርዘኛው ጎራ ነበር። ይህንንም በተለይ ከኦነግ ጋራ ባለው ግንኙነት እና በኦሮሚያ ክልል ባከናወናቸው የፖሊሲ እና የአፈጻጸም አካሄዶች መገንዘብ ይቻላል። ኢህአዴግ ከፍተኛ የፖለቲካ ተቀባይነት ችግር አለበት በሚባልባቸው ክልሎች አንዱ በሆነው በኦሮሚያ ጥያቄው የአጀንዳ ሳይሆን በመሠረቱ የአፈጻጸም መጠን/ጥራት ወደ መሆን እየወረደ መሆኑ ይሰማል። ከዚህ ካለፈም ክርክሩ የታሪክ ቀዳሚነት ብቻ ወደ መሆን ይወርዳል፤ “ቀድሜ የነበርኩትና ጥያቄውን ያነሳሁት እኔ ነኝ” የሚል አይነት ክርክር። የቋንቋ፣ ራስን የማስተዳደር ወዘተ ጥያቄዎችን በምሳሌነት መጥቀስ ይችላል። አፈጻጸም በራሱና ብቻውን ትልቅ የፖለቲካ አጀንዳ አይሆንም እያልኩ ግን አይደለም።

የባንዲራው ቀን አከባበር እና ዙሪያውን የሚከተሉትን ንግግሮች ለሚተነትን ታዛቢ ኢሕአዴግ ቢያንስ በዚህ ጉዳይ “የቀኞቹን” አጀንዳ ማንሳቱ መሠረታዊ ሽግሽግ መሆኑ የሚያሻማ አይደለም። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት አቀንቃኙን አንድ “ትልቅ” አጀንዳ የሚያሳጣው ነው። እርግጥ ቀደም ሲል እንዳልኩት የባንዲራን ጉዳይ ሁሉም ወገን የሚስማማበት ቢሆን አገረዊ ጠቀሜታው የላቀ በመሆኑ የሚደገፍ ነው። በፓርቲ ፖለቲካ ግን “የአጀንዳው አቀንቃኝ እኔ ነኝ፤ ኢሕአዴግ ደግሞ ተቃዋሚ ነው” በማለት ጉዳዩን አጀንዳ አድርጎ ለቆየው ጎራ ፖለቲካዊ ዋጋ የሚያስከፍለው ነው።

ጥያቄዬ ይህ ጎራ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ተረድቷል ወይ የሚል ነው። ሌላው ቢቀር ኢሕአዴግ አጀንዳውን መጋራቱን ሳይነቅፍ ፖለቲካዊ ነጥብ ለማስቆጠር እንደሚችል ወይም ይችል እንደነበር ያውቃል ወይ? ወይስ ኢሕአዴግ አሁን ቢሆን “ባንዲራው ይወክለዋል ለሚባለው ነገር ተግባራዊ ታማኝነት የለውም” ብሎ የሚከራከርበት አጀንዳ አለው? በአርማው ላይ ሕዝበ ውሳኔ ይካሔድ ብሎ መጠየቅ ለዚህ የተሰጠ የታሰበበት መልስ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል?

አቶ መለስ በ1980ዎቹ ስለ ኢትዮጵያ ባንዲራ በሰጡት መልስ “ከባንዲራው ጀርባ” የሚደረገውን ነገር እንደሚቃወሙ ተናግረው ነበር። “ባንዲራው ጨርቅ ነው” ወይም “ከጨርቁ ጋራ ችግር የለብንም” ማለታቸው የፈጠረው ስሜት አሁንም ድረስ አለ። ምጸቱ ግን አሁን እርሳቸውም “ከባንዲራው ጀርባ” አጀንዳ ነጠቃ መጀመራቸው ብቻ አይደለም። ከባንዲራው ፊት ለፊት ያለውን ኢትዮጵያዊ የጋራ ስሜት ማወደስ መጀመራቸው ጭምር ነው፤ ለዚያውም “በመቶ ዓመት ታሪክ” አላዋቂነት ሳይሆን የሺህ ዓመታት ስልጣኔ፣ የጋራ ታሪክ እና ተጋድሎ እየጠቀሱ…ከባንዲራው ስር።

በነገራችን ላይ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲት ንግግር እንዲያቀርቡ የቀረበላቸው ግብዣ እንዳሰቡት አልተሰካም። ጭራሹንም ያልታሰበ ትኩረት ስቦ አሳጣቸው እንጂ። ከንግግሩ በኋላ ወደ መኪናቸው ሲያመሩ አንድ የሚያጽናና ንግግር ለራሳቸው ማድረግ አለባቸው፤ ብቻቸውን….(ለምሳሌ እንዲህ የሚል)

አንዳንድ ጊዜ ያጋጥማል። ለምሳሌ ንግግር እንድታረግ ተጋብዘሃል እንበል። ግን የሆኑ ሰዎች ይቃወሙሃል። እርግጥ ከነሱ መካከል እንዳይናገሩ የከለከልካቸው፣ የሰደብካቸው፣ በጣም የጎዳሃቸውም ሊኖሩ ይችላሉ። ስለዚህ ድምጽህ እንዳይሰማ ጭምር ይጮሃሉ። ችግሩ ግን እነርሱ የተሰማቸው ሕመም አንተን ሊሰማህ አይችልም፤ የተሰማህ እለት ግን ….። በሆነ አጋጣሚ ብዙም ሳታስብበት “በቀን ሶስት ጊዜ እንበላልን” ተባብለህ ቀጠሮ ሰጠህ እንበል፤ ዝናብ ዘንቦ ቀጠሮ ሊሰረዝ ይችላል። ዝናብ እንዳይዘንብ ማረግ ትችላለህ? ያጋጥማል። አንድ የሆነ ሐሙስ ወይም ቅዳሜ ቀን ስምንት ሰዓት ላይ በአምስት አመት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ እንሰለፋለን የሚል ሕልም ማየት ጀምርክ እንበል፤ በመካከል ሕልሙ ሳያልቅ አምስቱ ዓመት ደርሶ ከእንቅልፍ ልትባንን ትችላለህ። ያጋጥማል። የሆነ ምርጫ አደረክ እንበል፤ ከዚያ ተሸነፍክ ወይም የተሸነፍክ መሰለህ። ትደነግጣለህ፤ ታስራለህ፤ ትገድላለህ። እልህህን ለመወጣት እና ጀግንነትህን ለማስመስከር እንደገና ሌላ ምርጫ ታረጋለህ። 99.6 በሞቶ ታሸንፋለህ፤ እንደገና ትደነግጣለህ…ለምን 100 በመቶ ሳለሸንፍ ቀረሁ የሚለው ጥያቄ እረፍት ይነሳሃል። አይገርምም?

እርዳታ መቀበል ሳይሆን የሚረዱህ ሰዎች ጥያቄ ሰለቸህ እንበል፤ ከዚያ በአምስት ዓመት ውስጥ እርዳታ መቀበል አቆማለሁ ብለህ ለቤተ ዘመድ ቃል ትገባለህ። ግን እርዳታ መቀበል ታቆማለህ ማለት አይደለም። እንደውም እርዳታው እንዲጨምር ትታገላለህ ማለት ነው። መልሰህ ስታስበው የሚሰጥ እስካለ ድረስ መረዳት መጥፎ አይደለም፤ ስለዚህ በአምስተኛው ዓመት ይህን ቃል ትረሳዋለህ። ስንት ቃል ተረስቶ የለምን? ሕይወትም ትቀጥላለች። ከኮሎምቢያ የፈለከውን አትናገር ይሆናል…ንግግርህን ለመረበሽ የሚጮሁ ይኖሩ ይሆናል፤ በኢትዮጵያ ግን ሕይወት አንተ እንደጻፍካት ትተወናለች፤ አንተ እንደተየብካት ትተረካለች…ኦ ኮሎምቢያ ዳግም ፈታችንን አታዪም…ኦ ኢትዮጵያ…

8 Responses to “[አንድ ለቅዳሜ!] አጀንዳ ነጠቃ ከባንዲራው ጀርባ?”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ባይተዋር መምህር ለማይጨበጠው ሥርዐተ-ትምህርት

ስብሰባ . . . ስብሰባ . . . ስብሰባ! ለኢትዮጵያ መምህራን አዲስ አይደለም። የፖለቲካው ግለት ቢጨምር፣ በኑሮ መጎሳቆል ማኅበረሰቡ ቢያጉረመርም፣ ተማሪዎች በፖሊስ ላይ ድንጋይ ቢወረውሩ ወይም መምህራኑ ራሳቸው በተቃዋሚነት ቢጠረጠሩ አስቸኳይ ስብሰባ አያጣቸውም። ድንገተኛ ጥሪ ከየትኛውም የኢሕአዴግ ካድሬ ሊመጣ ይችላል። ፖለቲከኛ ብርቱካን ሚደቅሳ በድጋሚ ወደ እስር ቤት እንዲገቡ ሲደረግ ርምጃው “ሕጋዊ ነው” ለማለት መምህራኑ ለስብሰባ [...]

ስብሰባ . . . ስብሰባ . . . ስብሰባ! ለኢትዮጵያ መምህራን አዲስ አይደለም። የፖለቲካው ግለት ቢጨምር፣ በኑሮ መጎሳቆል ማኅበረሰቡ ቢያጉረመርም፣ ተማሪዎች በፖሊስ ላይ ድንጋይ ቢወረውሩ ወይም መምህራኑ ራሳቸው በተቃዋሚነት ቢጠረጠሩ አስቸኳይ ስብሰባ አያጣቸውም። ድንገተኛ ጥሪ ከየትኛውም የኢሕአዴግ ካድሬ ሊመጣ ይችላል። ፖለቲከኛ ብርቱካን ሚደቅሳ በድጋሚ ወደ እስር ቤት እንዲገቡ ሲደረግ ርምጃው “ሕጋዊ ነው” ለማለት መምህራኑ ለስብሰባ እንደተጠሩት ሁሉ፤ አብዛኞቹ የግዴታ ጥሪዎችም ከመማር ማስተማር ጉዳይ ጋር የቀጥታ ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

ዛሬም፣ አዲስ የትምህርት ዘመን ሲመጣ እንደሚኾነው የ2003 መባቻን ተከትሎ ከመስከረም 4 ቀን 2003 ጀምሮ ስብሰባ እንዲቀመጡ ተጠርተዋል፤ “የትምህርት ንቅናቄ” በሚል ጉዳይ። በግልጽ መፈክሩ እንደተቀመጠው የትምህርት ጥራትን በማምጣት የአምስት ዓመቱን የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማገዝ ለስብሰባው በዓላማነት ተቀምጧል። ይኹንና የትምህርት ጥራት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ በመጠመቅ  ይመጣ ይመስል ስብሰባውን የሚመሩ ካድሬዎች እንደተለመደው ከመፈክሩ አፈንግጠው ስለ አዲሱ ዕቅድ “የማይቀር” ስኬት የሚተርኩበት ሌላኛው መድረክ አድርገውታል። መምህሩ ተቀበለም አልተቀበለ ይኼን ዲስኩር የመስማት ግዴታ አለበት።

የአምስት ዓመቱ ሕልም የሚተረክለት መምህር ግን የትምህርት ጥራት ወጉ እንደቀረበት እንጂ ሌላ በቀጥታ እርሱን የሚመለከት ጉዳይ እንደተነፈገ የሰማ አይመስልም። ባለጉዳዩ መምህር አድማጭ እንጂ ተሳታፊ ባልኾነበት መድረክ ያልተነሳው ጉዳይ ግን አድማስን አካሏል። ካድሬዎችም ሰለ“ሰማያዊው” ዕቅድ ደጋግመው ቢሰብኩም በ2003 የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም “የሥርዐተ ትምህርት” ለውጥ ማድረጉን ለማስተዋወቅ አልደፈሩም።

ይኹንና መንግሥት ባለፈው ሳምንት በብዙኀን መገናኛ ይፋ እንዳደረገው ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ የሚተገበር በሁሉም የክፍል ደረጃዎች የሥርዐተ ትምህርት ለውጥ አድርጓል። የሥርዐተ ትምህርት ለውጡን ተከትሎ አጋዥ የትምህርት መጻሕፍት የታተሙ ሲኾን በተያዘው ዓመት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ይኾናል ተብሎ ይጠበቃል። ለማስፈጸሚያም 150 ሚልዮን የአሜሪካን ዶላር መመደቡን ትምህርት ሚኒስቴሩ ይገልጻል።

መንግሥት መምህራን ቅድመ ዝግጅት ሳያደርጉ እና በቂ ሥልጠና ሳያገኙ የትምህርትም ጉዳይ እንዳሻው መቀያየሩ የተለመደ ነው። በተለይ ደግሞ የአንድ የትምህርት ዘመን እንኳ ዕድሜ ሳይኖራቸው የሚለዋወጡት መርጃ መጻሕፍት የመምህሩን ይኹንታም ኾነ አስተያየት ሳያገኙ ለትግበራ የሚዘጋጁ ናቸው። በተያዘው ወር የኾነውም ጉዳይ ከዚህ ራቀ አይደለም። ይህም ያለመምህሩ ቅድመ እውቅና እና አስተያየት ያልዳበረ እንዲሁም ለመምህሩ ቅድመ ትውውቅ ያልተደረገለት የትምህርት ሥርዐት የሚያመጣው ለውጥ ለባለሞያዎቹ እንቆቅልሽ እንዲኾን አድርጎታል። የትምህርት ጥራት በተደጋጋሚ የካድሬ ስብሰባዎች ሳይኾን በትምህርት ቤቶች ውስጥ መኾኑን ለሚያውቁት መምህራንም ምንነቱ ያልተብራራውን ለውጥ ከሰማይ እንደወረደ ታምር ከመቀበል ውጪ የለውጥ መሣርያ ማድረግ ፈተናቸው ነው።

በርግጥ የሥርዐተ ትምህርት ለውጥ አለ?

ኢሕአዴግ ሥልጣን በያዘ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ካደረገባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የትምህርት ፖሊሲ ነው። አዲሱ የትምህርት እና ሥልጠና ፖሊሲ የተቀረጸው በ1986 ዓ.ም ሲኾን በወቅቱ አዲስ ሥርዐተ ትምህርት፣  የትምህርት አስተዳደር መዋቅር እና የትምህርት መስጫ ቋንቋ በአዲስ መልኩ ትግበራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል። በለውጡም የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ዝግጅት ሥልጣኑን ለክልሎች በመስጠት በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማርን እንደ አንድ አማራጭ እንዲጠቀሙም የፈቀደ ነው።

በወቅቱ የትምህርት ፖሊሲው በያዛቸው ዓላማዎችም ይኹን ዓላማዎቹን መሠረት አደርጎ በተቀረጸው ሥርዐተ ትምህርት የተገኘው የባለሞያም ኾነ የተቀረው ሕዝብ ድጋፍ እጅግ ዝቅ ያለ ነበር። ብዙዎች ተቃውመዋል። በተለይም በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ የኾነው አሃዳዊ (Self-contained) የማስተማር ሥነ-ዘዴ፣ የሁለተኛ ደረጃ የፕላዝማ ትምህርት አሰጣጥ፣ የሲቪክ ትምህርት ይዘት፣ የመጻሕፍት የጥራት ደረጃ እንዲሁም የመምህራን ሥልጠና እና የትምህርት ቤቶች አስተዳደር ኹናቴ ትችት ከቀረበባቸው አጨቃጫቂ ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። እስከ አሁንም ትችቱ አልረገበም፤ አጨቃጫቂነቱም አልቀረም።

ከሁሉ በላቀ ግን በቀጥታ ከሥርዐተ ትምህርቱ ጋራ የተያያዙት የባለሞያ ትችቶች የበረከቱ ነበሩ፤ ናቸውም። በተለይም በሥርዐተ ትምህርቱ መሠረታዊ ጽንሠ ሐሳብ ግድፈቶች፣ የመምህራን ሥርዐተ ትምህርቱን አለመቀበል እና ከሥርዐተ ትምህርቱም ጋራ የማይጣጣሙ የመጻሕፍት ዝግጅቶች በተደጋጋሚ መስተዋል የፖሊሲውን የማያዋጣ መንገድ ቀድመው ያመላከቱ ነበሩ። ትችቶቹ የበረከቱ ይኹኑ እንጂ መንግሥት በወቅቱ መፍትሄ ለመስጠት አልፈቀደም። ከዚህ ይልቅ የባለሞያዎቹን ምክር ወደጎን በመተው የሥርዐተ ትምህርት ማሻሻያ ሳያደርግ የመጻሕፍት ለውጥን በተደጋጋሚ ማድረግ እንደ ዋነኛ መፍትሄ ተቀበለው። በዚህም በትምህርት ገበታ ለአንድ ዓመት እንኳ ሳያገለግሉ በሌላ የሚተኩ መጻሕፍት በርካቶች ነበሩ።

በአብዛኛውን ጊዜም መጻሕፍቱ በመምህራን አስተያየቶች ያልዳበሩ፣ ይወክሉታል ተብሎ የታሰበላቸውን የክፍል ደረጃ የማይመጥኑ እና በግድፈት የተሞሉ መኾናቸው የመማር ማስተማሩን ሂደት ወደኋላ ከሚጎትቱ ሰንኮፎች መካከል ዋነኛውን ሚና የሚጫወቱ ናቸው። መንግሥትም በተደጋጋሚ ለሚያሳትማቸው መጻሕፍት የሚያወጣው ወጪ ሌላ የኢኮኖሚው ራስ ምታት በመኾን ችግሩን ይበልጥ አወሳስቦታል።

ይህን የመንግሥት ግትር አቋም በወጉ ለሚከታተሉ ባለሞያዎች ግን አሁንም የሥርዐተ ትምህርት ለውጥ አደርጌያለሁ የሚለው ዜና የሚዋጥ አይደለም። መጻሕፍትን በየትምህርት ዘመኑ መለዋወጥ እና ሥርዐተ ትምህርትን ሙሉ ለሙሉ መቀየር የተለያዩ ጉዳዮች መኾናቸውን ይረዳሉ። እስካሁን ለመምህራን እንኳ ሊገለጽ የተፈራው ጉዳይ ምን ይዘት ቢኖረው ነው የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ቢኾንም መንግስት ሥርዐተ ትምህርቱን ቀይሬያለሁ በሚለው ዜና ላይ ግን እምነቱ የለም።

ሽግግር Vs ባይተዋሩ መምህር

ባለፉት ዐሥራ ዘጠኝ ዓመታት እንደታየው መንግሥት በመምህሩ በኩል ለማስፈጸም ለሚፈልጋቸው ፖለቲካዊ ጉዳዮች ካልኾነ በቀር መምህሩን አጥብቆ የያዘበትም ኾነ የፈለገበት ጊዜ ማግኘት ይቸግራል። መምህራን ለማስተማር በሚጠቀሙባቸው መጻሕፍት ዝግጅት ላይ የመሳተፍ ዕድል የላቸውም። በትምህርት ሥራ ላይ ምርምር እና ጥናት በማድረግ የመማር ማስተማር ተግባሩን ሂደት ማገዝ የሞያ ግዴታቸው ቢኾንም የመንግሥትን ድጋፍ እና ይኹንታ በማጣት ከምርምር ተግባር እንዲርቁ ይገደዳሉ። አብዛኛውን ጊዜም መንግሥት ለሚፈልገው ፖለቲካዊ ጉዳይ ካልኾነ በቀር በነጻነት የመሰብሰብ መብትን ስለሚነፈጉ የጠነከረ የሞያ ማኅበር በመመሥረት የሞያቸውን ክብር ለማሰጠበቅ እንኳ አልቻሉም።

ይህም በመኾኑ ምክንያት ትምህርት ሚኒስቴር የመርኀ ትምህርት (Syllaubs) ለውጥ በማድረግ ብቻ ሥርዐተ ትምህርቱ እንደተለወጠ አድርጎ በአደባባይ ሲደሰኩር ተመልካች ከመኾን የዘለለ ሚና አልነበራቸውም። እነርሱ ባልተስማሙበት ትምህርት ተምረው ወደ ሌላኛው እርከን መሸጋገር ያቃታቸው ተማሪዎች በትዕዛዝ እንዲያሳልፉ ሲገደዱም ድምፅ የማሰማት አቅም እንደሌላቸውም አሳይተዋል።

ይኹንና ሁሉን በቁጥጥሩ ሥር ያደረገው መንግሥት ከዚህ በፊት ያደርገው እንደነበረው ዛሬም በወጉ ለመምህራን ያላስተዋወቀውን “ሥርዐተ ትምህርት” ለመተግበር እነዚሁኑ ባይተዋር መምህራንን ያሰማራል። በዚህም የአምስት ዓመቱን “ዕቅድ” እውን ለማድረግ እንደሚቻለው ይተነብያል። የትምህርት ሥራ ግን  በክፍል ውስጥ እንጂ በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አይሠራም። ዋነኞቹ ባለጉዳዮች የኾኑት ተማሪ እና አስተማሪ ክፍል ውስጥ ምን እንደሚሠሩ ያውቁታል። ክፍል ውስጥ ባይተዋር የለም፤ የአምስት ዓመቱ ዕቅድም የለም። ያም ኾኖ የተማሪው ውጤት የአገሪቱን ዕጣ ፈንታ ቁልጭ አድርጎ እንደሚያሳይ የሚጠራጠር አይኖርም።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

“መግባት እና መውጣት” ለውይይት ቀረበ

“የሥነ-ጽሑፍ ቀዳሚው ዓላማ ማዝናናት ነው። ማሳቅ በራሱ ትልቅ ዋጋ አለው። እኔ የምጽፈው(በዕለት ተዕለት)የሕይወት ግርግራችን እና ውጣ ውረዶቻችን የማስተውላቸውን ኹነቶች ተንተርሼ ነው። ደራሲው ማዝናናት መቻሉን በራሱ እንደ አንድ ግብ መውሰድ አለበት። መጽሐፌ ከማዝናናቱ በተጨማሪ አንባቢያን አንዳች ሕይወታዊ ቁም ነገር ወይም ምስጢር የሚያገኙበት ከኾነ ግቤን በበለጠ መትቼያለሁ ማለት ነው። በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙት ቀልዶች መሠረት እና መነሻ ትካዜ ነው። መሪ እንጂ ደራሲ አገር የመለወጥ አቅም የለውም። መንግሥቱ ኀይለማርያም እንጂ መንግሥቱ ለማ አገር የመለወጥ አቅምና ብቃት የለውም. . .” ሲል መልሷል።

(ባህሩ ጀማል)

ሚዩዚክ ሜይዴይ የኢትዮጵያ የመጻሕፍት ንባብ እና ውይይት ክበብ በየ15 ቀኑ በተመረጡ መጻሕፍት ላይ ውይይት ሲያደርግ ሰባት ዓመታትን አስቆጥሯል። ይኸው ክበብ ባለፈው ሳምንት እሁድ በቅርቡ ለኅትመት የበቃውን “መግባት እና መውጣት” የተሰኘውን የበእውቀቱ ስዩምን መጽሐፍ በአምስት ኪሎው የብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ ውይይት እንዲካሄድበት አድርጓል።

በእውቀቱ በቅርቡ ለኅትመት ያበቃው “መግባት እና መውጣት” ከቀኑ 8፡00 እስከ 11፡00 ድረስ የተካሄደ ሲኾን ለውይይቱ የሚኾነውን የመነሻ ሐሳብ ያቀረቡት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቴአትር ጥበባት ዲፓርትመንት የሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሠሩት መምህር ጳውሎስ አእምሮ ናቸው። የመምህር ጳውሎስ የመነሻ ሐሳብ መገምገሚያ ነጥቦች ለታዳሚው መቅረብ ከጀመሩ ከግማሽ ሰዓት በኋላ በእውቀቱ ወደ አዳራሹ ዘግይቶ ገባ።

መምህር ጳውሎስ የበእውቀቱን “መግባት እና መውጣት” በተለምዶ ይቀርብ ከነበረ መመዘኛ እና መገምገሚያ በተለየ መንገድ ነበር ያቀረቡት። መሠረታዊ በኾኑት የሥነ ጽሑፍ አላባውያን ላይ በመንተራስ “ጭብጡን”፣ “ሤራውን”፣ “የቋንቋ አጠቃቀሙን”፣ “የገጸ ባሕርያት አሳሳሉን” እና “ቅርጹን” ወደ ማየት አላዘነበሉም። ይልቁኑም ዕይታቸውን መጽሐፉን ከሲግመንድ ፍሮይድ የፍካሬ ልቡና (psychoanalysis)አቅጣጫ ለማየት እንደፈለጉ ገልጸዋል። ፍካሬ ልቡና የሚለውን አቻ ትርጓሜ ለሳይኮአናሊሲስ የሰጡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነ ጽሑፍ መምህር የኾኑት አቶ ቴዎድሮስ ገብሬ ናቸው። መምህር ቴዎድሮስ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ ባሳተመላቸው “በይነ ዲስፕሊናዊ የሥነ ጽሑፍ ንባብ” በተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ ያቀረቡትን ትንተና በመንተራስ ነበር።

በአዳራሹ ውስጥ ታድመው የነበሩ ሰዎች ለደራሲው እና ለመምህር ጳውሎስ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። በእውቀቱ ጥያቄዎቹን ለመመልስ ወደ አዳራሹ መድረክ ሲወጣ የመድረኩን መንፈስ በፈገግታ እንዲታጀብ አድርጓል። “ብዙ ጊዜ ለመናገር ወደ መድረክ ስወጣ ለፍርድ የቀረብኩ ይመስለኛል” ብሎ ታዳሚውን አስቆ ነበር። በእውቀቱ በመድረኩ ላይ “መውጣት እና መግባት” ን እንዲጽፍ ያስቻሉትን ምክንያቶች ተናግሯል።

“ለበርካታ ሳምንታት በ“አዲስ ነገር” ጋዜጣ ላይ “መግባት እና መውጣት” በሚል ርእስ ሲቀርቡ የነበሩትን ጽሑፎች በማዳበር፣ በማሻሻል እና አዳዲስ ምዕራፎችን በመጨመር ወደ መጽሐፍ ማሳደጉ በእኔ የተጀመረ አይደለም። ይህን ልምድ የወሰድኩት ከሩሲያ ደራሲያን ነው ማለት እችላለሁ። የሊዮ ቶልስቶይ “አና ካራኒና”  እና “ሰላም እና ጦርነት” ለረጅም ጊዜያት በጋዜጣ ላይ ይቀርቡ ነበር። ፌዮዶር ዶስቶቨስኪም ተመሳሳይ ልምድ ነበረው። በእኔ መጽሐፍ ውስጥ ዐቢዩ መቼት (ቤቶቨን) ካፌ ነው። ካፊቴሪያ ደግሞ ለመግባት እና ለመውጣት ይመቻል” ብሏል።

“አዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ ጽሑፎቹን ሲያነቡ የነበሩ አንዳንድ አንባቢያን “በዕውቀቱ ሥነ-ጽሑፍን ቢዝነስ አድርጎታል” ይላሉ። ለእነዚህ ሰዎች ያለህ መልስ ምንድን ነው? ሲል አንድ ታዳሚ ላቀረበለት ጥያቄ በዕውቀቱ እንዲህ ሲል መልስ ሰጥቷል፦ “አንድ ሰው መጽሐፍ ሲደርስ የደራሲነት ሞያውን እየተወጣ ነው። ለእኔ ደራሲነት ሞያዬ ነው። ሥራዬ መጻፍ ነው፤ አንድ ገበሬ በብርቱ ድካም ያመረተውን እህል እንደሚሸጥ ሁሉ እኔም መጽሐፍ እሸጣለሁ። ኾኖም የምጽፈው ሽያጭን ዋና ግቤ አድርጌ አይደለም”።

በዕውቀቱ ስዩም የቀረቡለትን ጥያቄዎች እንደመለሰ በውይይት አዳራሹ የመጨረሻ ረድፍ መጀመሪያ የተቀመጠበት ወንበር ላይ ከፍቅረኛው ተዋናይት መቅደስ ወርቅነህ ጎን ቢቀመጥም ከታዳሚዎች የቀረቡት ተጨማሪ ጥያቄዎች ወደ መድረኩ እንዲመለስ አስገድደውታል፡፡ በዚህ ወቅትም “ያው እየተወያየንበት ያለው መጽሐፍ “መግባት እና መውጣት” እንደመኾኑ ስገባ እና ስወጣ እንደማትቀየሙ ተስፋ አደርጋለሁ” በማለት ታዳሚውን አስቋል።

“በመጽሐፉ ውስጥ ጳውሎስ ኞኞ እና ከበደ ሚካኤል ላይ አሉታዊ በኾከነ መልኩ ተሳልቀኻል። ምክንያትህ ምንድነው?” የሚል ስሜት ላላቸው ተደጋጋሚ ጥያቄዎችም ደራሲው መልስ ሰጥቷል፤ “የከበደ ሚካኤልን እና የጳውሎስ ኞኞን ስም ተዋስኩ እንጂ በመጽሐፉ ውስጥ የሰጠኋቸው ሚና ልቦለድ ነው። ይህን እንደ ቴክኒክ ነው የተጠቀምኩት። ሌላ ስም ብጠቀም የምፈልገው ተጽዕኖ አይኖውም” ብሏል።

ሌላኛው ጠያቂ ያተኮሩት የመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት ወደ መሳቅ ያዘነበለ ነው በሚለው ላይ ነው። ጠያቂው “ከእኔ በፊት የተናገሩት እንደገለጹትም “መግባት እና መውጣት” በርግጥም በጣም የሚያስቅ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ የኮሜዲ ፊልም እስኪመስለኝ ድረስ በጣም አስቆኛል። የሥነ-ጽሑፍ ዋና ዓላማ ግን ማሳቅ አይመስለኝም። ደራሲው ትውልድን የመቅረጽ እና አገርን የመለወጥ ሐላፊነት አለበት። አንተ ይህን እንዴት ትመለከተዋለህ?” ላለው እና ከሌሎችም ታዳሚዎች ለተነሡ ተያያዥ ጥያቄዎች በዕውቀቱ ስዩም በምሳሌ እና በቧልት አዋዝቶ መልስ ሰጥቷል።

“የሥነ-ጽሑፍ ቀዳሚው ዓላማ ማዝናናት ነው። ማሳቅ በራሱ ትልቅ ዋጋ አለው። እኔ የምጽፈው(በዕለት ተዕለት)የሕይወት ግርግራችን እና ውጣ ውረዶቻችን የማስተውላቸውን ኹነቶች ተንተርሼ ነው። ደራሲው ማዝናናት መቻሉን በራሱ እንደ አንድ ግብ መውሰድ አለበት። መጽሐፌ ከማዝናናቱ በተጨማሪ አንባቢያን አንዳች ሕይወታዊ ቁም ነገር ወይም ምስጢር የሚያገኙበት ከኾነ ግቤን በበለጠ መትቼያለሁ ማለት ነው። በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙት ቀልዶች መሠረት እና መነሻ ትካዜ ነው። መሪ እንጂ ደራሲ አገር የመለወጥ አቅም የለውም። መንግሥቱ ኀይለማርያም እንጂ መንግሥቱ ለማ አገር የመለወጥ አቅምና ብቃት የለውም. . .” ሲል መልሷል።

በውይይቱ ወቅት ገምጋሚው መምህር ጳውሎስ አእምሮ የደራሲውን ጥልቅ የሕይወት ምልከታዎች፣ ጥልቅ ንባብ እና የሰውን ውስጣዊ ሥነ-ልቡና የመረዳት ልዩ ክህሎት በተደጋጋሚ አወድሰዋል። በውይይቱ ማሳረጊያ አካባቢ አንድ አዛውንት ታዳሚ ደራሲው በመጽሐፉ ውስጥ የተጠቀማቸውን እንደ “እግሮቼን አቀባብዬ” እና “ሽንትን መቋጨት” ያሉ በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ከዚህ በፊት ያልተስተዋሉ እንግዳ እና ግራ ገብ ሐረጎችን እና አገላለጾችን ለምን እንደተጠቀመ ጠይቀዋል። በዕውቀቱም “ደራሲው አዳዲስ ቃላት እና አገላለጾችን በአዳዲስ አገባብ የመጠቀም እና የማስተዋወቅ ነጻነት አለው። “ነጠላ መቋጨት” እንዲሁም “ሐሳብን መቋጨት” እንደሚባለው ሁሉ “ሽንት መቋጨት” የሚለውን በአዲስ አውድ እና አገባብ ተጠቅሜያለሁ። “ጠመንጃዬን አቀባብዬ” እንደሚባለው ሁሉ መጽሐፉ ውስጥ በተቀመጠው አገባብ “እግሮቼን አቀባብዬ” የሚለውን ተጠቅሜያለሁ” ብሏል።

ውይይቱ ካለቀ በኋላ ሚዩዚክ ሜይዴይ ከተመሠረተ ጀምሮ የመጻሕፍት ንባብ እና ውይይት ክበቡ ቋሚ ታዳሚ የኾነው አርታኢው ተስፋዬ ወ/ጻድቅ “ገምጋሚው መጽሐፉን በመሠረታዊ የሥነ-ጽሑፍ መመዘኛዎች አንጻር ቢያቀርበው ከዚህ በበለጠ ብርቱ የሐሳብ ፍጭቶች ሊኖሩ ይችሉ ነበር” ነበር ሲል ተናግሯል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ክፍል ሁለተኛ ዓመት ተማሪ የኾነው “ኤሊያስ ተፈሪ” በመምህር ጳውሎስ አእምሮ አቀራረብ ደስተኛ ነበር። “ቴዎድሮስ ገብሬ እንደሚለው ሥነ ጽሑፍ በይነ ዲሲፕሊናዊ(ሁሉን አቀፍ) ነው። መምህር ጳውሎስም በሳይኮአናሊስስ መነጽር የበዕውቀቱን “መግባት እና መውጣት” ባልለመድነው ኹኔታ ተመልክተውታል። ገምጋሚው ሌሎች ባለሞያዎችም መጻሕፍትን በተለየ ዲሲፕሊን መመልከት እንደሚችሉ ዐሳይተውናል። በዚህ ክበብ ውስጥ እንደዚህ ዐይነት የተለዩ አቀራረቦች እምብዛም የተለመዱ አይደሉም”

ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም ሥራዎቻቸው በሚዩዚክ ሜይዴይ የመጻሕፍት ንባብ እና ውይይት ክበብ ለሂስ እና ለግምገማ በሚቀርብበት ወቅት በአካል ከሚገኙ ጥቂት ደራሲያን አንዱ ነው። በዕውቀቱ ስዩም ከዚህ ቀደም ሦስቱ መጻሕፍቱ በአምፔሪያል ሆቴል ለውይይት የቀረቡ ጊዜም(ሚዩዚክ ሜይዴይ ውይይቶችን በብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ ማካሄድ የጀመረው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ነው) በአካል ተገኝቷል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው መምህርና ሃያሲ ገዛኽኝ ጌታቸው “ኗሪ ዐልባ ጎጆዎች” የተሰኘውን ተወዳጅ የግጥም መድብሉን እና የመጀመሪያ መጽሐፉን፣ ሟቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር፣ የሥነ ጽሁፍ ተመራማሪ እና ሃያሲ የነበረው ብርሃኑ ገበየሁ “በራሪ ቅጠሎች” የተሰኘውን የአጫጭር ልቦለዶች እና ታሪኮች መድበሉን እና ሁለተኛ መጽሐፉን እንዲሁም አሁን የመን ሰንአ የሚገኘው የሥነ ጽሑፍ ሃያሲ አብደላ ዕዝራ “እንቅልፍና ዕድሜ” የሚለውን የረጅም ልቦለድ ሥራውን በኢምፔሪያል ሆቴል ባቀረቡት ሂስ ላይ ውይይት ተካሄዶ ነበር።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

‹‹የዳንኩት በህክምና ሳይሆን በኢትዮጵያ ህዝብ ፀሎት ነው››ድምፃዊ ታምራት ሞላ

ለረዥም ጊዜት በደም ካንሰር/ሉኩሚያ  በሽታ ሲሰቃይ ቆይቶ አሁን በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኘው ድምፃዊ ታምራት ሞላ ከበሽታው ካገገመ በኋላ ከጎኑ የቆሙትን ሁሉ ለማመስገን ልዩ የጥበብ ድግስ  አሰናድቷል፡፡ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 15 በማዘጋጃ ባህልና ትያትር አዳራሽ የተዘጋጀው ይኸ ልዩ የጥበብ ድግስ የታምራት ሞላ ሙዚቃ አድናቂዎቹ በሙሉ በነፃ እንዲታደሙ ድምፃዊው ግብዣውን አቅርቧል፡፡ ከ46 ዓመታት በላይ በሙዚቃ ህይወት የቆየው [...]

