የሃና እና የቻይና ግንኙነት፣ በናዝሬት ፔንስዮን
ሃናን ከሌሎች የ“ናዝሬት ፔንስዮን” ኮማሪቶች ልዩ የሚያደርጋት ከቻይናውያን እና ከፊሊፒንስ አገር ሰዎች ጋራ ያላት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ነው። ሃና ለሀበሻ ወንድ ጊዜ እና ግድ የላትም። ሁልጊዜ በቁመት ከሚያንሷት የሩቅ ምሥራቅ ኮበሌዎች ክበብ ሥር ናት፤ ትኾናለች፤ ይወዷታል። በጊዜ መጥተው እርሷን የእነርሱ ለማድረግ ይሟሟታሉ። ቋንቋ በማይመስል ቋንቋ የኾነ ነገር እያሏት ከት ብለው ይስቃሉ። እርሷም በቻይንኛ ከት ብላ ትስቃለች። ሳቃቸው ቤጂንግ እና ማኒላ ይሰማል።
(ገዛኸኝ ይርጋ)
ሃና አገር አይደለችም፤ ኢትዮጵያዊት የቡና ቤት ሠራተኛ/ ዝሙት አዳሪ እንጂ። ገላዋን ለቻይናውያን እና ለእነርሱው መሰል ዜጎች በማከራየት የምትተዳደር የሌት ለፍቶ አዳሪ። የሃና እና የቻይናውያን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት “ናዝሬት ፔንስዮን” ባለጌ ወንበር ላይ ተጀምሮ ጓሮ 150 ብር በሚከፈልበት አልጋ ላይ ፍጻሜውን ያገኛል። ሁል ጊዜ፤ ማታ ማታ።
“ናዝሬት ፔንስዮን” ኮሜርስ አካባቢ ከቴሌ ባር ገባ ብሎ የሚገኝ ሰፊ የአስረሽ ምቺው ቤት ነው። መካከለኛ ገቢ ያላቸው አዲስ አበቤዎች አማርጠው ዝሙት መግዛት ሲሹ ሦስት ቤቶችን ያዘወትራሉ። የፒያሳውን “በአካል. ፀ”፣ የኻያ ሁለት ማዞርያውን “ሰገን”ን እና የኮሜርሱን “ናዝሬት ፔንስዮን”ን። ሦስቱም ተመሳሳይ የአስተዳደር፣ የአሠራር እና የአመራር ስልትን ይከተላሉ። በእነዚህ ሦስት ቤቶች ምን የመሰሉ ዲጄዎች ምን የመሳሰሉ ሙዚቃዎችን ያጫውታሉ፡፡ ደንበኞችን በሁሉም መልኩ የሚያጫውቱ ብዙ የቡና ቤት ሴቶች ያሉትም በእነዚህ ሦስት የአዲ’ሳባ ዝነኛ መሸታ ቤቶች ውስጥ ነው። ነጭ ጋውን የለበሱ ተቆጣጣሪዎች፣ ደረታቸውን ያሳበጡ ቦዲጋርዶች፣ ቢራ የሚያቀርቡ ወንድ አስተናጋጆች በሦስቱም መሸታ ቤቶች ተመሳሳይ በሚባል መልኩ ይገኛሉ።
ናዝሬት ፔንስዮን ይህ ጽሑፍ በሚጻፍበት ወቅት 27 ኮማሪቶችን ያስተዳድር ነበር። ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ጀምሮ ወደ ሥራ የሚገቡት የናዝሬት የምሽት ኮማሪቶች ልክ እንደ መደበኛ የመንግሥት መሥርያ ቤት የሚተዳደሩበት ያልተጻፈ ሕግ እና ደንብ አላቸው። ለምሳሌ ሁሉም ሴቶች ወደ ሥራ ሲገቡ በረንዳው ላይ በተቀመጠ መዝገብ ላይ ፊርማቸውን እና የገቡበትን ሰዓት ያኖራሉ። ባልተጻፈው ሕግ መሠረት ማንኛዋም ሴተኛ አዳሪ ደንበኛን ማንጓጠጥ በፍፁም አይፈቀድላትም። ለዳንስ ከተዘጋጀው ስፍራ ውጭ በጠረጴዛ ዙርያ ከደንበኛ ጋራ መላፋትም ኾነ መደነስ አይቻልም። ደንበኛ ለአጭሬ /ሾርት/ መስተናገድ ካሻው ሴቷ ለሚመለከተው አለቃዋ በቃል ወይም በጥቅሻ ማሳወቅ ግዴታዋ ነው። ለአዳር ከኾነ ደግሞ የመውጫ ግብር ብር 30 መክፈል ይጠበቅባታል።
