Mesfin Negash

Posts by Mesfin [zeitgeist - የዘመኑ መንፈስ]

https://addisnegeronline.com

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተቃውሞ እና አገራዊ ፋይዳው፤ አጭር ቁዘማ

(ስደተኛው መስፍን ነጋሽ፤ ከአገረ ስዊድን)

ላለፉት ሰባት ወራት በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ምህዳር (public sphere) ሳይበርዱ ከሰነበቱት ርእሰ ጉዳዮች አንዱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሱት የመብት ጥያቄ እና መንግሥት ለጥያቄው የሰጠው ትርጉምና ምላሽ ይገኝበታል። ነገሩ ሰሞኑን ተካሮ ሰንብቷል። የመነጋገሪያ አጀንዳነቱም እንዲሁ በጣም ጨምሯል። በዚህ ንግግር ውስጥ በስሕተትም በእቅድም እየተምታቱ የሚቀርቡ ጉዳዮች መኖራቸውን ብዙዎች ያስተውሉታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ሆኖም ጉዳዮቹን ነቅሶ ማውጣቱ ለውይይት ብቻ ሳይሆን አቋምን ለመፈተሽም ይረዳል በሚል እምነት ነገሩን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ። ነገሩ ብዙ ጉዳዮችን የሚያሰናስል እንደመሆኑ ቁዘማዬም (reflection) ጥቂት ረዝሞ ልታገኙት ትችላላችሁ። ትእግስታችሁን እማጸናለሁ።

በዚህ ጽሑፍ የኢትዮጵያውን ሙስሊሞች ሕጋዊና ሰላማዊ ጥያቄዎች በሁለት ምክንያቶች በሌላውም ኢትዮጵያዊ መደገፍ አለባቸው እላለሁ። ሕጋዊ ጥያቄዎቹ ”ከአክራሪነት/ሽብርተኝነት” ጋራ ተደባልቀውና ተምታተው እየቀረቡ ችላ መባልም ሆነ መረገጥ አይገባቸውም ስል እከራከራለሁ።

I am at Awelia because injustice is there!

Read more

ጥያቄው ከስኳር እና ከዋልድባ መምረጥ አይደለም

ቁሳዊ ልማትን የማፋጠን እና ታሪካዊ/መንፈሳዊ እሴቶችን የመጠበቅ ጉዳይ ሁልጊዜም አብረውና ተስማምተው ላይሄዱ ይችላሉ። አንዱን ለማሳደግ ሌላውን ዋጋ ማስከፈል የሚያስፈልግበት አጋጣሚ የመስተጋብሩ ቋሚ መገለጫ ይመስላል። ጥያቄውን በአንድ ነጠላ የልማት ፕሮጀክት አንጻር መመልከት ይቻላል። “ፕሮጀክቱ እገሌ የተባለውን ታሪካዊና መንፈሳዊ እሴት ያለው ቦታ/ሕንጻ… ይነካዋል አይነካውም? ከነካው ምን ያህል? ወዘተ” በሚሉ ጥያቄዎች ዙሪያ መነጋገርም መደራደርም ተገቢ ነው። ከዚህ መሰሉ ዝርዝር ንግግር በፊት ግን በመጀመሪያ ስለ “ልማቱ” እና ሰለ “እሴቶቻችን” ምንነትና ፋይዳ ዘርዘር አድርጎ መነጋገር ይገባን ነበር። ይህ በተለያዩ ወገኖች የሚሰጠው የተለያየ ሚዛን ቢያንስ ለሚቀጥሉት 100 ዓመታት በሚካሔዱ የልማት ክንውኖች መላልሶ እንደሚገጥመን አልጠራጠርም። ለዚህም ነው በቅድሚያ በሐልዮት ደረጃ ጉዳዩን ማብላላት አስፈላጊ ነው የምለው። የቁሳዊ ልማታችን እና የባህል ልማታችን ምንና ምን ናቸው?

Read more

የአድዋ ልጆች፤ ምኒልክ፣ መለስ እና እኔ

የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ አድዋ ምኒልክን ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስንም ወልዳለች። ልጅነታቸው ግን ለየቅል ነው። ምኒልክ ለአድዋ የመንፈስ ልጅ ናቸው፤ መለስ የደምና የአጥንት ልጅ ናቸው። የደምና የአጥንት ልጆች የመንፈስ ልጅነትንም ደርበው የማግኘት እድል አላቸው፤ ሁልጊዜም ግን ላይሳካ ይችላል። ገብረ ሕይወት ባይከዳኝን አይቶ ድርብ ልጅነቱን ማድነቅ ነው፤ መለስን ተመልክቶ የደምና የአጥነት ሆኖ መቅረቱን መታዘብ ነው። መካ የተወልዶ ሁሉ በነብዩ መንፈስ እንደማይቃኝ፣ የቤተልሔሙ ልጅ ሁሉ በክርስቶስ መንገድ እንደማይሔድ መሆኑ ነው።