ለረዥም ጊዜት በደም ካንሰር/ሉኩሚያ  በሽታ ሲሰቃይ ቆይቶ አሁን በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኘው ድምፃዊ ታምራት ሞላ ከበሽታው ካገገመ በኋላ ከጎኑ የቆሙትን ሁሉ ለማመስገን ልዩ የጥበብ ድግስ  አሰናድቷል፡፡ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 15 በማዘጋጃ ባህልና ትያትር አዳራሽ የተዘጋጀው ይኸ ልዩ የጥበብ ድግስ የታምራት ሞላ ሙዚቃ አድናቂዎቹ በሙሉ በነፃ እንዲታደሙ ድምፃዊው ግብዣውን አቅርቧል፡፡

ከ46 ዓመታት በላይ በሙዚቃ ህይወት የቆየው ድምፃዊ ታምራት ከአመት በፊት ጤንነቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶ እንደነበረና በአገር ቤትና በሰሜን አሜሪካ ልዩ የእርዳታ ርብርብ ሲካሄድለት ቆይቶ ነበር፡፡ በመጨረሻም  በሼህ ሁሴን አላሙዲን አገዛ የውጭ ህክምና አግኝቶ ጤንነቱን ማግኘት ችሏል፡፡

ክብር ለአንጋፋዎቹ  በሚል ርእስ ይህንን ልዩ የምስጋና የጥበብ ድግስ በማሰናዳት ረገድ ‹‹ሙሉ ሰለሞን ፍኖተ ምስጋና የበጎ አድራጎት ድርጅት››እና የአፍሪካ ሴት ደራሲያን ማህበር ትብብር አድርገዋል፡፡

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ለኮሪያ ዘማቾች የ‹‹እናመሰግናለን›› ልዩ ዝግጅት ተደግሷል

በኮሪያ መንግስትና በኢትዮጵያ የኮሪያ ኤምባሲ አዘጋጅነት የቃኘው ዘማቾች 60ኛ ዓመት ልዩ ክብረ በዓል መሰናዳቱን ኤምባሲው ለአዲስ ነገር ኦንላይን ገለፀ፡፡ የዘንድሮው ክብረ በዓል ‹‹ You Are Not Forgotten›› በሚል መሪ ቃል ለቃኘው ዘማቾች ምስጋና በማቅረብ እንደሚከበር ኤምባሲው ጨምሮ ገልጧል፡፡ የፊታችን ሰኞ በሸራተን አዲስ እንዲሁም በማግስቱ ጥቅምት 18 በብሔራዊ ትያትር በሚካሄደው በዚህ ልዩ የምስጋና ፕሮግራም ዲፕሎማቶችና ልዩ [...]

በኮሪያ መንግስትና በኢትዮጵያ የኮሪያ ኤምባሲ አዘጋጅነት የቃኘው ዘማቾች 60ኛ ዓመት ልዩ ክብረ በዓል መሰናዳቱን ኤምባሲው ለአዲስ ነገር ኦንላይን ገለፀ፡፡ የዘንድሮው ክብረ በዓል ‹‹ You Are Not Forgotten›› በሚል መሪ ቃል ለቃኘው ዘማቾች ምስጋና በማቅረብ እንደሚከበር ኤምባሲው ጨምሮ ገልጧል፡፡

የፊታችን ሰኞ በሸራተን አዲስ እንዲሁም በማግስቱ ጥቅምት 18 በብሔራዊ ትያትር በሚካሄደው በዚህ ልዩ የምስጋና ፕሮግራም ዲፕሎማቶችና ልዩ ልዩ የመንግስት ባለስልጣናት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩ አምባሳደር ሞሀመድ ድሪር ከበዓሉ ታዳሚዎች መካከል ናቸው፡፡

ሰኞ በሸራተን አዲስ ለሚከበረው የኮሪያ ብሔራዊ ቀን የኮሪያ ዘማቾች የሚታሰቡ ሲሆን ጥቅምት 18 በብሔራዊ ትያትር በተዘጋጀው ድግስ ከ1000 በላይ የኮሪያ ዘማቾች ከነቤተሰቦቻቸው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህንን ልዩ የምስጋና በዓል ለማድመቅ “The Little angels” የተሰኙ በተባበሩት መንግስታት አለምአቀፍ የሰላም ፌዴሬሽን ስር የታቀፉ 70 የሚሆኑ የኮሪያ ታዳጊ ህፃናት ልዩ የሙዚቃና የዳንስ ትርኢት ለማቅረብ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የዚህ ቡድና አባላት የባሌ ዳንስና የኮሪያ ባህላዊ ሙዚቃዎችን እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡ ቡድኑ ከዚህ ዝግጅት በኋላ በቤተ መንግስት የምሳ ግብዠና የፎቶ ስነስርዓት እንደሚካሄድለት ተገልጧል፡፡

በብሔራዊ ትያትር በሚቀርበው ልዩ የምስጋና ዝግጅት ለቃኘው አባላት ‹‹አንረሳችሁም፣ እናመሰግናለን›› በሚል በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ሚስተር ቻንግ ሱን ሱክ በተገኙበት ምስጋና እንደሚቀርብላቸው የበአሉ አስተባባሪ ወይዘሪት ቃልኪዳን ሀይሉ  አስታውቀዋል፡፡

ለዚህ የኮሪያና ኢትዮጵያ ግንኙነት መታሰቢያ አፍንጮ በር አካባቢ ከዚህ ቀደም ሀውልት እንደቆመ ሲታወቅ ለተመሳሳይ የምስጋና ፕሮግራም ከወራት በፊት ሀያ የሚሆኑ የቃኘው ባታሊዮን አባላት ኮሪያ ድረስ ተጋብዘው እንደሄዱ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በሁለቱ ኮሪያዎች ጦርነት ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ሀይል ጋር በመሆን ከአንድ ሺህ እስከ 3500 የሚሆኑ ወታደሮችን ቃኘው ባታሊዮን በሚል ስም በጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ የሚመራ ሰራዊት መላኳ ይታወሳል፡፡ በዚህ ጦርነት 121 ወታደሮች እንደሞቱና 536ቱ እንደቆሰሉ ይገመታል፡፡ የኮሪያ ጦርነት እ.ኤ.አ ከ1950 እስከ 1953 ድረስ የዘለቀ ጦርነት ሲሆን የሁለቱን ኮሪያዎች ሰሜንና ደቡብ መለያየት ያስከተለ ነበር፡፡

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

“የብርሃን ናፍቆት” ረቡዕ ዕለት በቸርችል ሆቴል ተመረቀ

የመጽሐፉ ደራሲ እንዳለ ሸዋንግዛው መጽሐፉን በረጅም ልቦለድ መልክ ያቀረበው ጅማ ውስጥ የጀምበር የቴአትር ክበብ አባል እያለ በደረሳቸው እና በጅማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ዘንድ ለበርካታ ዓመታት በመታየት ከፍተኛ ተቀባይነትን ባስገኙለት የመጀመርያ ቴአትሩ “አቤል እብዱ” እና በሁለተኛ ቴአትሩ “ የብርሃን ናፍቆት” ላይ ተመስርቶ ነው።

በሦስት ቤተሰቦች ሕይወታዊ መስተጋብር ላይ እያጠነጠነ አቤል የአእምሮ ሕመምተኛውን በአስተኔ ገጸ-ባሕርይነት እየተረከ በማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው እና በ230 ገጾች የተጠናቀረው “የብርሃን ናፍቆት” የተሰኘው የረጅም ልቦለድ መጽሐፍ ረቡዕ መስከረም 12 ቀን 2003 ዓ.ም ቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ በቸርችል ሆቴል ተመረቀ።

የመጽሐፉ ደራሲ እንዳለ ሸዋንግዛው መጽሐፉን በረጅም ልቦለድ መልክ ያቀረበው ጅማ ውስጥ የጀምበር የቴአትር ክበብ አባል እያለ በደረሳቸው እና በጅማ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ዘንድ ለበርካታ ዓመታት በመታየት ከፍተኛ ተቀባይነትን ባስገኙለት የመጀመርያ ቴአትሩ “አቤል እብዱ” እና በሁለተኛ ቴአትሩ “ የብርሃን ናፍቆት” ላይ ተመስርቶ ነው።

ደራሲው “የብርሃን ናፍቆት” የተሰኘውን መጽሐፉን ያቀረበው አቤል እ. በሚል ስም ሲሆን ይህን ያደረገውም አቤል የአእምሮ ሕመምተኛው በጅማ ነዋሪዎች ዘንድ በልዩ ኹኔታ የሚታወስ ስለኾነ ነው “ሁለቱም ቴአትሮቼ በጅማ ዩኒቨርስቲ፣ በሲኒማ ጅማ፣ በጅማ መምህራን ኮሌጅ፣ በቦንጋ፣ በሚዛን እና በቴፒ ለረጅም ጊዜያት ታይተው ከፍተኛ ተቀባይነትን አግኝተው ነበር፡፡ የጅማና አካባቢዋ ነዋሪዎች አቤል የአእምሮ ሕመምተኛውን በተለየ ኹኔታ ስለሚስታውሱት እና “የብርሃን ናፍቆት” መጽሐፉ አስተኔ ገፀ-ባሕርይ ስለኾነም ነው መጽሐፌን በሱ ስም ያወጣሁት” ብሏል።

የ”ብርሃን ናፍቆት” ባለፈው ዓመት ታትሞ ሁለት ዕትም ያለቀ ቢኾንም መጽሐፉ ነገ ትላንት ሲመረቅ የመጀመርያው ነው። ከጥቂት ወራት በፊት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት በጀመረው ባለ አራት ኮከብ ሆቴሉ ቸርችል ሆቴል በተካሄደው የመጽሐፉ የምረቃት ሥነ ሥርዐት ላይ የ”ወዲያነሽ” እና “ጉንጉን” በተሰኙት የረጅም ልቦለድ መጻሕፍቱ የሚታወቀው ደራሲ ኀይለመለኮት መዋዕል ስለ “የብርሃን ናፍቆት” አጭር ዳሰሳ አቅርቧል። ገጣምያኑ ኤፍሬም ስዩም፣ ትዕግስት ማሞ፣ የኢትዮጵያ ሴት ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት የሆነችው ደራሲና ገጣሚት የምወድሽ በቀለ፣ ተዋናይት እና ገጣሚት የዱርፍሬ ይፍሩ እና የመጽሐፉ ደራሲ እንዳለ ሸዋንግዛው በዚሁ ዝግጅት ላይ የግጥም ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል።

“የመጽሐፉ የሽፋን ሥዕል ከጀርባዋ እርቃኗን የኾነች ሴትን ማሳየቱ መጽሐፉን ወሲብ ተኮር (Pornographic) ሥነ-ጽሑፍ አያስመስለውም?” ተብሎ የተጠየቀው ደራሲው “በመጽሐፉ የሽፋን ገጽ ላይ ከሴቷ በከፊል የተራቆተ ገላ ሌላ የሙዚቃ ኖታዎች፣ የሰማይ ክዋክብት፣ የወንዴ እና የሴቴ የዘር ፍሬ እንዲሁም አበባ ይታያል። ሴቷ በጨለማ ውስጥ ከመኾኗም በላይ ከአንገቷ በላይ ስለማትታይ ማንነቷ አይታወቅም። ኾኖም ብርሃን ፈላጊ ናት። ለእኔ ብርሃን የተለየ ትርጓሜ አለው። በሕይወት ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚጥሩት በመጽሐፌ ውስጥ የሚገኙ ተባዕታይ እና አንስታይ ገጸ ባሕርያት በሙሉ ብርሃናማ እና ብርሃን ናፋቂዎች ናቸው። መጽሐፌን የሚያነቡ የአባባሌን እውነትነት ይረዱታል” ሲል መልስ ሰጥቷል። ደራሲው እንዳለ ሸዋንግዛው ዲፕሎማውን በሰርቬይንግና ድራፍቲንግ እንዲሁም የመጀመሪያ ዲግሪውን በአካውንቲንግ አግኝቷል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

በአይነቱ ልዩ የሆነ አፍሪካ አቀፍ የፋሽን ሳምንት በኢትዮጵያ ይካሄዳል፡፡

(ማህሌት ይታገሱ) ከመስከረም 23 ጀምሮ ለሶስት ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆየው የፋሽን ትርዒት በትልቅነቱ ለኢትዮጵያ የመጀመርያው እንደሆነ ነው አዘጋጆቹ የገለፁት፡፡ ከሰባት የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ዲዛይነሮችና ሞዴሎች የሚሳተፉበት የፋሽን ሳምንት ዘላቂ እድገትን በፋሽን ኢንደስትሪ ለማምጣት ያለመ እንደሆነ ዛሬ ረፋዱ ላይ በጁፒተር ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተወስቷል፡፡ The Hub of Africa, Fashion week በሚል ርእስ የሚካሄደው ይኸው የፋሽን [...]

Index-1_11

(ማህሌት ይታገሱ)

ከመስከረም 23 ጀምሮ ለሶስት ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆየው የፋሽን ትርዒት በትልቅነቱ ለኢትዮጵያ የመጀመርያው እንደሆነ ነው አዘጋጆቹ የገለፁት፡፡ ከሰባት የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ዲዛይነሮችና ሞዴሎች የሚሳተፉበት የፋሽን ሳምንት ዘላቂ እድገትን በፋሽን ኢንደስትሪ ለማምጣት ያለመ እንደሆነ ዛሬ ረፋዱ ላይ በጁፒተር ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተወስቷል፡፡

The Hub of Africa, Fashion week በሚል ርእስ የሚካሄደው ይኸው የፋሽን ሳምንት አዲስ አበባ ከአለም ሶስተኛዋ የዲፕሎማቶች መቀመጫ መሆኗን ግምት ውስጥ በማስገባት ስያሜ እንደተሰጠው አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ ዝግጅቱ ላይ ሥራቸውን ከሚያቀርቡት መካከል ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ፣ ከኬንያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከታንዛኒያ እንዲሁም ከሶማሊያ ሁለት መንትዬ ዲዛይነሮች ይገኙበታል፡፡ አቅራቢዎቹ ወጣትና ወደሙያው እየገሰገሱ ያሉ ታዳጊዎችን መሰረት ያደረገ እንደሆነ በጋዜጣ መግለጫው ተመልክቷል፡፡

በፋሽን ሳምንቱ ሸማቾች፣ በጨርቃ ጨርቅ ኢንደስትሪ የተሰማሩ ባለሀብቶች፣ በፋሽን ኢንደስትሪው ተሳትፎ ያላቸው ኢንስቲትዩቶች ከመላው አፍሪካ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡‹ከሌርቮያንት ማርኬቲንግ ኢንደስትሪ› ከ‹‹የሃ ኢንተርቴይመንት›› ጋር በመቀናጀት ያዘጋጀው ይኸው አፍሪካ አቀፍ የፋሽን ትርኢት የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስትር፣ የአፍሪካ ህብረት፣ ዩኤስኤይድ፣የቱርክ አየር መንገድና ሌሎች ከ 20 በላይ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እገዛ አድርገውለታል፡፡

የፋሽን ሳምንቱ በዋናነት በአፍሪካ የሚገኙ ሞዴሎች፣ ዲዛይነሮችና በፋሽን ኢንደስትሪው ተሳትፎ ያላቸው ድርጅቶችን ለማቀራረብ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው የዝግጅቶ ክርኤቲቭ ዳይሬክተር ወይዘሮ ሊንዳ ሙሪቲ ለአዲስ ነገር ተናግረዋል፡፡ በዚሁ የፋሽን ሳምንት ተሳትፎ ለማድረግ መቀመጫቸውን ኒው ዮርክ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ሞዴሎች አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ዝግጅቱ ሳርቤት አካባቢ በሚገኘው ላፍቶ ኢንተርቴይመንት ማእከል እንደሚካሄድም ለመረዳት ተችሏል፡፡

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

አርቲስት ሙላቱ አስታጥቄ ለታላቁ ሽልማት ድምፅ ለማግኘት በቅስቀሳ ተጠምዷል፡፡

(አሮን ዘገየ) የእንግሊዞች ግራሚ አዎርድ በሚል የሚታወቀው ‹‹ሞቦ የሙዚቃ ሽልማት›› የታጨው ኢትዮጵያዊው የጃዝ አባት ሙላቱ አስታጥቄ በቂ መራጭ ለማግኘት ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ‹‹ሞቦ አዎርድ›› ለ2010 በ‹‹ምርጥ አፍሪካን አክት›› ካጫቸው አስራ አምስት ስመጥር ሙዚቀኞች ሙላቱ አንዱ ሲሆን የሚያስፈልገውን ድምፅ ለማግኘት እንዲያስችለው በአገር ቤት ሚዲያዎች የመዝናኛ ፕሮግራሞች ላይ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ትናንት ‹‹ኢትዮጲካ ሊንክ›› በተሰኘው [...]

MulatuW2

(አሮን ዘገየ)

የእንግሊዞች ግራሚ አዎርድ በሚል የሚታወቀው ‹‹ሞቦ የሙዚቃ ሽልማት›› የታጨው ኢትዮጵያዊው የጃዝ አባት ሙላቱ አስታጥቄ በቂ መራጭ ለማግኘት ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ‹‹ሞቦ አዎርድ›› ለ2010 በ‹‹ምርጥ አፍሪካን አክት›› ካጫቸው አስራ አምስት ስመጥር ሙዚቀኞች ሙላቱ አንዱ ሲሆን የሚያስፈልገውን ድምፅ ለማግኘት እንዲያስችለው በአገር ቤት ሚዲያዎች የመዝናኛ ፕሮግራሞች ላይ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ትናንት ‹‹ኢትዮጲካ ሊንክ›› በተሰኘው የሬዲዮ ፋና የመዝናኛ ዝግጅት ለሁለት ሰአት ያህል የአየር ሽፋን የተሰጠው አርቲስት ሙላቱ ህዝቡ ድምፅ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡ ብቸኛው የእንግሊዝኛ ኤፍ ኤም 105 አፍሮ ኤፍ ኤም  በተመሳሳይ መልኩ የሙላቱን ስራዎች ለአድማጮች በማቅረብ ህዝቡ ድምፅ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

‹‹ሞቦ አዎርድ›› በ1996 ጀምሮ ለ‹‹አርባን›› ሙዚቃ የሚሰጥ በአውሮፓ ትልቁ ሽልማት ሲሆን ስነ ስርዓቱ በመላው አለም ከ250 ሚሊዮን ህዝብ በላይ በቀጥታ ይመለከተዋል ተብሎ ይገመታል፡፡ ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ ስነ ስርዓቱ በሊቨርፑል ከተማ ይካሄዳል፡፡

ዘንድሮ ለመጀመርያ ጊዜ በዚህ አዎርድ እጩ ለመሆን የበቃው አርቲስት ሙላቱ በ‹‹ምርጥ አፍሪካን አክት›› ካታጎሪ ከሌሎች 14 ገናና ሙዚቀኞች ጋር ተፋጧል፡፡ የቤኒኗ አንጀሊ ኪጆ፣ የሶማሊያው ከነአን፣ የናይጄሪያው ባንኪ፣ የኢኳቶሪያል ጊኒው ኮንቻ ቡካ ከኢትዬጵያዊው ሙላቱ ጋር እጩ ሆነው ከቀረቡ አፍሪካውያን ሙዚቀኞች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ከአስራ አምስት እጩዎች መሀል አምስቱ የሚመረጡት መቶ በመቶ በህዝብ ድምፅ ሲሆን ይህም በቀጥታ በኢንተርኔት የሚካሄድ የአመራረጥ ስነ ስርአት የሚካሄድ ነው፡፡ ብዙም የኢንተርኔት ተጠቃሚ በሌለባት ኢትዮጵያ የሙላቱ አስታጥቄ ድምፅ ማግኘት አጠያያቂ እንደሆነ የሚገልፁ ታዛቢዎች አልጠፉም፡፡

በ1935  ዓ.ም  ጅማ የተወለደው ሙላቱ በለንደን ፣ በኒውዮርክና ቦስተን የሙዚቃ ትምህርቱን ተከታትሏል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በለንደን ካጠናቀቀ በኋላ በበርከሌይ የሙዚቃ ኮሌጅ የመጀመርያው አፍሪካዊ ተማሪ ለመሆን በቅቷል፡፡ ሙላቱ ከደረሳቸውና ካቀናበራቸው የሙዚቃ ስራዎች ውስጥ ‹‹የከርሞ ሰው››፣‹‹አስዮ ቤሌማ››፣ ‹‹ሙላቱ ስቴፕ አሄድ›› የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ሙላቱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦች ብቻ የሚሸጡ ሁለት ሲዲዎችንም ሰርቷል፡፡ ከዚህ ቀደም የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ፌሎው በመሆን እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተጋባዥ ሌክቸረር ሆኖ አገልግሏል፡፡

ሙላቱ የዛሬ አመት ልክ በዚህ ወር በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው ‹‹አፍሮ ካሪቢያን ሚይዚክ አዎርድ›› ‹‹ The best CD of the year›› በሚለው ዘርፍ ማሸነፉ ይታወሳል፡፡ የሞቦ አዎርድ የፊታችን ጥቅምት 20 በሊቨርፑል ይካሄዳል፡፡

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

የአገር ቤት ጋዜጦች ምን ጻፉ?

ፕሮፌሰር መስፍን ወይዘሪት ብርቱካን እንዲፈቱ ጠየቁ አውራምባ ከፕሮፌሰር መስፍን ጋራ ያደረገውን ሰፊ ቃለ ምልልስ አስነብቧል። ፕሮፌሰሩ “ብርቱኳን አጥፍታለች ከተባለም እስካሁን የታሰረቸው ይበቃል” ሲሉ መንግሥት እንዲፈታት ተማጽነዋል። ስለ እድገት እና ትራንስፎርሜሽን በአውራምባ የተጠየቁት ፕሮፌሰሩ ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው መናገራቸው ግርምትን ጭሮ አልፏል። ግርማ ዋቄ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሰናበቱ አየር መንገድን በከፍተኛ ስኬት ላለፉት ስድስት ዓመታት በዋና [...]

ፕሮፌሰር መስፍን ወይዘሪት ብርቱካን እንዲፈቱ ጠየቁ

አውራምባ ከፕሮፌሰር መስፍን ጋራ ያደረገውን ሰፊ ቃለ ምልልስ አስነብቧል። ፕሮፌሰሩ “ብርቱኳን አጥፍታለች ከተባለም እስካሁን የታሰረቸው ይበቃል” ሲሉ መንግሥት እንዲፈታት ተማጽነዋል። ስለ እድገት እና ትራንስፎርሜሽን በአውራምባ የተጠየቁት ፕሮፌሰሩ ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው መናገራቸው ግርምትን ጭሮ አልፏል።

ግርማ ዋቄ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሰናበቱ

አየር መንገድን በከፍተኛ ስኬት ላለፉት ስድስት ዓመታት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት የመሩት አቶ ግርማ ዋቄ በጡረታ ተሰናብተዋል ሲል ሳምንታዊው ካፒታል ጋዜጣ ጽፏል። ስድስት ልጆች እና ስድስት የልጅ ልጆች ያሏቸው አቶ ግርማ ዋቄ በአቪየሽን ኢንዱስትሪ ላለፉት 30 ዓመታት አገልግለዋል። ኾኖም እ.ኤ.አ በ1993 ዓ.ም አየር መንገዱን ለቀው ወደ ገልፍ አየር መንገድ በመሄድ ለሰባት ዓመታት፤ እንዲሁም ዲ.ኤች.ኤል ውስጥ ለሁለት ዓመታት እንደገና ወደ ገልፍ አየር መንገድ ለተጨማሪ ሦስት ዓመታት ከሠሩ በኋላ ነበር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲኾኑ የተጋበዙት። አቶ ግርማን የሚተኩት አየር መንገዱን በማርኬቲንግ እና ሽያጭ ክፍል ዋና ኀላፊ ኾነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ይኾናሉ። አቶ ተወልደ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከእንግሊዝ አግኝተዋል።

የአዲስ አበባ ብዙ ሰፈሮች ለመልሶ ማልማት ይፈርሳሉ

የአዲስ አበባ ዋና ዋና ጭርንቁስ ሰፈሮች ናቸው የተባሉ ከ4500 በላይ የሚኾኑ ቤቶች በያዝነው ዓመት ይፈርሳሉ ሲል ካፒታል ጻፈ። ለሸራተን አዲስ ማስፋፍያ በዙርያው ያሉ ከ2275 ቤቶች በላይ በቅርቡ ሊፈርሱ ይችላሉም ብሏል።

ወሎ ሰፈር ከዓለም ምግብ እና እርሻ ወኪል ጽ/ቤት ፊት ለፊት የሚገኙ መኖርያ ቤቶች በትንሹ 471 የሚኾኑት ፈራሽ ናቸው። በቂርቆስ ክ/ከተማ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አቅራቢያ የሚገኙ ከ250 በላይ ቤቶችም በቅርቡ የመፍረስ ዕጣ ይገጥማቸዋል። በአራዳ ክ/ከተማ ልዩ ስሙ ባሻ ወልዴ ችሎት ሰፈር ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ የሚገኙ ቤቶች መፍረስ ከጀመሩት መካካል ናቸው። በዚህ አካባቢ ከ1700 በላይ የሚኾኑ ቤቶች በመፍረስ ላይ እንደኾኑ ይኸው ጋዜጣው ዘግቧል። በቀጣዩ አምስት ዓመት ወደ መስቀል አደባባይ በሚወስዱ ዋና መንገዶች አቅራቢያ የሚገኙትን ሰፈሮች በሙሉ አፍርሶ ለማልማት ዕቅድ መያዙንም ጨምሮ ጽፏል

ቢ ኤች የተባለ ድርጅት አገር ውስጥ የገጣጠማቸውን መኪናዎች ለደንበኞች አስረከበ

በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በአገር ውስጥ የተገጣጠሙ ፎር ሁዊል ድራይቭ መኪናዎች “ቢኤች” በተባለ ካምፓኒ ተመርተዋል። ካምፓኒው ለመጀመርያ ጊዜ ያመረታቸውን ስምንት መኪናዎችን ለደንበኞቹ አስረክቧል። መኪናዎቹ ስቴሽን ዋገን እና ፒክ አፕ ሲኾኑ 400 ሺሕ እና 450ሺሕ ብር ዋጋ ያወጣሉ። “ቢኤች” ከሆላንድ ካር እና ከሊፋን ካር ቀጥሎ ሦስተኛው የመኪና መገጣጠምያ ፋብሪካ ኾኖ ተመዝግቧል።

ሌሎች ዜናዎች

-ሜታ ቢራ ፋብሪካን በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዛወር መንግሥት ፍላጎት ማሳየቱን፤ ከፍተኛ ጉልበት ያለው ዝናም የተንዳኾ ስኳር ፋብሪካ ለመስኖ ሊጠቀምበት የነበረ ግድብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን፤ የሕንድ ግዙፍ ባንክ የኾነው ኤክሲም ባንክ በአዲስ አበባ ቢሮ መክፈቱን ካፒታል ጋዜጣ ሽፋን ከሰጣቸው ዜናዎች መካከል የሚገኙ ናቸው።

-አውራምባ ታይምስ ተስፋዬ ገብረብ አቶ ስዬ አብረሃ በቅርቡ ባሳተሙት መጽሐፍ ላይ የከታተበውን የሰላ ሂስ ሙሉ ገጽ ሰጥቶ አስተናግዷል። ተስፋዬ እንደለመደው ስዬን እና የጻፉትን መጽሐፍ ያፌዝባቸዋል። መጽሐፉ ውስጥ ዐየሁ ያላቸውን እርስ በርስ የሚጣረሱ መረጃዎችን እያነሳ ይሸነቁጣል። የስዬ ሚስጥሮች ብሎ በጠራው ጽሑፉ።

-አውራምባ ከዚህ ሌላ በዜና አምዱ አንድ የ23 ዓመት ወጣት ኻያ ሁለት ማዞርያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በፖሊስ ግንባሩን ተመትቶ መገደሉን አስታውሶ ተጠርጣሪው ፖሊስ ግን እስካሁንም በቁጥጥር ሥር እንዳልዋለ ጽፏል። የዐይን ምስክሮችም ቢኾኑ ለመመስከር በሄዱበት እስር እንደገጠማቸው ጋዜጣው ዘግቧል። ሟች ዓለማየሁ ለማ ከጓደኞቹ ጋራ በመዝናናት ላይ ሳለ ከሆቴሉ አስተናጋጅ ጋራ ሳይግባባ ይቀራል። ችግሩን ለመፍታት የመጡ ፖሊሶች ሟችን ጓደኞች ሲመቱዋቸው “ለምን ትደበድቡናላችሁ፣ በሥነ ሥርዐት ወደ ሕግ ቦታ ውሰዱን እንጂ” ብሎ በመናገሩ ፖሊስ ጭንቅላቱን ተኩሶ እንደገደለው የሟችን ቤተሰቦች ጠቅሶ አውራምባ ዘግቧል።

-የቅዳሜዎቹ አዲስ አድማስ እና ኢትዮ ቻናል ጋዜጦች በአመዛኙ የኢሕአዴግን ጉባዔ አስመልክቶ ሰፊ ሽፋን ሰጥተው ዘግበዋል። የእንግሊዘኛው ፎርቹንም ከአዳማ ጉባኤ ያጠናቀረውን ሰፊ ዘገባ በፊት ገጹ ይዞ ወጥቷል። በሳምንቱ መጨረሻ የወጡት የአገር ቤት ጋዜጦች ከሞላ ጎደል ይህን ይመስሉ ነበር።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

አዲስ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ የኢትየጵያን ፕሬስ ይቀላቀላል

“Abyssinian Business Gazette” ሳምንታዊ የቅዳሜ ጋዜጣ እንደሚኾን የተናገሩት መሥራቾቹ አሁን በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ በጉልህ የሚታየውን ጽንፍ ይዞ የመዘገብ ባሕል ለማጥበብ እንደሚሞክሩ ይናገራሉ። “ብዙዎቹ የግል ጋዜጦች የመንግሥትን የልማት ዜናዎች ለመዘገብ አይፈቅዱም፣ የመንግሥት ሚዲያዎችም መንግሥት ላይ የሰላ ሂስ የሚሰነዝሩ ጽሑፎችን አያስተናግዱም። እኛ ይህንን ለማቀራረብ እንሠራለን” ይላሉ መሥራቾቹ።

(ፋና ፍቅሬ)

“Abyssinian Business Gazette” ይሰኛል በቅርቡ ወደ ገበያ የሚገባው ጋዜጣ። ፊት እና ጀርባው ባለቀለም እንደሚኾን የሚነገርለት ይኸው ጋዜጣ 32 ገጾች ይኖሩታል። ትኩረቱን የሚያደርገው በዋናነት በቢዝነስ ጉዳዮች ላይ ቢኾንም የከተማ ሕይወት እና መዝናኛ ብዙ ገጾቹን የሚሸፍኑ ርእሰ ጉዳዮች ይኾናሉ። ሦስቱ የጋዜጣው መሥራቾች ከዚህ ቀደም በተለያዩ የአገር ውስጥ፣ የግል እና የመንግሥት ሚዲያዎች ላይ ቆይታ ያደረጉ ናቸው።

“Abyssinian Business Gazette” ሳምንታዊ የቅዳሜ ጋዜጣ እንደሚኾን የተናገሩት መሥራቾቹ አሁን በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ በጉልህ የሚታየውን ጽንፍ ይዞ የመዘገብ ባሕል ለማጥበብ እንደሚሞክሩ ይናገራሉ። “ብዙዎቹ የግል ጋዜጦች የመንግሥትን የልማት ዜናዎች ለመዘገብ አይፈቅዱም፣ የመንግሥት ሚዲያዎችም መንግሥት ላይ የሰላ ሂስ የሚሰነዝሩ ጽሑፎችን አያስተናግዱም። እኛ ይህንን ለማቀራረብ እንሠራለን” ይላሉ መሥራቾቹ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በወረቀት ዋጋ መናር እና በፖለቲካዊ ችግሮች ምክንያት ቁጥሩ እየተመናመነ ቢኾንም አዳዲስ መጽሔት እና ጋዜጦችም በአንጻሩ ወደ ገበያው እየመጡ ይገኛሉ። ጥበባዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው “ዜን” መጽሔት፣ ፋሽን ላይ የሚሰራው “ዞማ” መጽሔት በዚህ ረገድ ተጠቃሾች ናቸው።

“Abyssinian Business Gazette” የኢትዮጵያን ፕሬስ በቀጣዮቹ ሳምንታት ሲቀላቀል በአገሪቱ የሚታተሙ የእንግሊዝኛ ጋዜጦችን ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ ያደርገዋል። ከ“ዴይሊ ሞኒተር” ውጭ ሁሉም ጋዜጦች ሳምንታዊ ሲኾኑ፣ ዘወትር ቅዳሜ የሚታተመው ሪፖርተር፣ ዘወትር አርብ የሚታተመው “ሰብ ሰሃራን ኢንፎርመር”ን ጨምሮ “ካፒታል”ና “ፎርቹን” የተሰኙ ጋዜጦች ብቸኞቹ በኢትዮጵያ የሚታተሙ የእንግሊዝኛ የግል ጋዜጦች ናቸው። ትልቁን የሥርጭት ሽፋን በመያዝ “ፎርቹን” ጋዜጣ ገበያውን ይመራል። ኾኖም የሥርጭት ሽፋኑ በመላ አገሪቱ 8ሺሕ ኮፒ ብቻ ነው።

One Response to “አዲስ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ የኢትየጵያን ፕሬስ ይቀላቀላል”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

በአበበ ቢቂላ ሕይወት ዙርያ የተሠራው ፊልም ተመረቀ

እንደ አበበ ቢቂላ ኾኖ የተወነው ራሴላስ ላቀው ሲኾን የአበበ አሠልጣኝ ኾኖ የተወነው ስፔናዊው አክተር ዳግ ቢልበርግ ነው። በሲኒማ ኢቶጲካ ፕሮዲዩስ የተደረገው “አትሌቱ” ስለ አበበ ቢቂላ ኅብረተሰቡ የማያውቃቸው አያሌ መረጃዎችን እንደሚዳስስ አቶ ተስፋዬ ይናገራሉ። ለምሳሌ አበበ ከአትሌቲክሱ ውጭ በቀስት ውድድር እንዲሁም በበረዶ የውሻ ሩጫ ውድድር ማሸነፉን የሚያውቅ ሰው ጥቂት እንደኾነ ይጠቅሳሉ።

Abebe_Bikila

(ገዛኸኝ ይርጋ)

በሆሊውድ ባለሞያዎች እና በኢትዮጵያውያን አቻዎቻቸው ጥምረት የተሠራው “አትሌቱ” የተሰኘው ፊልም ትላንት በብሔራዊ ቴአትር ተመረቀ። ፊልሙ በተመረቀበት በትላንትናው ዕለት የአበበ ቢቂላ ልጅ የትናየት አበበ፣ ባለቤቱ ወይዘሮ የውብዳር ወልደ ጊዮርጊስ፣ ማርሽ ቀያሪው ምሩፅ ይፍጠር፣ በአበበ ቢቂላ ዘመን ሯጭ የነበረው ዋሚ ቢራቱ እና ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ሙላቱ አስታጥቄ በስፍራው ተገኝተው ነበር።

እነዚሁ ታዋቂ ሰዎች እና ቤተሰቦች በተገኙበት የተመረቀው ይኸው ፊልም የእንግሊዝኛ ትርጉም የተዘጋጀለት ሲኾን “The athlet” የሚል ተለዋጭ የእንግሊዝኛ ርእስ ተሰጥቶታል። የፈልሙ ቀረጻ ከኢትዮጵያ ውጭ በኖርዌይ እና በቡልጋሪያ እንደተካሄደም ታውቋል። እስከ ትላንት ድረስ በምን ያህል ወጪ እንደተሠራ ይፋዊ አኀዝ ያልቀረበለት ይኸው ፊልም ሚልዮን ዶላሮች እንደፈሰሱበት በሥራው ላይ የተሳተፉት ባለሞያዎች ይናገራሉ።

በኢትዮጵያዊው ራሴላስ ላቀው እና በአሜሪካዊው ቤቢ ፍራንክል ዳይሬክት የተደረገው “አትሌቱ” ከምረቃው ቀደም ብሎ በተሳተፈባቸው የፊልም ፌስቲቫሎች ሁሉ አሸናፊ እንደኾነ የዚሁ ፊልም ሜክአፕ አርቲስት አቶ ተስፋዬ ለአዲስ ነገር ገልጸዋል። በእንግሊዝ ኤደንበርግ የፊልም ፌስቲቫል፣ በጀርመን ሮተርዳም የፊልም ፌስቲቫል፣ በስፔን ታሪፋ እንዲሁም በአሜሪካ ናሽቢል ፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተካፍሎ በሁሉም ላይ ምርጥ ሲኒማ በሚል አሸናፊ እንደነበር የተገለጸለት ይኸው ፊልም ከ250 በላይ የአገር ውስጥ እና የውጭ ተዋናዮች እንደተሳተፉበትም ታውቋል።

እንደ አበበ ቢቂላ ኾኖ የተወነው ራሴላስ ላቀው ሲኾን የአበበ አሠልጣኝ ኾኖ የተወነው ስፔናዊው አክተር ዳግ ቢልበርግ ነው። በሲኒማ ኢቶጲካ ፕሮዲዩስ የተደረገው “አትሌቱ” ስለ አበበ ቢቂላ ኅብረተሰቡ የማያውቃቸው አያሌ መረጃዎችን እንደሚዳስስ አቶ ተስፋዬ ይናገራሉ። ለምሳሌ አበበ ከአትሌቲክሱ ውጭ በቀስት ውድድር እንዲሁም በበረዶ የውሻ ሩጫ ውድድር ማሸነፉን የሚያውቅ ሰው ጥቂት እንደኾነ ይጠቅሳሉ።

‹‹አትሌቱ›› ፊልም ልክ እንደ ጤዛ ፊልም ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ 35 ሚሊሜትር ፊልም የተሠራ ሲኾን ፊልሙን ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት ፈጅቷል። የካሜራ ባለሞያዎቹ በአመዛኙ በሆሊውድ ሰፊ ልምድ ያካበቱ የውጭ ዜጎች እንደነበሩ ተብራርቷል። ፊልሙ የ93 ደቂቃ ርዝማኔ ሲኖረው በቅርቡም በኤድናሞል ሲኒማ መታየት ይጀምራል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ምን? “ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ”?