ናዝሬት ፔንስዮን በሚያስተዳድራቸው ሴተኛ አዳሪዎቹ ብዛት ብቻም ሳይኾን ጥራትም ጭምር ይታወቃል። ብዙም ጉስቁልና ያልደረሰባቸው፣ ሰውነታቸው ያልሟሸሸ እና የጨዋ የሚመስል፣ የዕድሜ ኪሎ ሜትራቸው ከሰላሳ ያልዘለለ፣ ብዙ ያልተጎበኙ የሚመስሉ ሴቶች ለወንዶች ዐይን ማረፍያ የኾኑበት ቤት መኾኑ ተመራጭ ያደርገዋል ይላሉ የረዥም ጊዜ ደንበኞቹ።
ይህ ቤት ሁለት ዐይነት የዝሙት ዋጋ ሜኑ የሚያቀርብ ነው። ለዜጋ እና ለሀበሻ። በዚህ ቤት አጠራር ዜጋ የሚባሉት ከኢትዮጵያውያን ውጭ ዜግነት ያላቸውን ሲኾን በተለይም የቻይና እና የፊሊፒንስ ዜጎች ላይ ያተኮረ ዐይነት ነው። አንዲት የቤቱ ኮማሪት አንድ የቻይና ዜጋ ለማውጣት መውጫ ግብር 50 ብር መክፈል ሲጠበቅባት ከሀበሾች ጋራ ሲኾን ግን 30 ብር ብቻ በቂዋ ነው። በናዝሬት ፔኔሲዮን ለሾርት/quickie/ አንድ አልጋ ለዜጋ (ቻይና እና ቻይና መሰል ደንበኞች ማለት ነው)150 ብር ሲወሰንባቸው ሀበሾቹ 100 ብር ብቻ ይከፍላሉ።
ሃና ወደዚህ ቤት በከፍተኛ ዝውውር ከመጣች ሁለት ዓመት ለመድፈን ጥቂት ሌሊቶች ይቀሯታል። የሕዋ ርቀት በብርሃን ይለካል፣ ኀይሌ ገብረ ሥላሴ በማይክሮ ሰከንድ ይቆጥራል፣ ሃና በሌሊቶች ብዛት ዕድሜዋን ታሰላለች። የኻያ አራት ወራት ሌሊቶችን ከሞላ ጎደል በናዝሬት ፔንስዮን አልጋዎች ላይ አሳልፋለች። ከዜጎች ጋር።
ሃናን ከሌሎች የ“ናዝሬት ፔንስዮን” ኮማሪቶች ልዩ የሚያደርጋት ከቻይናውያን እና ከፊሊፒንስ አገር ሰዎች ጋራ ያላት ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ነው። ሃና ለሀበሻ ወንድ ጊዜ እና ግድ የላትም። ሁልጊዜ በቁመት ከሚያንሷት የሩቅ ምሥራቅ ኮበሌዎች ክበብ ሥር ናት፤ ትኾናለች፤ ይወዷታል። በጊዜ መጥተው እርሷን የእነርሱ ለማድረግ ይሟሟታሉ። ቋንቋ በማይመስል ቋንቋ የኾነ ነገር እያሏት ከት ብለው ይስቃሉ። እርሷም በቻይንኛ ከት ብላ ትስቃለች። ሳቃቸው ቤጂንግ እና ማኒላ ይሰማል።
ኾኖም በአንድ ሌሊት ከአንድ አልያም ከሁለት ቻይናውያን ጋራ ብታድር ነው። ሌሎች ቤቱን የሚሞሉት ቻይና መሰል ዜጎች ግን ሃናን በቢራ አታለው፣ ጭኗን ደባብሰው ሹልክ ይላሉ። ተንጠራርተው አንገቷ ሥር ሳስመው ይሰናበቷታል።
