ስብሐት ፣ ከጳውሎስ እስከ ማኅበረ ቅዱሳን
“ዝነኛው” አቦይ ስብሐት የዛሬ ሦስት ሳምንት ገደማ በ“ፍትሕ” ጋዜጣ ለወጣባቸው ትችት የሰጡት መልስ አስተያየት የሚጋብዝ ነው። የ“ፍትሑ” አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝም አቦይ ስብሐት ሕዝብ በተሰበሰበበት የተናገሩትን ለንባብ ማቅረቡ የሚጠቅም ነው፤ “ሰውየው መዘባረቅ ልማዳቸው ነው” ብሎ አለመተዉን ለማድነቅ ነው። (ተጨማሪ ምልልሶችን በ “ፍትሕ” ጋዜጣ ድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል።) ስብሐት በይፋዊው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከፓራላማ አባልነት የዘለለ ቦታ [...]
“ዝነኛው” አቦይ ስብሐት የዛሬ ሦስት ሳምንት ገደማ በ“ፍትሕ” ጋዜጣ ለወጣባቸው ትችት የሰጡት መልስ አስተያየት የሚጋብዝ ነው። የ“ፍትሑ” አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝም አቦይ ስብሐት ሕዝብ በተሰበሰበበት የተናገሩትን ለንባብ ማቅረቡ የሚጠቅም ነው፤ “ሰውየው መዘባረቅ ልማዳቸው ነው” ብሎ አለመተዉን ለማድነቅ ነው። (ተጨማሪ ምልልሶችን በ “ፍትሕ” ጋዜጣ ድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል።)
(አቦይ) ስብሐት ነጋ
ስብሐት በይፋዊው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከፓራላማ አባልነት የዘለለ ቦታ ይዘው ባይታዩም በተግባራዊው ዓለም ግን ከአገሪቱ “ስውር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች” አንዱ ናቸው። እናም ተለቅ ያለ ቢዝነስ ለመጀመርም ሆነ በፖለቲካው ባህር ላይ “በመጋኛ ሳይመቱ” ያለስጋት ለመራመድ የአቦይ ስብሐትንና የእመት … ምክርና ቡራኬ የሚጠይቁ ብዙ ሰዎች እንደነበሩም እንዳሉም የታወቀ ነው። አሁን ደርሶ “የሩቅ ተመልካች ነን” ሊሉን ሞከሩ እንጂ በቤተክህነቱም ጉዳይ ምእመናን ደጅ የሚጠኑላቸው፣ “ሰይጣናችሁን አስታግሱልን፣ ምን ብናደርገው ይሻላል?” እየተባሉ መፍትሔ የሚጠየቁ “አዋቂዎች” ናቸው።
አቦይ ስብሐት ከብዙዎቹ የህወሓት ሹማምነት በተለየና በግሌ በማደንቀው ሁኔታ ከሕዝብ ጋራ የመገናኘት እድል አላቸው። የሕይወት ዘይቤያቸውም ለዚህ የተመቸ ነው፤ ወይም ደግሞ ይሁነኝ ብለው ይህን አኗኗር ተከትለዋል። እዚህ ዝርዝር ውስጥ ገብቶ በሚወራው ነገር ላይ አስተያየት መስጠት አልፈልግም፤ አያገባኝም፤ ለውይይታችንም ጠቃሚ አይደለም። ሰውየው በአጭሩ ቢያንስ የተወሰኑ ሰዎችን አመለካከት፣ ፍላጎትና ብሶት የደኅንነቱ ሜክአፕ ሳያሳምረው በቀጥታ የማግኘት እድል አላቸው። ከዚሁ የአኗኗር ዘይቤ የሚመነጭ በሚመስል ሁኔታም ሐሳባቸውን “በየአጋጣሚው” የመግለጽ ልምድ አካብተዋል።
ጋዜጠኛ ተመስገን እንዳስነበበን አቦይ ስብሐት ሁለት አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ጉዳዮች አንስተዋል። እርሳቸውም ያላቸውን አቋም በድጋሚ በሰጡት መልስ አረጋገጥዋል። የአድዋ ጉዳይ እና የቤተ ክህነት ጥገኝነት። ወደ ዝርዝሩ ከመግባቴ ከመግባቴ በፊት ስብሐት በድፍረት የተናገሯቸውና እኔም የምስማማባቸው አጠቃላይ እውነታዎች እንዳሉ ላረጋግጥ። ለዚህም ስብሐትን ማመስገን ይገባኛል። ማንም ሊቃወማቸው የማይችላቸውን አጠቃላይ እውነታዎች አስከትለው የሚያቀርቡት ዝርዝር ግን ራሳቸውንና ድርጅታቸውን ከተጠያቂነት ለማዳንና ለማድበስበስ የቀረቡ ናቸው።
1. አድዋ