የሚቀርቡ ሙዚቃዎች፣ ግጥሞች፣ፊልሞች ወዘተ የይዘት እና የጥራት ደረጃም “በልማታዊ መንገድ” የሚመዘን ይሆናል። ይህ ለአስተያየት ሰጭዎች የጥበብ የእዝ አሰራር (ሴንሰርሺፕ ) ዳግም ምፅዓት ነው። በሠነዱ እርምት እንዲያደርግ ጥቆማ ከተሰጣቸው ተቋማት አንዱ የሕጻናት እና ወጣቶች እና ቴአትር ነው። ቲአትር ቤቱ ወደ ፊት ለሕፃናት የዴሞክራሲ ጽንሰ ሐሳብ ፣ መልካም አስተዳደር እና የልማት ጠቀሜታን ትኩረት የሚያሳዩ ሥራዎችን ትኩረት በመሥጠት ሊሠራበት እንደሚገባ አመልክቷል።

SocialRealism_Kommissarka_P

“ምነው እመ ብርሐን ኢትዮጵያን ጨቀንሽባት፤ ቀኝሽን ረሳሻት” የሚል  አሳዛኝ፣ የሞትን ጽዋ ለመጎንጨት የተፋጠጥ የሚመስል  ድምጽ ከሀገር ፍቅር ቴአትር ባለሞያዎች ከአንዱ ከሰማችሁ ያለምንም ጥርጥር ይህ ድምፅ የአብራር አብዶ መኾኑን ርግጠኛ ኹኑ። አንጋፋው አርቲስት የሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህንን “ጴጥሮስ ያችን ሰዓት”   ሲጫወት አቡነ ጴጥሮስ አሁንም በድጋሚ የሚረሽኑ ይመስላል።  አብራር በአንጋፋው ቴአትር ቤት የሕይወቱን አብዛኛውን ጊዜ አሳልፏል። የተካፈለባቸው የመድረክ ሥራዎችም እጅግ ብዙ ናቸው። ባለፈው አርብ በአዲስ ዓመት ዋዜማ  ደግሞ አብራር በሚሊኒየም አዳራሽ ነበር። አሁን እንደድሮው “ምነው እመ ብርሃን…” ሊል አልነበረም የተገኘው፡፡ የኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ወክሎ  “እንኳን ለእድገት ዘመን ዋዜማ በሰላም አደረሳችሁ”፤ …“አቤት እንዴት ግሩም ተስፋ ይታየናል”ሊል እንጂ።

ቦሌ የሚገኘው የሚሊኒየም አዳራሽ ባለፈው ጳጉሚ 5 ምሽትየተደረገው የበዓል ዝግጅት የአዲስ አመት ዋዜማ እና የኢድ አልፈጥር ምክንያት በማድረግ ብቻ የተዘጋጀ አልነበረም። የአምስት አመቱን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ መጀመርን ለማብሰርም ነበር።  “ድህነትን ለመሰናበት” በሚል በተደረገው ዝግጅት  የመንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በታዋቂ አርቲስቶች ተመስለው ወደ መድረክ መጥተዋል። የ”እድገት እና  የትራንስፎርሜሽን” ዋዜማ ለማብሰር እና ለመቀስቀስ ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሚዘልቁ የባህልና ዘመናዊ ዘፋኞች፣የፊልም ባለሙያዎች፣ስም ያላቸው አርቲስቶችና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የዝግጅቱ ተካፋዮች ናቸው።

ጥበብ ያችን ሰዓት

የደስታ ሲቃ የዋጣት የምትመስለው አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ከፊት ለፊቷ እንዲቦርቁ የተደረጉ ልጆችን እያየች ”በዚህ በእውቀት እና በለውጥ ዘመን ስትቦርቁ ሳይልቤ ሙልት ይላል” ብላለች የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንን ወክላ። በችሮታው ከልካይ የተወከለው የግብርና ገጠር ልማት ሚኒስትር ‹‹…ስንዴ መለመን ድሮ ቀረ፣ 80 ሚሊዮን ህዝብ እንመግባለን›› ሲል ፉከራውን በመድረክ አሰምቷል፡፡ መጪው ዘመን የጥጋብ ነው ሲልም በእልልታ የታጀበ ውዝዋዜን አሳይቷል፡፡  በ”መንጠቆ” ኮሜዲ ቲአትሩ የሚታወቀው ጥላሁን ጉግሳ የኢንዱስትሪ ሚኒስትርን ወከሎ ‹‹ሊረከብ ነው!›› የሚል ፉከራን አሰምቷል፡፡ ንጉስ አርማህ እና በውበት ፍለጋ ቴአትሮቿ  የማትረሳው ሙሉዓለም ታደሰ  መብራት ሃይልን ወክላ “ኩራዝ ሙዚየም ሊቀመጥ ተወስኗል” ስትል፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ተወዳጅ በሆነው “ገመና” ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ  ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያገኘችው  መሠረት መብራቴ የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽንን ወክላ “ቴሌ በድህነት ላይ ሊሣለቅ ተዘጋጅቷል” ብላለች።

በአርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ “ሠራዊት መልቲ ሚዲያ” እና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ትብብር የተሰናዳውን ዐይነት መሰል ዝግጅት ለህዝብ ለማቅረብ ሲታሰብ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ነጋድራስ ጋዜጣ በግንቦት ወር እትሙ እንዳስነበበው በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች  የምርጫውን በሠላም መጠናቀቅ በማስመልክት “የሰላም እና የዴሞክራሲ የሙዚቃ ፌስቲቫል” የማድረግ እቅድ እንደነበር ጽፎ ነበር። ይህንን የሙዚቃ ዝግጅት ድርጀቶች ስፖንሰር እንዲያደርጉ በአቶ በረከት ስምዖን ምክትል በአቶ ሽመልስ ከማል የድጋፍ ደብዳቤ ታጅቦ ነበር።

ምን መጣ?

ላለፉት 18 የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ በአቶ መለስ መንግሥት ፈጽሞ ተረስቶ ኖሯል።  ቀዳማዊ ኀይለስላሴ  ካስገነቧቸው ቴአትር ቤቶች ባለፉት 40 ዓመታት የተጨመረ የለም። ቴአትር ቤቶች አሉም ፣ የሉምም ለማለት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ኢህአዴግ ወደ ቲአትር ቤት እጁን ያስገባው በ1998 ዓመት ምህረት በብዙ ልፋት ሊመረቅ ተቃርቦ ነበረውን የጌትነት እንየውን “ወይ አዲስ አበባ” ሙዚቃዊ ቴአትርን ለማገድ ብቻ ነው።  ለፓርቲው አንዳንድ ሰዎች የኢትዮጵያ ቴአትር ቤቶች  ያለፈው ሥርዓት ናፋቂዎች መጠራቀሚያ ነው። ከመስከረም 2002 ጀምሮ ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ጋር አዲስ ፍቅር የያዘው መሰለ።

ኪነ ጥበብን ገሸሽ አድርጎ ቢቆይም አዲስ ዜማ መሰማት ጀመረ።   ሕወሀት በትጥቅ ትግሉ ወቅት በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት በተለየው በኢያሡ በርሔ መሪነት የትግራይ ብሔርተኛነትን ለማሥረጽ ሙዚቃን እንደ መሳሪያ ተገልግሏል። ብዙዎች ኢያሡ እና ጓዶቹ እንደተሳካላቸው  ያምናሉ። አቶ መለስ መፍጠር ለሚፈልጉት አብዮታዊ ዴሞክራሲያ የኅብረተሰቡ ሁለተኛ ተፈጥሮ የማድረግ ጥልቅ ፍላጎት ከግብ ለማድረስ  “ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ” ወደ ኢትዮጵያ የሥን ሕይወት ዘው ብሎ እንዲገባ ተደረጓል።  የአዲስ አመት ዋዜማ “ደማቅ”  ዝግጅት  ““ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ” በሥራ ላይ መኾኑን ማሳያ  ነው።

ጥቅምት 2002 ዓ.ም ቁጥራቸው 350 የሚደርሱ  በአዲስ አበባ መስተዳድር ሥር የሚሠሩ የቲአትር እና የሙዚቃ ባለሞያዎች “ኪነ ጥበብ ለመሠረታዊ ለውጥ” የሚል አንድ በቅጡ ባልታሰበበት ሰነድ የተደገፈ ሥልጠና ተሰጣቸው። የሠነዱ አዘጋጅ ግልጽ ባይሆንም የውስጥ ምንጮች ጣታቸውን ወደ ሁለት ሰዎች ይጠቁማሉ። ለአርቲስቶቹ ስልጠናውን በሰጡት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ክፍያለው አዘዘ እና  አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ።

52 ገጽ እና ዘጠኝ ክፍሎች ያካተተው ይህ “ኪነ ጥበብ ለመሠረታዊ ለውጥ” የተሰኘ ሰነድ “የልማት እና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታችን  ውስጥ ኪነ ጥበብ ግንባር ቀደም ተዋናይ ለማድረግ “ ሀሳብ እንዳለው ይገልጻል።  ሰነዱ ለኢትዮጵያ ተስማሚ የኾነ የኪነ ጥበብ ፍልስፍና እንደሚያስፈልግ  በመናገር ፤ “ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ”  አማራጭ የሌለው  ብቸኛ መንገድ አድርጎ  ያስቀምጠዋል። “ከድህነት ለመውጣት ተግባራዊ  እንቅስቃሴ እያደረገ ለሚገኝ ሕዝብ እና መንግሥት ብቸኛው  አሠራር ፍልስፍና የልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ የኪነ ጥበብ ሚና ነው” ይላል።  በዚህ መሠረት ቴአትር፣ ሙዚቃ፣  ሙዚቃዊ ድራማ፣ ፊልም ፣  የሥዕል፣ ቅርጻ ቅርጽ እና የሬዲዮ ድራማ እና ሌሎች  የሥነ ጥበብ ዘርፎች ሁሉ “ለልማት እና ዴሞክራሲያዊ “ጠቀሜታ  የሚውሉበትን  ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ አሠራር እንደሚከተል ይገልጻል። የኪነ  ጥበብ ተቋማት ዋና ግብም “ የተጀመረውን ፈጣን እድገት ማገዝ ነው ።  አመራሩም  የኪነ ጥበብ ውጤቶችን ይዘት እና አሰራር በልማታዊ  ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ መርህ መቀረጹን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።  የሚቀርቡ ሙዚቃዎች፣  ግጥሞች፣ፊልሞች ወዘተ የይዘት እና የጥራት ደረጃም “በልማታዊ  መንገድ” የሚመዘን ይሆናል። ይህ ለአስተያየት ሰጭዎች የጥበብ የእዝ አሰራር (ሴንሰርሺፕ ) ዳግም ምፅዓት ነው። በሠነዱ እርምት እንዲያደርግ  ጥቆማ ከተሰጣቸው ተቋማት አንዱ የሕጻናት እና ወጣቶች እና ቴአትር ነው።  ቲአትር ቤቱ ወደ ፊት ለሕፃናት የዴሞክራሲ ጽንሰ ሐሳብ ፣ መልካም አስተዳደር እና የልማት ጠቀሜታን ትኩረት የሚያሳዩ ሥራዎችን ትኩረት በመሥጠት ሊሠራበት እንደሚገባ አመልክቷል።

የ”ኪነት” መመለስ?

የ“ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ” በደርግ ሥርዓት የተተገበረውን የሶሻሊስት እውናዊነት (ሶሻሊስት ሪያሊዝም) ግልባጭ ነው።  በቀድሞው የደርግ መንግሥት ዘመን  ከቀበሌ እስከ ከፍተኛው የመንግሥት አስተዳደር ድረስ ኪነት “የወዛደሩን አምባገነንነት እና  የአብዮቱን አንጸባሪቂ ድሎች “ ለማሳወቅ እና የማስረጽ ሐላፊነት ተሸክመው ተንቀሳቅሰዋል። ከእነ ሬፒን የሶሻል ሪያሊዝም ማህጸን  ፈለቀው የሶሻሊስት ሪያሊዝም አስተሳሰብ በቭላድሚር ማይኮቭስኪ ግጥሞች እና በማክሲም ጎርኪየ “እናት” ከፍ ወደ አለ ዝና ወጥተዋል።

ጆሴፍ ስታሊን የሶሻሊስታዊ እውናዊነት አቀንቃኞችን “የነፍስ መሀንዲሶች“ ይላቸዋል።  የሠራተኛውን መደብ ትግል እና የኑሮ  ኹኔታን መገለጽ፣ የሠራተኛው ፓርቲ አምባገነንነት ማወደስ ፣ ለእናት አገር የሚኖር ብሔራዊ ስሜትን መፍጠር ፣ ምርታማነትን መጨመር  የሶሻሊስት ሪያሊዝም አቀንቃኞች የሚከተሏቸው መርሆች ናቸው።  በአንጻሩ ሶሻሊስት ሪያሊዝምን ገዢዎች የዜጎችን ነጻነት ለማፈን እና አመለካከታቸውን ለመቆጣጠር ይጠቀሙበታል።  ታዋቂው ፈላስፋ አይዛ በርሊን የቀድሞዋ የሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ የጥበብ ሰዎች የደረሰባቸውን ፍዳ እና የነጻነት እጦት ይተርካሉ። ይህን የሩሲያን ምሳሌ ወዳጅ ሶሻሊስት ሀገሮችም ተሳካላቸውም አልተሳካላቸውም ሲተገብሩት ኖረዋል። በኢትዮጵያም። ነገር ግን ሶሻሊስት ሪያሊዝም አካሉ ሳይሆን መንፈሱ ብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ ዳክሯል።

ደርግ ሶሻሊስት ሪያሊዝምን ወደ ኢትዮጵያ ለማስረጽ ሲሞክር የወደቀው ከጅምሩ ነበር።  ሶሻሊስት ሪያሊዝም  የሚያቀነቅናቸው መሠረታዊ መርሆች የተመቸ መሠረት አልነበራትም። ደርግ ሶሻሊስት ሪያሊዝምን እንዲያቀነቅኑለት የሚፈልጋቸው አርቲስቶች ጸሐፌ ተውኔቶች፣ ሠዓልያን በአብዛኛው በምዕራብ አገሮች የተማሩ እና ለምእራቡም፤ለምስራቁም አስተሳሰብ የተጋለጡ ናቸው። ሶሻሊስት ሪያሊዝም የሚፈልጋቸው በቀቀኖች እንደሚፈለገው አልተፈለፈሉም። ይህ ወቅት የአካባቢያዊ የኪነት ቡድኖች የፈለቁበት እና ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን “እናትዓለም ጠኑን” ለመድረክ ያቀረቡበት፤ ድምጽ አልባ ቲአትሮች(ማይም ድራማዎች) ነፍስ መዝራት የጀመሩበት ነው። ብዙ  ያልተጠና ወርቃማ የሥን ዘመንም ነበር።

የአሁኑ የኪነ ጥበብ መመሪያ መርህ  “አብዮት“ የሚለው ቃል “ልማት” በሚል ተክቶታል። እንደ በፊቱ በቀጥታ ልተግብር አይልም። ከሰሜን ኮሪያ የ“ጁቼ ሪያሊዝም“ አተገባበር የተማረ ይመስላል። “ጁቼ” የሰሜን ኮሪያ ገዢ ፓርቲ የፖለቲካ መስመር ነው። ራስን መቻል እንደማለት።  የቀድሞው የሰሜን ኮሪያ መሪ ከቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት፣ ቻይና የተዋሱትን ሶሺያሊስ ሪያሊዝም ፒዮንግ ያንግ ሲደርስ ከራሳቸው ፓርቲ መሪ ሀሳብ ጋር እንዲታረቅ አድርገው አተገባበሩንም በዚያው ቃኝተው፤ጁቼ ሪአሊዝም እንዲፈጠር አርገዋል። ይህ ሂደት ”ሶሻሊስታዊ ይዘቶችን ፣በሀገራዊ ቅርፆች የማጎልበት “ ሥራ ነው-ለቀድሞው ሰሜን ኮሪያ ሊቀመንበር።

ጁቼ ሪያሊዝም ሰሜን ኮሪያ ሲደርስ  የክርስትና ስም ቢሰጠውም  በስልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ርዕዮተ ዓለም በማስረፅ እና የተለዩ ሃሳቦች ዝር እንዳይሉ በማድረግ ከ”ሶሻሊስት ሪያሊዝም” የተለየ ሚና የለውም። የኢሕአዴግ የ“ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ” ዋና ግብ “ሀገራዊ ቅርፃች መፍጠር”  የሚፈልግ “ በባህርይውም ከጁቼ ሪያሊዝም ጋር የሚዛመድ መርህ ነው። ኪነትን በቁጥጥር ሥር በማዋል አንድ አይነት አስተሳሰብ በማራመድ ሁሉን  ለመቆጣጠር  የሚፈልግ ነው።

ጥበብን ለፖለቲካዊ እና ርዕዮተ ዓለማዊ ግቦች ብቻ  በመቀየድ እና የአንድ አስተሳሰብ  ባሪያ  ማድርግ  በተለያዩ ሀገሮች ወደ ስልጣን የወጡ አምባገነን እና ጠቅላይ ሥርዓቶች  መንገድ ነው። በፍጹም አምባገነን  ሥርዓት ውስጥ  ጥበብ በአርቲስቱ ምርጫ  የሚፈልቅ ሳይሆን በስልጣን ላይ ያለው አካል  በሚያወጣው መስፍርት እና መመሪያ የሚተገበር ነው።  ይህን መርህ  የገዢውን ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም የዜጎች ሁለተኛ ተፈጥሮ ለማድረግ የሚተጋ ነው።  “ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ ሃሳብ የመነጨው “ሁሉን ለመቆጣጠር ከሚፈልግ  እምቅ የገዢው ፓርቲ ምኞት የሚቀዳ መሆኑን አዲስ ነገር ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጭዎች ያስረዳሉ።  “ርዕዮተ ዓለም ፍጹም ሲሠራ ሁለተኛ  ተፈጥሮ ያህል ይሆናል”ይላሉ ሀሳባቸውን ለአዲስ ነገር ጋዜጣ ያካፈሉ አንድ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር።

“ከዚህ በፊት ፓርቲው በዋናነት ለመቆጣጠር የፈለገው የሚጨበጡ እና የሚዳሰሱ ጉዳዮችን ብቻ ነበር። ይህ  ብቻውን በቂ ሆኖ አልተገኘም። አሁን የማይዳሰሱትን እና  ዜጎችን የአስተሳሰብ አድማስ የሚወስኑ ጉዳዮችን ለመቆጣጠር እየሠራ ነው” ይላሉ።  የ“ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ” አንዱ ስውር  ግብም  “የአስተሳሰብ ልእልና መኖር የለበትም፤ ቦታም ማግኘትም አይገበውም” ከሚል አስተሳሰብ  የመነጨ መርህ እንደሆነ ሃሳብ ይሰጣሉ። የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ እዚህ ደርሷል።አየሩ  “የልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ”ን መሽተት ጀምሯል። ” ምነው እመ ብርሃን  ኢትዮጵያን ጨከንሺባት “…ማለት የደከመው ይመስላል።

One Response to “ምን? “ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኪነ ጥበብ”?”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

[አንድ ለቅዳሜ!] መለስ ኮሎምቢያ – ፖፕ ቤኔዲክት እንግሊዝ

በነገራችን ላይ

የሰሞኑ የኢሕአዴግ ጉባኤ ምን ማለቱ ነው? እኛ እኮ ቻይና ሞዴላችን ናት ሲባል በኢኮኖሚ ብቻ መስሎን ነበር። ውይ በፓርቲ ልብስም ጭምር ሆነ እንዴ? ኮፍያው አልቀረ፤ ምንጣፉ አልቀረ። አይ እንዲህ ከሆነ አንድ ፊቱን አጠራርም ይቀየርልና። ሊቀ መንበር መሌ ይባልልን፤ ልክ ሊቀ መንበር ማኦ ወይም ሊቀ መንበር መንጌ እንዲል። ጉባኤው በኢቲቪ የተዘገበበት መንገድ ደግሞ በልጅነታችንን ያየነውን የኢሰፓ ጉባኤ የሚያስታውስ ነው። “አውራ ፓርቲ” በደንብ እየገባችን ነው።

ግን ግን ይሄ “አውራ ፓርቲ” የሚለው ስያሜ በድርጅቱ ሊቀ መንበር ታምኖበት የጸደቀ ነው? ትርጉሙ እኮ ያምታታል። ለምሳሌ “አውራ” የሚለው ዋና፣ ታላቅ፣ መሪ፣ የጫጩቶቹ ፓርቲዎች ሁሉ አባት የሚል በጎ ትርጉም ይሰጣል። እናቲቱን ዶሮ መፈለግ የሕዝብ ጉዳይ ነው።
ጸረ ልማትና ጸረ ሕዝብ ኀይሎች ግን “አውራ” የሚለውን “እንደልማድህ ለፍልፍ፣ ተናገር፣ ወሬ እንደሆን አያልቅብህም፣ አንተን ከማዳመጥ ሌላ ምን ምርጫ አለን አውራብን፣ ደሞ ጀመረህ በል አውራብን ልባችንንም አውልቀው” እያሉ የተሳሳተ ትርጉም ሊሰጡት ይችላሉ። እስቲ አሁን አንዱ ተንኮለኛ “አውራ ፓርቲያችን” ሲል ምን ማለቱ ነው? ደግሞስ ይህ ስያሜ አጋር የምንላቸውን ፓርቲዎች ጸረ ሕዝቦች “ጫጩት ፓርቲዎች” እንዲሏቸው በር አይከፍትም ወይ? በሒደት “አውራ ፓርቲ” ምስጋና መሆኑ ቀርቶ ስላቅ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ወይ ይህንን ቃል አለአግባባ አጥብቆ ወይም አላልቶ ማንበብን፤ እንዲሁም ለራስም ሆነ ለሌላ ሰው ከተፈቀደው ውጭ የሆነ ትርጉም ሊሰጥ በሚችል ወይም ሊሰጥ ይችላል ተብሎ በሚያስጠረጥር ቃናና ድምጽ መናገርን የሚከለክል ሕግ ማውጣት የአዲሱ ፓርላማ የመጀመሪያ ስራ ይሁን አለዚያም ሳይለመድ ይቀየር። አማራጭ መጠሪያዎችን እንቀበላለን።

[ቅዳሜ ልዩ ነች። ያው ቅዳሜ ቅዳሜ ነው። በየሳምንቱ ቅዳሜ ትወጣ በነበረችው አዲስ ነገር ጋዜጣ ይቀርቡ የነበሩትን ሐሳቦችና ጽሑፎች ለማስታወስ፤ ቅዳሜ ማለዳ “አንድ ሐሳብ ለቅዳሜ!” ማለትን ለለመዱ ጭምር በየሳምንቱ እንዲህ እንገናኛለን። አንድ ለቅዳሜ! ለመባባል።]

ሁለት ጉዳዮች ትኩረቴን ስበውት ሰነበቱ። አንዱ የኢትዮጵያ፤ ሌላው ደግሞ የአውሮፓ ናቸው። ጉዳዮቹ ግን በመሠረታዊ ምንነታቸው ሁሉን አቀፍ የሆኑ ጭብጦችን የሚቀሰቅሱ ናቸው። በአንድ በኩል መለስ ዜናዊ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ንግግር እንዲያቀርቡ መጋበዛቸውን ተከትሎ የተቃውሞ ድምጽ እየተሰማ ነው። እኔ እንኳን ስንት መልእክት ደረሰኝ። በሌላው አገር በእንግሊዝ ደግሞ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ በእንግሊዝን የጀመሩት ይፋዊ ጉብኝት የጋበዘው ፈርጀ ብዙ ክርክር ቀጥሏል። መቼም የአውሮፓ ሚዲያ የፖፑን ጉብኝት እየሰነጣጠቀና እየገለባበጠ የሚዳስስበት መንገድ በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት የምስራች አለመሳማቱን እንደሚያስታውሰኝ አልደብቅም።

መለስ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በሚያዘጋጀው አንድ ተከታታይ መድረክ ተናጋሪ እንዲሆኑ ጋብዟቸዋል። ይህም መለስ መልአክ እየመሰሏቸው ጀርባቸውን ለመዳበስ ለሚመኙ ደጋፊዎቻቸው እንደ ትልቅ ድል የሚቆጠር ነው። ለነገሩ እነዚህ ሰዎች የመለስ መጋበዝ የሚያስደስታቸው ተቃዋሚዎቻቸውን ስለሚያናድድላቸውም ጭምር ይመስላል። ደግነቱ ተቃዋሚዎቻቸውም አላሰፈሩዋቸውም፤ በየድረ ገጹ የሚነበበው አስተያየት በአብዛኛው የመለስን በተናጋሪነት መጋበዝ የሚያወግዝ ነው። አንዳንዱ ተቃውሞ ይህንንም ድንበር ያለፈ ነው።

ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ለሊ ቦሊንግረ የተቃውሞ ደብዳቤ እየጎረፈላቸው እንደሆነ መገመት አይከብድም። ተቃውሞው ግን ከኢትዮጵያውያን ብቻ አይደለም። የተለያዩ ግለሶቦች እና ቡድኖችም የመለስን መጋበዝ እየተቃወሙ ነው። ዋሽንግተን-ኤግዘማይነር ዓርብ ዕለት ባስነበበው አንድ የተቃውሞ ጽሑፍ የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ “የዓለም መሪዎች መድረክ” (World Leaders Forum) ብሎ የሚጠራውን መለስ የተጋበዙበትን ዝግጅት “የአምባገነኖች መዘላበጃ” (Demagoguery from Dictators) ተብሎ እንዲሰየም በመጋበዝ በስላቅ ሁሉንም ጎንትሏል። አንዱ መነሻው ደግሞ የዛሬ ሦስት ዓመት የኢራኑ መሪ ማሐሙድ አህመዲነጃድ በዚሁ መድረክ ተጋብዘው መናገራቸው ነው። ዩኒቨርሲቲው እና ፕሬዚደንቱ ግን የዛሬ ሦስት ዓመትም ሆነ ዛሬ የሚመልሱት መልስ ተመሳሳይ ነው።

የአቶ መለስ መጋበዝ በተቃዋሚዎቻቸውና በደጋፊዎቻቸው መካከል የቀሰቀሰው አዲስ ፖለቲካዊ ቃና የሚጫነው ውዝግብ አዲሱን ዓመት የተቀበልንበት ትልቁ ዓለም አቀፋዊ ትኩረት የሳበ ትእይንት ነው። በዚህ ክርክር ውስጥ ተከራካሪዎቹ ገባቸውም አልገባቸውም አንዱ ቁልፍ ጭብጥ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ነው። ዩኒቨርሲቲውን ጨምሮ መለስና መሰሎቻቸው “ሊደመጡ ይገባል” የሚሉት ወገኖች ስሕተታቸውን በማረም እንጂ እንዳይናገሩ በመከልከል መታገል እንደሌለባቸው ያምናሉ። ተቃዋሚዎቻቸው ለዚህ የሚሰጡት አጸፋ ቀላል ግን መሰረታዊ ጥያቄ ነው። የሌሎችን ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት ሆን ብሎ የሚያፍን ግለሰብ የእርሱ መብት ለዚያውም እንዲህ ባለው የገዘፈ ዩኒቨርሲቲ መድረክ ላይ ሊከበርለት ይገባልን? ይህስ ጥፋቱን በተዘዋዋሪ መደገፍ አይሆንምን? ፕሬዚዳንቱ በአህመዲነጃድ ግብዣ ወቅት በሰጡት መግለጫ ለዚህ መልስ ለመስጠት ሞክረዋል።፡እንዲህ በማለት

I would also like to invoke a major theme in the development of freedom of speech as a central value in our society. It should never be thought that merely to listen to ideas we deplore in any way implies our endorsement of those ideas, or the weakness of our resolve to resist those ideas or our naiveté about the very real dangers inherent in such ideas. It is a critical premise of freedom of speech that we do not honor the dishonorable when we open the public forum to their voices. To hold otherwise would make vigorous debate impossible.