ሃና ገላዋን ለመጋራት ለሚሹ ዋጋዋ የሚያደራድር አይደለም። ለአጭሬ ብር 350፣ እንዲሁም ለአዳር ብር ከ500-650 ትጠይቃለች። ከሀበሾች ይልቅ “ዜጋዎች” ይንከባከቡኛል ትላለች። በተለይ ፊሊፒኖች።
ናዝሬት ፔንስዮን ቀኑ ገና ለዐይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር ይከፈታል። የመጀመርያዎቹ ተስተናጋጆች ግን ቻይናውያን ፊሊፒንሶች ናቸው። አንዳንዴ የሥራ ሽርጣቸውን እንኳ ሳያወልቁ ናዝሬት ተንደርድረው ይገባሉ። ጊዮን አካባቢ አላልቅ ያለውን የኢትዮጵያ ሰማይ ጠቀሱን ናኒ ሕንፃ የሚገነቡ ናቸው ብዙዎቹ። ቀሪዎቹ ደግሞ ቀለበት መንገድን ለማገናኘት የሚተጉ ናቸው። ሃና እና ጓደኞቿ እስኪመጡ ቢራ እየቀማመሱ ፑል በመጫወት ጊዜ ይገድላሉ።
“ናዝሬት ፔንስዮን” ዕድሜ ጠገብ መሸታ ቤት ቢኾንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እድሳት አድርጎ በአዲስ የሥራ መንፈስ ነው ገበያውን የተቀላቀለው። የሰከረ ሰው ራሱን እያየ የሚደንስበት ስፍራን አዘጋጅቷል። በባለጌ ወንበሮች ላይ ቂብ ብሎ መጠጣት ያማረው በቤቱ የግራ ማእዘን አካባቢ መሰየም ይችላል። ኳስ እያየ የጀበና ቡና ከቢራ ጋራ እያጣጣመ ከቤቱ ሴቶች ጋራ ድርድር ማድረግ የፈለገ በረንዳ ላይ በተዘረጋ ሰፊ አዳራሽ ውስጥ ባሉ ሶፋዎች ላይ መንጋለል ይችላል። ቤቱ ውስጥ ቆሞ፣ ቁጭ ብሎ፣ ተንጋሎ ለመጠጣት የሚያስችሉ ምቹ ስፍራዎች ተሰናድተዋል። ሲጋራ፣ ማስቲካ፣ ሶፍት፣ ኮንዶም እና የመሳሰሉትን ለመግዛት ወደ ውጭ መውጣት አይጠበቅም። “አማረ” የሚባል ልጅ እግር የሚያስተዳድራት ትንሽዬ ኪዮስክ ግቢው ውስጥ ተቋቁማለች። እነ ሃና አሁንም አሁንም እየሄዱ አንድ ጊዜ ሲጋራ፣ አንድ ጊዜ ኮንዶም፣ ሌላ ጊዜ ሞባይል ካርድ ይሸምታሉ፡፡
“አማረ ቆንጆ፣ እስኪ የሞባይል ካርድ ስጠኝ፤”
“የቅድም የሲጋራ አልከፈልሽኝም እኮ…፤”
“ብር ጨርሻለኹ አንድ “ዜጋ” ላውጣና አሰጥኻለኹ …”
“ትናንት ለሜሪ 10 ብር ስጣት ብለሽኝ ሰጥቻታለሁ፣ እሱም አለብሽ።”
“አውቂያለኹ! እሰጥኻለሁ አልኩህ እኮ፣ ያንን ዜጋ እያዳከምኩት ነው፣”
“አሁን ካርድ ባለ ስንት ልስጥሽ፣”
“የ‘ተሾመ ቶጋን’ አርግልኝ፤ አዲሱን፣”