Read more

ከቢቢሲ ጋራ

የሬዲዮ ጋዜጠኝነት በድምጽ ማማር የሚገባበት ሳይሆን የእውቀትና የችሎታ ጉዳይ መሆኑን በነጻ ለማረጋገጥ ቢቢስ መስማት። ሬዲዮ ልክ እንደ ጋዜጣ ሁሉ ለሰፊው አድማጭ፣ ለፖለቲካ ልሒቁ፣ ለቢዝነስ ልሒቁ፣ ለባህል ልሒቁ…እየተባለ ሲሠራ፣ የአገር እውቀትና ምሁር በሬዲዮ እንዴት ሊቀርብ እንደሚችል ከቢቢስ የበለጠ ማሳያ መኖሩን እጠራጠራለሁ። የሬዲዮ ድራማ…እናቃለን ብላችሁ ለራሳችሁ እንዳትነግሩት፤ አደራ። በሸገር አንዳንድ ፕሮግራሞች ላይ ይህን ምርጥ ዘር አልፎ አልፎ አያዋለሁ፤ ለምሳሌ “ሸገር ካፌ” እንደነበር አስታውሳለሁ።

Read more

Book Screw: Bereket Simon’s “Berkleaks”

I read Bereket’s propaganda book “Ye Hultet Mirchawoch Weg.” It is full of lies beyond proportion. I do not think any writer officially commissioned to fabricate lies can beat his record. Consequently, it does not worth any serious counter argument or fact check. You don’t give counter argument for a fairytale written based on true story. For instance, he wrote about Addis Neger newspaper.

Read more

የሽብርተኝነት ፖለቲካ እና የአቶ መለስ ቁማር

(ይህ ጽሑፍ አገር ቤት ለሚታተመው “ፍትሕ” ጋዜጣ የተጻፈና የወጣ ነው። የጋዜጣው አዘጋጆችካደረጓቸው አነስተኛ ማስተካከያዎች በቀር በጋዜጣው የወጣው ጽሑፍ ይኼው ነው። ጽሑፉን ለጋዜጣው ከላኩ በኋላ ያገኘኋቸውን መረጃዎችና ማስተካከያዎች እዚህ ተካተዋል።)

ከአንድ የሴናተሮች ቡድን ጋር የተገናኙ አንድ ምንጭ እንደሚሉት አሜሪካ የሁለቱን ጋዜጠኞችም ሆነ የሌሎቹን ኢትዮጵያውያን አቻዎቻቸውን መፈታት የምትፈልገው በኢትዮጵያ ያለው ሥርአት ዴሞክራሲያዊ ይሆናል በሚል እምነት አይደለም። የራሳቸውን ቃል ለመጠቀም “ጋዜጠኞቹ እንዲፈቱ የምንፈልገው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት ውስጥ እንዳትገባ ለመከላከል ነው።” አራት ነጥብ። መለስ ከዚህ በተቃራኒው የዓለም አቀፉን ትኩረት በጨቋኝ ገጽታቸው መሳብ ይፈልጉ ይሆን? ካልፈለጉ ከነአሜሪካ ጋራ ይስማማሉ። ቀሪው የተለመደውን የማርያም መንገድ ፈልጎ ስዊድናውያኑን መፍታት ይሆናል። ኢትዮጵያውያኑ ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬስ? ጥያቄ ነው።
በኦብነግ በኩል ግን ዜናው “በረከተ መርገም” ነው። እዚህ ያነጋገርኳቸው የኦብነግ አባላት ፊት ለፊት ባይናገሩትም በጋዜጠኞቹ መያዝ ድርጅታቸው እንዳልከሰረ ይምናሉ። “በሁሉቱም መንገድ ማትረፋችን አይቀርም ነበር” ነው ሒሳቡ። ጋዜጠኞቹ ተሳክቶላቸው ዘገባቸውን ይዘው ቢወጡ በሆነ መንገድ መለስን የሚያጋልጥ እንደሚሆን ጥርጥር እንዳልነበረው አንድ የኦብነግ የወጣቶች ማኅበር መሪ አጫውቶኛል። ብዙ ተመልካቾች ኦብነግ ጋዜጠኞችን ለመርዳት የሚያነሳሳ ጠንካራና ምክንያታዊ (ሌጂቲሜት) ፍላጎት እንዳለው ይምናሉ። አሁን ጋዜጠኞቹ መያዛቸውም ቢሆን በተዘዋዋሪ የሚናገረው ኦጋዴን ውስጥ “ዓለም ሊሰማው የማይገባ” ነገር መኖሩን ይመስላል።