መለስ በዩኒቨርሲቲው መድረክ መናገራቸው የሚቀር አይመስለኝም። ይልቅ የሚያጓጓኝ መሪዎቹን በከረሩ ጥያቄዎች የሚያፋጥጡት ፕሬዚዳንቱ ወይም ወኪላቸው ለመለስ የሚያቀርቡላቸው ጥያቄ ነው። ከዚያም በበለጠ ደግሞ በጉባኤው የመታደም እድል የሚያገኙት ኢትዮጵያውያን የሚሉትን መስማት ያጓጓል፤ በተለይ ተቃዋሚዎቻቸው። ደግነቱ የመለስ የንግግር ጭብጥ ለሽወዳ የሚመቻቸው ይመስላል፤ “The Current Global Economy and its Impact”።

ቢሆንም መለስ ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ለሚያውቅ እና የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ ሊያሳይ የሚችል መረጃ ይዞ ለሚገኝ ሰው እንደምንጊዜውም ለትችት የተመቹ ናቸው። አገር ቤት ፓርላማ እንደለመዱት የኢኮኖሚ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር “ኢኮኖሚክስ 101” በሁለት ሰዓት መስጠተት ኮሎምቢያ ላይ አያዋጣም። እርሳቸውም ይቺን አያጡዋትም፤ ለዚያውም ፒኤችዲያቸውን በሰሩበት ዩኒቨርሲቲ? አማካሪያቸውና አድናቂያቸው ጄፍሪ ሳክ ባሉበት? እናያለና። መቼም ኢቲቪ ይህንን ዝግጅት ቢያንስ ቀድቶ በኋላ ማቅረብ አለበት። እንዲህ ከሚል መግቢያ ጋራ “ይህን መድረክ ልዩ የሚያደርገው አቶ መለስ ለመጨረሻ ጊዜ የፓርቲያቸው ሊቀ መንበር ሆነው በተመረጡበት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ 99.96 በመቶ በሆነ ድምጽ ተመሳሳይ ነገር በመረጠበት ማግስት…ማግስት…ማግስት…ዋዜማ…ዋዜማ…ዋይ ዜማ…”

የካቶሊኩ ፓፕ ቤንዲክት እንግሊዝ ላይ የገጠማቸው ከመለስ ይለያል። ቤኔዲክት 16ኛ የቤተ ክርስቲያናቸው ቀሳውስት ፈጽመውታል በሚባለው ድርጊት የተነሳ ተቃዋሚዎች ተነስተውባቸዋል። “ይህን መሰሉን ሰው በመጋበዝ የታክስ ገንዘባችንን ለምን እናባክናለን?” እስከማለት የዘለቁም አሉ። እርግጥ ከተቃዋሚዎቻቸው የተወሰኑት ፖፑን ሳይሆን በአጠቃላይ ሃይማኖት የሚባለውን ነገር የሚኮንኑ ናቸው። ፖፑ ግን ትናንት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አማኞችና ተመልካቾች በተገኙበት ቡራኬ ሰጥተዋል፤ ንግስቲቱን አግኝተዋል፤ የካንተርበሪውን ጳጳስ ጎብኝተዋል። ቀኑን ሲጨርሱም በትችት ሲሸነቁጡዋቸው ለሰነበቱት ጋዜጠኞች አዳዲስ ርእሰ ጉዳዮችን ሰጥተዋቸዋል። ስለዚህ ቀኑ የባከነ አልሆነባቸውም።

ቤኔዲክት 16ኛ በጥልቅና አንዳንድ ጊዜ አወዛጋቢ በሆኑ ንግግሮቻቸው እየታጀቡ የቤተ ክርስቲያናቸውን መንፈሳዊ መነቃቃት ለማወጅ የቆረጡ ይመስላሉ። ቢያንስ የራሳቸውን ሐውልት አሰርተው፤ ራሳቸው መራቂ ሆነው አይገኙም። አንድ እንግሊዛዊ ምእመናቸው የቅድስና ማእርግ እንዲያገኝ የሚያበቃውን የመጀመሪያ ደረጃ () ይሰጡታል ተብሏል። አባ ጳውሎስ ቀጥሎ አውሮፓን ሲጎበኙ ግን መጀመሪያ የሚያረጉት የሆነ ቦታ ሄደው ቢቻል ሀውልታቸውን አለዚያም ፎቷቸውን መመረቅ ነው። ራሴን በራሴ ካላቀዳደስኩት…

በነገራችን ላይ

የሰሞኑ የኢሕአዴግ ጉባኤ ምን ማለቱ ነው? እኛ እኮ ቻይና ሞዴላችን ናት ሲባል በኢኮኖሚ ብቻ መስሎን ነበር። ውይ በፓርቲ ልብስም ጭምር ሆነ እንዴ? ኮፍያው አልቀረ፤ ምንጣፉ አልቀረ። አይ እንዲህ ከሆነ አንድ ፊቱን አጠራርም ይቀየርልና። ሊቀ መንበር መሌ ይባልልን፤ ልክ ሊቀ መንበር ማኦ ወይም ሊቀ መንበር መንጌ እንዲል። ጉባኤው በኢቲቪ የተዘገበበት መንገድ ደግሞ በልጅነታችንን ያየነውን የኢሰፓ ጉባኤ የሚያስታውስ ነው። “አውራ ፓርቲ” በደንብ እየገባችን ነው።

ግን ግን ይሄ “አውራ ፓርቲ” የሚለው ስያሜ በድርጅቱ ሊቀ መንበር ታምኖበት የጸደቀ ነው? ትርጉሙ እኮ ያምታታል። ለምሳሌ “አውራ” የሚለው ዋና፣ ታላቅ፣ መሪ፣ የጫጩቶቹ ፓርቲዎች ሁሉ አባት የሚል በጎ ትርጉም ይሰጣል። እናቲቱን ዶሮ መፈለግ የሕዝብ ጉዳይ ነው።
ጸረ ልማትና ጸረ ሕዝብ ኀይሎች ግን “አውራ” የሚለውን “እንደልማድህ ለፍልፍ፣ ተናገር፣ ወሬ እንደሆን አያልቅብህም፣ አንተን ከማዳመጥ ሌላ ምን ምርጫ አለን አውራብን፣ ደሞ ጀመረህ በል አውራብን ልባችንንም አውልቀው” እያሉ የተሳሳተ ትርጉም ሊሰጡት ይችላሉ። እስቲ አሁን አንዱ ተንኮለኛ “አውራ ፓርቲያችን” ሲል ምን ማለቱ ነው? ደግሞስ ይህ ስያሜ አጋር የምንላቸውን ፓርቲዎች ጸረ ሕዝቦች “ጫጩት ፓርቲዎች” እንዲሏቸው በር አይከፍትም ወይ? በሒደት “አውራ ፓርቲ” ምስጋና መሆኑ ቀርቶ ስላቅ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ወይ ይህንን ቃል አለአግባባ አጥብቆ ወይም አላልቶ ማንበብን፤ እንዲሁም ለራስም ሆነ ለሌላ ሰው ከተፈቀደው ውጭ የሆነ ትርጉም ሊሰጥ በሚችል ወይም ሊሰጥ ይችላል ተብሎ በሚያስጠረጥር ቃናና ድምጽ መናገርን የሚከለክል ሕግ ማውጣት የአዲሱ ፓርላማ የመጀመሪያ ስራ ይሁን አለዚያም ሳይለመድ ይቀየር። አማራጭ መጠሪያዎችን እንቀበላለን።

5 Responses to “[አንድ ለቅዳሜ!] መለስ ኮሎምቢያ – ፖፕ ቤኔዲክት እንግሊዝ”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ገጣሚ ኤፍሬም ሥዩም የግጥም ሥራዎቹን በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ አቀረበ

“ሶልያና” የተሰኘ የግጥም ሥራውን በ1998  ለገበያ ያበቃው ኤፍሬም ስዩም  አዲስ እና ነባር  ግጥሞቹን መስከረም 6 በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ አቀረበ። ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ለቀጣይ ሕትምት ካዘጋጃቸው “የብርሃን ክንፎች” እና “ኪያፋህ” ከተሰኙ የግጥም ስብስቦቹ መካከል የተወሰኑ ግጥሞችን ሲያቀርብ በዋሽንት፣ በሳክስፎን እና በፒያኖ ታጅቦ ነበር።  በዚሁ ቀን ምሽት ላይ ኤፍሬም 15 ያህል ግጥሞቹን ሁለት ሰዓት በፈጀው ፕሮግራም ላይ [...]

ephrem seyum


“ሶልያና” የተሰኘ የግጥም ሥራውን በ1998  ለገበያ ያበቃው ኤፍሬም ስዩም  አዲስ እና ነባር  ግጥሞቹን መስከረም 6 በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ አቀረበ። ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ለቀጣይ ሕትምት ካዘጋጃቸው “የብርሃን ክንፎች” እና “ኪያፋህ” ከተሰኙ የግጥም ስብስቦቹ መካከል የተወሰኑ ግጥሞችን ሲያቀርብ በዋሽንት፣ በሳክስፎን እና በፒያኖ ታጅቦ ነበር።  በዚሁ ቀን ምሽት ላይ ኤፍሬም 15 ያህል ግጥሞቹን ሁለት ሰዓት በፈጀው ፕሮግራም ላይ አቅርቧል።

ግጥሞቹ ረዣዥም የሚባሉ ናቸው። እነዚሁ ግጥሞች በኤፍሬም በሚነበቡበት ወቅት ታዋቂው ፒያኒስት እና ሳክሰፎን ተጨዋቹ ጆርጋ መስፍን እና በሌሎች የሙዚቃ ባለሞያዎች ታጅቦ ነበር።  የ“ፍቅር እስከ መቃብር” መጽሐፍ ትረካ ማጀቢያ የኾነውን ዋሽንት የተጫወተው  ዮሐንስ አፈወርቅ በዚሁ ምሽት የኤፍሬምን ግጥሞች ሲያደምቅ አምሽቷል።

ኤፍሬም ስዩም በዚህ የግጥም ምሽት ላይ “ሶሊያና” ከተሰኘው የግጥም ሲዲው ላይ “ውሸት ነው”፣ በቅርቡ ለገበያ ከሚያቀርበው “የብርሃን ክንፎች” ከተሰኘው የግጥም ሲዲው “የሹሩባው ትንቢት”፣ “የምኒልክ አናት”፣ “እሳትና ዝናብ” እና ሌሎች አራት ግጥሞችን ያቀረበ ሲሆን ለሦስተኛ የግጥም ሲዲው ብሎ ካዘጋጀው “ኪፋያህ” ከተሰኘው ስብስቡ ውስጥ ደግሞ “እውነት፣ ሕይወት፣ ውበት”፣ “ክረምት እና ፀደይ” የተሰኙትን እና ሌሎች ግጥሞችንም አቅርቧል።

“ሙዚቃል” የሚል መሪ ቃል የተሰጠው ይኸው ምሽት ስያሜውን ያገኘው በገጣሚው ኤፍሬም እና በዶክተር ሄራን ሰረቀ ብርሃን የተሰየመ እንደኾነ ገጣሚው ገልጿል። የሙዚቃል ትርጓሜ የሙዚቃ እና የቃልን ውህደት መግለጽ ማለት እንደኾነም ያብራራል።

ኤፍሬም ስዩም አያይዞም “የብርሃን ክንፎች” በተሰኘውና በቅርቡ ለገበያ በሚቀርበው የግጥም ሲዲው ውስጥ  18 ግጥሞች እንደተካተቱ እና ዝነኞቹ የሙዚቃ ባለሞያዎች አበጋዙ ሺዮታ ክብረወርቅ፣ ሔኖክ ተመስገን፣ ኦላፍ ቮልሰን፣ ፒያኒስት ግርማ ይፍራሸዋ፣ ጆርጋ መስፍን፣ ቴዎድሮስ አክሊሉ፣ ባለዋሽንቱ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲሁም ዶ/ር ሄራን ሠረቀ-ብርሃን በክራር እንደተሳተፉበት ገልጿል።

የኤፍሬም ስዩም “ሶሊያና” ለመጀመሪያ ጊዜ በ1998 ዓ.ም ከታተመ  በኋላ በድጋሜ  ሁለት ጊዜ ታትሟል።  የመጀመሪያው እና ሁለተኛው ሶሊያና 30 ግጥሞችን የያዙ ሲኾኑ በጃፋር መጻሕፍት መደብር አሳታሚነትና አከፋፋይነት የተዘጋጀው ሦስተኛው ሶሊያና  “ማንዴላ” የሚል ግጥም እንደተጨመረበት ይታወቃል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

“የትዝታዎች ትዝታ” የተሰኘ የአንጋፋና ወጣት ድምፃውያን የትዝታ ዘፈኖችን ለገበያ ዋለ

በዚህ የመስከረም ወር የመጀመርያ ሳምንት ግን ናሆም ሪከርድስ የአንጋፋ እና የወጣት ድምፃውያንን የትዝታ ሥራዎች አሳትሞ ለገበያ አውሏል፤ ሰኞ ዕለት። አብዛኞቹ በዚህ አልበም የተካተቱት ሥራዎች አዲስ ናቸው፤ ከማዲንጎ አፈወርቅ ሥራ በቀር። በዚሁ አልበም ላይ ከቀደምት ድምፃውያን መካከል የማሕሙድ አሕመድ እና የጌታቸው ካሳ ሥራዎች ይገኙበታል። በ1980ዎቹ እውቅናን እያተረፉ የነበሩት ፀጋዬ እሸቱ እና በዛወርቅ አስፋው ደግሞ አዳዲስ ሥራዎችን ይዘው መጥተዋል።

ye tezitawoch tezita

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በአገሪቱ ውስጥ መልክ መያዝ ባልቻለው የቅጂ መብት ምክንያት ከኅትመት ከራቀ ቆየ። ባለፈው ዓመት አልበም በሙዚቃ ኢንዱስትሪው ውስጥ የውኃ ሽታ ኾኖ ነበር። በየጊዜው በሚሠሩት ሙዚቃዎች ላይ ከየአቅጣጫው የሚሰጡት አስተያየቶች እና በተለያዩ ጋዜጦች እና የብሮድ ካስት ሚዲያዎች ላይ የሚወጡት ትችት አዘል ጽሑፎች አዳዲስ የዘፈን አልበሞች ቶሎ ቶሎ መታተም እንዳይችሉ ጫና ፈጥረውም ነበር። አልፎ አልፎ ከሚደመጡት ነጠላ ዜማዎች ውጭ አልበም የማሳተም ፍርኀት የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ሰዎችን ከዋጣቸውም ሰነበተ። አሁንም ይኼው አካሄድ ገና ያበቃለት እና የሚገፈፍ አልመሰለም። “አያዋጣም” የሚለው የማኅሌት ደመረ አልበም በነሐሴ ወር ከመለቀቁ ውጭ ያለፈው ዓመት የተጠናቀቀው የነጠላ ዜማ ዓመት በመኾን ነበር።

በዚህ የመስከረም ወር የመጀመርያ ሳምንት ግን ናሆም ሪከርድስ የአንጋፋ እና የወጣት ድምፃውያንን የትዝታ ሥራዎች አሳትሞ ለገበያ አውሏል፤ ሰኞ ዕለት። አብዛኞቹ በዚህ አልበም የተካተቱት ሥራዎች አዲስ ናቸው፤ ከማዲንጎ አፈወርቅ ሥራ በቀር። በዚሁ አልበም ላይ ከቀደምት ድምፃውያን መካከል የማሕሙድ አሕመድ እና የጌታቸው ካሳ ሥራዎች ይገኙበታል። በ1980ዎቹ እውቅናን እያተረፉ የነበሩት ፀጋዬ እሸቱ እና በዛወርቅ አስፋው ደግሞ አዳዲስ ሥራዎችን ይዘው መጥተዋል።

በታደሰ ገለታ የተጻፈው ግጥም የተዘፈነው ፀጋዬ እሸቱ ነው። በዚሁ የፀጋዬ እሸቱ የትዝታ ዘፈን ላይ ሙዚቃ የተጫወቱት የሊድ ጊታር ተጨዋቹ ክብረት ዘኪዎስ፣ የሳክስፎን ተጨዋቹ ፈለቀ ኀይሉ እና የቤዝ ጊታር ተጨዋቹ ደረጄ ተፈራ ናቸው። እነዚህ ሦስት ሙዚቀኞች የኤክስፕረስ ባንድ አባላትም ናቸው።

በዚሁ አልበም ላይ ወጣት ድምፃውያን አዳዲስ የትዝታ ዘፈኖቻቸውን አቅርበዋል። ማዲንጎ አፈወርቅ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ብዙዐየሁ ደምሴ፣ ታምራት ደስታ ትዕግስት ፋንታሁን እና ሕብስት ጥሩነህ ተካፋይ ኾነዋል። አዲስ ነገር ያነጋገራቸው የሙዚቃ ባለሞያዎች ማዲንጎ አፈወርቅ በዚህ ሥራው ላይም ያሳየው የድምፅ አወጣጥ ከቀድሞው ያልተዛነፈ እና ጥሩ የኾነ የአዘፋፈን ስልት እንዳሳየ ተናግረዋል። በተለይ በክራር ታጅቦ መዝፈኑ ውበቱን እንደጨመረለትም ይገልጻሉ። በጌትነት እንየው የተጻፈለትን የዘፈን ግጥም ያዜመው ሚካኤል በላይነህም በሮክ ስልት አጨዋወቱ የሙዚቃ ባለሞያዎቹን ቀልብ ስቧል። ይህ ዘፈን የተቀናበረው በሚካኤል ኀይሉ ነው።

አዲስ ነገር ያነጋገራቸው የሙዚቃ አድናቂዎች እና ባለሞያዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዳግም ከአዲስ ሥራዎቹ ጋራ ሊመጣ ነው ተብሎ በተለያዩ የብሮድካስት እና የኅትመት ሚዲያዎች ላይ በተደጋጋሚ ሲዘገብለት ስለቆየው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ያላቸው አስተያየት የተለየ ነው። ሁሉም ከዚህ በፊት በነበረው ዘፈኑ የሚማረኩ እና ለድምፁም ኾነ ለአዘፋፈን ስልቱ እንከን ለማውጣት ይቸገራሉ። ነገር ግን በዚህ የትዝታዎች ስብስብ ላይ ይዞት የመጣው ሥራ የጠበቁትን ያህል የልባቸውን አላደረሰላቸውም። እንዲያውም ለአንዳንዶቹ ጌታቸው ካሳ በዚህ አልበም ውስጥ ግጥሞቹን ለውጦ የጥንቱን የትዝታ ዘፈን ከማቅረብ ውጭ ያደረገው አንዳች ነገር እንደሌለም ያስባሉ። በ1960ዎቹ የሠራው የትዝታ ዘፈንም ኾነ በ1982 በከይፋ ሪከርድስ አሳታሚነት ያቀረበው ትዝታ ከዚህኛው ጋራ በፍጹም ለመነጻጸር የሚበቃ አይደለም የሚል አስተያየትም ይሰነዝራሉ። ይህን አዲሱን ሥራውን ጌታቸው ራሱ የደረሰው ሲኾን ኪቦርዱን ዳንዔል ወልደ ገብርዔል፣ ሳክስፎኑን ሞገስ ሀብቴ፣ ቤዝ ጊታሩን የኔ ሰው ተፈራ፣ እና ሊድ ጊታሩን እውቁ የሮሃ ባንዱ ሰላም ስዩም ተጫውተዋል። ማሕሙድ አሕመድ በዚህ የትዝታ ስብስብ ሥራ ውስጥ ያቀረበውን ዘፈን የደረሰለት ንጉሴ ጣዕመ ወርቅ ሲኾን የጌታቸውን ዘፈን ያቀናበሩት የሙዚቃ ተጨዋቾች በሙሉ ተሳትፈውበታል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

እነ አስቴር አወቀ ቤት ቡና ጠጡ!!

በ‹ካቡ› ካፌ ውስጥ ማክያቶ ፉት እያሉ ሳለ አስቴር አልፎ አልፎ እንደምታደርገው በአካል ድንገት ልትከሰት ትችላለች፡፡ በዚህን ጊዜ የልብ አድናቂዋ ከሆኑ ትን ሊልዎት ይችላል፡፡ ሆኖም ለመረጋጋት ይሞክሩ፡፡ አስቴር በሞቀ ፈገግታ ሰላምታ ታቀርብሎታለች፡፡ አድናቂዎቿ በሞባይላቸውም ቢሆን አብረው ፎቶ ለመነሳት ይጣደፋሉ፡፡ አውቶግራፍ ለማግኘትም እንዲሁ፡፡ ኋላ ግን ያስፈረሙትን ፊርማ ለአስተናጋጁ ቢያሳዩም ሂሳብ አይቀነስልዎትም፡፡ የአስቴር ቤት ዋጋ እንደ ኮንሰርቶቿ ውድ የሚባል ነው፡፡ በአስቴር ቤት ሻይ መጠጣትና የአስቴርን አዲስ ካሴት መግዛት ዋጋው እኩል ነው፡፡ ዘጠኝ ብር! ‹‹ስኳር ስኳር አለኝ…››የሚለውን ጣፋጭ ዜማዋን ጋብዣችኋለሁ፡

kabu 3

(መሀመድ ሰልማን)

ከቦሌ መድኃኔያለም ወደ አትላስ በሚወስደው ጎዳና ላይ እንገኛለን፡፡ የዋናውን መንገድ ግራ ይዘን ትንሽ እንራመድ፡፡‹‹ሰሌክት ፐብ›› እና ‹‹አልባብ የባህል ምግብ ቤት››ን  አለፍን፡፡የአዲሳባ ኬክ ቤቶች ቁንጮ ነው የሚባልለትን ‹‹ቢሎስ ኬክ ቤት›› ከማግኘታችን በፊት ቆም እንበል፡፡  ፍቃድዎ ከሆነ ከአስቴር አወቀ ቤት ጎራ ብለን፣ ቆንጆ ቡና እየጠጣን፣ እንጨዋወት፡፡

‹‹ካቡ ካፌ››!

‹‹ካቡ ካፌ›› ከተወለደ ገና ሁለት ወራትን አልደፈነም፡፡ ሆኖም የሰፈሩ አድባር ለመሆን ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ በደጁ የሚቆሙ መኪናዎችን ብዛት በማየት ይህንኑ መመስከር ይቻላል፡፡ ካቡን ለመሳለም የሚመጡ የላይኛው መደብ ደንበኞች በሁለቱም የአስፋልት አቅጣጫ ያቆሟቸው መኪናዎች በረዥም መስመር ተሰድረዋል፡፡ የመኪናዎትን ደህንነት ለካቡ ካፌ ጥበቃዎች እርግፍ አድርገው ይግቡ፡፡ ይህ ካልሆነም መኪናዎን እየቃኙ ማክያቶ ፉት ማለት ይችላሉ፤ከአስቴር አወቀ ቤት፡፡

‹‹ካቡ››እንደብዙዎቹ የከተማችን ካፌዎች አይወብቅም፡፡ ሲገቡ የሚያገኙት ለጥ ብሎ የተዘረጋ በግምት በ500 ካሬ ላይ ያረፈ አውላላ ክፍል ነው፡፡ ፈረስ ያስጋልባል የሚባልለት፡፡ ከዚህ ሰፊ ስፍራ ነጣ ያለ ማክያቶ ፉት እያሉ ነጩን ሰማይ ለማየት የሚያግድ ምንም ነገር የለም፡፡ ከደጅ የሚተላለፍ እግረኛና ተሽከርካሪም ከእይታዎ ውጭ አይሆንም፡፡ ምንም የመታጠር ስሜት አይሰማዎትም፡፡ እሁድ እሁድ ቤትዎ ደጅ ላይ ከሳሎን ወንበር አስመጥተው ፀሐይ ሲሞቁ ያለውን ስሜት ‹‹ካቡ›› ያገኙታል፡፡ ወንበሮቹ ምቾት ናቸው፡፡ ቡናማ ቀለም ካላቸው ባህላዊ በርጩማዎች እና ተመሳሳይ ቀለም ካላቸው ዘመነኛ ወንበሮች ጋር ተጣምረው ለመቀመጫነት ተዘጋጅተዋል፡፡

‹‹ካቡ ካፌ›› ለቡናማ ቀለም እጁን የሰጠ ይመስላል፡፡ ወደ ቀጣዩ ክፍል የሚያስገቡ መስታወቶቹ በቡና ፍሬ ፎቶዎችና ቡናማ ቀለም ባላቸው ፍሬሞች ያጌጠ ነው፡፡ የ‹‹ካቡ ካፌ›› የአምፖል ማቀፍያዎች የተሰሩት በአገር ቤት የውሀ ማከማቻና ማመላለሻ ከሆነው ቡናማ እንሰራ ነው፡፡ የካቡ ምሶሶዎች መደባቸው ቡናማ ነው፡፡ ‹‹በቤቱ ማእዘናት የተፃፉ ማስታወቅያዎችም ‹‹ coffee redefined›› የሚሉ ናቸው፡፡ በጥቅሉ የቤቱ ህብረ ቀለም ቡናማ ሆኖ ቡና ያስጠማል፡፡ ውጡ ወጡ አይልም፡፡ አንዳች የመረጋጋት ስሜትን የመፍጠር ኃይል አለው፡፡

ከዚህ የተንጣለለ ጊቢ አልፈው ወደ ሁለተኛው ክፍል ሲገቡ የሚያገኙት ካፌም እንዲሁ መልካም ስሜትን የመፍጠር አቅም አለው፡፡ ይህ ክፍል መደበኛ ኬክ ቤቶችን ቢመስልም የቀለም ስብጥሩና የብርሀን አጠቃቀሙ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ካውንተሩ አካባቢ ያሉ መብራቶች ማቀፍያቸው የብርሌ ጠርሙስ እንዲሆን ተደርጎ ነው የተሰራው፡፡ በግድግዳዎቹ ላይ የተሰቀሉ ስእሎችም ተጨማሪ ዉበቶች ናቸው፡፡ ሆኖም አስቴር ይህኛውን ክፍል ይበልጥ ውብ ማድረግ ይቻላት እንደነበር ታሰቦኛል፡፡ የርሷንና ሌሎች አንጋፋ ድምፃውያንን ፎቶዎች በትልልቅ ፍሬም በነጭና ጥቁር ቀለም አድርጋ ብትሰቅል ማንም መታበይ አድርጎ የሚያይባት አይመስለኝም፡፡ ወይም ደግሞ የአልበሞቿን ሽፋኖች በዘመናዊ ፍሬም ብትሰቅላቸው ካቡን ሌላ የዉበት ካባ ባጎናፀው፡፡ በዚህ ሀሳቤ የማይስማማ ካለ የአዲሳባን ካፌዎችና ፑል ቤቶች ያጥለቀለቁትን የነማሪያ ኬሪና ቡስታራያምስ ፎቶዎች እያነሳሁ ሽንጤን ገትሬ ልሟገተው ዝግጁ ነኝ፡፡

አስቴር አወቀ ስመ ጥር አቀንቃኝ እንደመሆኗ ለመገናኛ ብዙሀን ልዩ መስህብ ናት፡፡ ሆኖም አስቴር ለሚዲያ ጋጋታ አይናፋር ከሚባሉ ዝነኞች የምትመደብ ናት፡፡ ዘለግ ባለ ጊዜ ነው ጋዜጠኞች እርሷን ማዋራት የሚሳካላቸው፡፡ ፓፓራዚ/ አንድ ወዳጄ ‹‹ጥላ- ጋዜጠኝነት›› ሲል ይህን ቃል ተርጉሞታል/ ፓፓራዚ እዚህ አገር ቢፈጠር ከዘሪቱ ቀጥሎ አስቴር የምትቸገር ይመስለኛል፡፡ የአስቴርና የጋዜጠኞች አለመናበብ ዘፋኟ ‹‹እነ ቆርጦ ቀጥል እንዴት አደራቹ››ብላ እንድታዜም አድርጓታል የሚሉ ከነፃ ምንጭ ያልተረጋገጡ ወሬዎችን ሰምቻለሁ፡፡ እውን ‹‹ ፀጉር አትሰንጥቁ…ሰርታችሁ እደሩ›› ብላ ያዜመችው በጋዜጠኞች ላይ ይሆን? እርግጠኛ አልነበርኩም፡፡ ይህንን ጥያቄ እያሰላሰልኩ ለዚሁ አጭር ፅሁፍ መረጃ ለማግኘት የ‹‹ካቡ ካፌ›› ኃላፊዎችን ለማነጋገር በሞከርኩበት ወቅት ያየኋቸው ውጣ ውረዶች ግን ጥርጣሬየን አጉልተውልኛል፡፡ ‹‹ጋዜጠኛ ማናገር አልተፈቀደልንም›› ያሉኝ ሰራተኛም አሉ፡፡ ያም ሆኖ የካቡ ካፌን ቡና ከማጣጣም አልቦዘንኩም፡፡ ለያውም በአስቴር ተስረቅራቂ ድምፅ እያወራረደኩ፡፡

በ‹‹ካቡ ካፌ›› እስካሉ ድረስ አስቴር በነጻ ታዜምልዎታለች፡፡ በካቡ መእዘናት ጥቃቅን ስፒከሮች ኩልል በሚል፣ ነገር ግን ዝግ ባለ ድምፅ፣ የአስቴርን ተስረቅራቂ ዜማ ለጆሮ ያደርሳሉ፡፡  ‹‹ካቡ ካፌ››ን እጅግ ያስወደደኝ የድምፅ ምጣኔው ነው፡፡ ብዙ ካፌዎች ጥሩ ሙዚቃ ከፍተው ድምፁን የአምቡላንስ ያደርጉትና ነገር ያበላሻሉ፡፡ ሳስበው አስቴር ለካፌው አስተዳዳሪዎች ጠበቅ ያለ መመርያ ሳታስተላልፍ አልቀረችም፡፡ ‹‹ሙዚቃዬን ስትከፍቱ፣ አደራ እላችኋለሁ! ድምፁን እጅግ… እጅግ… እጅግ ቀነስ ታደርጉት ዘንድ ይሁን!››

ሆኖም የ‹‹ካቡ ካፌ›› ቴፕ ከአስቴር ሌላ ዘፋኝ አያውቅም፡፡ ሌላ ካሴትም ጎርሶም የሚያውቅ አይመስለኝም፡፡ ደግነቱ የአስቴር ዜማዎች አይሰለቹም፡፡ አንድ ሰው ጧት ‹‹ካቡ ካፌ›› ገብቶ ማታ ለመውጣት ቢወስን አንድም ዜማ ሳይደገም ከውብሸት ፍሰሀ ጋር በክራር እየተቀባበለች ካዜመችው የመጀመርያ ርእስ አልባ የካሴት ስራዋ ጀምሮ በነ‹‹ሙናዬ ሙናዬ›› አድርጎ እስከ ‹‹ፍቅር››ና ‹‹ስኳር›› አልበም ድረስ መኮምኮም ይችላል፡፡ አስቴር ከ27 አመት ዘለግ በሚል የሙዚቃ ህይወቷ 18 አልበሞችን አድርሳናለች፡፡

በዚህ ሁሉ የሙዚቃ ህይወት ውስጥ ‹‹ካቡ›› ለአስቴር ልዩ ቦታ የሚሰጠው ስም ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ መጨረሻ ከአለም አቀፉና ስመ ጋናናው የ‹‹ሶኒ ሙዚክ ኢንተርቴይመንት ካምፓኒ›› ጋር ለመፈራረም ከበቃች በኃላ ነበር ‹ካቡ› እና ‹አስቴር› የተሰኙትን አልበሞች ያሳተመችው፡፡ ይህም በወቅቱ አስቴርን አለምአቀፍ እውቅናን አጎናፅፏት ነበር፡፡ ‹‹ካቡ›› እንደነ CBS,BBC,CNN,NBC,TIME,NEWSWEEK,WASHINGTON POST, NEWYORK TIMES በመሳሰሉ ገናና አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ሽፋን አስገኝቶላታል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም የ‹‹ካቡ›› ስኬት፡፡ በ CMJ የሙዚቃ ቻርት ‹‹ካቡ›› የተሰኘው ስራዋ ለአራት ሳምንታት በአንደኝነት ተቀምጦላታል፡፡ይኸው ‹‹ካቡ›› የተሰኘው ስራዋ በቢልቦር የ”ዎርልድ“ ሙዚቃ ቻርት ከምርጥ አስር ዝርዝር ውስጥ ሳይወጣ ለአስር ሳምንት ቆይቶላታል፡፡ ይህም አስቴርን በአለምአቀፍ መድረክ የሙዚቃ ሰጠረዥ ውስጥ ለረዥም ጊዜ በመቆየት ብቸኛዋ ኢትዮጵያዊት ያደርጋታል፡፡ ከዚህ በኃላ አስቴር ‹‹ካቡ ሪከርድስ›› የተሰኘ የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅትን መስርታለች፡፡  የአስቴርና የካቡ ፍቅር ወደ ካፌ ደረጃ ያደገው በቅርቡ ቢሆንም አስቴር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የቢዝነስ አድማሷም ልክ እንደ ካብ አየተደራረበ ይመስላል፡፡ ‹‹ቆርጦ ቀጥል›› ተብለው ከማይታሙ ጋዜጠኛ ወዳጆቼ እንደሰማሁት  መረጃ ከሆነ አስቴር በደብረዘይት ባቦጋያ መዝናኛን በ30 ሚሊዮን ብር ወጪ እያለማች ሲሆን በቅርቡም ባለ አራት ኮከብ ሆቴል ካዛንቺስ አካባቢ ለመገንባት የቦታ ጥያቄ አቅርባ ፍቃድ በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች፡፡ የሆቴሉን የክርስትና ስም እንገምት ከተባለ የመጀመርያ ግምታችን የሚሆነው ‹‹ካቡ ሆቴል›› የሚል ነው፡፡ ወጋችንን ወደ ‹‹ካቡ ካፌ›› እንመልስ፡፡

ዘፋኞቻችን የሙዚቃ ስራቸውን ጋብ አድርገው ወደ ካፌ እንዳይዘምቱብን ተግተን መፀለይ ሳይኖርብን አይቀርም፡፡ ህዝባችን ለኦሪጅናልን ማክያቶ እንጂ ለኦሪጅናል ካሴት ብር ማውጣት መተዉ ሊሆን ይችላል ሙዘቀኞቹን እያሳሰባቸው ያለ ጉዳይ፡፡ እነርሱም ወደሚያዋጣቸው እየመጡ ይመስላል፡፡ በቅርቡ 11 ሙዚቀኞች በጥምረት ፒያሳ አካባቢ ‹‹ሙዚክ ካፌ››ን መክፈታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ብዙ ድምፃውያንም ቤቱን ያዘወትሩታል፡፡ ነገሩ በዚሁ ከቀጠለ አዲስ አበባ እንዲህ የሚባሊ ካፌዎች ይኖሯታል፡፡ ‹‹ጃ ካፌ››፣‹‹ዘሪቱ ቡና››፣ ‹‹ኦማሂሬ ሻይ ቤት››፣‹‹ዲምቢ ኬክ ቤት››፣‹‹ባላገሩ ክትፎ››፣‹‹ላፎንቴ በርገር››፣‹‹ሀኪሜ ነሽ ባር›› ወዘተ፡፡

ጨዋታችንን ፈር እናስይዝ፡፡ እነ አስቴር አወቀ ቤት ቡና እየጠጣን ነበር፡፡ በዉቡ የካቡ ካፌ ውስጥ፡፡ የዚህ ካፌ አብዛኛዎቹ ተስተናጋጆች ለግላጋ ሴቶች እንደሆኑ አስተውያለሁ፡፡ የአስቴር አፍቃሪዎች በአመዛኙ ሴቶች መሆናቸው ይሆን ብዬ ጠረጥርኩ፡፡ እነ አስቴር ቤት አንድ ቴራሚሶ ኬክ ለመብላት 18 ብር ያስፈልጋል፡፡ ብላክ ፎረስት በቶርታ አሰርተው ለመውሰድ ከፈለጉ ደግሞ 173 ብር መያዝዎን ማረጋገጥ አለብዎት፡፡

/ይበለውና/ በ‹ካቡ› ካፌ ውስጥ ማክያቶ ፉት እያሉ ሳለ አስቴር አልፎ አልፎ እንደምታደርገው በአካል ድንገት ልትከሰት ትችላለች፡፡ በዚህን ጊዜ የልብ አድናቂዋ ከሆኑ ትን ሊልዎት ይችላል፡፡ ሆኖም ለመረጋጋት ይሞክሩ፡፡ አስቴር በሞቀ ፈገግታ ሰላምታ ታቀርብሎታለች፡፡ አድናቂዎቿ በሞባይላቸውም ቢሆን አብረው ፎቶ ለመነሳት ይጣደፋሉ፡፡ አውቶግራፍ ለማግኘትም እንዲሁ፡፡ ኋላ ግን ያስፈረሙትን ፊርማ ለአስተናጋጁ ቢያሳዩም ሂሳብ አይቀነስልዎትም፡፡ የአስቴር ቤት ዋጋ እንደ ኮንሰርቶቿ ውድ የሚባል ነው፡፡ በአስቴር ቤት ሻይ መጠጣትና የአስቴርን አዲስ ካሴት መግዛት ዋጋው እኩል ነው፡፡ ዘጠኝ ብር! ‹‹ስኳር ስኳር አለኝ…››የሚለውን ጣፋጭ ዜማዋን ጋብዣችኋለሁ፡፡ ቸር እንሰንብት!

One Response to “እነ አስቴር አወቀ ቤት ቡና ጠጡ!!”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

አውዳመቱ በአገር ቤት እንዲህ እየተከበረ ነው

ዶሮ ከ45 ብር ጀምሮ እንደልብ ነው፡፡ ጣርያው ዘጠና ብር ሲሆን የወላይታና አርባምንጭ ዶሮዎች ናቸው በዚህ ዋጋ እየተሸጡ ያሉት፡፡ በግ ትንሽ ሳትወደድ አልቀረችም፡፡ ቀደም ሲል በ900 ብር ይገኝ የነበረው የወላይታ ለያውም ያልሸረፈ ምን የመሰለ በግ አሁን ከ1100 ብር ወይ ፍንክች፡፡ ከዚያ በታች በጉን ከገመቱት በግ ሻጩና አንድ ላይ ያሉ በጎች በሙሉ ከት ብለው ይስቁብዎታል፡፡ እጅግ ልማታዊ በጎች እንደሆኑ አይርሱ፡፡ ሚሊየነር ገበሬ የወለዳቸው በጎች፡

addi amet

(መስፍን ዓለሙ)

አዲሳባ በአውደ አመት የባህል ዜማዎች እስክስታ እየወረደች ነው፡፡ ስድስት የኤፍ ኤም ጣብያዎቿ ጰግሜን በአውዳመት ወሬዎች፣ባውዳመት ዜማዎች፣ ባውዳመት ዜናዎች እያምነሸሸዋት ነው ፡፡ አንድዬ ቴሌቪዥናችን ዶሮ ወጥ የበዛባቸውን ክሊፖች በብዛትና በተከታታይ እያሳየ ህዝቤን እንቁልልጭ ይለዋል፡፡ስልክ የማይቆጥርባቸው የሚመስሉ የሬድዮ አድማጮች የነጭ ሽንኩርትን ዋጋ መናር አስመልክተው ወግ ይጀምራሉ፡፡ በአውዳመትም ኤፍኤሞች በአውዳመትም ቢሆን  ፖለቲካን ያላምጣሉ፡፡

‹‹ሀሎ፣ ኤፍ ኤም ነው…አሁን ባነሳችሁት ሀሳብ ላይ አስተያየት ለመስጠት ነበር››

‹‹ይቀጥሉ ይቀጥሉ››

‹‹ምን መሰለህ…እኔ አሁን ማለት የፈለኩት…ሀሉ ይሰማል››

‹‹ይቀጥሉ እየሰማዎት ነው!››

‹‹እና እንዳልኩህ ሽንኩርት ሽንኩርት ነው፡፡ ቀይ፣ ነጭ እያሉ ህብረተሰቡን መበዝበዝ ትክክል አይመስለኝም፡፡ መንግስትና የሚመለከተው አካል በዚህ በኩል ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ይገባዋል ለማለት ነው፡፡››

‹‹በዘጠኝ ብር ቀይ ሽንኩርት እየሸጡ ነጩን 30 ብር መሸጥ ምን ማለት ነው፡፡ ነጭ ሽንኩርት በነዳጅ ነው እንዴ የሚበቅለው ሆ…››

ሌላ አድማጫችን በስልክ መስመራችን ላይ ይገኛሉ…‹‹ሀሎ ማን ልበል..››

‹‹ይቀጥሉ!››

ሌላ አድማጭ ሌላ ወግ ሌላ ብሶት ይዘከዝካሉ፡፡

‹‹አድማጮቻችን በሽንኩርት ባህሪና አይነት እንዲሁም የዋጋ ተለዋዋጭነት ዙርያ ማብራርያ እንዲሰጡን ከየካ ክፍለከተማ ባለሙያ ጋብዘናል፡፡››

ባለሙያው ድምፃቸውን ጎርነን አድርገው ይጀምራሉ፣

‹‹በርግጥ ሽንኩርት መወደዱ በኛ አገር ብቻ የሚታይ ችግር እይደለም፡፡ ስግብግብ ነጋዴዎች ባሉባቸው የምእራብ አገራት ሁሉ መከሰቱን ከታሪክ እንረዳለን፡፡ ሆኖም አሁን ማተኮር ያለብን መፍትሄው ላይ ይመስለኛል፡፡ ሽንኩርትን ነጭና ቀይ እያሉ ለያይቶ ዋጋ መጨመር በአንዴ በአቃራጭ ለመበልፀግ የሚደረግ ሩጫ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የሚኮነን ተግባርም ነው…የሩቅ ምስራቅ ሀገራት ይህንን ችግር እንዴት ፈቱት ብለን ስናጠና…›› ባለሙያው ቻይና ደርሰው እስኪመለሱ ዶሮ አስራሁለት ብልቱ ተሰርቶ ተበልቶ ያልቃል፡፡

ዘንድሮ አዲስ አበቤ ዶሮና ዶላር ጨምሮበት በአሉን በኩርፊያ ነው እያከበረ ያለው የሚሉ ብዙ ቢሆኑም ገበያውን በእርግጥ ተዘዋውረው ያዩ ግን ይህንን ሀሳብ አይስማሙበትም፡፡ ዶላሩ በጂንስ ሱሪ እንጂ በምግብ ዙርያ ብዙ ችግር አላስከተለም፡፡   ዶሮ ከ45 ብር ጀምሮ እንደልብ ነው፡፡ ጣርያው ዘጠና ብር ሲሆን የወላይታና አርባምንጭ ዶሮዎች ናቸው በዚህ ዋጋ እየተሸጡ ያሉት፡፡ በግ ትንሽ ሳትወደድ አልቀረችም፡፡ ቀደም ሲል በ900 ብር ይገኝ የነበረው የወላይታ ለያውም ያልሸረፈ ምን የመሰለ በግ አሁን ከ1100  ብር ወይ ፍንክች፡፡ ከዚያ በታች በጉን ከገመቱት በግ ሻጩና አንድ ላይ ያሉ በጎች በሙሉ ከት ብለው ይስቁብዎታል፡፡ እጅግ ልማታዊ በጎች እንደሆኑ አይርሱ፡፡ ሚሊየነር ገበሬ የወለዳቸው በጎች፡፡

አትክልት ተራ የሚገኘው ዘጋቢያችን ያሰባሰበው ዋጋ እንደሚያትተው ፣ቃርያ 7 ብር በኪሎ፣ካሮት 4 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት 30 ብር፣ ቀይ ሽንኩርት ዘጠኝ ብር፣ ቲማቲም ስምንት ብር በኪሎ እያለ ይቀጥላል፡፡

አዲስ አበቤዎች በአሉን ፖለቲካ፣ ሙዚቃውን ፖለቲካ፣ ዶሮውን ፖለቲካ ካላደረጉ አይዋጥላቸውም መሰለኝ፡፡ የስልክ መልእክት ሲለዋወጡ የሆነች ፖለቲካ ጣል ያደርጋሉ፡፡ መጪው አመት መብራት የማይሄድበት፣ ዶላር የሚረክስበት፣…የሆነ ፓርቲ የሚወርድበት ያድርግልን ይላሉ፡፡ እኔ ግን እላለሁ፡፡ ይህ ህዝብ ህገ መንግስቱን አያነብም፡፡ ፖለቲካ በአውዳመት፣ አውዳመት በፖለቲካ ጣልቃ አይገቡም፡፡

መልካም በዓል ይሁንልዎ!