ለረዥም ጊዜ በገበያ ላይ ያሉት የሞባይል ካርዶች ባለ 100፣ ባለ 50 እና 25 ብር ብቻ ነበሩ። በቅርቡ ቴሌ ባለ 15 ብር ካርድ ገበያ ላይ እንዲኖር አድርጓል። ‘ተሾመ ቶጋ’ የሚል ስም የወጣለት ይኸው በቅርቡ ቴሌ ያስተዋወቀው ባለ 15 ብር የሞባይል ካርድ ነው። ሃናን ለምን የካርዱ ስም እንደዚያ እንደተባለ ጠየቅኋት። “ሐሳብ አያስጨርስም አለችኝ።” ስቄ ለማባራት ጊዜ ወሰደብኝ። ባለፈው አምስት ዓመት የፓርላማው አፈ ጉባዔ ሲያሳዩት የነበረው ጠባይ እና ሐሳብ የማያስጨርሱ ናቸው ለማለት ይኼ ካርድ ገበያ ላይ መምጣት ነበረበት ለካ።
“ናዝሬት ፔንስዮን” ኪዮስክ ብቻ አይደለም ያለው። አይበለውና ተጠናቀው ሲወጡ ፓንትዎ ቢበላሽ ደጅ ሳይወጡ እዚያው ይሸምታሉ። አይበለውና ለሾርት ሊገቡ ሲሉ የእግርዎ ጠረን አሳሰበዎ። አዲስ ካልሲ እዚያው ይሸጣል። ያውም የቻይና። ለሴቶች ጡት መያዣ እና ንጽሕና መጠበቅያም በግቢው ይሸጣል።
“ናዝሬት” ጥሎበት በቻይና እና ቻይና በሚመስሉ ዜጎች ይወደዳል። የቤቱ 60 በመቶ ደንበኞች እነዚህ ዐይናቸው ጠበብ ያሉ ዜጎች ናቸው። ለምን ይህን ቤት መረጡ ሲባል ግን መልስ የሚሰጥ የለም። በየዕለቱ የእነዚህ ቻይና መሰል ፍጡሮች ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም። የገዥው ፓርቲን የዲፕሎማሲ አዝማምያ ተከትሎ የሚሠራ ቤት ይመስላል። የቤቱ ዲጄዎችም ይህንኑ በመረዳት አንድ መላልሰው የሚያጫውቱት የቻይና ዜማ እንዳለም ተነግሮኛል።
ሁሉም አስተናጋጆች ዐይኑ የጠበበን ሁሉ ቻይና እያሉ ይጠራሉ። ሃና ግን ማን ምን እንደኾነ ጠንቅቃ ከማወቋም በላይ ቋንቋቸውን ትሞካክራለች። ከሁሉም ዜጎች ሃና በፊሊፒንሶች ፍቅር የወደቀች ይመስላል። እርሷ እንደምትለው ፊሊፒኖች ለሴት ልጅ ክብር ይሰጣሉ፣ ጥሩ ይከፍላሉ። ጥሩ ይጋብዛሉ፣ ርኅራሄ አላቸው። ፍቅር ይሰጣሉ። ሃና ከእኔ ጋራ በነበረችበት ወቅት በተደጋጋሚ ከፊሊፒኖች ስልክ ሲደወልላት ሰምቻለኹ። እንግሊዝኛ እና ፊሊፒኖ እየቀላቀለች ታወራቸዋለች።
ብዙዎቹ ፊሊፒኖች ሜድሮክ ውስጥ ሠራተኞች እንደኾኑ ሃና ነግራኛለች። የማያልቀውን ናኒ ሕንፃ የሚሠሩትም እነርሱ ናቸው። ገብርዔል አካባቢ የሚገኘው ዳግም ሚሌኒየም ሆቴል ውስጥ ነው የሚኖሩት። የተወሰኑት ደግሞ “ራስ ሆቴል” ያድራሉ። ሃና በተደጋጋሚ እዚያ ይዘዋት እንደሚሄዱ ትናገራለች። “አንድም ጉዳት አድርሰውብኝ አያውቁም። አብረን አድረን፣ ጋብዘውኝ፣ ሸኝተውኝ እንለያያለን” ትላለች። የተወሰኑት ቋሚ ደንበኞቿን ስም እየጠራች በእርግጠኝነት አግብተው እንደሚወስዷትም ትናገራለች። “ጃክ በጣም ነው የሚወደኝ፣ እኔም እወደዋለሁ፣ የሚስቴን ፍቺ እንደጨረስኩ ይዤሽ እሄዳለኹ ብሎኛል” ትላለች ለእርግጠኝነት ሩብ በጎደለው ተስፋ።