የአገራችን ታሪክ እንደማንኛውም አገር በሒደት በጥናትና በምርምር የሚጠሩ ብዙ ነገሮች እንዳሉት ብዙዎቻችንን እንስማማለን። ይህ አቦይ ስብሐት የተለየ ዋጋ የከፈሉለትና የሚከፍሉበት በኢትዮጵያ ላይ የወረደ ቁጣ ወይም የምኒልክ ሴራ አይደለም። እንኳን እንደኢትዮጵያ ረጅምና ብዙ ሕዝቦች የተሳተፉበት ታሪክ ቀርቶ የትናንትናዎቹ አዳዲስ አገሮችም ከታሪክ ትርጉምና አተራረክ ውዝግብ አልወጡም። ከዚህ ውጭ ያለው አንድም ፖለቲከኞች የሚጽፉት ታሪክ ነው፤ አለዚያም “ሕዝባዊ” ታሪክ ነው። ሁለቱም ያስፈልጋሉ፣ መኖራቸውም አይቀርም፤ የታሪክ ጥናትና ምርምርን ግን አይተኩም። ሦስቱም በተቻለ መጠን በየክልላቸው ቢታቀቡም መታደል ነው። ከዚህ አጠቃላይ መነሻ አንጻር የኢትዮጵያ ታሪክ በሰፊና ጥልቅ ምርምር “እየጠራ” የሚሄድ ገጽታ እንዳለው አምናለሁ፤ ከስብሐትም ጋራ እስማማለሁ።
የአድዋው ጉዳይ አቦይ ስብሐትና ፓርቲያቸው በብሔር መነጽር ብቻ እንደገና ሊጽፉት የሚሞክሩት የኢትዮጵያ ታሪክ አንዱ ምእራፍ ነው። የነስብሐት ችግር “ከዚህ በፊት የተጻፈው ሁሉ ስሕተት ነው” የሚል መሆኑ እንጂ በተጻፈው ውስጥ ያለው እውነት በምርምር ይጣራ የሚል ጥያቄ ቢነሣ አግባብ ነው። አድዋን ልዩ የሚያደርገው ነገር ካለ እነስብሐት “የአድዋ አካበቢ ተወላጆች ስለሆንን ታሪኩን የመጻፍ መብቱ የእኛ ብቻ ነው” በሚል ስሁት እምነት የታጀበ መሆኑ ነው። እውቀት ከጠመንጃ አፈሙዝ ይመነጫል የሚለውን ብሒል ብቻ ያስታውሰናል።
ከጽሑፋቸው ለመረዳት እንደሚቻለው የአቦይ ስብሐት ችግር የታሪክን ፖለቲካ (Politics of History) ከታሪክ፣ ከታሪክ ጥናት እና አጻጻፍ ጋራ እያምታቱ መመልከታቸው ነው፤ ሆን ብለው አይመስለኝም። ስብሐት እንዲህ ይላሉ፤
“ስለኢትዮጵያ ተጽፎ የሚገኘው ታሪክ በጣም የተዛባ ቅጥ ያጣ ሕዝብ ለሕዝብ የሚያጣላ ታሪክ ነው፡፡ ተጽፎ የምናገኘው የቤተ መንግሥት ታሪክ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪክ አይደለም፡፡ በአንድ ሕዝብ አንድ ቋንቋ አንድ ሃይማኖት ወዘተ አመለካከት የተጻፈ የሕዝቦች እኩልነትን መሠረት ያላደረገ ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ችግር እየፈጠረ ያለ ነው ታሪካችን፡፡…ስለዚህ ታሪካችንን በትክክል ማስቀመጥ የሃገራዊ ደኅንነትና ልማት አንዱ መሣሪያችን ነው፡፡”
ሕዝብን “የሚያጣላው” ታሪኩ ነው ወይስ ታሪኩ የተጻፈበት መንገድ? “ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ለማረጋገጥ” የሚያስችለው የታሪክ አጠናን እና አጻጻፍ ምን አይነት ነው? ታሪካችንን “በትክክል ማስቀመጥ” ማለት ምን ማለት ነው? አንድ የታሪክ ጽሑፍ “ዴሞክራሲያዊ አንድነትን የሚያረጋግጥ” ወይም “ታሪካችንን በትክክል ያስቀመጠ” መሆኑን የሚወስነው ማነው? አንድ የታሪክ ተመራማሪ እና/ወይም ጸሐፊ ይህንን የአቦይን አስተሳሰብ እንዲከተል የሚያስገድደው ምን መነሻ አለ? አቦይ ስብሐት “ትክክል” የሚሉትን ታሪክ አንድ የታሪክ ተመራማሪ ወይም ተራ ዜጋ ባይቀበለው ምን ችግር አለው? “የቤተ መንግሥት ታሪክ” መጻፉ በራሱ ስሕተት ነው? የአቶ ስብሐት ኢቲቪ ከኢትዮጵያ ቀደምት ነገሥታት ጸሐፊዎች የባሰ አሳፋሪ “የቤተ መንግሥት ታሪክ” ጸሐፊ አይደለም እንዴ? ለመሆኑ “የቤተ መንግሥት” ታሪክ ራሱ የሕዝብ ታሪክ አካል አይደለም ወይ? “ቤተ መንግሥቱ” አንድን የታሪክ ክስተት የተመለከተበት አንጻርና የመዘገበበት/የተረከበት መንገድስ ቢሆን የአገራችን ታሪክ አካል አይደለም ወይ፣ ለታሪክ ምርምርስ እጅግ አስፈላጊ ግብአት አይደለም ወይ? በየትኛው “የፊውዳል” ማኅበረሰብ እነስብሐት የሚንቆጫቆጩበት “የሕዝብ ታሪክ” ተጽፎ ያውቃል? ታሪክን ለመጻፍ ከቤተ መንግሥቱ የተሻለ አቅምና እድል ያለው ተቋም ወይም ግለሰብ ባልነበረበት የቀድሞ ማኅበረሰብ የተለየ የታሪክ መዝገብ አለማግኘታችን ምን ያስገርማል፣ ምንስ ያናድዳል? “ሕዝቡ” አቅምና አጋጣሚ ቢፈቅድለት ኖሮ እኮ “ታሪኩን” ጽፎ ያቆይልን ነበር። ለመሆኑ “የሕዝብ ታሪክ” ማለት ምን ማለት ነው? አሁን እነአቦይ የሚያጽፉት ታሪክ አዲስ “የቤተ መንግሥት” ታሪክ አለመሆኑን ማን ይነግረናል?