No Responses to “አውዳመቱ በአገር ቤት እንዲህ እየተከበረ ነው”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ከንቲባው ተሰርቀዋል!

ኢንጂነር ክፍሎም ሃድጉ ጥርሱን በነቀለባት ከተማ ክፉኛ የኾነ የዘረፋ ድራማ መሰል ታሪክ ተፈጽሞበታል፤ ለዚያውም ሦስት ጊዜ። ያም ኾኖ ምሬት ባደረቀው አንደበቱም ቢኾን በራሱ ከመቀለድ ወደኋላ አይልም “ሃትሪክ ሠሩኝ እኮ” እያለ።የግል ተቋራጭ የኮንስትራክሽን ድርጅት ያለው ኢንጂነር ክፍሎም ደከመኝ የማይል ሠራተኛ ነው። ረዥም ሰዓት በሥራ ላይ ያሳልፋል። ኾኖም ማምሸት እንደሌለበት ቀጥሮ ከሚያሠራቸው የጉልበት ሠራተኞቹ ጭምር ዘወትር ይነገረዋል። [...]

ኢንጂነር ክፍሎም ሃድጉ ጥርሱን በነቀለባት ከተማ ክፉኛ የኾነ የዘረፋ ድራማ መሰል ታሪክ ተፈጽሞበታል፤ ለዚያውም ሦስት ጊዜ። ያም ኾኖ ምሬት ባደረቀው አንደበቱም ቢኾን በራሱ ከመቀለድ ወደኋላ አይልም “ሃትሪክ ሠሩኝ እኮ” እያለ።የግል ተቋራጭ የኮንስትራክሽን ድርጅት ያለው ኢንጂነር ክፍሎም ደከመኝ የማይል ሠራተኛ ነው። ረዥም ሰዓት በሥራ ላይ ያሳልፋል። ኾኖም ማምሸት እንደሌለበት ቀጥሮ ከሚያሠራቸው የጉልበት ሠራተኞቹ ጭምር ዘወትር ይነገረዋል። የምክሩ መብዛት ‹‹ምንድነው ነገሩ…›› እንዲል አስገድዶታል። የዕቃ ዕቃ ጭቃ አብኩቶ ባደገባት እና አሁን ደግሞ ሲሚንቶ አያስቦካ ፎቅ በሚያሠራባት “ሰላማዊቷ” መቀሌ ውስጥ “አታምሽ” የሚለው ምክር ብዙም ሳይዋጥለት ቆይቷል።

መስከረም 16፣ 1999 ዓ.ም ምሽት 1፡30

ለዐይን ያዝ ሲያደርግ ኢንጂነር ክፍሎም “አብረሃ ካስትል” ጀርባ ወደሚገኘው የቤተሰቦቹ ቤት በእግር ያዘግማል። ሦስት ወጣቶችን ከቤተሰቡ ቤት ደጃፍ እንደነገሩ ያያቸዋል። ገዳዮቹ ሊኾኑ እንደሚችሉ ግን ፍጹም አልጠረጠረም። ‹‹ከመቅጽበት አንደኛው በቦክስ አጣደፈኝ፤ መነጽሬ ዐይኔ ላይ ተሰባበረ፣ የቡጢው ኀይል መነጽሩን አልፎ ክፉኛ ጎዳኝ፣ የተቀሩት ሁለቱ ወንበዴዎች ደግሞ ጉሮሮዬን አንቀው ጣሉኝ፤ አረፋ ደፍቄ በሞት እና በሕይወት መሀል ሳለኹ ከአካባቢው ሆያ ሆዬ ጨፍረው የሚመለሱ ወጣቶች እንደታረደ በግ ሳጓራ ሰምተው ደረሱልኝ። ሌቦቹ ሞባይሌን እና የኪስ ቦርሳዬን ይዘው ተሰወሩ:: ነፍሴ ግን አልተሰወረችም። ለመስቀል በዐል ጨፍረው ይመለሱ በነበሩ ትንንሽ ልጆች ምክንያት ተረፈች።” ይላል ሦስት ዓመታትን የኋሊት ተጉዞ።

ክፍሎም ባደገባት አገሩ ለያውም በሰፈሩ ለያውም በቤቱ ደጃፍ እንዲያ ወደሞት አፋፍ ያስጠጉትን ወንጀለኞች ሊፋለም ተነሳ። ለሳምንታት እየደማ ያስቸግረው የነበረውን ጉሮሮው እስኪድን እንኳ ሳይጠብቅ ዉሎ እና አዳሩን ፖሊስ ጣብያ አደረገ። ኾኖም “እንኳን አተረፈህ የሚል እንጂ ወንጀለኞቹን ለማደን የተዘጋጀ ፖሊስ  አላጋጠምኝም።” ይላል። በዚያው ሰሞን፣ በዚያው ሰፈር ሌላ ሴት እርሱ ለኮንስትራክሽን ብቻ እንደሚያገለግል በሚያውቀው “ቴንዲሞ” በተባለ ብረት በሌቦች ተመታ ሆስፒታል መግባቷን ሰማ። ከዚያ በኋላ ባሉት ሳምንታት በተለያየ አጋጣሚ ከሚያገኛቸው ሰዎች የሚነገረው ወሬ ተመሳሳይ ነበር፤ ወንበዴዎች በሌሎች አጎራባች ሰፈሮች የፈጸሟቸው ጀብዶች። “አንድም የወንጀል ዜና ሳልሰማ ያሳለፍኩበት ሳምንት አልነበረም” ይላል ክፍሎም።

ሚያዚያ የፋሲካ ዋዜማ፣ 2002

ኢንጂነር ክፍሎም ጠንከር ያለ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ነው። የፋሲካ ዋዜማ ምሽት የግል መኪናውን እያሽከረከረ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ደረሰ። እስከ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ለፈጣሪው ሰላምን ተማጸነ። ቅዳሴ አልቆ ‹‹ሀውልቲ- ዳግም አምሳል››  አካባቢ አዲስ ወዳሰራው ቤቱ መኪናውን ማሽከርከር ጀመረ። ቤቱ ሲደርስ በዓል በዓል የሚል አውድ አልጠበቀውም። ይልቁንም ዋናው በር ተገንጥሎ፣ የሳሎን በር ተፈልፍሎ ንብረቱ ተዘርፎ የሚያቀውቀው ቤቱ ጅምር ቤት መስሎ ጠበቀው። ወደሌላኛው ክፍል ዘለቀ። ሠራተኛው እንቅልፍ ጥሏታል። በግምት 40 ሺሕ ብር የሚጠጋ ንብረት በአንድ ሌሊት ተዘረፈ። ፋሲካን ፖሊስ ጣብያ አከበረ። በታላቅ ሐዘን እና ተስፋ መቁረጥ።

“ሌሊት ቤቴ መዘረፉን እንደተረዳኹ ፖሊስ ጣብያ ደወልኩ። እኔን በገረመኝ ፍጥነት መጥተው የኾነውን ሁሉ ካዩ በኋላ ጠዋት መጥተው ምርመራ እንደሚጀምሩ እና አሻራ እንደሚያነሱ ነግረውኝ ሄዱ” ሌሊቱን ቁጭ እንዳልኹ ነጋ፤ ጠዋት ይመጣሉ ብዬ ብጠብቅ ግን ዝር የሚል ፖሊስ አጣኹ። ትእግስቴ ሲሟጠጥ ደወልኩላቸው፤ “ምን ኾንክ ተዘረፍክ እንዴ፣ መቼ… የት አካባቢ ነህ…” ብለው እንደ አዲስ ጠየቁኝ። ደግሜ የኾንኹትን ሁሉ ነገርኳቸው። ኾኖም ሥራ በዝቶባቸው ይኹን ረስተውኝ ምንም ሊመጡ አልቻሉም። ከዚያ በኋላ በተደጋጋሚ ጣቢያ እየተመላለስኩ ምርመራ እንዲጀምሩልኝ፣ ቢያንስ አሻራ አንስተው እንዲሄዱ ብማጸንም “ቢዚ ነን” እያሉ የውኃ ሽታ ኾኑ” ይላል ወራትን የኋሊት እያሰበ።

ሐምሌ 25፣ 2002

ኢንጂነር ክፍሎም ከሦስት ዓመት በፊት ከደረሰበት የማጅራት መቺዎች ጥቃት ቢያገግምም ከአራት ወር በፊት ቤቱ ላይ ከደረሰበት ዝርፊያ ግን እምብዛምም አላገገመም  ነበር።ሰሞኑን ሁሌም እንደሚያደርገው የሚያስገነባቸው ሳይቶችን ለማየት ከመሄዱ በፊት ሮማናት አካባቢ ወደሚገኘው ቢሮው አቀና። የእርሱ ቢሮ የሚገኘው “ስየ ሆቴል” ጎን ሲኾን አካባቢው ዘወትር ሌሊት አስረሽ ምቺው የሚደምቅበት አካባቢ ነው። በሰፈሩ በተደጋጋሚ ግለሰቦች በማጅራት መቺዎች ጥቃት ስለሚደርስባቸው የከተማው ፖሊስ ቋሚ ጥበቃዎችን ይመድባል።

ኢንጂነር ክፍሎም በዚህ አካባቢ የሚገኘው ቢሮው ሊዘረፍ ይችላል ብሎ ግን የገመተ አይመስልም። ማልዶ ወደ ቢሮው ያቀናው ወጣቱ ኢንጂነር መኪናውን አቁሞ የቢሮውን ቁልፍ ለማግኘት እጁን ወደ ኪሶቹ ሰደደ። ያን ዕለት ግን ቢሮውን ለመክፈት ቁልፍ አያስፈልገውም ነበር። እንደ ቤተሰብ እየተላመዱት የመጡት ሌቦች ሌሊት ቢሮውን ከፍተው ከበረበሩ በኋላ ያስቀሩለት የቤት ፕላን የተሠራባቸውን ወረቀቶች፣ ማስመርያዎች እና ጠረጴዛውን ብቻ ነበር። “ሦስት ላፕቶፕ (ሁለቱ ቢሮውን የሚጋሩት የሥራ ባልደረቦቹ ናቸው)፣ ዐሥራ ሦስት ሺሕ ብር፣ ሲዲኤምኤ፣ ሃርድ ዲስክ) ተዘረፍኩ። ለሦስተኛ ጊዜ። መዘረፌንም እንደተለመደው ሪፖርት ላደርግ ሄደኩ ይላል” ስልቹነት በሚነበብበት ስሜት።

ኢንጂነር ክፍሎም በንዴት ጦፎ፣ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ፖሊስ ጣብያ ሲደርስ ተመሳሳይ አቤቱታ ለማቅረብ የተሰለፉ ሰዎችን ማግኘቱ በትንሹም ቢኾን እንዲጽናና አደረገው። ከመርማሪ ፖሊሶች የሰማውን ግን ማመን ተስኖታል። “ንብረትህን ለማስመለስ ከሌቦቹ ጋራ መደራደር ነው የሚበጅህ፣ እኛ እጃችንን ካስገባንበት ንብረትህን ላታገኝ ትችላለህ። ሌቦቹ ሐራምቤ ሆቴል አካባቢ ነው የሚዉሉት። የአስመራ ልጆች ናቸው። በሚያውቃቸው ሰው አድርገህ ዕቃህን ለማስመለስ ሞክር። ሁሉም የተሰረቀ ሰው እንደዚያ ነው የሚያደርገው። ላንተው ብለን ነው።”

ኢንጂነር ክፍሎም የፖሊሶቹን “ቅን ምክር” ሰምቶ ንብረቶቹን ለማስመለስ መንገዱን ተያያዘው፤ በቀላል ኪስ አውላቂነት የተሰማሩ የመቀሌ ልጆችን በአማላጅነት ወደ አስመራ ልጆች ዘንድ ልኮ ምላሻቸውን በጉጉት መጠባበቅ ጀመረ፤ ውስጡ ግን ፖሊስ ጣብያ በመሄድ ያጠፋውን ጊዜ እያሰላ ይቃጠል ነበር።

ሌሊት የምትበረበር ከተማ

መቀሌ በክፍሎም ላይ የደረሱ የዝርፍያ ታሪኮችን በተለያየ መንገድ ታስተናግዳለች። እንደ ወይዘሮ ሸዊት ገብረ ጻድቅ ያሉ ሰዎችም የዚሁ ዕጣ ተካፋይ ኾነዋል። የ‹‹ቀልቀል ደብሪ›› ሰፈር ነዋሪ የኾኑት ወይዘሮ ሸዊት ሌቦች መኪና አምጥተው በራቸውን ከፍተው መቶ ሺህ ብር የሚጠጋ ወርቅ ያስቀመጡበትን ኮሞዲኖ ጨምሮ ሶፋ፣ብፌና ሌሎች ለአያያዝ እንኳ የማይመቹ የቤት ቁሳቁሶችን ጭነው ሲወስዱባቸው እንቅልፍ አላሸለባቸውም ነበር። ከሌቦቹ ጋራ በዚያ ሌሊት መጋፈጥ ለሕይወታቸው አስጊ መስሎ ስለታያቸው የሚኾነውን ሁሉ ድምፅ አጥፍተው ይከታተሉ ነበር። ከሳምንት ቀደም ብሎ በዚያው ‹‹ቀልቀል ደብሪ›› ሰፈር ከእርሳቸው አምስተኛ ቤት ላይ የሚገኙ ጎረቤቶቻቸው መዘረፋቸውን ሰምተዋል። ተራዬ በዚህ ፍጥነት ይደርሳል የሚል ግምት ግን አልነበራቸውም።

ዘራፍ ለማለት የሞከረች ሠራተኛቸውን የመጋረጃ ያህል እንኳ ሳይቆጥሯት ገፍተር አድርገዋት የቤታቸውን ዕቃ አንድ በአንድ ሲጭኑ ወይዘሮዋ የሌቦቹን ጤንነት እስከመጠራጠር ደርሰው ነበር። ሌቦቹ ግን ሥራ ላይ ናቸው፤ ሥምሪት ላይ። ንጋት አካባቢ የሌቦቹን ከአካባቢው መሰወር እንደተረዱ ሠራተኛቸውን አስከትለው ፖሊስ ዘንድ ቢደርሱም ከተረኛ ፖሊሱ ያገኙት ምላሽ ቁጣ የተቀላቀለበት ነበር። “ቤታችኹን ነቅታችኹ አትጠብቁም! እኛን ምን አድርጉ ነው የምትሉን! ስማችንን ለማጥፋት ነው እንጂ…”

ወይዘሮ ሸዊት የሰሙትን ጉድ ጆሯቸው ማመን አልቻለም። “በእንቅርት ላይ. . .” እንዲሉ የኾኑትን የሚነግሩት ዘመድ ወዳጅ ኹሉ ሌሎች የተዘረፉ ሰዎችን ስም ዝርዝር ከአዘራረፍ ቴክኒኮች ጋራ እያዋዛ የሚያጫውታቸው በዛ። ‹‹እከሌም እኮ ተዘርፏል፣ እከሊትስ ብትይ፣…እንትናን ያረጓትን ሰምተሻል…እንቶኔንማ አላስተረፉትም እኮ…” ወይዘሮ ሸዊት የቀጣይ ቀን የመጀመርያ ሥራቸው አደገኛ የኤሌክትሪክ አጥር ማስገጠም ነበር።

የፖሊስ ያለህ አትሉም ወይ…

የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዬ ዘጋቢ የኾኑት አቶ ግርማይ ገብሩ ስለዚሁ ጉዳይ የታዘቡት ነገር አላቸው። ላለፉት ሦስት ዓመታት ለቁጥር የሚያታክቱ ተደጋጋሚ “የተዘረፍን” የሕዝብ ጥቆማ ደርሷቸዋል እንደደረሳቸው ያወሳሉ። በዚሁ ርእሰ ጉዳይ ላይ “በመቀሌ ወንጀል ስለመበራከቱ” አንድ ዘገባ ከዓመታት በፊት ለሚሠሩበት የሬዲዮ ጣብያ መላካቸውን የሚያስታውሱት ጋዜጠኛው ከፕሮግራሙ ወዲህም ቢኾን የነዋሪው አቤቱታ እየበረታ እንጂ እየቀነሰ እንዳልመጣም ይጠቅሳሉ።  ከሁለት ቀናት በፊት እንኳ ተመሳሳይ የድረሱልን የስልክ ጥሪዎችን ተቀብለዋል።  ከእነዚህ አንዱ መቀሌ አየር ማረፍያ አካባቢ 2000 የአሜሪካን ዶላር የተዘረፈች ወጣትን ጉዳይ ይመለከታል። አቶ ግርማይ እንደሚናገሩት የመቀሌ የዘረፋ ጀብዱዎች ከአገር ውስጥ አልፈው በሌላውም ዓለም ጭምር እየተሰሙ ነው። ምክንያቱም ይላሉ አቶ ግርማይ “ምክንያቱም በፓልቶክ የኢንተርኔት መረብ ውይይት የማገኛቸው ዳያስፖራዎች ጭምር ስለዚሁ ጉዳይ ይነግሩኛል።››

መቀሌ ረዘም ላለ ጊዜ ሌቦችን ጉያዋ ውስጥ ሸጉጣ ተንከባክባለች። አልፎ አልፎ በአድናቆት የሚያስጨበጭቡ የሆሊውድ ፊልም የሚመስሉ የሥርቆት ዐይነቶች ይካሄዱባታል። ከዓመታት በፊት በከተማዋ እንብርት የሚገኝ በምሳ ሰዓት ተዘግቶ የነበረ አንድ ወርቅ ቤት በጠራራ ፀሐይ የቴሌ ሠራተኞችን ዩኒፎርም አስመስለው የለበሱ፣ መሰላላቸውን ዘርግተው፣ የስልክ ሽቦ እንደሚዘረጉ ኾነው፣ የሠራተኞቹን እግር ውልቅ ማለት አስተውለው ወርቅ አፍሰው፣ በወርቅ አጊጠው ወጡ አሉ፤ የአስመራ ልጆች። ይህ ወሬ አንድ ሰሞን ለወራት ያህል የማያቋርጥ የከተማዋ ዋነኛ የማኪያቶ ርእሰ ጉዳይ ኾኖ ሰነበተ። የኋላ ኋላ ግን ጀብደኞቹ ሌቦች መያዛቸው ተሰማ። በሌላ ጊዜ የትግራይ ክልል ክብርት አፈ-ጉባኤ የኾኑት ሴትዮ መኖርያ ቤት ጣርያ ላይ ሊሰርቅ በዝግጅት ላይ የነበረ ወጣት በርብርብ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ተደረገ፡  ግብረ አበሮቹ ግን ወድያውኑ ተሰውረዋል።

የፕሮፌሰሩ ላፕቶብ

የመቀሌ ነዋሪዎቿ ብቻ አይደሉም የሚበረበሩት። ብርበራው ለእንግዶቿም ይተርፋል። የሕንድ፣ የባንግላዲሽ፣ የጀርመን፣ የኬንያ እና የቻይና ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በተለያዩ ጊዜያት ላፕቶፖቻቸውን ተሠርቀዋል፤ ከመኖርያቸው። በዚህም የተነሳ ብዙዎቹ በከተማዋ የሚገኙ የውጭ ዜጎች በተለይም የሕንድ መምህራን ላፕቶፖቸውን ጡት እንዳልጣለ ልጅ ታቅፈው ይዝናናሉ። ቀሪዎቹ ደግሞ ዩኒቨርስቲ ቢሮ አስቀምጠውት ወደቤታቸው ይሄዳሉ። ይኹን እንጂ የመቀሌን ዝርፍያ የዩኒቨርስቲ ግንቦችም አያግዱትም። መቀሌ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ብቻ ባለፉት ስድስት ወራት ስምንት መምህራን ላፕቶፕ መሰረቃቸውን ሪፖርት አድርገዋል። ስማቸውን ለመግለጽ ያልፈቀዱ አንድ ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ፕሮፌሰር ከአንድ ወር በፊት በዩኒቨርስቲው በጊዜያዊነት በተሰጣቸው ቢሮ ውስጥ ላፕቶፓቸውን አስቀምጠው ማኪያቶ ፉት ብለው ሲመለሱ ምድር ትዋጠው ሰማይ ይሰልቅጠው ማወቅ አልቻሉም። እኚህ ፕሮፌሰር ለሌቦቹ ያላቸውን አድናቆት እየነደዳቸውም ቢኾን ከመግለጽ አልተቆጠቡም። “በዚህ ፍጥነት የኔ አገር ሰዎችም አይሰርቁም።”

የአሥመራ ልጆች

ከባድ እልቂት ያስከተለውን የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት ተከተሎ በነበሩት ዐሥር ዓመታት ውስጥ አያሌ ኢትዮጵያዊያን መረብን ተሻግረዋል። በልዩ ልዩ የኤርትራ እሥር ቤቶች ታሽተው፣ መራር ጊዜን አሳልፈው ለእናት አገራቸው ከበቁ በኋላ ብዙም የመቦረቅ ጠባይ አያሳዩም። ብዙዎቹን ተጠግተው ሲያወሯቸው አሥመራ ያሳለፉትን አስቸጋሪ ጊዜ ከማውራት ይልቅ መልካም መልካሙን ማውሳት ይቀናቸዋል። አሥመራን የሌላ አገር ሌላ ከተማ አድርገው አያስቧት ይኾናል። ኾኖም አትርፎ መግባት ከለመዱባት አሥመራ ሲመለሱ ሀብት ንብረታቸውንም ኾነ የቋጠሩትን ጥሪት እንዲሸክፉ አልተፈቀደላቸውም። በመኾኑም ብዙዎች ሞያቸውን ጥቂቶች ደግሞ ባዶ እጃቸውን ይዘው ነበር መረብን ተሻግረው መቀሌ የከተሙት።

የአሥመራ ልጆች ፈጣን ጭንቅላት እና ከተሜነት ይታይባቸዋል። እነርሱን ከነባር ከተሜው ለመለየት ብዙ ብዙ ጥረት አይጠይቅም። ሌላው ቢቀር ንግግራቸው ያሳብቅባቸዋል። በአዲስ አበባ “እሳት የላሱ” የሚባሉትን ዐይነት ናቸው።  “ምሽ”፣ “ሕራይ”፣ “ክንጭርብ በጃኻ” የሚሉ ቃላትን አሁንም አሁንም ደጋግመው ይጠቀማሉ። ዜማ የሚጫነው የትግርኛ ድምፃቸውም የት እንደከረሙ ይናገራል።

የአሥመራ ልጆች በሚያስገርም ፍጥነት የመቀሌን ቢዝነስ ሰርገው ገብተው ለመቆጣጠር የቻሉ ናቸው። የከረንቡላ ሥራ፣ የጋራዥ ሥራ፣ የብረታ ብረት ሥራ፣ የእንጨት ሥራ የመሳሰሉ ሞያ ነክ ዘርፎችን ተዐምር በሚመስል ፍጥነት ጀምረው በአጭር ጊዜ ውስጥ የበቁ የቢዝነስ ሰዎች ኾነዋል። የሚገርመው የአሥመራ ልጆች የበር እና መስኮት የብረት ፍሬሞችን፣ እጀታዎችን ሰረገላዎችን መገጣጠም ብቻ አይደለም የሞያቸው አጽናፍ። ቀን በጠራራ ፀሐይ የገጠሙትን  ሌሊት መጥቶ መፍታቱንም ተክነውታል። “ቦርባሪዎች” ይሏቸዋል ነባር መቀሌያውያን።

ከንቲባውም ተሰርቀዋል

ሐራምቤ ሆቴል አካባቢ የምትገኘው የመቀሌ አንዷ መንደር ከአዲስ አበባዋ የቀድሞዋ ‹‹ሶማሌ ተራ›› በሁለመናዋ ጭምር ትመሳሰላለች። የሚገርመው ሐራምቤን መቀሌዎች “ሞቃዲሾ” እያሉ ይጠሯታል፤ ሁለቱም ከሶማልያ አልራቁም። በዚህ አካባቢ የቤት ቁልፍ፣ ሰረገላ፣ የበር እጀታ፣ የባጃጅ፣ የሞተር ሳይክል እና የሳይክል መለዋወጫዎች ይሸጥባታል። በስፍራው የጋራዥ ቱታ የሚለብሱ ወጣቶች ይበዙበታል። የተለመዱት የአሥመራ ልጆች። አሁን አሁን የመቀሌ ነዋሪዎች በነፍስ ወከፍ ሁለት እና ሦስት የዘረፋ ልብ አንጠልጣይ ትረካዎችን ማውጋት ኹነኛ የጊዜ ማጥፊያ ወግ አድርገው ይዘውታል።

“ሰሚእካ ንዶ!”

”ታይ”

“ትማሊ ምሸት…”

እየተባባሉ።

በከተማዋ ከምንጊዜውም በላይ ሥርቆት ተበራክቷል። አዲስ ነገር ለዚህ ጽሑፍ የፖሊስን መረጃ ለማካተት ያደረገችው ሙከራ ባይሳካም ስማቸው እንዲገለጽ የማይፈልጉ የፖሊስ ባልደረቦች ግን በሳምንት በትንሹ ከአምስት እስከ ዐሥራ አምስት የተቀናጁ የዘረፋ ሪፖርቶች እንደሚደርሷቸው አልሸሸጉም። ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈቀደ አንድ ፖሊስ አባል ደግሞ እንዲህ ይላል “ከንቲባውምኮ ተሰርቀዋል!” ሞባይላቸውን። መኪና ሲነዱ ተጋጭተው ከመኪናቸው ሲወርዱ ሌባው ሞባይላቸውን ይዞ ተሰወረ።” ሰሚው መደነቁን ሳያባራ ግን ፖሊሱ እንዲህ ሲል አሳረገ። “ግን አስመልሰንላቸዋል።”

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

‹‹ድህነትን ለመሰናበት›› ልዩ የመዝናኛ ዝግጅት ለኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ እየተላለፈ ነው፡፡

በሰራዊት መልቲ ሚዲያ አስተባባሪነትና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፊታውራሪነት ድህነትን ለመሰናበትና እንዲሁም የአምስት አመቱን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ መጀመርን ለማብሰር ልዩ የመዝናኛ ድግስ በቴሌቪዥን እየተላለፈ ይገኛል፡፡ ዝግጅቱ  ከሚሌኒየም አዳራሽ  በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አማካኝነት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ እየተላለፈ ሲሆን በዋና ዋና የክፍለ ሀገር ከተሞች ደግሞ ለዚሁ ዝግጅት ሲባል ግዙፍ የሶኒክ ስክሪኖች እንደተሰቀሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዝግጅቱ መግቢያ ላይ [...]

በሰራዊት መልቲ ሚዲያ አስተባባሪነትና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፊታውራሪነት ድህነትን ለመሰናበትና እንዲሁም የአምስት አመቱን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ መጀመርን ለማብሰር ልዩ የመዝናኛ ድግስ በቴሌቪዥን እየተላለፈ ይገኛል፡፡ ዝግጅቱ  ከሚሌኒየም አዳራሽ  በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አማካኝነት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ እየተላለፈ ሲሆን በዋና ዋና የክፍለ ሀገር ከተሞች ደግሞ ለዚሁ ዝግጅት ሲባል ግዙፍ የሶኒክ ስክሪኖች እንደተሰቀሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በዝግጅቱ መግቢያ ላይ በመድረክ አስተዋዋቂዎች ‹‹ድህነትን ቻው በሉ›› በማለት ታዳሚውን የጠየቁ ሲሆን ከመድረኩ ፊት ለፊት በተሰቀለ ስክሪን በአዲስ አበባ የተገነቡ ዘለግ ያሉ ህንፃዎችና አዳዲስ መንገዶች እንዲሁም የጋራ መኖርያ ቤቶች እንዲታዩ ተደርጓል፡፡ ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሚዘልቁ የባህልና ዘመናዊ ዘፋኞች፣የፊልም ባለሙያዎች፣ስም ያላቸው  አርቲስቶችና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የዝግጅቱ ተካፋይ ናቸው፡፡ የአዲስ አመት ዋዜማና የኢድ አልፊጥር ማምሻ ላይ እየተካሄደ ያለው ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ የመዝናኛ ዝግጅት በዋናነት የተሰናዳው መንግስት በቅርቡ ይፋ ያደረገው የአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን በህዝብ ዘንድ አፅእኖት እንዲሰጠው ለማድረግ የታለመ እንደሆነ ይገመታል፡፡

Goodbye poverty tonight! ‹‹ድህነትን ቻው በሉልን›› የሚሉ ተደጋጋሚ ቃላት ከመድረክ የቀረበ ሲሆን የመንግስት ሚኒስተር መስሪያ ቤቶች በታዋቂ አርቲስቶች ተመስለው ህልማቸውን በመድረክ እንዲያቀርቡ ተደርጓል፡፡ የትምሀርት ሚኒስትር ‹‹ወጣቱን ኤክስፖርት ሳይሆን ኤክስፐርት አደርጋለሁ›› ያለ ሲሆን በአርቲስት አብራር አብዶ የተወከለው ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ‹‹ በሽታ የማይነካቸው የሚቦርቁ ህፃናትን›› አፈጥራለሁ ብሏል፡፡

በሀረገወይን አሰፋ የተወከለው የመንገዶች ባለስልጣን ደግሞ ‹‹ ደራሽ ውሀ በስር ይለፍ እኛ በህዳሴው ድልድይ እናልፋለን›› ሲል ተናሯል፡፡ በችሮታው ከልካይ የተወከለው የግብርና ገጠር ልማት ሚኒስትር ‹‹ ስንዴ መለመን ድሮ ቀረ፣ 80 ሚሊዮን ህዝብ እንመግባለን›› ሲል ፉከራውን በመድረክ አሰምቷል፡፡ መጪው ዘመን የጥጋብ ነው ሲልም በእልልታ የታጀበ ውዝዋዜን አሳይቷል፡፡  ዝናን እያጣጣመች የምትገኘው አርቲስት መሰረት መብራቴ የቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤትን የወከለች ሲሆን ቴሌ በቀጣይ አምስት አመት ‹‹በድህነት ላይ ሊሳለቅ ተዘጋጀቷል›› ‹‹ኔትወርክ ተጨናነቀ ተረት ይሆናል›› ስትል ተናግራለች፡፡ ድህነትን አከርካሪውን ሰብሮ አይለመደኝም እስኪል እንመታዋለን›› ያሉት ደግሞ ሜድሮክን የወከሉ አርቲስቶች ናቸው፡፡

‹‹ሻማ ለልደት ብቻ ለች፡፡   ጥላሁን ጉግሳ የኢንዱስትሪ ሚሊበራ፣ ኩራዝ ሙዚየም ሊቀመጥ›› ወስኗል ያለው አርቲስት ሙሉአለም ታደሰ ‹‹ አሁን ብልጭ ድርግም ቢልም ግድ የለም ይሁን ሊነጋ ሲል ይጨልማል›› ስትል ህልሟን ተናግራኒስትርን የወከለ ሲሆን ‹‹ሊረከብ ነው!›› የሚል ፉከራን አሰምቷል፡፡ አርቲስት ሙሉአለም ታደሰ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን ወክላ መድረክ ላይ የቆመች ሲሆን ሸዋፈራሁ ደሳለኝ ና ሌሎች ታዋቂ አርቲስቶችም በተመሳሳይ መልኩ በመድረኩ ላይ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን እየወከሉ ፉከራና ቀረርቶ አሰምተዋል፡፡

3 Responses to “‹‹ድህነትን ለመሰናበት›› ልዩ የመዝናኛ ዝግጅት ለኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ እየተላለፈ ነው፡፡”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

‹‹ድህነትን ለመሰናበት›› ልዩ የመዝናኛ ዝግጅት ለኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ እየተላለፈ ነው

Goodbye poverty tonight! ‹‹ድህነትን ቻው በሉልን›› የሚሉ ተደጋጋሚ ቃላት ከመድረክ የቀረበ ሲሆን የመንግስት ሚኒስተር መስሪያ ቤቶች በታዋቂ አርቲስቶች ተመስለው ህልማቸውን በመድረክ እንዲያቀርቡ ተደርጓል፡፡ የትምሀርት ሚኒስትር ‹‹ወጣቱን ኤክስፖርት ሳይሆን ኤክስፐርት አደርጋለሁ›› ያለ ሲሆን በአርቲስት አብራር አብዶ የተወከለው ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ‹‹ በሽታ የማይነካቸው የሚቦርቁ ህፃናትን›› አፈጥራለሁ ብሏል፡፡ በሀረገወይን አሰፋ የተወከለው የመንገዶች ባለስልጣን ደግሞ ‹‹ ደራሽ ውሀ በስር ይለፍ እኛ በህዳሴው ድልድይ እናልፋለን›› ሲል ተናሯል፡፡ በችሮታው ከልካይ የተወከለው የግብርና ገጠር ልማት ሚኒስትር ‹‹ ስንዴ መለመን ድሮ ቀረ፣ 80 ሚሊዮን ህዝብ እንመግባለን›› ሲል ፉከራውን በመድረክ አሰምቷል፡፡ መጪው ዘመን የጥጋብ ነው ሲልም በእልልታ የታጀበ ውዝዋዜን አሳይቷል፡