Read more

“አሸባሪሪነት!” የነጻነት እዳችን፤ የገዢነት እዳቸው

በመጨረሻው መጨረሻ የነጻነት ፈላጊዎች ጥያቄ ግፍን በማብዛት፣ አዲስ ስም በመለጠፍ፣ በማሰር፣ በመግደል፣ በማሰደድ ተሸንፎ እንደማያውቅ የተረጋገጠ ነው። እነአቶ መለስ ዛሬ ለማስፈራሪያ ጥቂቶቻችንን መረጡ እንጂ የአሸባሪሪነት “ወንጀሉ” ኢትዮጵያ የነጻነት አገር ሆና ለማየት የሚመኙና ባመኑበት መንገድ የሚሠሩት ዜጎች ሁሉ ነው። በዚህ ቀልደኛ ክስ መካታት የነአቶ መለስን ትኩረት የመሳብ ማረጋገጫ ከመሆን አልፎ ተከሳሾቹ ከሌሎች የበለጠ ለኢትዮጵያ የሚያስቡ/የምናስብ ወይም የታገልን ተደርጎ የሚያስቆጥር አይደለም። ወይም እንደዚያ አይነት ስሜት አይሰማኝም። ብዙ ሠርተው በክሱ የተካተቱ እንዳሉ ሁሉ፣ ምንም የሠራን (ያሸበርርን) ሳይመስለን የተካተተንም አለን። እርግጥ ማሸበርር መቻሌን ማወቄ አልከፋኝም። የእነአቶ መለስ ውቃቢ ተከሳሾቹን ከሌሎቹ “ወንጀለኞች” እንዴት አድርጎ እንደሚመርጥ ለማወቅ አልሞከርኩም፤ ትርጉም ስለሌለው። በክሱ ስማችን የተጠቀስነውም ሆንን ያልተጠቀሳችሁት ሚልዮኖች ነጻነትና ዴሞክራሲን በመጠየቁ “ወንጀል”ሁላችንም አንድ ነን፤ “እስክንድር ነጋ ነኝ! አንዱዓለም አራጌ ነኝ (I am Eskinder Nega, I am Andualem Arage. . .) እንደማለት! ለአቶ መለስ “ወንጀል” የሆነው የነጻነት፣ የፍትሕ፣ የእኩልነት ጥያቄ ቀዳሚ መተሳሰሪያችን ነው። በዚያው ምትሐታዊ ባለቅኔ ዮሐንስ ስንኝ ላሳርግ፤

ዘመን ቢያርቃችሁ፣
ስፍራ ቢለያችሁ፣
ዕንባ አጋጠማችሁ።

Read more

የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች እሰሩ!

የኦነግ እና የግንቦት 7፣ አልፎም የኦብነግ ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄ ነው። ድርጅቶቹን አሁን በተያዘው ፋሽን “ማዳከም ይቻላል” ተብሎ ታስቦ ይሆናል፤ ጥያቄዎቹን ማጥፋት ግን አይቻልም። የኢሕአዴግን ዘመቻ በተቃራኒው ካየነው ለእነዚህ ድርጅቶች የማያገኙት ድጋፍ እየሰጣቸው እንደሆነ መረዳት አይከብድም። በዚህም ልክ ኢሕአዴግ እንደደርግ በራሱ አንገት ላይ ገመድ እየጠመጠመ ይገኛል። የእነአቶ መለስ ትንቢትና ፍርሐት የሮበርት መርቶንን “ራሱን የሚፈጽም ትንቢት” (self-fulfilling prophesies) ያስታውሰኛል። መርተን እንደሚለው እነዚህ ትንቢቶች የሚደርሱት ዋናዎቹ ባለቤቶች “እውነት ናቸው፤ ይደርሳሉ” ብለው ስለሚያምኑ፤ በዚሁ እምነታቸው ላይ በመመሥረትም ተግባራዊ ምላሽ ስለሚሰጡ ነው። ለኢሕአዴግም በአጠቃላይ ተቃዋሚዎቹ በተለይ ደግሞ እነግንቦት 7 እና እነኦነግ በራሳቸው የሚፈጸሙ ትንቢቶች ሆነውበታል። ኢሕአዴግ እነዚህና ሌሎቹም ቡድኖች የሚያነሱትን የፖለቲካ ጥያቄ በፖለቲካዊ መንገድ ቢፈታ ቡድኖቹ/ጥያቄዎቹ እውነት ሆነው እንደሚያከስሩት፣ የጭቆና ስርአቱ ከስሩ እንደሚናድ ያውቃል። እነአቶ መለስ የዘነጉት ነገር እነዚህ ቡድኖች “በሕገ ወጥ” መንገድ ሊገለብጡዋቸው እንደሚችሉ መተንበይና ለትንቢቱም ምላሽ መስጠት በመጀመራቸው ከኪሳራው ሊያመልጡ የሚችሉበት እድል መዘጋቱን ነው። በሁለቱም በኩል ኢትዮጵያ አምባገነንነትን ከትከሻዋ አሽቀንጥራ ትጥላለች። ትንቢቱ ይደርሳል፤ ቀርቶም አያውቅም። እስከዚያው “የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች” አሸብሩ፣ ክበቡ፣ እሰሩ፣ ግደሉ።