ብዙ ጥልቅ ትንተና የሚሹ፣ አልፎም ወደ ታሪክ ፍልስፍና (philosophy of history) የሚጠቁሙ ጥያቄዎችን መደርደር ይቻላል። እነዚህን ጥያቄዎች በምሳሌነት የዘረዘርኩት እነአቦይ ስብሐት የሚያቀርቡት ጥያቄ “በታሪክ ፖለቲካነቱ” እንጂ በደንበኛው የታሪክ ፍልስፍናና ጥናት መስክ እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን ለመጠቆም ያህል ብቻ ነው። “ዴሞክራሲያዊ አንድነትን ለማረጋገጥ” ብሎ ታሪክን የሚያጠና እና/ወይም የሚጽፍ ባለሞያ ስለመኖሩ ሰምቼ አላውቅም፤ አዳዲሶቹ የአገራችን የታሪክ “ምሁራን” እንደዚያ ያደርጉ ከሆነ በሒደት እናየዋለን። ያን ጊዜ የታሪክ ጥናት ዘርፍ ወደ ሽምግልናና ወደፖለቲካ ይሸጋገራል።
ለአገራችን የሚበጀው እነስብሐት እጃቸውን በተቻለ መጠን ከታሪክ ጥናትና አጥኚዎች ቢሰበስቡ፤ ብዙም የማያሻሙ ጠቃሚ የታሪካችንን ገጾች ለአገራዊ ማንነታችን ማጉያነት መጠቀም (“የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ ዓመት ነው”፣ “ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ተገዝታለች” እያሉ ከመዘላበድ መቆጠብን ጨምሮ)፤ የአካዳሚክ ነጻነትን አክብሮ በታሪካችን ላይ ግልጽ ምርምሮችና ውይይቶች እንዲካሄዱ መፍቀድ፣ ከዚህም አገራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ወደ ሕዝባዊ እውቀትነት መቀየር ናቸው። ቀሪው ጉንጭ አልፋ “የታሪክ ፖለቲካ” ክርክር ነው።
2. ከቤተ ክህነት እስከ ማኅበረ ቅዱሳን
ሀ. ቤተ ከህነቱ
አቦይ ስብሐት ከተናገሩት ሁሉ ብዙ የምስማማበት ነገር ያገኘሁት ስለ ቤተ ክህነቱና ስለጳጳሳቱ የገለጹት ነው። ለ“ፍትሕ” ጋዜጣ ከሰጡት መልስ ለማስታወስ ያህል፤
- “ለሁሉም ነገር ወሳኙ ውስጣዊ ሁኔታ ስለሆነ ኦርቶዶክስ ከመንግሥት ሳይለያይ ለመቆየቱ ዋናው ተጠያቂዎች የቤተክህነት ሐላፊዎች የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ መንግሥታቱ በሁለተኛ ደረጃ ይጠየቃሉ፡፡”
- “ቤተክህነት ከመንግሥት ተጣብቆ በመቆየቱ የሃይማኖት ተቋምነቱ እየወደቀ መጥቷል፡፡ አሁንስ ሃይማኖትና ፖለቲካ በሕገ መንግሥት ደረጃ በጽኑ እምነት ከተለየበት ወዲህ ከደረሰበት ድቀት እያንሰራራ ነው ወይስ በነበረበት የጉዳት ደረጃ ነው ያለው? የአሁኑ ፓትርያርክ ሥራ ከጀመሩ ጀምሮ ስለ ቤተክህነቱ የሚወራው እጅግ በጣም ዘግናኝና አሳፋሪ የአስተዳደር ጉድለት ተነስተን ስናየው ግን በነበረበት የመዳከም ደረጃ ሳይሆን ወደ ሞት አፋፍ እየሄደ ነው የሚያሰኝ ነው፡፡”
- “ጳጳሳቱ አይረቡም ያልኩበት ምክንያት ከዚህ አጠቃላይ መርህ ብቻ ተነስቼ አይደለም፡፡ አብዛኞቹ ከድሮ ጀምረው በአቡነ ጳውሎስ አስተዳደር እንደሚያለቅሱ አውቃቸዋለሁኝ፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያለው ሥራ አልሠሩም፡፡ ለዚህ ነው አይረቡም ያልኩበት ምክንያት፡፡ አሁንም ልጨምርበትና ለእምነታቸው አልረቡም፡፡”
-
ቋንቋውና አቀራረቡ ቢለያይም በእነዚህ የአቦይ ስብሐት አጠቃላይ ምልከታዎች ላይ አለመስማማት አልችልም። በዚህ የማይስማማ ካለ አንድም የቤተ ክርስቲያኒቱን ታሪክና አሁን የደረሰችበትን አሳፋሪ ውስጣዊ ዝቅጠት የማያውቅ ነው፤ አንድም፣ እውነታውን ቢያውቅም በአደባባይ የመነገሩን ሕመም መጋፈጥ የማይፈልግ ነው፤ አንድም፣ ፈጣሪ ተአምር እንዲሰራ በመመኘት በመጽናናቱን የመረጠ ነው፤ አለዚያም የምናወራው ስለተለያዩ ተቋማት ነው ማለት ነው። ይህ የመጨረሻው ሰው ከዚህ ቀጥሎ የተጻፈውን ማንበብ አያስፈልገውም።
የድቀቱ መታሰቢያ
አቦይ ስብሐት እንዳሉት ቤተ ክርስቲያኒቱ “ከመንግሥት ጥገኝነት እንላቀቅ የሚሉ” ቆራጥ ጳጳሳትን አላፈራችም፤ ጥቂቶች ቢኖሩም በብዙሃኑ “ለእምነታቸው የማይረቡ” (ስለቋንቋው ከይቅርታ ጋራ) አበው ታፍነው ቀርተዋል። በውስጥም በውጭም ከሚያለቅሱት የሚበዙት የዚህ አበሳ ተካፋዮች ናቸው። በሃገረ ስብከቱ ሙስናን እስከመጨረሻ የተዋጋው ጳጳስ ማነው? ችግሩ ሲብስበት ስልጣኑን ትቶ ገዳም በመግባት በጸሎት ፈጣሪውን፣ በተቃውሞ ፓትርያርኩንና መንግሥትን ያስጨነቀው አባት ማነው? (መቼም ስለግብጹ አቡነ ሼኖዳ አልሰሙም አይባልም።) አቡነ መርቆሪዎስ በመንግሥት ተጽእኖና በገዛ ወንድሞቻቸው የሴራ ተባባሪነት ከሥልጣን ሲሻሩ የትኛው አባት እውነትን አደባባይ ቆሞ ተናገረ? የትኛው አባት ከመንበሩና ከክብሩ ይልቅ ለምእመኑ ሕይወት ቅድሚያ ሰጠ? ለመሆኑ አባ ጳውሎስን እንዲህ መረን የለቀቃቸው ማነው- ሲኖዶሱ አይደለም እንዴ? አባ ጳውሎስን ስለተቃወሙ ወንድሞቻቸው ሲደበደቡ፣ ሲታገቱ፣ እንደወንጀለኛ በለሊት ከቤታቸው ተወስደው ሲመረመሩ “አሁንስ በዛ” ያለው ቀናኢ አባት ማነው? በማግስቱ የጥፋቱን ፊት አውራሪ- አባ ጳውሎስን- ደጅ ለመጥናት ያልተሰበሰቡት ስንት ናቸው? ንጹሐን በአደባባይ ስለመሞታቸው አዝኖ “ነፍስ ይማር” ለማለት በኀዘነተኞቹ ቤት የተገኙ ስንት ናቸው? ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱና ስለቤተክነቱ ጥፋት በአጥቢያው (በሃገረ ስብከቱ አላልኩም) ምህላ ያዘዘ አባት አለ? ለ“ዓለም ሞቱ” የተባሉ መነኮሳትና ጳጳሳት የዚህ ዓለም ኑሮ እንደሚያሳሳን ሁሉ ለስደት የሚሽቀዳደሙት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማን ትተው ነው? ምንስ ለማግኘት ነው? ከከሰረው ፖለቲካ ጋራ እየነፈሱ በብሔር ላይ የተመሠረተ ቤተ ክርስቲያን ለመክፈት የሚሽቀዳደሙት “ያልሞቱ” ጳጳሳት በምን ሞራል መንግሥትነ ይወቅሳሉ? የስነ ምግባሩ፣ የዘረኝነቱ፣ የሙስናው…ችግር እዚህ ዘርዝረን የምንጨርሰው አይደለም። ስንቱን በመንግሥት ማሳበብ ይቻላል? ስንቱንስ ጥፋት “የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው” እያሉ ራስን ማጽናናት ይቻላል? ከዚህስ በላይ ለእምነት አለመርባት ያለ አይመስለኝም።
አሁን ከአቦይ ጋራ እንለያይ። ስብሐት የመንግሥት ተጠያቂነት በሁለተኛ ደረጃ ነው ባሉት እስማማለሁ። ሃይማኖቱን፣ ቤቱን መጠበቅ መጀመሪያ የባለቤት ፋንታ ነው። ሌባ የሚጋበዘው በባለቤቱ አቅምና ቁርጠኝነት አንጻር ነው። ይህ ግን ሌባውን ከተጠያቂነት አያድነውም። ሌባው የአቶ አቦይ መንግሥት ነው። አባ ጳውሎስ እኮ ፊት ሳያዩ አይደለም ወደዚህ ደረጃ የደሱት። “ልጆቻችን እስካሉ ምንም አንሆንም” እያሉ ጳጳሳቱን የሚያስፈራሩት እኮ ፊት አይተው ነው። አቶ መለስን ጨምሮ አባ ጳውሎስን እንደ እዳ የሚመለከቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዳሉ ይነገራል። ችግሩ ግን በዚሁ መንግሥት ውስጥ በጥቅም፣ በገንዘብና በደም የተገዙ ቀንደኛ ደጋፊዎችም አሉዋቸው። ለመሆኑ የጳጳሳቱ ድብደባና እገታ በፖሊስ ሳይጣራ የቀረው ለምንድን ነው? ይቺን የምታህል ቤተ ክርስቲያን አባቶች በአደባባይ መዋረድ መንግሥትን አይመለከተውም ነበር? ነገሩ ሌላ ነው፤ ጳውሎስ ከሙስና መሠረታቻው ሊፈናቀሉ የመሆኑ አደጋ ያሰጋቸው የመንግሥት አካላት አሉና በነፍስ ደረሱ።
የአቦይ ስብሐት መንግሥት አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያኑቱን እንደግል ንብረት ሲበውዙዋት፣ በብሔር ፖለቲካ ሲበጠብጡዋት “ችግሩ ለሕዝብ ይተርፋል” በሚል “ቅንነት” ምክር ያልሰጠው ለምንድን ነው? በተቃራኒው በምርጫ 97 ማግስት የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅሮች እስከ አጥቢያ ድረስ በፓርቲ አባላት ለሙላት የተከፈተው ዘመቻ የሕገ መንግሥቱን ቃል ኪዳን የሚያፈርስ አይደለምን? የአባ ጳውሎስ የሥልጣን ኢምፓየር ገና ሲነቃነቅ በነፍስ ደርሶ የታደገው “በአቡነ አባይ” (ይቺ ስያሜ በቤተ ክህነቱ አዋቂዎች ለአቶ አባይ ፀሐዬ የተሰጠች ነች) የተመራው ቡድን የነፍስ አድን ጣልቃ ገብነት ስሙ ምን ይባላል? ደግነቱ አቦይ ስብሐት “መንግሥት ተጠያቂ አይደለም” አላሉም። ደረጃው አያጣላንም። መቋጫውም ቤተ ክርስቲያኒቱ ከገባችበት የውደቀትና የድቀት አዙሪት ለመውጣት የምትችለው መንግሥት የድርሻውን ከተወጣ ብቻ ነው። እስከዚያ ድረስ ግን በውድቀቷ ተባብሮ ከደሙ ንጹህ መሆን እንደማይቻል ግልጽ ነው። ይህ የመንግሥት አፍራሽ ሚና በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጎልቶ ቢታይም ሌሎቹንም የሃይማኖት ተቋማት ለጥፋት እንደዳረገ አስታውሼ ወደ ቀጣዩ ጉዳይ ልለፍ።
ለ. ማኅበረ ቅዱሳን
አቦይ ስብሐት ስለ ቤተ ክህነቱና ስለቤተ ክርስቲያኒቱ ሲዘረዝሩ በአጭሩ ጠቀስ ያደረጉት ሌላው ጉዳይ ስለማኅበረ ቅዱሳን ያላቸው “ቀጥተኛ ትዝብት” ነው። ነገሩ “እግረ መንገድ” የተነሣ ቢመስልም የአቶ አቦይ መንግሥት “ሁለትና ከዚያ በላይ ሆናችሁ በተሰበሰባችሁበት ሁሉ እገኛለሁ” የሚል አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ቃል ኪዳን እንዳለው ለማሳየት ጥሩ ምሳሌ መሆኑን በቅርበት ስለማውቅ ላልፈው አልፈለኩም። አቶ ስብሐት እንዲህ ይላሉ በ “ፍትሕ” ጋዜጣ ላይ፤