በሰራዊት መልቲ ሚዲያ አስተባባሪነትና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፊታውራሪነት ድህነትን ለመሰናበትና እንዲሁም የአምስት አመቱን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ መጀመርን ለማብሰር ልዩ የመዝናኛ ድግስ በቴሌቪዥን እየተላለፈ ይገኛል፡፡ ዝግጅቱ  ከሚሌኒየም አዳራሽ  በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት አማካኝነት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ እየተላለፈ ሲሆን በዋና ዋና የክፍለ ሀገር ከተሞች ደግሞ ለዚሁ ዝግጅት ሲባል ግዙፍ የሶኒክ ስክሪኖች እንደተሰቀሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በዝግጅቱ መግቢያ ላይ በመድረክ አስተዋዋቂዎች ‹‹ድህነትን ቻው በሉ›› በማለት ታዳሚውን የጠየቁ ሲሆን ከመድረኩ ፊት ለፊት በተሰቀለ ስክሪን በአዲስ አበባ የተገነቡ ዘለግ ያሉ ህንፃዎችና አዳዲስ መንገዶች እንዲሁም የጋራ መኖርያ ቤቶች እንዲታዩ ተደርጓል፡፡  ቁጥራቸው ከ50 በላይ የሚዘልቁ የባህልና ዘመናዊ ዘፋኞች፣የፊልም ባለሙያዎች፣ስም ያላቸው አርቲስቶችና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የዝግጅቱ ተካፋይ ናቸው፡፡ የአዲስ አመት ዋዜማና የኢድ አልፊጥር ማምሻ ላይ እየተካሄደ ያለው ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ የመዝናኛ ዝግጅት በዋናነት የተሰናዳው መንግስት በቅርቡ ይፋ ያደረገው የአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን በህዝብ ዘንድ አፅእኖት እንዲሰጠው ለማድረግ የታለመ እንደሆነ ይገመታል፡፡

Goodbye poverty tonight! ‹‹ድህነትን ቻው በሉልን›› የሚሉ ተደጋጋሚ ቃላት ከመድረክ የቀረበ ሲሆን የመንግስት ሚኒስተር መስሪያ ቤቶች በታዋቂ አርቲስቶች ተመስለው ህልማቸውን በመድረክ እንዲያቀርቡ ተደርጓል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ‹‹ወጣቱን ኤክስፖርት ሳይሆን ኤክስፐርት አደርጋለሁ›› ያለ ሲሆን በአርቲስት አብራር አብዶ የተወከለው ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ‹‹ በሽታ የማይነካቸው የሚቦርቁ ህፃናትን›› አፈጥራለሁ ብሏል፡፡  በሀረገወይን አሰፋ የተወከለው የመንገዶች ባለስልጣን ደግሞ ‹‹ ደራሽ ውሀ በስር ይለፍ እኛ በህዳሴው ድልድይ እናልፋለን›› ሲል ተናሯል፡፡ በችሮታው ከልካይ የተወከለው የግብርና ገጠር ልማት ሚኒስትር ‹‹ ስንዴ መለመን ድሮ ቀረ፣ 80 ሚሊዮን ህዝብ እንመግባለን›› ሲል ፉከራውን በመድረክ አሰምቷል፡፡ መጪው ዘመን የጥጋብ ነው ሲልም በእልልታ የታጀበ ውዝዋዜን አሳይቷል፡፡

ዝናን እያጣጣመች የምትገኘው አርቲስት መሰረት መብራቴ የቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤትን የወከለች ሲሆን ቴሌ በቀጣይ አምስት አመት ‹‹በድህነት ላይ ሊሳለቅ ተዘጋጀቷል›› ‹‹ኔትወርክ ተጨናነቀ ተረት ይሆናል›› ስትል ተናግራለች፡፡ “ድህነትን አከርካሪውን ሰብሮ አይለመደኝም እስኪል እንመታዋለን›› ያሉት ደግሞ ሜድሮክን የወከሉ አርቲስቶች ናቸው፡፡   ‹‹ሻማ ለልደት ብቻ ሊበራ፣ ኩራዝ ሙዚየም ሊቀመጥ ወስኗል ›› ያለው  ታምሩ ብርሃኑ ነው።  አርቲስት  ሙሉአለም ታደሰ ‹‹ አሁን ብልጭ ድርግም ቢልም ግድ የለም ይሁን ሊነጋ ሲል ይጨልማል›› ስትል ህልሟን ተናግራለች፡፡

ጥላሁን ጉግሳ የኢንዱስትሪ ሚኒስትርን የወከለ ሲሆን ‹‹ሊረከብ ነው!›› የሚል ፉከራን አሰምቷል፡፡ አርቲስት ሙሉአለም ታደሰ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን ወክላ መድረክ ላይ የቆመች ሲሆን ሸዋፈራሁ ደሳለኝ ና ሌሎች ታዋቂ አርቲስቶችም በተመሳሳይ መልኩ በመድረኩ ላይ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን እየወከሉ ፉከራና ቀረርቶ አሰምተዋል፡፡

2 Responses to “‹‹ድህነትን ለመሰናበት›› ልዩ የመዝናኛ ዝግጅት ለኢትዮጵያ ህዝብ በቀጥታ እየተላለፈ ነው”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

አንድ ሺህ አራት መቶ ሰላሳ አንደኛው የኢድ አልፊጥር በዓል እየተከበረ ነው፡፡

በመላው ኢትዮጵያ የኢድ አልፊጥር በአል እየተከበረ ሲሆን በአዲስ አበባ የሚገኙ ሙስሊሞች የኢድ ሰላትን በአዲስ አበባ ስታድየምና አካባቢው በመገኘት የሶላት ስነ ስርአት አካሄደዋል፡፡ ሼህ አህመዲን ሼህ አብዱላሂ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ሊቀመንበር፣ የሳይንስና ቴክኖሎጆ ሚኒስትር ሚኒስትር አቶ ጁነዲን ሳዶ፣ በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ አሊ አብዶ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በሶላት ስነ ስርዓቱ ተገኝተዋል፡፡ የኢድ ሶላት [...]

በመላው ኢትዮጵያ የኢድ አልፊጥር በአል እየተከበረ ሲሆን በአዲስ አበባ የሚገኙ ሙስሊሞች የኢድ ሰላትን በአዲስ አበባ ስታድየምና አካባቢው በመገኘት የሶላት ስነ ስርአት አካሄደዋል፡፡ ሼህ አህመዲን ሼህ አብዱላሂ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ሊቀመንበር፣ የሳይንስና ቴክኖሎጆ ሚኒስትር ሚኒስትር አቶ ጁነዲን ሳዶ፣ በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ አሊ አብዶ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በሶላት ስነ ስርዓቱ ተገኝተዋል፡፡

የኢድ ሶላት ላይ የተገኘው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሙስሊሙ ህብረተሰብ በምስራቅ እስከ ሜክሲኮ፣ በሰሜን እስከ ኢሲኤ የመሰብሰብያ አዳራሽ፣ በምእራብ እስከ ዑራኤል እንዲሁም በደቡብ እስከ ፊላሚንጎ አካባቢ የሚደርስ ቁጥር ነበረው፡፡ የኢድ ሶላትን የመሩት የአንዋር መስጊድ ኢማም ሀጂ ጣሀ ሀሩን ነበሩ፡፡

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

የአካል ጉዳተኛዋ ሕፃን ጩኸት – “የትምህርት ቤት ያለህ”

“በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ሚስጥረን ለመቀበል ፈቃደኛ የኾነ ትምህርት ቤት በድፍን አዲስ አበባ ማግኘት አልቻልኹም።” ይላሉ የሚስጥረ አባት አቶ ዳንኤል። አቶ ዳንኤል ሚስጥረን ለማስመዝገብ በአቅራቢያቸው ካለው ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ ተነስተው ብዙ ቦታዎችን አካለዋል። ”አሚጎኒያ”፣ “ፊቸር ሆፕስ”፣ “ኤል ቤቴል”፣ “ቀለመ ወርቅ” እና ሌሎች ከ10 በላይ የሚኾኑ የትምህርት ቤት ደጃፎችን ያለመታከት ተመላልሰውበታል። መልሱ ግን አንድ ዐይነት እና ተመሳሳይ ነው። “እንዲህ ዐይነት ልጅ አንቀበልም፣ ሌላ ቦታ ይሞክሩ” የሚል። “እጅግ ብሩህ አእምሮ ያላት ልጄ እንዴት በእግሯ (በአካል ጉዳተኝነቷ) ምክንያት ብቻ ከትምህርት ገበታ እንድትገለል ትኾናለች?”ሲሉ ተስፋ በቆረጠ ድምፅ ይጠይቃሉ።

ትምህርት ቤት ያላገኘችው የአካል ጉዳተኛ ሕፃን ሚስጥረ ዳንዔል

(ገዛኸኝ ዘርጋ)

ሕፃን ሚስጥረ ዳንኤል ገና የአምስት ዓመት ልጅ ናት። ባልታወቀ የተፈጥሮ እክል ምክንያት በጣቶቿ እንጂ በተረከዟ ረግጣ መቆም አትችልም። የጀርባ አጥንቷ ቀጥ ብላ እንድትራመድ አይፈቅድላትም። በመኾኑም በምትራመድበት ጊዜ የሰው ድጋፍ ያስፈልጋታል። የሚስጥረ እናት ጎደሎውን ኑሮ ለመሙላት ወደ ዐረብ አገር በማቅናታቸው፤  አቶ ዳንኤል ለሚስጥረ እንደ እናትም እንደ አባትም ኾነው ያኖሩዋታል፤ ይኖሩላታል። የአዲሱን ዓመት መምጣት ምክንያት አድርገው የመኖርን ትርጉም ሙሉ ያደርገዋል ብለው ወዳሰቡት የትምህርት ዓለም ልጃቸውን ለመጨመር በየትምህርት ቤቱ መዞር ከጀመሩም ሰንብተዋል። እውነቱ ግን ያሰቡትን ያህል ኾኖ አላገኙትም፤ ለልጃቸው የሚኾን ትምህርት ቤት ማግኘት ሕልም ወደ መኾን እየተቀየረ ነው። ሁሉም ትምህርት ቤቶች በራቸውን መለሱባቸው፤ ዘጉባቸው።

“በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ሚስጥረን ለመቀበል ፈቃደኛ የኾነ ትምህርት ቤት በድፍን አዲስ አበባ ማግኘት አልቻልኹም።” ይላሉ የሚስጥረ አባት አቶ ዳንኤል። አቶ ዳንኤል ሚስጥረን ለማስመዝገብ በአቅራቢያቸው ካለው ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ ተነስተው ብዙ ቦታዎችን አካለዋል። ”አሚጎኒያ”፣ “ፊቸር ሆፕስ”፣ “ኤል ቤቴል”፣ “ቀለመ ወርቅ” እና ሌሎች ከ10 በላይ የሚኾኑ የትምህርት ቤት ደጃፎችን ያለመታከት ተመላልሰውበታል። መልሱ ግን አንድ ዐይነት እና ተመሳሳይ ነው። “እንዲህ ዐይነት ልጅ አንቀበልም፣ ሌላ ቦታ ይሞክሩ” የሚል። “እጅግ ብሩህ አእምሮ ያላት ልጄ እንዴት በእግሯ (በአካል ጉዳተኝነቷ) ምክንያት ብቻ ከትምህርት ገበታ እንድትገለል ትኾናለች?”ሲሉ ተስፋ በቆረጠ ድምፅ ይጠይቃሉ።

ሚስጥረ እንደማንኛው አዲስ አበባ ውስጥ እንዳለ ሕፃን ትምህርት ያስፈልጋታል በሚል እምነት በየትምህርት ቤቶቹ ሲዞሩ የነበሩት አባቷ ብቻ አልነበሩም። የሴት አያቷም እንዲሁ በሙከራ ማስነዋል፤ ባክነዋል። የትምህርት ቤት ሐላፊዎችን ለማግባባት ያላደረጉት ነገር የለም። አብዛኞቹ ሐላፊዎች ግን “ማስመዝገቢያ ብር ከሌለዎት እንስጥዎ እንጂ ልጆዎትን እኛ አንቀበልም” ሲሉ ነበር መልስ የሰጧቸው። “ትምህርት ቤቶቹ ሞግዚት ከሌላቸው እኔ ራሴ እንደሞግዚት አብሪያት ትምህርት ቤት ለመዋል ፈቃደኛ እኾናለኹ ብዬ ብናገርም የሚሰማኝ አላገኘኹም” ይላሉ።

እንደ ሚስጥረ ዐይነት የአካል ጉዳት ያለባቸው ሕፃናት መፍትሔ ለማግኘት የሚችሉበትን ስፍራ ማፈላለግ ሌላኛው የአቶ ዳንኤል ቀጣይ ሥራ ነበር። አእምሮዋ ጤናማ የኾነችው ልጃቸው ትምህርት ማግኘት አለባት ከሚለው አቋማቸው ዝንፍ የሚያደርጋቸው ነገር እንዲኖር አልፈለጉም። ስለዚህ መንግሥታዊ ወዳልኾኑት እና በአካል ጉዳተኝነት ላይ ትኩረት አድርገው ወደሚሠሩት ድርጅቶች ጎራ አሉ። አምስት ያህል የሚኾኑትንም በዚሁ ጉዳይ ላይ ለማነጋገር ጥረት አደረጉ። ምክራቸውንም እንዲለግሷቸው እና መፍትሄ እንዲያመላክቷቸው ጠየቁ። ይኹንና መፍትሄ ሊሰጣቸው የሚችል አንድ ስንኳ ማግኘት አልኾነላቸውም። “በርታ እንደውልልኻለን” የሚል ባዶ ተስፋ ከመስጠት በቀር።

አቶ ዳንኤል አካል ጉዳተኛ ልጃቸውን ከጀርባቸው አይነጥሏትም። ለቅሶ እና ሠርግን በመሳሰሉ ማኅበራዊ ግንኙነቶች ላይም ሕፃን ሚስጥረ አብራቸው ናት። ይህን እንደ ፈተና እና አስቸጋሪ ነገር አይቆጥሩትም። ከሁሉም በላይ ለእርሳቸው ፈተና የኾነባቸው እንደ ሕፃን ማግኘት የሚገባትን የትምህርት ዕድል መነፈጓ እና ማግኘት አለመቻሏ ነው። በአገር ውስጥ ሕክምና መታገዝ ያልቻለችው ሕፃን ሚስጥረ ከጥቁር አንበሳ ሪፈር እንደታጻፈላትም ያወሳሉ። ይህ ሕክምናዋ እውን እንዲኾንም ቀን ከሌት እየጣሩ ነው። ይኹንና አሁን ስለ ልጃቸው ትምህርት የማግኘት ዕድል የሚሰማቸው ስሜት የተዘበራረቀ ነው። ተስፋ በማድረግ እና ተስፋ በማጣት መካከል ያለ የስሜት ትግል። እስካሁን የሄዱበትን ጉዞ ወደ ኋላ መለስ ብለው ሲቃኙ ግን ሙሉ ለሙሉ የትምህርት ዕድል የማግኘቷ ነገር ተስፋ አስቆራጭ ይኾንባቸዋል። “ጨልሞብኛል” ይላሉ።

አቶ ዳንኤል ጴጥሮስ ስለልጃቸው ሲናገሩ ሳግ ይተናነቃቸዋል። “የየዕለት ሥራዬ ልጄን ማባበል ኾኗል” ሲሉ ለአዲስ ነገር ያብራራሉ። “ትምህርት ቤት ካልወሰድከኝ ምግብ አልበላም ትለኛለች። እርሷን ለማባበል እና ምግብ እንድትበላልኝ ለማድረግ ነገ ትምህርት ቤት አስገባሻለሁ እያልኩ እዋሻታለሁ። በማግስቱ በትምህርት ቤት ባለቤቶቹ እግር ሥር ወድቄ አለምናቸዋለኹ። ሁሉም ግን ለትምህርት ቤታችን ስም ጥሩ አይደለም እያሉ ልጄን ላለመቀበል ምክንያት ያቀርባሉ።” ይላሉ ዕንባቸውን ወደ ውስጥ እየዋጡት። የትምህርት ቤቶቹን አስተያየት ለማካተት አዲስ ነገር ያደረገችው ተደጋጋሚ ሙከራ በትምህርት ቤቶቹ አስተዳደሮች እምቢተኝነት ምክንያት አልተሳካም። በጉዳዩ ላይ ለማውራትም ኾነ ለመነጋገር ፈቃደኞችም አልኾኑም። ሕፃን ሚስጥረ ግን “የትምህርት ቤት ያለህ” የሚል የሕፃን ጩኸት እየጮኸች ነው።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

“ፋታ ያልሰጠኝ ሕይወቴ” ረዥም ልቦለድ ለገበያ ቀረበ

በሞያቸው የመካኒካል ኢንጂነር የኾኑት አቶ ዮሐንስ መጽሐፉን ለመሥራት የተነሳሱበትን ምክንያት ሲገልጹ ከሚኖሩበት እንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት መታጠብያ ቤት ሳሉ ድንገት ሐሳቡ እንደፈለቀላቸው እና ወድያዉኑ ርእሱን እንደጻፉት ተናግረው፤ ይህን ካደረጉ በኋላም መጽሐፉን የጨረሱት ያህል ደስ የሚል ስሜት እንደተሰማቸው በመጽሐፉ መግቢያ ላይ አብራርተዋል።

(አሮን ዘገየ)

ላለፉት 16 ዓመታት መኖርያቸውን በእንግሊዝ ያደረጉት አቶ ዮሐንስ ኀይለ ማርያም የመጀመርያ ሥራቸው የኾነውን “ፋታ ያልሰጠኝ ሕይወቴ” የተሰኘ ረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ እሁድ ነሐሴ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው የ‹‹ዲ ኤች ገዳ ታወር›› ሎቢ ውስጥ አስመረቁ።

ደራሲው ይህን መጽሐፍ ለመጻፍ ዘጠኝ ወራት እንደወሰደባቸው በምረቃ ሥነ ሥርዐቱ ላይ ተናግረዋል።  በሞያቸው የመካኒካል ኢንጂነር የኾኑት አቶ ዮሐንስ መጽሐፉን ለመሥራት የተነሳሱበትን ምክንያት ሲገልጹ ከሚኖሩበት እንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት መታጠብያ ቤት ሳሉ ድንገት ሐሳቡ እንደፈለቀላቸው እና ወድያዉኑ ርእሱን እንደጻፉት ተናግረው፤ ይህን ካደረጉ በኋላም መጽሐፉን የጨረሱት ያህል ደስ የሚል ስሜት እንደተሰማቸው በመጽሐፉ መግቢያ ላይ አብራርተዋል። ደራሲው ጨምረው እንደገለጹት አማርኛ ቋንቋ ለጽሑፍ አስቸጋሪ እና ውስብስብ እንደኾነባቸው አልሸሸጉም።

226 ገጾች ያሉት “ፋታ ያልሰጠኝ ሕይወቴ” ረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ ሜጋ ማተሚያ ቤት የታተመ ሲኾን ዋጋው 20 ብር ኾኖ ለመጀመርያ ዙር ዐሥር ሺሕ ኮፒ ለገበያ ማቅረባቸውን ደራሲው ለአዲስ ነገር ተናግረዋል። የመጽሐፉ ደራሲ በቀጣይነት ለኅትመት ያዘጋጇቸውን “አሮጊቷን ማን ገደላቸው” እና “ጣፋጭ ከረሜላ” የተሰኙ ሥራዎቻቸውን ለሕዝብ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ስብሓት ነጋን ጨምሮ ስምንት አንጋፋ የህወሓት አባላት ከማእከላዊ ኮሚቴ ተሰናበቱ

ዛሬ ማምሻውን ይጠናቀቃል ተብሎ የሚገጠበቀው የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ስምንት ነባር አባላቱን ከማእከላዊ ኮሚቴ ውጭ አድርጓል፡፡ ያልተረጋገጡ ዘገባዎች እንዳብራሩት ከስምንቱ ተሰናባቾች መካከል የፓርቲው አንጋፋ ታጋይና የመለስ ቀኝ እጅ ናቸው የሚባሉት አቶ ስብሓት ነጋ፣ የመቀሌ ከንቲባ ፍሰሀ ዘሪሁን፣ የትግራይ ልማት ማኅበር ዳይሬክተር አምባሳደር ተወልደ ገብሩ፣ አቶ ሙሉጌታ አለምሰገድ ይገኙበታል፡፡

ቀሪዎቹ አራት ተቀናሽ አባላት ዶክተር አድሀነ ሀይለ፣ ዶክተር ገብረአብ ባርናባስ፣ ዶክተር ሀይለሚካኤል አበራና ዶክተር ወልደሩፋኤል አለማየሁ ናቸው፡፡

ስብሐት ነጋ ከኮሚቴው ለመውጣታቸው በጉባኤው የተሰጠው ምክንያት “እርጅና” ነው። የመቀለ ከንቲባም በተመሳሳይ “በጤና ችግር” ምክንያት ከኮሚቴው መሰናበታቸው ተገልጿል። ቀሪዎቹ ስድስት አባላት በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው ተነግሯል። ስምንቱን ተሰናባቾች የተኳቸው አዲስ ተመራጮች የቆዩ የፓርቲው አባላት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ተሰምቷል።

ዛሬ ማምሻውን ይጠናቀቃል ተብሎ የሚገጠበቀው የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ ስምንት ነባር አባላቱን ከማእከላዊ ኮሚቴ ውጭ አድርጓል። ያልተረጋገጡ ዘገባዎች እንዳብራሩት ከስምንቱ ተሰናባቾች መካከል የፓርቲው አንጋፋ ታጋይ እና የአቶ መለስ ቀኝ እጅ ናቸው የሚባሉት አቶ ስብሓት ነጋ፣ የመቀሌ ከንቲባ ፍሰሃ ዘሪሁን፣ የትግራይ ልማት ማኅበር ዳይሬክተር አምባሳደር ተወልደ ገብሩ እና አቶ ሙሉጌታ አለምሰገድ ይገኙበታል። ቀሪዎቹ አራት ተቀናሽ አባላት ዶክተር አድሃነ ኀይለ፣ ዶክተር ገብረዐብ ባርናባስ፣ ዶክተር ኀይለሚካኤል አበራ እና ዶክተር ወልደ ሩፋኤል ዓለማየሁ ናቸው።

ስብኀት ነጋ ከኮሚቴው ለመውጣታቸው በጉባዔው የተሰጠው ምክንያት “እርጅና” ነው የሚል ነበር። የመቀሌ ከንቲባም በተመሳሳይ “በጤና ችግር” ምክንያት ከኮሚቴው መሰናበታቸው ተገልጿል። ቀሪዎቹ ስድስት አባላት በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውም ተነግሯል። ስምንቱን ተሰናባቾች የተኳቸው አዲስ ተመራጮች የቆዩ የፓርቲው አባላት ሳይኾኑ እንዳልቀሩ ተሰምቷል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ሥራ አስኪያጅ ዘርዐይ አስገዶም “ሐላፊነታቸውን በሚገባ አልተወጡም፤ የአቅም ችግር አለባቸው፤ ለፓሪቲያቸው ትኩረት አይሰጡም” ተብለው መገምገማቸውን እነዚሁ ምንጮች ጠቁመዋል።

ዘግይተው የወጡ ወሬዎች እንደሚያትቱት ከኾነ ጉባዔው አቶ መለስ ዜናዊን ሊቀመንበር እንዲሁም አቶ ዐባይ ወልዱን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧቸዋል። ጉባኤው አሁንም በመቀሌ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

ጉባኤውን በባህር ዳር ከተማ ያካሄደው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) የፓርቲው ሊቀ መንበር የነበሩትን አቶ አዲሱ ለገሰን አውርዶ በደመቀ መኮንን ተክቷቸዋል። በተመሳሳይም የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሊቀ መንበር አባዱላ ገመዳ ቦታውን ለአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ለቀዋል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ድምጻዊት ፀደንያ ገብረ ማርቆስ አዲስ ነጠላ ዜማዋን ዛሬ ትለቃለች

“ቢሰጠኝ” በተሰኘው የመጀመሪያ አልበሟ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘችውና “እወድኻለሁ” በሚለው የሙዚቃ ሥራዋ አህጉራዊውን የኮራ የሙዚቃ ሽልማት ያገኘችው ድምፃዊት ፀደንያ ገብረ ማርቆስ “ሕመሜን በእቅፉ” ነጠላ ዜማዋን ዛሬ ትለቃለች። ይህንኑ ነጠላ ዜማ ያቀናበረው ዓቤል ጳውሎስ ሲኾን ግጥሙን አብዲ ራህዋ፣ ዜማውን ደግሞ ድምፃዊቷ ፀደንያ ሠርታዋለች። ተራማጅ ወሮታው ማሲንቆ እንዲሁም ሙሳ ጊታሩን ተጫውተዋል። ድምፃዊቷ ሁለተኛ አልበሟን አስመልክቶ ላቀረብንላት ጥያቄ “መቼ [...]

“ቢሰጠኝ” በተሰኘው የመጀመሪያ አልበሟ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘችውና “እወድኻለሁ” በሚለው የሙዚቃ ሥራዋ አህጉራዊውን የኮራ የሙዚቃ ሽልማት ያገኘችው ድምፃዊት ፀደንያ ገብረ ማርቆስ “ሕመሜን በእቅፉ” ነጠላ ዜማዋን ዛሬ ትለቃለች። ይህንኑ ነጠላ ዜማ ያቀናበረው ዓቤል ጳውሎስ ሲኾን ግጥሙን አብዲ ራህዋ፣ ዜማውን ደግሞ ድምፃዊቷ ፀደንያ ሠርታዋለች። ተራማጅ ወሮታው ማሲንቆ እንዲሁም ሙሳ ጊታሩን ተጫውተዋል።

ድምፃዊቷ ሁለተኛ አልበሟን አስመልክቶ ላቀረብንላት ጥያቄ “መቼ ለገበያ እንደሚቀርብ በእርግጠኝነት መናገር ባልችልም ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል” ብላለች፡፡ ድምፃዊቷ አያይዛም በመጪው ዓመት በሕዳር ወር በካናሪ ደሴቶች ላይ ከ7 እስከ 10 በሚፈጀው  ዎማድ በተሰኘው የዓለም የሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ ለመሳተፍ እንደተዘጋጀች ገልጻለች።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ “አርቲፊሻል” የተሰኘውን አዲስ ነጠላ ዜማዋን ለቀቀች

ከድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ጋራ በመኾን በመስከረም እና ጥቅምት ወራት በአምስት የኢትዮጵያ ከተሞች የሙዚቃ ኮንሰርት ታቀርባለች

“ዘሪቱ” በተሰኘው የመጀመሪያ አልበሟ አገር አቀፍ ተቀባይነትን ያገኘችው ተወዳጅዋ ድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ዋና ትኩረቱን በአካባቢ ጥበቃ እና ክብካቤ ላይ ያደረገ እና “አርቲፊሻል” የተሰኘ አዲስ ነጠላ ዜማ ቅዳሜ ነሐሴ 29 ቀን 2002 ዓ.ም ለቀቀች።

የሮክ ስልት ቅኝትን ለተከተለው ለዚሁ ዘፈን ግጥም እና ዜማ የሠራችው ራሷ ዘሪቱ ናት፤ አጠቃላይ ፕሮዳክሽኑን ደግሞ ሚካኤል ኀይሉ ሰላም በተባለው ስቱዲዮው ውስጥ ሠርቶታል። ቀረጻ እና ሚክሲንጉን አበጋዙ ሺዮታ በላንጋኖ ስቱዲዮ የሠራው ሲኾን ናትናኤል ተሰማ ድራሙን እንዲሁም ሚካኤል ኀይሉ አኩስቲክ ጊታር፣ ቤዝ ጊታር፣ ሊድ ጊታር እና ኪቦርድ ተጫውተዋል፡፡ ድምፃዊቷ ይህን ነጠላ ዜማ የሠራችው በቅርቡ ከድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ ጋራ “ኢትዮጵያ አረንጓዴ” በሚል ርእስ በአካባቢ ጥበቃ እና ክብካቤ በሚያተኩረው እና በስድስት ዋና ዋና የኢትዮጵያ ከተሞች ላይ ከሚያቀርቡት ተጓዥ የሙዚቃ ኮንሰርት ጋራ በተያያዘ እንደኾነ ገልጻለች። ኮንሰርቱ በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በመቀሌ፣ በአዳማ፣ በአዋሳ እና በድሬዳዋ እንደሚቀርብ የፕሮግራሙ አስተባባሪ የኾኑት የኬር አድቨርታይዚንግ እና ፕሮሞሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ ካሳ ገልጸዋል።

ይህ ተጓዥ የሙዚቃ ኮንሰርት መነሻውን እና መድረሻቸውን በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ያደርጋል።  ተጓዥ የሙዚቃ ኮንሰርቱ ከጥቅምት 1 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚቀርብም ታውቋል። ከዚህ ጋራ በተያያዘ የፕሮጀክቱ ሥራ አስፈጻሚዎች ስለተጓዥ የመዚቃ ኮንሰርቱ ጥልቅ እና ዝርዝር መረጃዎችን የሚሰጥ  አዲስ   ድረ ገጽ ከፍተዋል። ከአዘጋጆቹ ያገኘነው የውስጥ መረጃ እንደሚጠቁመው ድምፃውያኑ ዘሪቱ ከበደ እና ሚካኤል በላይነህ በጋራ የዘፈኑትን እና በዚሁ በአካባቢ ክብካቤ ዙሪያ የሚያጠነጥን ነጠላ ዜማ በቅርቡ ይለቃሉ።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

የኪነ-ሕንፃ ዐውደ-ርዕይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የአርት ጋለሪ ተከፈተ

ከነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜ 5 የሚቆይ የኪነ-ሕንጻ ዐውደ-ርዕይ “ኪነ-ሕንፃ ሥነ-ምሕዳርን ምሉዕ ያደርጋል” (Architecture completes the eco-system) በሚል ዐቢይ መርህ ነሐሴ 29 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ላይ በብሔራዊ ቴአትር የአርት ጋለሪ ለሕዝብ ክፍት ኾነ። ዐውደ-ርዕዩን ያዘጋጀው የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አርኪቴክቸር እና አርባን ፕላኒንግ   የትምህርት ክፍል ሲኾን ከአንደኛ እስከ አራተኛ ዓመት ያሉት የዲፓርትመንቱ ተማሪዎች በርካታ አዳዲስ የሕንጻ፣ [...]

ከነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜ 5 የሚቆይ የኪነ-ሕንጻ ዐውደ-ርዕይ “ኪነ-ሕንፃ ሥነ-ምሕዳርን ምሉዕ ያደርጋል” (Architecture completes the eco-system) በሚል ዐቢይ መርህ ነሐሴ 29 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ላይ በብሔራዊ ቴአትር የአርት ጋለሪ ለሕዝብ ክፍት ኾነ።

ዐውደ-ርዕዩን ያዘጋጀው የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ አርኪቴክቸር እና አርባን ፕላኒንግ   የትምህርት ክፍል ሲኾን ከአንደኛ እስከ አራተኛ ዓመት ያሉት የዲፓርትመንቱ ተማሪዎች በርካታ አዳዲስ የሕንጻ፣ የመናፈሻ፣ የመኖርያ ቤት፣ የወጣት መዝናኛ ማዕከላት፣ የሆቴል፣ የሙዚየምና ሌሎችም ሞዴል ዲዛይኖችን እንዲሁም የግራፊክስ፣ የሥዕልና የቅርጻ ቅርጽ ሥራዎችን አቅርበዋል።

የዩኒቲ ዩኒቨርስቲ “ስኩል ኦፍ አርክቴክቸር እና  አርባን ፕላኒንግ” የኾኑት አቶ ሚካኤል ብርሃነ ሥላሴ “ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ካሉት ስድስት ፋኩልቲዎች ውስጥ የኪነ-ሕንጻው ዲፓርትመንት አንዱ እና ጠንካራው ነው። ይህን የኪነ-ሕንጻ ኤግዚቢሽን በዚህ አዳራሽ ስናቀርብ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከሁለት ዓመታት በፊት የቀረቡት ሞዴል ዲዛይኖች፣ የግራፊክስ፣ የሥዕል እና የቅርጻ ቅርጽ ሥራዎች እንደ አሁኑ በቁጥር ባይበዙም የኪነ-ሕንጻ ኤግዚቢሽን አቅርበናል፡፡ ወደፊት ከዚህ በተሻለ መልኩ አገር አቀፍ የኪነ-ሕንጻ ኤግዚብሽን በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የማዘጋጀት ዕቅድ አለን” ብለዋል።

ኤግዚብሽኑን ሲጎበኝ የነበረው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነ ጥበብ እና ዲዛይን ተማሪ የኾነው እንድርያስ ታመነ በበኩሉ “በአሁኑ ወቅት በከተማችን በርካታ የአገራችን አርኪቴክቶች ዲዛይን ያደረጓቸው እና ከተማችንን ያደመቁ ሕንጻዎችን፣ የመኖሪያ ቤቶችንና የመዝናኛ ስፍራዎችን እየተመለከትን ነው። የከተማችን የመዝናኛ ማእከላት አሁን አሁን ለውስጥ ዲዛይን (interior design) ጭምር ከፍተኛ ትኩረት እየሰጡ ነው። ከዚህ በተጨማሪ እንደ መጻሕፍት እና የሥዕል ኤግዚቢሽን ሁሉ የኪነ ሕንጻ ኤግዚቢሽንም መዘውተር አለበት። ካሁን በፊት ይህን ዐይነት ኤግዚቢሽን የምናየው የአዲስ አበባ የሕንጻ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች በቅጥር ግቢው ውስጥ በሚያዘጋጁበት ወቅት ብቻ ነበር” ብሏል። የኪነ-ሕንጻ ኤግዚቢሽኑ እስከ ጳጉሜ አምስት ለሕዝብ ክፍት ኾኖ እንደሚቆይም ታውቋል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

አባዱላ ከኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸው ተነሱ ፤ ጁነዲን እና ሽፈራው ከሥራ አስፈጻሚነት ተገልለዋል

ኦሕዴድ ከሊቀመንበርነት ሥልጣን ባባረራቸው በአቶ አባዱላ ገመዳ ላይ የጠበቀ ሂስ እንዳደረገ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለአዲስ ነገር ገልጠዋል። የአባዱላን ስኬቶች እየተከታተሉ የነበሩ ታዛቢዎችን ባስገረመ ኹኔታ ቁልፍ የኾኑ የድርጅቱ መሪዎች እና ተከታዮቻቸው አባዱላን ከሙስና ጋር በተያያዘ የሰላ ትችት ሲከሷቸው ተደምጠዋል። የፓርቲ ሊቀመንበርነቱንም ሥልጣን በማስለቀቅ በፓርቲው ውስጥ ለረጅም ጊዜ ለቆዩት ለምዕራብ ኦሮምያው አቶ አለማየሁ አቶምሳ እንዲያስረክቡ ተደርገዋል። የኢሕአዴግ ቢሮ ኃላፊ የኾኑት ሙክታር ከድርም የምክትል ሊቀመንበርነቱን ቦታ ይዘዋል። አዲሱ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ድርጅት ሥራ አስኪያጅም በመኾን አገልግለዋል።
የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ጁነዲን ሳዶ እና የቀድሞው ፓርላማ የመንግሥት ተጠሪ የነበሩት አቶ ሽፈራው ጃርሶ በዚህ ኮንፍረንስ ላይ ቦታቸውን ካጡት ዋነኛ ሰዎች መካከል ይገኙበታል። ሁለቱም በሥራ አስፈጻሚው ውስጥ የነበራቸውን ቦታ ያጡ ሲኾን ይህም የፓርቲው ወሳኝ አካል በኾነው የማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ምንም አይነት ፖለቲካዊ ተጽእኖ እንዳይኖራቸው ያደርጋቸዋል ተብሏል። አቶ ጁነዲን እና አቶ ሽፈራው ፓርቲውን ዘግይተው የተቀላቀሉ “አዲስ ገቦች” መካከል የሚቆጠሩ ናቸው።

ኦሕዴድ ከሊቀመንበርነት ሥልጣን ባባረራቸው በአቶ አባዱላ ገመዳ ላይ የጠበቀ ሂስ እንዳደረገ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለአዲስ ነገር ገልጠዋል። የአባዱላን ስኬቶች እየተከታተሉ የነበሩ ታዛቢዎችን ባስገረመ ኹኔታ ቁልፍ የኾኑ የድርጅቱ መሪዎች እና ተከታዮቻቸው አባዱላን ከሙስና ጋር በተያያዘ የሰላ ትችት ሲከሷቸው ተደምጠዋል። የፓርቲ ሊቀመንበርነቱንም ሥልጣን በማስለቀቅ በፓርቲው ውስጥ ለረጅም ጊዜ ለቆዩት ለምዕራብ ኦሮምያው አቶ አለማየሁ አቶምሳ እንዲያስረክቡ ተደርገዋል። የኢሕአዴግ ቢሮ ኃላፊ የኾኑት ሙክታር ከድርም የምክትል ሊቀመንበርነቱን ቦታ ይዘዋል። አዲሱ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ድርጅት ሥራ አስኪያጅም በመኾን አገልግለዋል።
እንደ ምንጮቻችን ዘገባ አቶ አባዱላ፤ ኩማ ደመቅሳን እና ግርማ ብሩን በመከተል ሦስተኛውን ትልቅ ድምጽ በማግኘት ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴው አባልነት ገብተዋል። ኦሕዴድ 65 ሰዎችን ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የመረጠ ሲኾን ቀድሞ የነበረውም የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ቁጥር በዚህ ዓመት ከ40 ወደ 65 እንዲያድግም ተደርጓል።
በአዲስ አበባ ያሉ የፖለቲካ ተንታኞች ሰሞኑን በመካሄድ ላይ በሚገኙት የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች ኮንፍረንስ የሚደረጉት የስልጣን ሽግሽጎች በመጪው የአቶ መለስ ዜናዊ ካቢኔ ውስጥ የሚኖረውን አሰላለፍ የሚያመለክቱ እንደኾኑ ይናገራሉ። አንዳንድ ታዛቢዎች እንደተናገሩትም አባዱላ በአዲሱ ካቢኔ ውስጥ የብአዴንኑን አዲሱ ለገሰን ተክተው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኾኑ ይችላሉ።
በኦሕዴዱ ኮንፍረንስ በማዕከላዊ ኮሚቴው ውስጥ የነበሩ እና የአባዱላ ደጋፊ መሆናቸው የሚነገርላቸው አራት አባላትም መቀመጫቸውን አጥተዋል። እንደ ምንጮቹ ጥቆማ ጀማል አባሶ፣ ጂብሪል መሐመድ፣ ድሪባ ቱራ እና ሲሳይ ነጋሽ ናቸው የማዕከላዊ ኮሚቴ መቀመጫቸውን ያጡት።
የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ጁነዲን ሳዶ እና የቀድሞው ፓርላማ የመንግሥት ተጠሪ የነበሩት አቶ ሽፈራው ጃርሶ በዚህ ኮንፍረንስ ላይ ቦታቸውን ካጡት ዋነኛ ሰዎች መካከል ይገኙበታል። ሁለቱም በሥራ አስፈጻሚው ውስጥ የነበራቸውን ቦታ ያጡ ሲኾን ይህም የፓርቲው ወሳኝ አካል በኾነው የማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ምንም አይነት ፖለቲካዊ ተጽእኖ እንዳይኖራቸው ያደርጋቸዋል ተብሏል። አቶ ጁነዲን እና አቶ ሽፈራው ፓርቲውን ዘግይተው የተቀላቀሉ “አዲስ ገቦች” መካከል የሚቆጠሩ ናቸው።
15 ከሚሆኑት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባላት መካከል ፓርቲውን ወክለው በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚው ውስጥ የሚሳተፉት አባላት ዓለማየሁ አቶምሳ፣ ሙክታር ከድር፣ ግርማ ብሩ፣ ሶፊያን አህመድ፣ ኩማ ደመቅሳ፣ አባዱላ ገመዳ፣ ዘላለም ጀማነህ፣ አበዱላዚዝ መሐመድ፣ እና ድሪባ ኩማ መሆናቸውን “ዋልታ” ዘግቧል።
በተመሳሳይ ዜና ሌሎቹም የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች በመቀሌ፣ ባሕር ዳር እና ሀዋሳ ከተሞች ተመሳሳይ ስብሰባ እያደረጉ ይገኛሉ። የኢሕአዴግ ኮንፍረንስ መስከረም 7 ቀን 2003 በአዳማ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ብሔራዊ ቴአትር በአዲሱ ዓመት በዐል “በጥናት ላይ ተመሥርተው የተሠሩ” የብሔረሰብ ሙዚቃዎችን ሊያቀርብ ነው

ጥንት አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር እንግዶቹን በባህላዊ እና በዘመናዊ ሙዚቃ ማዝናናት የብሔራዊ ቴአትር ዋነኛ መለያው ነበር። ዓመት በዐል በመጣ ቁጥር የቴአትር ቤቱ ሠራተኞች ለሌሎች ደስታ የራሳቸውን ደስታ የሚሰውበት ነበር። ይህ እውነት እና ኹነት ግን ከብሔራዊ ቴአትር ከጠፋ እና ከተሰናበተ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል። ከሁለት ዓመት በፊት የኢት ጵያ ሚሊኒየም ሲከበር ወደ ቀደመ ትዝታው ለመግባት ተፍገምግሞ እንደገና [...]