ሃና ከፊሊፒኖ ቋንቋ ወሳኝ የምትላቸውን ቃላት ነግራኛለች። ልክ ትሁን አትሁን ግን የማውቀው ነገር የለም። “ቻካ ቻካ” /ጨዋ ያልኾነ ስድብ/፣ “ኢቃው”/ አንተ፣ አንቺ ማለት ነው/፣ “ሲራዉሉ”/ እብድ፣ “መሃላ ማልጊታ” /እወድኻለሁ/ ፣ “አዲባባህ” /አንተ የኔ ነህ/። የሃና የፊሊፒኖ መዝገበ ቃላት ታድያ ከስድብ እና ከፍቅር ቃላት ዘሎ አያውቅም።
ሃና ከቻይኖች ጋራ ያላት አግባብም እንደፊሊፒኖዎቹ አይሁን እንጂ መልካም ነው። እንደ ቡና ስኒ ተመሳሳይ የኾኑ ቻይናዊያንን አንዱን ከሌላው ለመለየት አፍንጫና ፀጉራቸውን አተኩራ ታያለች። ከዚያም በስማቸው ትጠራቸዋለች። ቻይኖች ጠንካራ ሠራተኞች ናቸው። ጥንካሬያቸው ግን ምሽት ላይ አይደገምም።
እንደ ሃና መረጃ ከኾነ ቻይናውያን እንደሚሠሩት ቀለበት መንገድ ዘለግ ያለ የፆታ ባንዲራ/ብልት/ የላቸውም። ሃና መጠኑን የምትገልጸው ትንሿን የእጅ ጣቷን ለብቻዋ አውጥታ በማሳየት ነው። ይህ መልካም ነገር ነው ለሃና። ለእርሷ ከዚያ ይልቅ ጠረናቸው ምቾት አይሰጣትም። “በጡት ፋንታ ሲጋራ ነው እንዴ እያጠቡ ያሳደጓቸው” ስትል ትሳለቃለች። ይህን እያወራች “እስኪ ሲጋራ ስጠኝ” ትላለች አስተናጋጁን በጥቅሻ እየጠራች። ሲጋራው ሲመጣላት ግን አስተናጋጁ እንዲለኩስላት አትፈቅድም። በአቅራቢያዋ እየተዝናና ካለ ቻይናዊ ጋራ ሄዳ ለኩስልኝ ትለዋለች። በቻይንኛ ይሽኮረመማል። የሃና እና የቻይናውያን ግንኙነትም ለቀጣዩ ደረጃ ሰዓቱን ይጠብቃል።
Interesting! I think the word ‘Comarit’ is not being used properly.
i know this house years ago. really true story. Thank you Gezehagn. Funny
Ere Gezehagn….You are amazing men. I was cracking throughout the reading. I feel like I was reading one of bewketu’s work. You have got a good writing ability so you should keep writing. Two thumbs up!!! please I do beseech you to keep writing. Good one!!!
ITS GOOD ZEGEBBA !!!….I LIKE IT !!!
I liked “teshome togga” the most – wey Addisaba!? I missed you a lot!!
Thanks Gezahegn
Oh Gezahegn, please go on writting;it is a nice piece.