“እኔ እንደሚመስለኝ ባለኝ ቀጥተኛ ትዝብትም ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክህነት እዳ ነው፡፡ ቀጥተኛ ትዝብቴ፣ የቤተክህነትን አስተዳደር ለማሻሻል መጠነኛ እንቅስቃሴ ሲጀመር ገንቢ ተራ ከመጫወት አፍራሽነት ይበዛበታል፡፡ አልፎ አልፎም ብልሽት እያዩ ዝምታ ይበዛል፡፡ የተቃዋሚ ፖለቲካ መድረክነትም እንዳለበት ይወራል፡፡ ይህ ትክክል ከሆነ እጅግ በጣም የሃይማኖት ብቻ ሳይሆን የሃገር ስርዓት ማለት ሕገ መንግሥት የመጣስ ክህደት ነው፡፡”
ይህን የአቦይን አነጋገር የማኅበረ ቅዱሳን የወቅቱ ዋና ጸሐፊ ከሆነው ከመምህር ሙሉጌታ ኀ/ማርያም ሰሞነኛ ቃለምልልስ ጋራ ስታገናኙት ነገሩ የበለጠ ሳቢ (interesting) ይሆንባችኋል። ሙሉጌታ እንዲህ ይላል፤
“…እነአባ ሰረቀ ብርሃን [አንድ የቤተ ክርስቲያኒቱ መምሪያ ሐላፊ ናቸው] አገር ውስጥ በተቃዋሚነት ይከሱናል። ውጪ ስንሄድ ደግሞ ‘የአቡነ ጳውሎስ ካድሬዎች’ ተብለን የወቀሳ ናዳ ይወርድብናል። ማኅበረ ቅዱሳን የምንም ፖለቲካ አራማጅ አይደለም። እውነቱን ለመናገር አብዛኞቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የኢሕአዴግ ደጋፊና አባላት ናቸው። በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው የምኅበረ ቅዱሳን ሥራ አስፈጻሚ መሆን አይችልም፤ አባል ሆኖ መቀጠል ግን ይችላል።…” (“ዕንቁ” መጽሔት የሰኔ 2003 እትም፤ ሙሉውን ቃለ መጠይቅ እዚህያገኛሉ።)
አቦይ ስብሐት “እንደዋዛ” “ይነገራል” በማለት የገለጹት ክስ “በመነገር” የሚቆም ሳይሆን መንግሥታቸው አቋም የያዘበት ጉዳይ ነው። ነገሩ በአጭሩ እንዲህ ነው። በምርጫ 97 ማግስት ድንጋጤ ያርበተበው ፓርቲ/መንግሥት በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማሰርና በመፍታት ስራውን አላጠናቀቀም ነበር። ይህን ተከትሎ እስከ ገጠር ቀበሌ ድረስ “ለምን ተሸነፍን? የጦስ ዶሮዎቹን አድኑ” የሚል አውጫጪኝ ተካሂዶ ነበር። ይህ በየክልኩ የደኅንነት አካሎችና በፓርቲው መዋቅር (አንድም ሁለትም ናቸው) የተካሄደው “ጥናት” አስደናቂ ውጤቶችን አስገኝቷል። ከእነዚህ ውጤቶች አንዱ “በአማራ እና በደቡብ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ኢሕአዴግ ለደረሰበት ሽንፈት፣ ተቃዋሚዎች ላገኙት ድጋፍ ሚና ከነበራቸው አካሎች አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን ነው” የሚል ነበር። ይህ ደግሞ በሹክሹክታ የተነገረ፣ በለሆሳስ የተወሳ ጉዳይ አልነበረም። የየክልል አካላት ባዘጋጁት ሪፖርት ጥራዝ ተካቶ ለውይይት የቀረበ፣ የክትትል ትእዛዝም የተሰጠበት ነው። ይህ መረጃም ለማኅበሩ እንዲደርሰው ተደርጓል። ኮፒ ለማድረግ ባይፈቀድልኝም በወቅቱ ሪፖርቱን ከሁለቱም ወገን አግኝቼ በማኪያቶ አወራርጄዋለሁ።
ከዚያ በኋላ ማኅበሩ የደኅንነቱ አንድ ኢላማ ሆነ። አባ ጳውሎስና ጋሻ ጃግሬዎቻቸውም የበኩላቸውን ሐላፊነት ለመወጣት በቤተ ክህነቱ ስር ማንም የማያውቀው በወቅቱ የቤተ ክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ የሚመራ “ኮሚቴ” አቋቁመው ሪፖርት አቀረቡ። ለማን አትሉም? ለመንግሥት የደኅነነት አካል። የሪፖርቱ “ግኝት” “ማኅበረ ቅዱሳን ቅንጅት ነው” የሚል ዝርዝሩ ሲታይ ከባልቴት ወሬ የማይሻል ዝንቅ ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱ በአገራዊ እርቅ ያላት ሚና በ“ሐመር” መጽሔት መጻፉ የተቃዋሚ ደጋፊነት ማሳያ ሆኖ ዛሬ ድረስ የሚሰማው ወቀሳ ስሩ ከዚያ ይጀምራል። ለማንኛውም ማኅበሩ በማጉያ መነጽር ይመነጠር ገባ። በኋላም በሚያስተዛዝብ የታሪክ ግምገማ “የቅንጅት ደጋፊዎች” የተባሉ አንዳንድ አገልጋዮች በውሃ ቀጠነ ፊት ተነሡ፣ ከቦታቸው ተነሡ። ምጸቱንና ታሪካዊ ስላቁን ፍጽም ለማድረግም የማኅበሩን ዋና ጸሐፊ ለመሾም የብሔር ማንነት በውስጠ ታዋቂ ለመጀመሪያ ጊዜ “መመዘኛ” እንዲሆን ተደረገ። “ክፉ ቀንን ለማለፍ” የተደረገ “ማጎንበስ” ቢመስልም መርሕ አልባ ስሕተት ሆኖ ተመዘገበ። በተቃራኒው ደግሞ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ምን ያህን ያገጠጠ እንደሆነም ያሳያል።