ጥንት አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር እንግዶቹን በባህላዊ እና በዘመናዊ ሙዚቃ ማዝናናት የብሔራዊ ቴአትር ዋነኛ መለያው ነበር። ዓመት በዐል በመጣ ቁጥር የቴአትር ቤቱ ሠራተኞች ለሌሎች ደስታ የራሳቸውን ደስታ የሚሰውበት ነበር። ይህ እውነት እና ኹነት ግን ከብሔራዊ ቴአትር ከጠፋ እና ከተሰናበተ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል። ከሁለት ዓመት በፊት የኢት ጵያ ሚሊኒየም ሲከበር ወደ ቀደመ ትዝታው ለመግባት ተፍገምግሞ እንደገና ወደ ነበረበት ተልሷል። ያ ዐይነቱ አካሄድ ግን የሚደገም የማይመስልበትን ኹኔታ በርትተው ለማሳየት የተነሱ የሚመስሉት ቴአትር ቤቱ ዳይሬክተር አቶ አዳፍሬ ብዙነህ በዚህ ዓመት “ድግሳችንን አጧጡፈናል” ይላሉ።

እርሳቸው ድግስ ማጧጧፍ የሚሉት በጥናት ላይ ተመስርተው ተሠርተዋል ብለው የሚያወሱዋቸውን የብሔረሰብ ሙዚቃ ለተመልካች ለማቅረብ ደፋ ቀና እያሉ መኾናቸውን በመግለጽ ነው። “የቴአትር ቤቱ የዘመናዊ እና የባህላዊ የውዝዋዜ አባላት እና ቡድኖች በአዳዲስ እና ተወዳጅ በኾኑ የሙዚቃ ሥራዎቻቸው የሙዚቃ አፍቃሪውን ለማስደሰት ተዘጋጅተዋል” ሲሉም ይገልጻሉ። እንደርሳቸው አገላለጽ ከኾነ በዚያው ቀን ከሙዚቃውም ባሻገር ድራማ ጭምር በማቅረብ ቀኑን ለየት ያለ ለማድረግ ታስቧል።

በዕለቱ በቦታው ላይ ተገኝተው መድረኩን ያደምቃሉ ተብለው ከሚጠበቁት መካከል ዝነኞቹ ድምጻውያን ማዲንጎ አፈወርቅ፣ አምሳል ምትኬ፣ ግዛቸው ተሾመ እና የቢፍቱ ኦሮምያ ባንዱ ድምፃዊ ብርሃኑ ከውጪ በተጋባዥ እንግድነት የሚመጡ ጭምር ናቸው። እንደ አቶ አዳፍሬ አባባል የዚህ አዲስ ዓመት የበዐል ድግስ የሚደምቀው እስከ ዛሬ ድረስ በሙዚቃ ዘርፍ ትኩረት ሳይሰጣቸው የቀሩ የብሔረሰብ ሙዚቃዎች ማቅረብ በመቻላቸው እንደሚኾን ያምናሉ። “የብሔራዊ ቴአትር የባህል ቡድን እነዚህን አዳዲስ ባህላዊ ሙዚቃዎች የሰራው በብሔረሰቦቹ ላይ ጥልቅ የባህል ጥናትና ምርምር ካደረገ በኋላ ነው። ተወዛዋዦቻችንም ረዘም ላለ ጊዜ ብርቱና ፈታኝ የኾነ ልምምድ አድርገውበታል” ብለዋል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

የኀይለ ጊዮርጊስ ማሞ “እውነት እና እምነት ጥበብ 8” በገበያ ላይ ዋለ

“ጥበብ” በተሰኙ የፍልስፍና ቅጾች የሚታወቀው ጋዜጠኛ ኀይለ ጊዮርጊስ ማሞ “እውነት እና እምነት- ጥበብ 8” የተሰኘ እና በ146 ገጾች የተጠናቀረ አዲስ መጽሐፍ ያሳተመ ሲኾን ሐሙስ ነሐሴ 27 ቀን 2002 ዓ.ም በገበያ ላይ ውሏል። ኀይለ ጊዮርጊስ በእነዚሁ በተከታታይ በሚቀርቡ ሥራዎቹ በተወሰነ አንባቢ ዘንድ ዕውናን እያተረፈ ቢመጣም “ሥራዎቹ ስለ ፍልስፍና ጥልቅ የኾነ ትንታኔ እና የእውቅት መሠረት የሚያሳዩ አይደሉም” [...]

“ጥበብ” በተሰኙ የፍልስፍና ቅጾች የሚታወቀው ጋዜጠኛ ኀይለ ጊዮርጊስ ማሞ “እውነት እና እምነት- ጥበብ 8” የተሰኘ እና በ146 ገጾች የተጠናቀረ አዲስ መጽሐፍ ያሳተመ ሲኾን ሐሙስ ነሐሴ 27 ቀን 2002 ዓ.ም በገበያ ላይ ውሏል።

ኀይለ ጊዮርጊስ በእነዚሁ በተከታታይ በሚቀርቡ ሥራዎቹ በተወሰነ አንባቢ ዘንድ ዕውናን እያተረፈ ቢመጣም “ሥራዎቹ ስለ ፍልስፍና ጥልቅ የኾነ ትንታኔ እና የእውቅት መሠረት የሚያሳዩ አይደሉም” የሚሉ ተቺዎችም አሉት። ከእነዚህ መጻሕፍቶቹ በተጨማሪ “ሴትና ፈጣሪ” የሚል የግጥም መድብልም ለኅትመት ማብቃቱ ይታወሳል። በአሁኑ ሰዓት “ዜን” በተሰኘችው እና በኪነ ጥበብ ጉዳይ ላይ በምታተኩረው መጽሔት ላይም በዋና አዘጋጅነት ይሠራል። ኀይለ ጊዮርጊስ ከዚህ በፊት በኔሽን ጋዜጣ ላይ እና በቁም ነገር መጽሔት ላይ ለረዥም ጊዜ በሚያቀርባቸው ጽሑፎቹም ይታወቃል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

የራስ ቴአትር እስክታ አዳራሽ እድሳቱን አጠናቆ የአማርኛ ፊልሞችን ማሳየት ጀመረ

የራስ ቴአትር እስክታ አዳራሽ በመባል የሚታወቀው ከሲኒማ አምፒር አጠገብ የሚገኘው አዳራሽ እድሳቱን አጠናቆ የአማርኛ ፊልሞችን ማሳየት ጀመረ።  የዚህ አዳራሽ አገልግሎት የቴአትር ቤቱ ተወዛዋዦች የባህላዊ እና ዘመናዊ የዳንስ ዐይነቶችን እንዲለማመዱበት ማድረግ ነበር። ይኸው አዳራሽ “ስቴርዮ ክለብ” የሚል መጠሪያም አለው። አዳራሹ እድሳቱን ካጠናቀቀበት ቀን አንሰቶ ከሰኞ በቀር በሌሎቹ ቀናት በሙሉ ፊልም ማሳየቱን እንደሚቀጥል የራስ ቴአትር ሥራ አስኪያጅ [...]

የራስ ቴአትር እስክታ አዳራሽ በመባል የሚታወቀው ከሲኒማ አምፒር አጠገብ የሚገኘው አዳራሽ እድሳቱን አጠናቆ የአማርኛ ፊልሞችን ማሳየት ጀመረ።  የዚህ አዳራሽ አገልግሎት የቴአትር ቤቱ ተወዛዋዦች የባህላዊ እና ዘመናዊ የዳንስ ዐይነቶችን እንዲለማመዱበት ማድረግ ነበር። ይኸው አዳራሽ “ስቴርዮ ክለብ” የሚል መጠሪያም አለው። አዳራሹ እድሳቱን ካጠናቀቀበት ቀን አንሰቶ ከሰኞ በቀር በሌሎቹ ቀናት በሙሉ ፊልም ማሳየቱን እንደሚቀጥል የራስ ቴአትር ሥራ አስኪያጅ ኩራባቸው ደነቀ ለአዲስ ነገር ገልጿል።

350 ተመልካቾችን እንዲያስተናግድ ታስቦ የተሠራው ይኸው አዳራሽ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከመስከረም ወር ጀምሮ የዘመናዊ እና የባሕላዊ ውዝዋዜዎችን እና ቴአትሮችን ከፊልሙ ጎን ለጎን እንደሚያቀርብ ሥራ አስኪያጁ ጨምሮ ገልጿል። በየቀኑ ከ10፡00 ሰዓት ጀምሮ ሁለት ፊልሞች የሚያሳየው ይኽው አዳራሽ እሁድ ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ሦስት ፊልሞችን የማሳየት ዕቅድ ማውጣቱንም የስቴርዮ ክለቡ ሐላፊ ወይዘሮ ዘነቡ ገሰሰ ይገልጻሉ። ይህ አዳራሽ ወደ ሲኒማ ቤትነት መቀየሩ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለውን የሲኒማ ቤት ቁጥር በአንድ ጨምሮ ለፊልም ተመልካቹ አማራጭ ቢያቀርብም ራስ ቴአትር ያለበትን የማሠልጠኛ ቦታ ችግር ሊያጠበው ይችልላ፤ ይህ ደግሞ በቴአትር ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ ቀላል አይደልም ሲሉ አንድ በቴአትር ቤቱ የሚሠሩ ሰው ለአዲስ ነገር ገልጸዋል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

“የኔ ብቻ” ሰኞ ይመረቃል

በክሬቲቭ ፊልም ፕሮዳክሽን እና በሃሌታ አድቨርታይዚንግ ኤንድ ሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን የተዘጋጀው “የኔ ብቻ” የተሰኘው አዲስ ፊልም ዛሬ ሰኞ ጷግሜ 1 ቀን 2002 ዓ.ም ከምሽቱ በዐሥራ አንድ ሰዓት ይመረቃል። ፊልሙ ልብን አንጠልጣይ የፍቅር ፊልም የሚባለውን ዘውግ የያዘ ሲኾን 1፡40 ደቂቃ እንደሚፈጅም ታውቋል። ይህንን ፊልም ለመሥራት በአጠቃላይ ከቅድመ ዝግጅት እስከ ድኅረ ዝግጅት የአንድ ዓመት ጊዜ እንደወሰደ እና ስክሪፕቱ [...]

በክሬቲቭ ፊልም ፕሮዳክሽን እና በሃሌታ አድቨርታይዚንግ ኤንድ ሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን የተዘጋጀው “የኔ ብቻ” የተሰኘው አዲስ ፊልም ዛሬ ሰኞ ጷግሜ 1 ቀን 2002 ዓ.ም ከምሽቱ በዐሥራ አንድ ሰዓት ይመረቃል።

ፊልሙ ልብን አንጠልጣይ የፍቅር ፊልም የሚባለውን ዘውግ የያዘ ሲኾን 1፡40 ደቂቃ እንደሚፈጅም ታውቋል። ይህንን ፊልም ለመሥራት በአጠቃላይ ከቅድመ ዝግጅት እስከ ድኅረ ዝግጅት የአንድ ዓመት ጊዜ እንደወሰደ እና ስክሪፕቱ ከሦስት ዓመት በፊት የተጻፈ መኾኑን ፕሮዲዩሰሩ ቴዎድሮስ ሞሲሳ ገልጸዋል። የዚሁ ፊልም ዳይሬክተር ዓለም ፀሐይ በቀለ ስትኾን  በፊልሙ ላይ የተሳተፉት ቢኒያም ወሩቁ፣ ብርቱካን በፍቃዱ፣ ጥላሁን ጉግሳ፣ ጌታቸው አበራ፣ ሉሌ አሻጋሪ፣ ጌድዮን ንጉሤ እና ሌሎችም ናቸው። ይህን ፊልም ፕሮዲዩስ ያደረጉት ድምጻዊው ቴዎድሮስ ሞሲሳ እና የዛየንስ ባንድ ሥራ አስኪያጅ ሚካዔል ዛየንስ መኾናቸውም ታውቋል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

በጁምዓ ሰጋጆች ላይ ድንጋይ የወረወሩት የአንድ አመት እስር ተፈረደባቸው፡፡

ገድፈው ምንውየለት እና ዋለልኝ አንዱምላክ የተባሉት እነዚሁ ተከሳሾች ሌሎች 30 ከሚሆኑ የግንባታ ሰራተኞች ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ከተደረገባቸው በኋላ ጳውሎስ የመጀመርያ ፍርድ ቤት ቀርበው ቅጣቱ የተወሰነባቸው ሲሆን ተካልኝ ከበደ በተባለ ሶስተኛው ተከሳሽ ላይ የ500 ብር የገንዘብ ቅጣት ተወስኖበታል፡፡ የተቀሩት 28 ተከሳሾችን ግን ፍርድ ቤቱ በነፃ አሰናብቷቸዋል፡

የዛሬ ሳምንት ጁምዓ ስግደት ላይ በነበሩ አማኞች ላይ ከድር ተራ ህንፃ ላይ ሆነው ድንጋይ ወርወራዋል የተባሉ ሁለት የኮንስትራክሽን ሰራተኞች እያንዳንዳቸው በአንድ አመት ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን በዛሬው የስግደት ስነ-ስርዓት ላይ የነበሩ አስተባባሪዎች ገለፁ፡፡

ገድፈው ምንውየለት እና ዋለልኝ አንዱምላክ የተባሉት እነዚሁ ተከሳሾች ሌሎች 30 ከሚሆኑ የግንባታ ሰራተኞች ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ከተደረገባቸው በኋላ ጳውሎስ የመጀመርያ ፍርድ ቤት ቀርበው ቅጣቱ የተወሰነባቸው ሲሆን ተካልኝ ከበደ በተባለ ሶስተኛው ተከሳሽ ላይ የ500 ብር የገንዘብ ቅጣት ተወስኖበታል፡፡ የተቀሩት 28 ተከሳሾችን ግን ፍርድ ቤቱ በነፃ አሰናብቷቸዋል፡፡

የዛሬ ሳምንት አርብ በጁምዓ ሶላት ወቅት በግንባታ ላይ ከሚገኘው የድር ተራ ሶስተኛ ፎቅ ላይ ሆነው ድንጋይ ወርውረዋል በሚል በመቶ የሚቆጠሩ ሰጋጆች ጥፋተኞቹ ተላልፈው እንዲሰጧቸው በመጠየቅ ከፖሊስ ጋር እልህ አስጨራሽ ፍጥጫ ውስጥ ገብተው የነበረ ሲሆን በዚህም ሳቢያ ወደጣና ገበያ የሚወስደው አስፋልት ለተወሰኑ ሰዓታት ለትራፊክ ዝግ ሆኖ ቆይቶ ነበር፡፡ የሶላቱ አስተባባሪዎች ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን ምእመናኑ እንዲበተኑ በማግባባት ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ሲሆን በእንደነዚህ ግዝያት ሊፈጠር ይችል የነበረውን ረብሻ እንዲረጋጋ አድርገዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በዛሬው እለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው አማኝ የጁምአ ስግደቱን ፈፅሞ በሚመለስበት ወቅት መርካቶ አምበሳ የከተማ አውቶብስ መናኸሪያ ውስጥ ‹‹መዳን በእየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፣ንሰሃ ግቡ›› እያለ ይሰብክ የነበረ ጎልማሳ ስብከቱን እንዲያቆም ቢጠየቅም ፍቃደኛ ባለመሆኑ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡ ፖሊስ በአካባቢው ከመድረሱ በፊትም መጠነኛ ግርግር የተፈጠረ ሲሆን ነገሩ ሳይበረታ  በአቅራቢያ የነበሩ ፖሊሶች ሰባኪውን ከስፍራው ገለል እንዲል አድርገውታል፡፡ በዛሬው የረመዳን የመጨረሻ የጁምዓ ስግደት ቁጥሩ የላቀ ምእመን በታላቁ አንዋር መስጊድና አካባቢው ተገኝቶ ነበር፡፡ የደህንነት ቁጥጥሩም ከቀድሞ ጊዚያት ጠንከር እንዲል ተደርጓል፡፡

No Responses to “በጁምዓ ሰጋጆች ላይ ድንጋይ የወረወሩት የአንድ አመት እስር ተፈረደባቸው፡፡”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

በመርካቶ ሻጭና ሸማች ተፋጠዋል

ከትላንት በስተያ ድንገተኛ የኾነው የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ሲታወጅ ያሻቀበው ታይቶ በማይታወቅ ኹኔታ ነበር። ወደ 2፡50 ሣንቲም የሚጠጋ ብር በአንድ የዶላር ዋጋ ላይ ጨምሮ መጥቷል። የዚሁ የዶላር ምንዛሪ የፈጠረው ግሽበት ትላንት ከሰዓት በኋላ እና ዛሬ በአንዳንድ ዕቃዎች ላይ የተጋነነ ጭማሪ ማሳየት ጀምሯል። እንዲያውም አንዳንድ የጅምላ ነጋዴዎች እና አከፋፋዮች ዕቃው በመጋዘን እና በየሱቆቻቸው ቢኖርም ለሽያች ለማቅረብ ፈቃደኛ [...]

ከትላንት በስተያ ድንገተኛ የኾነው የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ሲታወጅ ያሻቀበው ታይቶ በማይታወቅ ኹኔታ ነበር። ወደ 2፡50 ሣንቲም የሚጠጋ ብር በአንድ የዶላር ዋጋ ላይ ጨምሮ መጥቷል። የዚሁ የዶላር ምንዛሪ የፈጠረው ግሽበት ትላንት ከሰዓት በኋላ እና ዛሬ በአንዳንድ ዕቃዎች ላይ የተጋነነ ጭማሪ ማሳየት ጀምሯል። እንዲያውም አንዳንድ የጅምላ ነጋዴዎች እና አከፋፋዮች ዕቃው በመጋዘን እና በየሱቆቻቸው ቢኖርም ለሽያች ለማቅረብ ፈቃደኛ ሳይኾኑ የሚቀሩበት አጋጣሚም ሲስተዋል ነበር። የአዲስ ነገር ዘጋቢዎች በሲዳሞ ተራ፣ በምስማር ተራ፣ በዱባይ ተራ እና በኤግዚብሽን ማእከል ጭምር የግብይት ኹኔታው ምን እንደሚመስል ተዘዋውረው ሲመለከቱ ያገኙት የመገበያያ መደብሮቹ በሸማች እና በሻጭ መካከል አለመግባባት እና መፈራራት እንደሚስተዋልባቸው ነበር።

ከሁለት ቀናት በፊት 35 ጌጅ ቆርቆሮ በብር 83 ብር ይሸጥ ነበር። ከሰዓት በኋላ ሪፖርተሮቹ በተዘዋወረው የጎበኟቸው አንዳንድ የሕንፃ መሣሪያ መደብሮች በአንድ ቆርቆሮ ላይ የ9.65 ብር ጭማሪ በማድረግ 92 ብር አካባቢ ሲሸጡ ተመልክተዋል። ሌሎች ሸማቾች በአንጻሩ በቀጣዮቹ ቀናት ከዚህም የበለጠ ጭማሪ ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት በተባሉት ዋጋ ለመግዛት ፍላጎት ሲያሳዩም ተስተውለዋል። በሌላ መልኩ ደግሞ አንዳንድ አከፋፋዮች በመጋዘን ያከማቹት ዕቃ ይበልጥ ዋጋ እንደሚያወጣላቸው በማሰብ ለሸማቾች ከመሸጥ ሲቆጠቡ ታይተዋል። በምስማር ተራ የሚገኙ አንድ ነጋዴ ለአዲስ ነገር ሪፖርተሮች እንደገለጹት “አሁን ለመሸጥም ኾነ ላለመሸጥም መወሰን አዳጋች ነው።” ሲሉ ያብራራሉ። ፋብሪካዎች እና ዋና ዋና አከፋፋዮች በምን ያህል ፐርሰንት ጭማሪ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ሳያውቁ ትክክለኛ እና ተመጣጣኝ የሚባል ጭማሪ ለማድረግ እንደሚያዳግታቸው የሚናገሩት እኚኹ ነጋዴ በመጪዎቹ ሦስት እና አራት ቀናት የተሻለ የገበያ መረጋጋት ይኖራል ብለው እንደሚጠብቁም ይናገራሉ።

የዚሁ የገበያ መናር ጉዳይ የተስተዋለው በዱባይ ተራ በሚገኙ የልብስ ሱቆችም ውስጥ ነበር። የጅንስ ዋጋ ባልተጠበቀ ኹኔታ የተጋነነ ጭማሪ ያሳየ ሲኾን ከዶላር ዋጋ መጨመር በፊት 270 ብር ይሸጡ የነበሩ ‹‹ስኪኒ›› ሱሪዎች በዛሬው ዕለት እስከ 400 ብር በሚደርስ ዋጋ ሲሸጡ ውለዋል። ያም ኾኖ ግን በሁሉም መደብሮች የሚታየው የጭማሪ ዐይነት ተቀራራቢነት አይታይበትም። ነጋዴዎች የመሰላቸውን ጭማሪ ካወጡ በኋላ ሸማቾች ለመግዛት ሲወስኑ ሐሳባቸውን የሚቀይሩበት አጋጣሚም ታይቷል። በተመሳሳይ ኹኔታ በሌሎች የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶች ላይም ጭማሪው የተስተዋለ ሲኾን ነጋዴዎቸ የመሰላቸውን ዋጋ እየጨመሩ ሲሸጡ ውለዋል።

በተያያዘ ዜና በኤግዚብሽን ማእከል መጪዎቹን የአዲስ ዓመት፣ የኢድ አልፈጥር እና የመስቀል በዐላትን ምክንያት በማድረግ ሰፊ የሸማቾች ግብይት ተጠብቆ የነበረ ቢኾንም ከዶላር ጭማሪው ጋራ የተያያዘ በሚመስል መልኩ ግብይቱ ቀዝቀዝ ብሎ ተስተውሏል። አቶ ሙሕዲን አሕመድ የተባሉ የኤግዚብሽኑ ተካፋይ ለአዲስ ነገር እንደተናገሩት ባለፉት ሁለት የአዲስ ዓመት ባዛሮች ላይ መካፈላቸውን አስታውሰው ዘንድሮ ምክንያቱ ባልታወቀ ኹኔታ መቀዛቀዝ እንደታየ ገልጸዋል። የዶላር ጭማሪውን ተከትሎም የዋጋ ማስተካከያ ለማድረግ እንደተገደዱ የተናገሩት አቶ ሙሕዲን ቀደም ሲል በ300-400 ብር ይሸጡ የነበሩ ‹‹ጃፓንና ኮሪያ›› ብርድልብሶች በአማካይ የመቶ ብር ጭማሪ እንደተደረገባቸው ተናግረዋል። ጭማሪው ግን በቀጣይ ቀናት ዋጋ ሊንር ይችላል ከሚል ስጋት የመነጨ እንጂ ዕቃዎቹ ቀደም ሲል የገቡ በመኾናቸው የዶላር ጭማሪው ተጽዕኖ እንዳልነካቸው አልሸሸጉም።

መንግሥት ያደረገውን የዶላር ዋጋ ማስተካከያ ተከትሎ የሸማች እና የነጋዴ አለመግባባት የተፈጠረ ሲኾን አንዳንድ ነጋዴዎች የሸጡትን ዕቃ ሳይቀር ብር ጨምረው ለማስመለስ ጥረት ያደረጉበት ኾኖም ታይቷል። መንግሥት “ላኪዎችን ለማበረታት” በሚል ከትላንት በስቲያ የአንድ ዶላር ዋጋ 16 ብር ከ 35 ሳንቲም እንዲኾን መወሰኑ የሚታወስ ነው።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ሞኖፖሊ-የምርት ገበያው የምርት ገበያው የመጨረሻ ግብ

የምርት ገበያው ሲመሠረት አምራቹንም ሸማቹንም የሚያስማማ ዋጋ መፍጠር እና በዚህም ለዓመታት ሥርዐት ዐልባ የነበረውን የግብርና ምርት ግብይት በዘመናዊ መልክ ማቀላጠፍ ነበር። ባለፉት ሁለት ዓመታት ግን የምርት ገበያው ይኼንን እውን ማድረግ አልተቻለውም። ከዚህ ይልቅ የምርት ገበያው የገበያ ተቆጣጣሪነት ሚና በበላይነት እየነገሠ እንዲሁም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እና ድጋፍ ያላቸው ጥቂት ተቋማት ኀያልነታቸውን እየጎላ መምጣት የምርት ገበያው መለያ ለመኾን በቅቷል

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ (Ethiopian Commodity Exchange) መሥራች እና ዳይሬክተር ዶ/ር እሌኒ ገብረ መድኅን ለአዲስ ነገር ጋዜጣ የሩቅ ሰው የሚባሉ አልነበሩም። በመጋቢት ወር 2000 ዓ.ም የምርት ገበያውን በይፋ ሥራ ካስጀመሩበት ቀን አንስቶ በበጎም ኾነ በክፉ በጋዜጣው በተደጋጋሚ የሚነሱ ሴት ኾነው ነበር። ጋዜጣዋም ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የዓመቱን 25 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን ስትመርጥ ዶ/ር እሌኒ በሁለቱም ዓመታት ተመራጭ ነበሩ።

የሁለቱ ዓመታት ምርጫዎች ውጤታቸው ግን ከፍ እና ዝቅ ነበረበት። በ2000 ዓ.ም ለዓመታት በጉጉት ይጠበቅ የነበረውን ዘመናዊ የምርት መገበያያ መድረክ እውን ማድረጋቸው እና ለተጨማሪ ተስፋ መጋበዛቸው በአዎንታዊ መልኩ ተጽዕኖ ከፈጠሩት መካከል እንዲቀመጡ አድርጓቸው ነበር። የቀጣዩ ዓመት ተጽዕኖ አምጪነታቸው ግን በአሉታዊ መልኩ የገነነ ነበር። በአንድ ዓመት ውስጥ የታየው የአመራር ድክመት፣ የቡና ነጋዴዎች እና የምርት ገበያው የመረረ እሰጥ አገባ እንዲሁም በዚህ ምክንያት አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት ባለመቻላቸው የተከሰተው ችግር እና ቀስ በቀስ የምርት ገበያው የመንግሥት ተጽዕኖ እየተጫነው መምጣት በኢኮኖሚክስ ሞያቸው የማይታሙትን ባለሞያ ባለ ሁለት መልክ አደረጋቸው፡ ጥቁር እና ነጭ።

ባለሞያዋ ዛሬም እንዲሁ “በጥቁር እና ነጭ’” ውጤታቸው የሚቀጥሉ ይመስላሉ። ለበርካታ አገራት ሲያደርጉት በኖሩት ሞያዊ ዕገዛ አሁንም በአዎንታዊ መልክ ስማቸው ይነሳል፤ ይጠቀሳል። ይህ ግን የምርት ገበያቸውን ወደተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር የረዳቸው አይመስልም። ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተደመጠው ጉዳይ ደግሞ ተስፋ ተጥሎበት የነበረውን የምርት ገበያ አማራጭ ነጻ ገበያ የመኾን ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የከተተ እና የዶ/ር እሌኒንም ትጋት መና ያደረገ ነው።

አቶ መለስ ከንግዱ ማኅበረሰብ እና ማኅበራት ጋራ ባደረጉት ውይይት በሚቀጥሉት ዓመታት የሰብል ምርቶች ሁሉ በምርት ገበያው እንዲያልፉ ይደረጋል ብለዋል። ይህ ንግግር ለኢትዮጵያ የግብርና ምርት ገበያ ተስፋን የቋጠረ አይደለም። የምርት ገበያው ሲመሠረት አምራቹንም ሸማቹንም የሚያስማማ ዋጋ መፍጠር እና በዚህም ለዓመታት ሥርዐት ዐልባ የነበረውን የግብርና ምርት ግብይት በዘመናዊ መልክ ማቀላጠፍ ነበር። ባለፉት ሁለት ዓመታት ግን የምርት ገበያው ይኼንን እውን ማድረግ አልተቻለውም። ከዚህ ይልቅ የምርት ገበያው የገበያ ተቆጣጣሪነት ሚና በበላይነት እየነገሠ እንዲሁም የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እና ድጋፍ ያላቸው ጥቂት ተቋማት ኀያልነታቸውን እየጎላ መምጣት የምርት ገበያው መለያ ለመኾን በቅቷል። የጠቅላይ ሚኒስትሩም ንግግር የመንግሥትን ቀጣይ የተቆጣጣሪነት ሚና ያጎላ እና በምርት ገበያው ነጻ መድረክ መኾን ላይም ጥላውን ያጠላ ነው፡፡

የምርት ገበያው ቀውስ በዋነኝነት የጀመረው በታኅሳስ ወር 2001 ዓ.ም ያለ ምንም ቅድመ ኹኔታ እና ዝግጅት የቡና ግብይትን ሲጀምር ነበር። በወቅቱ የቡና ደረጃዎች ሙሉ ለሙሉ ተለይተው በመገበያያ መድረኩ አለመቅረባቸው፣ የክፍያ ሥርዐቱ ያልተቀላጠፈ መኾን እና ቀድሞ የነበረውን የቡና ነጋዴዎች ፍላጎት እና ልምድ አለማገናዘብ ተደማምሮ የቡና ንግዱ ላይ ብሎም በወጪ ንግዱ ሥርዐት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዲያስከትል ኾኗል። በወቅቱም በምርት ገበያው መጋዘን ከሚከማቸው ቡና 23 በመቶ ያህሉ ብቻ ለገበያ ይቀርብ ነበር። መንግሥትም ችግሩን ለመፍታት የሞከረበት መንገድ የቡና ነጋዴዎችን ቡና መውረስ እና ነጋዴዎችንም ከጨዋታ ውጪ ማድረግ መኾኑ የምርት ገበያውን ገለልተኝነት ጥያቄ ምልክት ውስጥ የከተተው ያኔ ነበር።

ከዚህም ባሻገር ከህወሓት የንግድ ተቋማት አንዱ የኾነው ጉና ትሬዲንግ በቡና ንግድ ውስጥ እየገነነ መምጣት የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት በግልጽ የሚያሳይ ኾኗል። ቀድሞ ለዓመታት በቡና ንግድ ለቆዩት ነጋዴዎች ተጨማሪ ስጋት በመኾን የምርት ገበያው ነጻ መድረክ ከመኾን ይልቅ ለአድሎአዊነት እና ተገቢ ላልኾን የገበያ ሥርዐት የመጋለጥ ዕድሉን ሰፊ ያደርገዋል።

አሁንም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደመጠው ጉዳይ መንግሥት የምርት ገበያውን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ሥር ለማስገባት የሚያደርገውን “ትጋት” ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።  እርሳቸው የሚሉት እውን ከኾነም በሚቀጥሉት ዓመታት መንግሥት እና በመንግሥት ብቻ የሚደገፉ የንግድ ተቋማት የምርት ገበያው ዋነኛ ተዋናይ ይኾናሉ። መድረኩም እንደታለመለት ነጻ የወጋ መተመኛ ከመኾን ይልቅ የጥቂቶች የበላይንነት የሚታይበት እና በውድድር ገበያውን ሊጠቀሙ የሚችሉ ነጻ የምርት ገበያ የሚናፍቁ ነጋዴዎች የማያገኙት ሕልም ኾኖ ይርቅባቸዋል። የዶ/ር እሌኒ የነጻ ገበያ አቀንቃኝነትም “ልጡ የተራሰ ጉድጓዱ የተማሰ” መኾኑ ይረጋገጣል።

ለዚህ ጽሑፍ አስተያየት በመስጠት የመጀመሪያ ይሁኑ!

