“ኤርትራን ያስገነጠልነው ኢትዮጵያን ከመበታተን ለማዳን ነው” የአቶ መለስ አዲስ ግኝት
አቶ መለስ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ህወሓት ከሻዕቢያ ጋር ለምን እንደወገነ ሲመልሱ “ኢትዮጵያን ከመበታተን ለማዳን ነው” ብለውናል፡፡ ይህ መቼም በጣም የሚያስገርም ግኝት ሳይሆን አልቀረም፡፡ አቶ መለስ አሳምረው እንደሚያውቁት፣ አቦይ ስብሐትም በቅርቡ ሲናገሩ እንደተደመጡት፣ ህወሓት የኤርትራ ጥያቄ “የቅኝ ግዛት ጥያቄ” መሆኑን ተቀብሎ ለኤርትራ ነጻነት ሲታገል የነበረ ድርጅት ነው፡፡ እንዲያውም የኤርትራን ነጻነት ከራሱ ከሻዕቢያ ሳይቀር የታደገ መሆኑን አቦይ ስብሐት በግልጽ አረጋግጠዋል፡፡ ይህ ዓላማ ኢትዮጵያን ከመበታተን ከማዳን ጋር አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡ ሲጀመር ስሙ እንደሚያመለክተው ህወሓት ትግራይን /እና ኤርትራን/ ነጻ ለማውጣት የተቋቋመ ድርጅት እንጂ የኢትዮጵያ አንድነት ጉዳይ ጉዳዩ የነበረ/የሆነ ድርጅት አልነበረም፡፡ ስለሆነም ህወሓት ትብብሩን የሚያራምደው “የትግራይን ሕዝብ” መብት ከማስጠበቅ አንጻር እንጂ የኢትዮጵያ አንድነት አስጨንቆት አልነበረም፡፡ …ሙሉውን ለማነበብ የድረ ገጹን የአማርኛ ክፍል ይጎብኙ።
Read more
Recent Comments