የማኅበሩ አመራር በአንድ በኩል በአባ ጳውሎስ በሌላ በኩል በመንግሥት የመጣበትን ጫና ለማሳለፍ የመረጠው መንገድ ከሞላ ጎደል “ትልቁን ሽፍታ ማስደሰት” ሆነ። እኔ እስከማውቀው ማኅበሩ በተቋም ደረጃ የትኛውንም ፓርቲ ወይም የፖለቲካ አቋም ደግፎ ወይም ተቃውሞ አያውቅም። ይብሱንም ብዙዎቹ አባላቱ “ፖለቲካን” እንደሐጢአት የመመልከት አዝማሚያ ይታይባቸው እንደነበረ በእርግጠኝነት አውቃለሁ። እንኳን ስለፖለቲካ ስለቤተ ክህነት ችግር ማውራት የማይፈልጉም ጥቂት አልነበሩም። ለማንኛውም ይህ እውነታ ማኅበሩን አልታደገውም።
ከዳር ቆሞ ነገሮችን በቅርበት ለሚመለከት ማኅበረ ቅዱሳን እና አባ ጳውሎስ (ከነሠራዊታቸው) መንግሥትን አለማስቀየም ብቻ ሳይሆን ማስደሰትም ጭምር የሕልውናቸው መሠረት ሊሆን እንደሚችል ማመናቸውን ይታዘባል። የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ሰሞኑን የገለጸው “እውነት”ም በዚህ ማእቀፍ ውስጥ የሚታይ ነው። ዋና ጸሐፊው “ማኅበረ ቅዱሳን የምንም ፖለቲካ አራማጅ አይደለም።” ብሎ ማቆም ሲችል “እውነቱን ለመናገር አብዛኞቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የኢሕአዴግ ደጋፊና አባላት ናቸው።” ያለን ለምን ይሆን? ይህ ንግግር እውነት “እውነት” ነው? “እውነት ምንድን ነው?” አለ መጽሐፉ።
ጸሐፊው ይህን ያለን ከምን ተነሥቶ ይሆን? “አሁን ባለንበት አገራዊ ተጨባጭ ሁኔታ በየሥራ በስኩ በሚደርስበት ጫና የኢሕአዴግ አባል ያልሆነ ሰው ቁጥሩ ጥቂት ነው፤ ይህ ደግሞ በማኅበሩ አባለትም ዘንድ መንጸባረቁ አይቀርም” ሊለን ፈልጎ ይሆን? እንደዚያስ ቢሆን ተገዶ አባል የሆኑ ሰዎችን ወደው ያደረጉት አስመስሎ “አብዛኞቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የኢሕአዴግ ደጋፊና አባላት ናቸው” ማለትን ምን አመጣው? “የኢሕአዴግ አባልና ደጋፊ የሆኑ በመካከላችን አሉ” በማለትና “አብዛኞቹ የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የኢሕአዴግ ደጋፊና አባላት ናቸው” በማለት መካከል ያለው ርቀት ስንት ነው? እነአቦይን እንዲህ በአደባባይ ተናዞ ካላስደሰቱ እረፍት ማግኘት ስለማይቻል ይሆን? እርግጥ የአቦይ ስብሐት ወቀሳም እኮ “ማኅበሩ በፖለቲካ ይገባል” አይደለም፤ “የተቃዋሚ ፓርቲ መድረክነት ይታያል” የሚል ነው። ችግሩ ተቃዋሚን “መደገፉ” ነው። የሕገ መንግሥት “ክህደቱም” እርሱ ነው፤ ተቃዋሚን መደገፍ።
አቡነ ጳውሎስ እና መንግሥት በተለያየ ምክንያት የሚጠረጥሩትና የሚፈሩት ማኅበር የድኀረ ምርጫ 97 አፈና አንድ ማሳያ ከመሆን አላመለጠም። ችግሩ ግን መንግሥትም ሆነ አባ ጳውሎስ ማኅበሩን የሚፈሩት በተሳሳተ ምክንያት መሆኑን ገና አልተረዱትም። ምናልባትም ደግሞ ሁለቱም (መንግሥት እና አባ ጳውሎስ) ባላቸው ከፍተኛ የተጣራጣሪነትና የበቀለኝነት ልምድ ማኅበሩን “ሳይጨርሱት” እንደማይለቁት መስጋት ይቻላል። ማኅበሩ ካለው ኅብረተሰብን ለመለወጥ የሚያስችል እምቅ አቅም አንጻር የሁለቱም ፍርሃት ለመረዳት የሚከብድ አይደለም። “የምስራቹ” ማኅበሩ ይህን የማድረግ ተልእኮም፣ ራእይም፣ አመራርም ሆነ ብቃት የሌለው መሆኑ ነው። አቦይ ስብሐት ካሉትም በላይ የመፍትሔው አካል የመሆን ጉዞን ወደመጨረሱ በመቃረብ ላይ የሚገኝ፣ በእንግሊዝኛ የችግሩ አካል ለመሆን (ቤተ ክህነቱን ለመቀላቀል) በማዝገም ላይ ያለ ነው። የኦቦይ ስብሐትን ጽሑፍ ተከትሎ ከማኅበሩ አመራሮች ገሚሶቹ የአቦይን “ቡራኬ” ደጅ መጥናት መጀመራቸው የቤተ ክህነቱ ዘይቤ ግልባጭ ነው። እንደዚህም ቢሆን ግን ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያኒቱና ለአገርም ጭምር ያበረከታቸውን አስተዋጽኦዎች አሳንሶ መመልከት ስሕተት ይሆናል። በቤተ ክህነቱ አያያዝ ቢሆን ያለፉት 20 ዓመታት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ቀብር በይፋ በተፈጸመ ነበር ማለት አስተዋጽኦውን ማጋነን አይመስለኝም።