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ትምህርት ሚኒስቴር አማርኛ ቋንቋን ከ3-12ኛ ክፍል መማር ግዴታ ሊያደርግ ነው

ትምህርት ሚኒስቴር ከሦስተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ከ2003 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ አማርኛ ቋንቋን በመደበኛነት (ኮምፐልሰሪ) እንዲማሩ ሊያደርግ ነው።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ያሳወቀው በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን በላከው ደብዳቤ ነው። ቀድሞ በነበረው አሰራር የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማርኛ ባልሆኑ ክልሎች ትምህርቱ ይሰጥ የነበረው ከአምስተኛ እስከ 10ኛ ክፍል ብቻ ነበር።

(ሙሉ ገ)

ትምህርት ሚኒስቴር ከሦስተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች ከ2003 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ አማርኛ ቋንቋን በመደበኛነት (ኮምፐልሰሪ) እንዲማሩ ሊያደርግ ነው።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ያሳወቀው በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን በላከው ደብዳቤ ነው። ቀድሞ በነበረው አሰራር የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማርኛ ባልሆኑ ክልሎች ትምህርቱ ይሰጥ የነበረው ከአምስተኛ እስከ 10ኛ ክፍል ብቻ ነበር።

በከተሞች ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ የግል እና የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤቶች የቋንቋ ትምህርቱን ከስርዓተ ትምህርታቸው (ካሪኩለም) ውጪ እስከማድረግ ደርሰው ነበር። በርካታ የግል ትምህርት ቤቶች በሚኒስቴሩ የተዘጋጀውን የመማሪያ መጽሐፍ ካለመጠቀም አንስቶ “አማርኛ ቋንቋ መናገርና ድንጋይ መወርወር በትምህርት ቤት ውስጥ የተከለከለ ነው” የሚል ማስታወቂያእስከመለጠፍ መድረሳቸውን በትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ በስርዓተ ትምህርት ቀረጻ የተሰማሩ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

በአዲሱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መመሪያ መሰረት የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማርኛ ያልሆኑ ክልሎች እና በከተማ የሚገኙ የግል እና የኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤቶች አጠቃላይ የትምህርት ቋንቋውን እንደ ፍላጎታቸው በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ አሊያም በክልሉ የሥራ ቋንቋ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ይህ አሰራር ተግባራዊ መደረግ የሚችለው ግን ከሦስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ባለው የትምህርት እርከን ብቻ እንደሆነ መመሪያው ይደነግጋል።

ከመዋለ ህፃናት እስከ ሁለተኛ ክፍል ድረስ ላለው የትምህርት እርከን የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ አጠቃላይ የትምህርት ቋንቋ ሆኖ ያገለግላል። ከ9ኛ እስከ 12ኛ ላለው የትምህርት እርከን ቀድሞም የነበረው የእንግሊዝኛ ቋንቋ እንዲቀጥል መወሰኑን የሚኒስቴሩ ምንጭ ገልጸዋል።

ቀድሞ የነበረው አሰራር በተለይ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማርኛ ካልሆኑ ክልሎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚገቡ ተማሪዎች ላይ ችግር ሲፈጥር መቆየቱን ምንጩ ያስረዳሉ። “የጋራ መግባቢያ እና ህሴት ያላዳበሩ ተማሪዎችን ተቀብለው የሚያስተምሩት ዩኒቨርስቲዎች በትምህርት ሥራ ላይ መቸገራቸውን ገልጸውልናል” ሲሉም ችግሩ በተማሪዎቹ ላይ ብቻ የተገደበ እንዳልሆነ ይጠቁማሉ።

መንግስት ለአመታት ሲከተለው የቆየውን ስርዓተ ትምህርት ለማሻሻል ከመነሳቱ ጀርባ ፖለቲካዊ ምክንያቶችም እንዳሉ የሚኒስቴሩ ምንጮች ያብራራሉ። ኢህአዴግ ለዓመታት በተከተለው ስርዓተ ትምህርት ምክንያት ተማሪዎች “ ለአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ለአማርኛ እና ለሀገራዊ ማንነት ደንታ ቢስ ሆነው እንዲቀረጹ ተደርጓል” ይላሉ ተቺዎች። ተማሪዎቹ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው በሲቪል ሰርቪስ ሥራ እና በኃላፊነት ቦታዎች ሲቀመጡም የፌደራል መንግሥቱን ዕቅዶችና ራዕዮች ለመጋራት እና ለማስፈጸም አለመቻላቸውንም የመንግሥት ምንጮች ለአዲስ ነገር ገልጸዋል። “ገዢው ፓርቲ ተማሪዎቹ ኪራይ ሰብሳቢ እና ቡድንተኛ ሲሆኑበት ስርዓተ ትምህርቱን መለስ ብሎ ለመቃኘት ተገዷል” ሲሉ ያጠቃልላሉ።

4 Responses to “ትምህርት ሚኒስቴር አማርኛ ቋንቋን ከ3-12ኛ ክፍል መማር ግዴታ ሊያደርግ ነው”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

ፀሐይዋ ለኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ አዘቅዝቃለች

ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ እንደጻፉት በሚነገርለት እና ፓርቲው በ1999 ዓ.ም ባሳተመው የፓርቲው “የዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ ትግል እና አብዮታዊ ዴሞክራሲ” በሚለው የፓርቲው ውስጣዊ ዶክመንት ከነጻው ፕሬስ ጋራ የሚኖረው ግንኙነት ዘዴን የተከተለ ማዳከም እንደሚጠቀም በይፋ አስቀምጦታል። ከ1997 ምርጫ በፊት ኢሕአዴግ የግሉን ፕሬስ ከሻዕቢያ ቀጥሎ በጠላትነት ፈርጆታል። የአሁኑ ለየት የሚለው ኢሕአዴግ አገሪቱን ማስተደደር ከሚፈልግበት እና ኢትዮጵያ ውስጥ መፍጠር ከሚፈልገው ሥርዐት አኳያ ሚዲያውን የሚያዳክምበት እና የፓርቲው ሐሳቦች ብቻ የሚንሸራሸሩበትን ዕቅድ እና ስትራቴጂ ነድፎ በመንቀሳቀሱ ነው።

እሁድ ሐምሌ 18 ቀን 2002 ዓ.ም በ”ዲፌንደር” ጋዜጣ የዜና ዐምድ ላይ ዐይን የሚስብ የዜና ርእስ ጎላ ብሎ ይነበባል። “አቶ ብርሃኑ አዴሎ ተባረሩ” ይላል የጋዜጣው የዜና ርእስ። በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የካቢኔት ጉዳዮች ሐላፊ የኾኑት እና የሲቪክ ማኅበራትን ሕግ በማርቀቅ ዙሪያ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ሰው የመባረር ዜና እንዲሁ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም። የዜናው አስኳል ያለው  አንደኛው አንቀጽ ሲታለፍ ነው። ባለፈው የግንቦቱ ምርጫ በከፋ ዞን በግል ተወዳዳሪው እና “የኢሕአዴግ ደጋፊ ለመኾን የማንም ይኹንታ አያስፈልገኝም” በሚሉት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ የተሸነፉት አቶ ብርሃኑ አዴሎ “ አሁን ደግሞ ምን ገጠማቸው?” ያሰኛል-ዜናው፤ መገረም አያስፈልግም፤ የካቢኔት ጉዳዮች ሚኒስቴሩ የተባረሩት ሐምሌ 11 ቀን 2002 ዓ.ም የከፋ መረዳጃ ዕድር በአራዳ ጊዮርጊስ ባደረገው ስብሰባ “ከዕድር አባልነታቸው” መኾኑን የ “ዲፌንደር” ጋዜጣ ዜና ያብራራል። በጣት ከሚቆጠሩት የነጻ ፕሬስ ጋዜጦች ውስጥ በአንዱ በመሥራት ላይ የሚገኝ  አንድ  ማንነቱን መናገር ያልፈቀደ ጋዜጠኛ  የ”ዲፌንደር”ን  ዜና “በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ላይ የተያዘ ዐይን ያወጣ ፌዝ“ ይለዋል።

ዲፌንደር ባለቤትነቱ የዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ መኾኑ ይነገራል። ጋዜጣው  ባለፈው የግንቦቱ ምርጫ በግል በተወዳደሩበት የካፋ ዞን ለምርጫ ቅስቀሳ ወደ ቦንጋ ዘምቷል። በነጻ ታድሏል። አቶ ብርሃኑን አብጠልጥሏል። ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ አንድን ጋዜጣ እርሳቸው ለሚፈቅዱት ግላዊ ዓላማ ብቻ በመክፈት እና የተቀናቃኞቻቸው ማጥቂያ በማድረግ ወይም እርሳቸው እንደሚሉት “ለመከላከል በመጠቀም” የናኘ ስም አላቸው። ከሦስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የተነሳ ከገቡበት ንትርክ በአሸናፊነት ለመውጣት “ቻሌንጅ” የሚል ጋዜጣ በመክፈት ከተቀናቃኞቻቸው ጋራ ተናንቀዋል።

“ዲፌንደር” በተከፈተ ሰሞን ሌላ ጋዜጣም ወደ አዲስ አበባ የጋዜጦች ገበያ ብቅ ብሏል፤ “ሰነድ”። ይህ ጋዜጣ በርእሰ አንቀጽ እና በዜናዎቹ የገዢው ፓርቲ ደጋፊ መኾኑን በግልጽ የሚያሳይ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እና የተቃውሞ ሐሳቦችን የሚያራምዱ ሰዎችን የሚያብጠለጥል ነው። ዶክተር አሸብርንም እንዲሁ። ከ“ሰነድ” ጋዜጣ ጀርባ ሁለት ሰዎች እንዳሉ በስፋት ይታመናል። ብርሃኑ አዴሎ እና የበረከት ስምኦን ምክትል የኾኑት የቀድሞው ዐቃቤ ሕግ አቶ ሽመልስ ከማል። አቶ ሽመልስ ደግሞ ራሳቸው አዘጋጅ የነበሩበትን “ኒሻን” የተባለ ጋዜጣ ካቆሙ ከዐሥር ዓመታት በኋላ ዋና ሥራቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ ፕሬስ እንዳያብብ የገዢው ፓርቲ ዋና ጉዳይ አስፈጻሚ በመኾን እያገለገሉ ነው። ዐቃቤ ሕግ በነበሩበት በ1990ዎቹ መጨረሻ ብዛት ያላቸውን ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት በማንከራተት የኢትዮጵያ ፕሬስ ከዚህ በኋላ መልካም ዘመን እንደማይጠብቀው ያስረገጡ ሰው ናቸው።

ነጻ ጋዜጦች እጅግ በተዳከመ እና ተስፋ የሌለው በሚመስል ወቅት ላይ ይገኛሉ። ከይፋዊ ምንጮች የተገኘው ያለፉት የስድስት ወራት የጋዜጦች ሥርጭት ቁጥር እንደሚያሳያው በሳምንት ከ10 ሺሕ በላይ የሚያሳትሙ ጋዜጦች ቁጥር ሁለት ብቻ ነው። በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተመው ሪፖርተር በአማካኝ 12 ሺሕ ኮፒ ሲያሳትም፤ አዲስ አድማስ ደግሞ በአማካይ 25 ሺሕ ኮፒ በየሳምንቱ ለገበያ ይቀርባል። ሁለቱ የእንግሊዝኛ ጋዜጦች(ፎርቹን እና ካፒታል) እና አውራምባ ታይምስ ከ5ሺሕ እስከ 8ሺሕ ባለው አማካይ ቁጥር መካካል ይዋልላሉ።  ቁጥራቸው ዐሥራ ሦስት የሚደርሱ የኅትመት ውጤቶች የሚያሳትሙት አማካኝ የኅትመት ብዛት ከ2500 ያነሰ ነው። ከእነዚህ ውስጥም ዳጉ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮ ቻናል እና ሰነድን የመሳሰሉት በግልጽ ኢሕአዴግን የሚያንቆለጳጵሱ እና የኢሕአዴግ ሐሳቦች ማስረጫ መሣርያ የኾኑ ጋዜጦች ሲኾኑ፤ አንዳንድ ጋዜጦች ደግሞ ከኢሕአዴግ ስውር ጡጫ ለመትረፍ ወይም ከዘመኑ ሂሳብ ለማትረፍ “ልማታዊ ሃሳብ”ን ቀስ በቀስ ወደ ማጠንጠን እየመጡ መኾኑን የአዲስ ነገር የሚዲያ ምንጮች ይናገራሉ። በአጠቃላይ በአገሪቱ በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ የ19 ጋዜጦች ሳምንታዊ አጠቃላይ ሥርጭት 82 ሺሕ ያህል ነው። ይህ የኬኒያው ዴይሊ ኔሽን ከሚያሳትመው የአንድ ቀን የኅትመት ብዛት ጋራ ሲነጻጸር 41 በመቶ የሚኾነውን ድርሻ ብቻ ይይዛል።  ይህ ቁጥር 80 ሚልዮን ሕዝብ ለሚኖርባት ኢትዮጵያ የሚያሰቅቅ ነው።

አዲስ ነገር ያነጋገረቻቸው አስተያየት ሰጭዎች “ጋዜጣ የሚባለው የኅትመት ሚዲያ ተቋም ታሪካዊ ወይም ሞያዊ ተልዕኮውን ለመወጣት በሚያስችል ኹኔታ ላይ አይገኝም” ይላሉ።  “በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ነጻ ፕሬስን የሚደግፍ የሶሺዮ-ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኹኔታዎችም የሉም” ይላሉ።  ለዚህም አራት ዐቢይ  ምክንያቶችን ይደረድራሉ። በዋናነት ኢሕአዴግ ፕሬሱን ጭራሹኑ ተዳክሞ እንዲቀር የሚያደርገው ያለሰለሰ ጥረትን በዋናነት ያነሳሉ። ሁለተኛው የኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ሐይሎች ወቅታዊ ቁመና እና ፖለቲካዊ ሕይወት ማጣት፣ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ባለቤቶች አቅም  እና ሞያዊ ችሎታ ውስንነት እንዲሁም የጋዜጠኞች ሥነ ልቡና እና የሞያው ሥነ ምግባር መሸርሸር  ዋና ዋናዎቹ ተደርገው ይጠቀሳሉ።

ኢሕአዴግ የግሉን ፕሬስ “የጥፋት ሚዲያ” በሚል ከፈረጀው ቆየ። የ1997ን ስኅትት ላለመድገም  በሚል  ከግሉ ፕሬስ ጋራ ያለውን ግንኙነት ከመቅጣት/ማባበል (ካሮት & ስቲክ) በሚለው ዘዴ መሥርቶ ነጻውን ፕሬስ እያዳከመው ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ እንደጻፉት በሚነገርለት እና ፓርቲው በ1999 ዓ.ም ባሳተመው የፓርቲው “የዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ ትግል እና አብዮታዊ ዴሞክራሲ” በሚለው የፓርቲው ውስጣዊ ዶክመንት ከነጻው ፕሬስ ጋራ የሚኖረው ግንኙነት ዘዴን የተከተለ ማዳከም እንደሚጠቀም በይፋ አስቀምጦታል። ከ1997 ምርጫ በፊት ኢሕአዴግ የግሉን ፕሬስ ከሻዕቢያ ቀጥሎ በጠላትነት ፈርጆታል። የአሁኑ ለየት የሚለው ኢሕአዴግ አገሪቱን ማስተደደር ከሚፈልግበት እና ኢትዮጵያ ውስጥ መፍጠር ከሚፈልገው ሥርዐት አኳያ ሚዲያውን የሚያዳክምበት እና የፓርቲው ሐሳቦች ብቻ የሚንሸራሸሩበትን ዕቅድ እና ስትራቴጂ ነድፎ በመንቀሳቀሱ ነው። ለዚህም ፓርቲው በ1999 ዓ.ም  ያሳተመው ስትራቴጂያዊ ዶክመንት “…ሚዲያው የኪራይ ሰብሳቢዎች መፈንጫ እንዳይኾን የሚያስፈልጉ ኢኮኖሚያዊ ርምጃዎችን መውሰድ፤ ጤነኛ የሚዲያ ተቋማትን በተለየ ኹኔታ መደገፍ …” የሚሉት የኢሕአዴግ አዲሱ ዘዬ እንደሚኾን አበክሮ አስቀምጦታል። ከዚህም የተነሳ  ጋዜጦች ከተጽዕኖ መውጣት የማይችሉበት፣ ነጻ ሐሳብን እና አመለካከትን ማራመድ የማይችሉበት  ኹኔታ ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል።

የኢትዮጵያ የነጻ ፕሬስ እና ኢሕአዴግ ሦስት መሠረታዊ የግንኙነት ምዕራፍ ነበራቸው። ቅድመ እና ድኅረ 1997 ምርጫ እንዲሁም በምርጫ 97 የነበራቸው የአይጥ እና ድመት ግንኙነት በዐቢይነት ይነሳሉ። ኢሕአዴግ ከ97 በፊት እና በኋላ ከፕሬሱ ጋራ ያለው ግንኙነት ወጥ አይደለም። በአቀራረብ እና አያያዙ፤ በኀልዮም ኾነ በገቢር የተወሰነ ልዩነት አለው። ከ1984 እስከ 1997 ዓ.ም የነበረው የግብር ይውጣ ግንኙነት ሲኾን የከ1997 እስከ ሚሊኒየሙ መዳረሻ ባለው ወቅት ኢሕአዴግ የድንበራ ርምጃ ወስዷል። ከ1999 ዓ.ም በኋላ በተጠና እና ብልኀትን በተከተለ መንገድ መረጃ የሚሰጡ እና ነጻ አመለካከት የሚያራምዱ የፕሬስ ውጤቶችን እንዳያቆጠቁጡ እና  እንዳያብቡ በእንጭጩ የማስቀረት አዲሱ የኢሕአዴግ አሠራር እና አካሄድ ናቸው። ላለፉት ዐሥራ ዘጠኝ ዓመታት ኢሕአዴግ እና የነጻው ፕሬስ ባላቸው የጋዜጠኝነት ፍልስፍና እና ግብ ላይ ስምምነት ኖሯቸው አያውቅም። ግንኙነታቸውም የአይጥ እና የድመት ዐይነት ነበር።

በፕሬስ ልጅነት ዘመን

በትጥቅ ትግል ታሪኩ የተለየ ሐሳብን በነጻ የማራመድ ድርጅታዊ ባህል ያልነበረው ኢሕአዴግ  በዓለም አቀፋዊ እውነታዎች የተነሳ ነጻ ፕሬስ እንዲኖር መፍቀዱ ዓለም አቀፋዊ ቅቡልነት እንዲያገኝ ፤ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስም ተራማጅ መሪ እንዲባሉ አስችሏል።  በኢሕአዴግ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ሐሳብን በነጻነት መግለጽ እንደ አዲስ ተጀመረ። ነገር ግን  የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ከተወለደበት ከ1984 ዓ.ም እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ ኢሕአዴግ እና ነጻው ፕሬስ የነበራቸው ግንኙነት ከጅምሩ በባላንጣነት የተሞላ ነበር። በ1984 ዓ.ም ፕሬስ ማበብ ሲጀምር በወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አጠንክሮ አይሠራም ነበር። ከዚያ ይልቅ በማኅበራዊ እና በፍቅር ግንኙነቶች ላይ የሚያተኩሩ፣ ስለ ፍቅር፣ ወሲብ፣ ሐይማኖት የሚያጠነጥኑ፤ በደርግ ዘመን ተፈጸሙ የሚባሉ ግፎችን እየፈለፈሉ የሚያስነብቡ እና ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አንድነት ላይ ያለውን ዳተኝነት ታሪክን እያጣቀሱ የሚሞግቱ፣ የኤርትራን ከኢትዮጵያ መገንጠል አጥብቀው በሚነቅፉ የነጻው ፕሬስ አባላት እና ታዳሚዎቻቸው ይታወቁ ነበር።

ከጋዜጦችም ይልቅ መጽሔቶች ገበያውን በስፋት ተቆጣጥረውት ነበር። በወቅቱ በነበረው ነጻ ፕሬስ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች በርዕዮተ ዓለም ደረጃ ከአዲሱ የኢሕአዴግ ሥርዐት ጋራ ፈጽመው የሚቃረኑ ኾኑ። ብዙዎቹም በደርግ ዘመን በተለያዩ የፕሬስ ክፍል ውስጥ ይሠሩ የነበሩ እና ከጽሑፍ እና ከጋዜጠኝነት ጋራ የቀጥታ እና የተዘወዋሪ ግንኙነት የነበራቸው ናቸው። ኢሕአዴግ ነጻውን ፕሬስ በጠላትነት መፈረጅ የጀመረው ከዚያ ዘመን አንስቶ መኾኑን አበክረው የሚናገሩ አሉ። በመጋቢት 1985 ዓ.ም በታሪክ፣ በርዕዮተ ዓለም እና በማኅበራዊ ጉዳይ ለተወጠረው የኢትዮጵያ ፕሬስ አንድ ዱብ እዳ መጣለት።  ከብዙ ዓመታት ቆይታ በኋላ አገሩን ለማየት ወደ ኢትዮጵያ የመጣ አንድ ወጣት፤ የኢትዮጵያ ሚዲያ ከወቅታዊ ጉዳዮች ይልቅ በታሪክ እና ርዕዮተ ዓለም ዙሪያ በሚያጠነጥኑ ጽሑፎች እንደተሞላ ተመለከተ። ብዙም ሳይቆይ የራሱን አንድ ጋዜጣ ጀመረ። ይህ ጋዜጣ እንደ ሌሎቹ አልነበረም። ወቅታዊዉን ፖለቲካ በቀጥታ ዐይኑን የሚጠነቁል ነበር። የጋዜጣውም ስም፤ ኢትዮጲስ። ጋዜጠኛውም እስክንድር ነጋ።  በወቅቱ ዋና አዘጋጅ ከነበረው እና አሁን በሕይወት ከሌለው ተፈራ አስማረ ጋራ ኾነው የጀመሩት ይህ ጋዜጣ የኢትዮጵያን ፕሬስ አቅጣጫ አካሄድ የቀየረ፤ የመጽሔቶችን የበላይነት ቀልብሶ የጋዜጦች ዘመን መምጣቱን ያበሠረበት ዕትም ለገበያ በቃ።  የኢትዮጲስ መውጣት ለኢሕአዴግ መሪዎች አስደንጋጭ ነበር። አዘጋጆቹ ታደኑ፣ ፎቷቸው እንደ ወንጀለኛ በዜና ማሠራጫዎች ተበተነ፤ ተሳደዱ። ጋዜጣዋም መውጣት የቻለችው አራት ዕትም ብቻ ሲኾን የጋዜጣዋ ፍጻሜ ፕሬሱ እና ኢሕአዴግ በሚቀጥሉት ጊዜያት የሚኖራቸውን ግንኙነት ወከክ አድርጋ ያሳየች ነበረች። ከኢትዮጲስ በኋላ የመጡት የፕሬስ ውጤቶችም እንደ መጀመርያዎቹ የፕሬስ ውጤቶች ታሪክን በዋናነት የሚተነትኑ ሳይኾኑ በወቅታዊ ፖለቲካዊ ኹኔታዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚሠሩ ናቸው።  ከኢትዮጲስ መምጣት በኋላ ቁጥራቸው የበዛ ጋዜጦች ወደ ሚዲያው በከፍተኛ ቁጥር ዘለቁ።

ለብዙዎቹ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች ሥራቸው “ጋዜጠኝነት” ብቻ አልነበረም”። አንድ ዐይነት አመለካከት በሁሉም ነጻው ፕሬስ አባላት ዘንድ ባይኖርም በአመዛኙ የነበረውን ገዥ አመለካከት ኢሕአዴግ የፈጠረውን ነባራዊ ኹኔታ  የመለወጥ፣ ወደ ተሻለ ኹኔታ/ሥርዐት የማሻገር ሐላፊነት ነበር። ብዙዎቹ ከዐምባገነን ሥርዐት ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የሚደረገውን ጉዞ በነጻ አውጭነት  አስተሳሰብ የሚመሩ ነበሩ።  ለአንዳንዶቹ ጋዜጠኞች ደግሞ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተቃጣውን አደጋ የማስቀረት “የእሳት አጥፊነት” ሚና ይዘው የሚንቀሳቀሱ ናቸው። በ1990ዎቹ አጋማሽ ብቅ ያሉ አንዳንድ የሚዲያው አባላት ደግሞ “በአምባገነን ሥርዐት የነጻ ፕሬስ ሚና ሐሳብን በነጻነት ለመግለጽ የሚደረገውን ትግል መምራት ነው” ብለው ያምኑ ነበር።

የኢትዮጲስ ጋዜጣ አዘጋጅ እና ባለቤት የመጀመርያውን እስር እና እንግልት ከቀመሱ ዓመታት በኋላም የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ዕጣ የኢትዮጲስን ዕጣ ከመከተል የዘለለ አልነበረም። በቀጠሉት ዓመታት የመጡት የነጻው ፕሬስ አባላት “የጋዜጠኝነትን ሥነ ምግባር” አልጠበቁም እየተባሉ ቢተቹም ለዓመታት የኢሕአዴግ የጥቃት ሰለባ ኾነው ዘልቀዋል። ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲታሰሩ፣ ሲንገላቱ፣ ሲደበደቡ፣ ከአገር ሲሰደዱ አሳልፈዋል ። ለ13 ድፍን ዓመታት።

በምርጫው ጥላ ሥር

የነጻው ፕሬስ አባላት የኾኑ ጋዜጦች ከፍተኛ ተነባቢነት ያገኙት በሦስት አጋጣሚዎች ነበር። በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ በ1993 ህወሓት ክፍፍል እና ከ1997 ምርጫ ጋራ በተገናኘ ነበር። በ1997 ምርጫ እስከ ሚያዝያ 30 ባሉት ሳምንታት ነጻው ፕሬስ ከፍተኛ የኾነ የኅትመት ቁጥር አላስመዘገበም ነበር። ከምርጫው አንድ ሳምንት ጀምሮ ብዙ ጋዜጦች የኅትመት ቁጥር ከሁለት እና ሦስት እጥፍ በላይ አደገ። ይህ እድገት ተሰሚነታቸው እንዲጨምር፣ ከመንግሥት ሚዲያ በላይ ተዓማኒነታቸው እንዲጎላ፤ ከምርጫው በኋላ በነበሩት ፖለቲካዊ ተዋስኦዎች ተሰሚነታቸው እንዲጎላ ግፊት አድርጓል። ብዙዎች የሚደግፏቸውን ያህል ፕሬሱ በፖለቲካው ላይ ያሳደረውን ሚና የሚነቅፉ ተቺዎችም አሉ።

ከፕሬሱ ጋራ የአይጥ እና የድመት ግንኙነት ያዳበረው ኢሕአዴግ ምርጫ 97ን ተከትለው  ለተነሱት አመጾች እና ሕዝባዊ መነሳሳቶች በሙሉ የፕሬሱ ተጠያቂነት ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ እኩል እንደኾነ ማወጅ ጀመረ። ከጥቅምት 1998 ዓ.ም የኢትዮጲስ ጋዜጣ መሥራች የነበረውን እስክንድር ነጋን ጨምሮ ብዛት ያላቸው ጋዜጠኞች ለእስር ተዳረጉ። ከ23 በላይ ነጻ ጋዜጦች ተዘጉ። ኢትዮጵያ ከ12 ዓመት በፊት ወደ ነበረችበት የሚዲያ ዐልባ አገርነት ቀስ በቀስ ተቀየረች። ለኢሕአዴግ የተዘጉት ሚዲያዎች እና የታሰሩት ጋዜጠኞች የጥፋት ሚዲያዎች እና ሠራተኞቻቸው ናቸው። የኢሕአዴግ የጅምላ ርምጃ ድርጅቱ ከሚዲያ ጋራ ላይ ያለውን ግንኙነት በደንብ እንዳላሰበበት እና ርምጃዎቹም ከድንበራ የመነጩ መኾናቸውን ማሳያ ተደርገው ተወስደዋል። ይኹንና ይህ ወቅት ኢሕአዴግ ከፕሬሱ ጋራ የነበረውን የግንኙነት ምዕራፍ ዘግቶ ሌላኛውን የከፈተበት ነበር።

ጭብጦ እና አለንጋ

ብዙዎች ከቅድመ ምርጫ 97 በፊት ኢሕአዴግ ለመድብለ ፓርቲ እና ሐሳብ ሥርዐት ትንሽም ብትኾን ቦታ ይሰጣል ብለው ያምኑ ነበር። የቅንጅት መፈጠር የዚህ እምነት ውጤት ነበር። በፕሬሱ ውስጥ የነበረው ተሳትፎ እና ሐሳበቸውን በግልጽ ለማፋጨት የሚፈልጉ ወገኖች በየፕሬስ ውጤቱ ላይ መታየት የዚህ እምነት ውጤት ፍሬ ነው። አንዳንዶች ባያምኑትም ኢሕአዴግም  ቢያንስ ብዙዎች በዴሞክራሲ ሥርዐቱ ተስፋ እንዲያደርጉ ፍንጭ መስጠቱ አልቀረም። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን ጋራ ያደረጉት ውይይት እና የምርጫ 97  ሂደት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ተስፋ እንዳይቆረጥ የሚያባብሉ ምልክቶች ይመስሉ ነበር።

ነገር ግን ከምርጫ 97 በኋላ የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መሥመር በሌላ አዲስ የዜማ ቅኝት ውስጥ ገባ። ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መሥመር የሚል። ኢሕአዴግ ከምርጫ 97 በኋላ ሙሉ በሙሉ የአንድ ፓርቲ እና አስተሳሰብ ሥርዐትን ለመመሥረት በግልጽ እና በማያሻማ ቋንቋ ዕቅድ አስቀምጦ እየተንቀሳቀሰ ነው። በ1999 ዓ.ም በፓርቲው ታትሞ  የተሠራጨው “የዴሞክራሲ ሥርዐት ግንባታ ትግል እና አብዮታዊ ዴሞክራሲ” የተሰኘው የፓርቲ ዶክመንትም የሚያስረግጠው ይህንኑ ነው። አንድ ፓርቲ (አውራ ፓርቲ) እና  ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የሚገነባበትን ሥርዐት ማስፈን። አሁን ያለው የኢሕአዴግ እና የኢትዮጵያ የነጻ ፕሬሶች ግንኙነትም የሚመነጨው ከዚህ በግልጽ ከተቀመጠው እና በባሕርይው አምባገነናዊ ከኾነ የኢሕአዴግ አስተሳሰብ ነው። ሐሳባቸውን ለአዲስ ነገር ያካፈሉ አስተያየት ሰጭዎችም የሚያነሱት አንኳር ሐሳብ ፕሬሱ ያለበት ኹኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተመሠረተ ያለው ሥርዐት አንድ መገለጫ አድርገው ይወስዱታል። ከምርጫ 97 በኋላ ብቅ ያለው ኢሕአዴግ እንደ መጀመርያው የፕሬስ ዘመናት ብዙውን ጊዜ ያለ “ሕግ” አይንቀሳቀስም። ነገር ግን የፖለቲካ ምኅዳሩን የሚያዳፍኑ የፕሬስ ሕግ፣ የሲቪክ ማኅበራት ሕግ እና የጸረ ሽብር ሕግን በማውጣት ፕሬስ ሰማዕትነትን የሚጠይቅ ሞያ እንዲኾን አደረገው። ነገር ግን አሁንም ሲሻው ኢሕአዴግ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ  ያለ ሕግ ያሻውን ያደርጋል። በዚህም ለ18 ወራት በእስር ያሳለፉትን ጋዜጠኞች እነ እስክንድር ነጋ እና ሲሳይ አጌናን ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዳይመለሱ አድርጓል።

የ“ነጻ” አብዮታዊ  ዴሞክራሲ ሚዲያ መባቻ

የእነዚህ ሕጎች መጽደቅ በዴሞክራሲ ማበብ ተስፋ ላይ ውኃ የቸለሱ ሲኾን አቶ መለስ ወደ ሚፈልጉት የአንድ ፓርቲ ፍጹም አምባገነንነት ሥርዐት ለመግባት ሕጋዊ የሚመስል ጭብጦ እና አለንጋ መጠቀምን እንደ አቅጣጫ አስቀምጧል። የኢሕአዴግን ሐሳብ የማይጋሩ ነጻ ሚዲያዎች የኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን በመቆጣጠር፣ በማዳከም፣ እና በማስፈራራት ለዘላቂው እንዳያብቡ በእንጭጩ የመከላከል ተግባር ላይ ተጠምዷል። አቶ በረከት የሚመሩት የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤትም ዋና ሥራ ይህ ነው። ከ2000 ዓ.ም በኋላ ብቅ ያሉትን የተለያዩ ጋዜጦች አዲስ ነገር፣ አውራምባ ታይምስ ከመሳሰሉ ጋዜጦች የሁለት ገጽታ ያለው ግንኙነት ለመፍጠር ሞክሯል።

አንዳንድ ጋዜጦች በተደጋጋሚ ከፍትህ ሚኒስቴር እና ከኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በደረሰባቸው ማስፈራሪያ ልካቸውን አውቀው የተሸማቀቁ ሲኾን የአዲስ ነገር ጋዜጠኞች ደግሞ ለስደት ተዳርገዋል። ከመንግሥት ሚዲያ ባሻገር “ልማታዊ እና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የሚዲያ ዕድል አጥቶ እንዳይደርቅ ለመከላከል”  አዳዲስ ደጋፊ የፕሬስ ውጤቶች ወደ ገበያው እንዲገቡ፣ በኢኮኖሚ አቅማቸው ደካማ የኾኑ ነባር ሚዲያዎችን “ማቀፍ” አዲሱ የኢሕአዴግ የፕሬስ ኮንትራት ውል ነው። ባለፉት ጥቂት ወራት በገበያው ባይቀናቸውም የኢሕአዴግን ሐሳብ የሚያቀነቅኑ አዳዲስ ፕሬሶች ወደ ገበያው ጎራ ብለዋል። አንዳንዶችም ነባር ጋዜጦች በፊት ከሚታወቁበት አሠራር በመለወጥ “ልማታዊ” ወደ ኾነ የአዘጋገብ ዝንባሌ ውስጥ እየገቡ ነው። አንዳንዶችም የኢሕአዴግን አሠራር ባይደግፉትም ቢያንስ ተቃዋሚ ኾነው ራሳቸው ላይ አደጋ መጋበዝ አይፈልጉም። እጅግ ጥቂቶች አሁንም ኤዲቶሪያል ነጻነታቸውን ላለማስደፈር እየታገሉ ነው።

ነጻው ፕሬስ ተዳክሟል። ይህች የኢሕአዴግ ኢትዮጵያ ናት። የነጻውን ፕሬስ መዳከም የተመለከቱ ታዛቢዎች ጀንበሯ በነጻ ፕሬስ ላይ አዘቅዝቃለችን? ሲሉ ጥያቄ ያነሳሉ። አንዳንዶች ደግሞ “ጌታ ኾይ ምልክቶቹ እነዚህ ብቻ ናቸውን?” ይላሉ።

One Response to “ፀሐይዋ ለኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ አዘቅዝቃለች”

  1. Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.

  2. i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny

  3. alemayehu tefera 4 October 2010 at 4:14 am

    Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!

  4. MELES TEW TEMELES 5 October 2010 at 9:32 pm

    ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!

  5. I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!

    Thanks Gezahegn

  6. Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.

Leave a Reply

You must be to post a comment.

Bad Behavior has blocked 5987 access attempts in the last 7 days.