አቦይ ስብሐት በሁለተኛ ደረጃ ያስቀመጡት የመንግሥት መልከ ብዙ ጣልቃ ገብነት በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በሌሎች ማኅበራዊ ተቋማት ውስጥ በማስከተል ላይ ያለው ቀውስ ሰፊ ዘገባ የሚወጣው ነው፤ በአጭር ጊዜ የሚፈታም አይደለም። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ በፖለቲካና በሃይማኖት ጉዳዮች ጥናት ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች አካባቢውን እንዳይዘነጉት እንጂ በሒደት ብዙ እንደሚያስነብቡን ተስፋ አደርጋለሁ።
ከ90 በመቶ የማያንሱት የማኅበሩ አባሎች ይህን ሁሉ የአስተዳደር ውጣ ውረድና ፖለቲካ አያውቁም፣ አይረዱም። ቢያውቁም “በአይናፋርነት” ማለፍን ይመርጣሉ። በየዋህነት የሚያገለግሉት ፈጣሪ ቅንነታቸውንና እንባቸውን እንደማይዘነጋው ተስፋዬ ነው።
(ማስታወሻ፤ በቤተ ክህነቱ እና በማኅበረ ቅዱሳን ጉዳዮች ላይ በሰነዘርኩት ሐሳብ ቅር የሚሰኝ ቢኖር ብዙ አልገረመም። አንዳንዱ የቋንቋ አገላለጼ ጠንከር ያለ ቢመስልም ከችግሩ የሚያንስ እንጂ የሚበልጥ አይደለም። ከዚያም በላይ ጽሑፉ ባነሳቸው ሐሳቦች ላይ ማተኮሩ የበለጠ ይጠቅማል እላለሁ።)
When do we start to think and do things in our own way and our own pace? Sibhat has brought this issue of Adwa Victory, the Church and ‘Mahibere Kidusan’ for his own purpose and now we have to follow suit and do the chorus.
The TPLF’ites are possessed with the backward politics of TPLF which is infected with bigotry and narrow mindedness. From the start they took the goal of separating Tigray from the rest of Ethiopia which in itself was absurd and nonsense. Tigray can never be a self-sufficient region let alone a separate nation and everyone knows this fact except these maniacs. That is why we still see this looting and uneconomic investments in the region at the expense of the rest of the Ethiopian people. Their understanding of history is very distorted and fictional, only to treat their inferiority complex and serve their myopic interests. When the Derg collapsed, as a result of a long and deep process of alienation and rejection by the Ethiopian people, the mutiny of the army and the international political crisis in the communist camp, these people got the chance to fill the vaccum in the political power. This very situation made them even megalomaniacal as they consider themselves as victors. They stayed in power for the past 20 years, recklessly playing with fire while the rest of the Ethiopian people is making every effort to keep the country stable and peaceful. However, they took this as a sign of their superiority and increasingly become arrogant and bigoted. Now they are trying to rewrite history to fit this phantom of theirs. In their mind the past history of Ethipia doesn’t go with their current ‘status’ and ‘achievement’, therefore it has to be changed. The current situation should be the standard against which all the past experience and the future course of events must be measured.
Please do not bring issues just because some TPLF leader happen to talk about it. The event of Adwa has been written and told by many people – disinterested foreigners, jouranlists and Ethiopians, who witnessed it with their own eyes.
As to Sibhat and co. I only ask them why did they abandon their very goal of making Tigray a separate nation after so much sacrifice? As to ‘Mahibere Kidusan’, they shouldn’t be our topic now. Perhaps, the regime doesn’t like to see any organized and functioning entity in the country, except of course EPRDF.
As the old saying goes ‘history is written by the victor’ and hence the reason for the huge contention that arises, say between Liberation fronts and unitary supporters etc… For example, I remember being thought at school that the largest ethnic group in Ethiopia migrated from Madagascar as recently as 150 years ago. This was the official history thought at Ethiopian schools, even to Oromo’s as many of you might remember. Now, I really don’t know how many people believe this fairytale but my suspicion is quite a lot of people who are not Oromo’s are still under that impression. Above all, although this issue might be insignificant for some, believing this story and telling your fellow countrymen that they are people who don’t have a shared history going back thousands of years, in their own land is tantamount to major declaration of negative intentions. The other issue is the fact that this kind of history was concocted in order to delegitimize and spread suspicion and exploitation. One of the reasons our country has been in the vicious circle of war and destruction. Hence the major reason why history is said to be very powerful in determining a country’s fate, so making sure we have a well documented, scientific and forensic history ironed out amongst all vested interests for the benefit of all rather than the very few elite is the only way forward.
Since I don’t have detailed knowledge about the church, I will reserve from making a comment. However, I would like to say how much I admire people who stand up and fighting for what they believe and how I really can’t stand the self centred, selfish vested interests who run abroad with their family at a drop of a hat and try to dictate there wish on our brave people who chose to remain and rebuild their country.
mesfine, thanks for your information. please always write. i always long for your writings.
now, it is better to follow up MK thoroughly. we shall not let it to finalize its run like haimanot abew. of course God keep it safe as there is no heretic position inside.
surely MK has been changing the attitude of hundreds of thousands of students of higher institution for good.
if we believe that MK has an ability to change people’s attitude we have to give attention. we have to report corruptions, wrong thoughts etc that are created inside it.
now, i believe openness is required as our lord said.
sorry for my English, thank you.
Your analysis is good except that of MK.The General Secratary of MK,Dn.Mulugeta said that because of our government policy most of the higher education students and government employees are either members of EPRDF or supporters of EPRDF,since most of MK members belong to these group ,it is true.Also,Mulugetas words are not only these some of them are removed on the editing process.If they were printed it will confront MK with the government.your point on the selection of GS of MK is completely wrong.MK has vision that is to work for the heavenly kingdom not for earthly one.Your conclusion is also completely Wrong,MK is still strong and it will accomplish its mission since God is with us.
Nice try Meles, (ewinetim Meles)!!! You deliberately made a wrong reference to the Oromo history thaught in Ethiopian schools to divert the discussion. Not only that, you want to open a debate between the so called ‘Nefitegnas’ and Oromos. Ayi Woyanewoch!! Kenante blay awaki yelem????
We are not talking here about supporting any political party’s stance but hard facts about our country’s past. Whether we like it or not these facts are not going to go away unless we confront them head on and debunk fairy tells and demystify myth that affected and continue to affect our collective psyche. Blaming the messenger instead of debating the message in order to reach consensus is a truly bad strategy. Especially since the facts will never go away by burying our head in the sand.
I will also be truly glad if blaming this or that group can change the facts. But unfortunately the blame game we have been playing and want to continue to play will only make things worst not better. Surly the most obvious strategy is confronting facts head on and rewriting our collective history together as suggested by Mesfin Negash. Learning from our best history, so we can build on it even a better future, and also our bad history so we can never repeat it. How else are we meant to deal with our past?
first of all i want to express my appreciation for your argumentative,well-evidenced and lucid writing style….please keep it up…keep on writing….writing…
one important evidence is the number of woyanne cadres watching out every sngle second to gush up their ‘comments’
what can i say about the reformulation of new history by tplf bandas as their ideology is shaped by (esp.legesse zenawi )the past dictators such as Machiavelli,Joseph Stalin who did attempt to change the course of history and wrote it unsuccessfully in his own way….
unless united strongly and react accordingly much more ruin and damage incurred to the church-’bete kihnet’
not only betekihnet but also every single civic and social institution including the education system ….have been infiltrated and destroyed and made ineffective by the regime-Mk is no exception…taking the nature of the government,socio-economic and political environment (ethnicity for example) into consideration mk appears to be stronger.
hence i don’t agree with your conclusion that it is going to be part of the problem of the church.rather you and every body should stand with the association in this very moment of time to save the church and mk itself..
You are such a phony. You are posturing as a genuine and concerned scholar. Tell me; which history course has taught you that the Oromos come from Madagascar 150 years ago? The 1850′s were the period where the Oromos reached their peak in the Ethiopian political power.
Whenever challenged, you Woyanes always try to bring a very sensitive subject in order to enrage the Oromos and the people in the south, to cultivate hatred and division. I think that time has passed my friend.
Your response exemplifies what has been and still is wrong on how we deal with our disagreements. Lack of maturity, intransigence, obduracy and inflexibility is the chosen method to deal with each others thought. If that is what will solve our problem, I say good luck! Let’s hope we will all live to see where this mulishness will take us.