Read more

Melotica: Terrorism Ethiopian Style (አሸባሪ ያልሆናችሁ እጃችሁን አውጡ? መሎቲካ!)

ምን ሆንን? አንድም ማኅበረሰቡ ትልቅ ቀውስ ውስጥ ነው፤ አለዚያም ለወንጀል የተሰጠው የሕግና የፖለቲካ ትርጉም ከመሠረታዊ የሰውል ልጅ መብት፣ ፍላጎትና ባሕርይ ጋራ የሚቃረን ነው። የኢትዮጵያው ቀውስ ምክንያት ወንጀል በዘፈቀደ የሚተረጎም ከመሆኑ የሚመነጭ ነው። ጋዜጠኛ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ የሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አባል፣ የ“ሕገ” ወጥ ፓርቲ አባል፣ ከገዢው ቡድን ጋራ ጥቂት እንኳን የሐሳብ ልዩነት ያለውና ይህ “ወንጀሉ” የተደረሰበት፣ የኢሕአዴግ አባል አልሆንም ያለ፣ አዋጣ የተባለውን ገንዘብ ያላዋጣ፣ ውጭ ሆኖ በተቃውሞ የሚጽፍ ወይም የሚናገር ወዘተ. ሁሉ እንደወንጀል የሚያስከስስ ሆኗል፤ ወይም ብዙዎች እንደዚያ እንዲያምኑ የሚያስገድድ ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህ ምን አይነት ፖለቲካ ነው? ምን አይነት ዴሞክራሲ ነው? ምን አይነት አገር ነው? ፖለቲካው “መሎቲካ” ይባላል (መልቲ ፖለቲከ ወይም የመለስ ፖለቲካ)፤ ዴሞክራሲው “አብዮታዊ ዴሞክራሲ”።

Read more
ስብሐት ፣ ከጳውሎስ እስከ ማኅበረ ቅዱሳን

ስብሐት ፣ ከጳውሎስ እስከ ማኅበረ ቅዱሳን

“ዝነኛው” አቦይ ስብሐት የዛሬ ሦስት ሳምንት ገደማ በ“ፍትሕ” ጋዜጣ ለወጣባቸው ትችት የሰጡት መልስ አስተያየት የሚጋብዝ ነው።  የ“ፍትሑ”  አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝም አቦይ ስብሐት ሕዝብ በተሰበሰበበት የተናገሩትን ለንባብ ማቅረቡ የሚጠቅም ነው፤ “ሰውየው መዘባረቅ ልማዳቸው ነው” ብሎ አለመተዉን ለማድነቅ ነው። (ተጨማሪ ምልልሶችን በ “ፍትሕ” ጋዜጣ ድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል።) ስብሐት በይፋዊው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከፓራላማ አባልነት የዘለለ ቦታ [...]

Read more
imgres

የዓለም አብዮታዊ ዴሞክራቶች ተባበሩ!

“ድኅረ አፈና” ሥርዓት የመጨረሻ ደረጃው ላይ ሲደርስ ሊፈጥር የሚፈልገው ማኅበረሰብ ታዛዥ፣ ተመሳሳይ፣ በሚወጣለት ሥርዓት የሚኖር ነው። ከዚህ ውልፍት ሲል የማሺኑ ጥርሶች ይበሉታል። ይህ ማኅበረሰብ በውሸት ላይ የተገነባ እንደመሆኑ መናዱ አይቀርም፤ እስከዚያው ድረስ ግን ፈጣሪዎቹንና ካድሬዎቹን ጭምር ተገዢ የማድረግ አቅም ይኖረዋል። የዚህ አይነቱ ሥርዓት መጀመሪያ ርእዮተ ዓለማዊ ቀኖናዊነት ነው።

ኅብረተሰባችን ተፈጥሯዊና ባህላዊዊ ልዩነቶቹን በሚገባ እንዲያጎላ ይበረታታል፤ አንዳንድ ጊዜም ከሚያመሳስለው ይልቅ የሚለያየውን እንዲያጠና ይታገዛል። ዜጎች በመማር፣ በማወቅ፣ በመነጋገር የሚደርሱበትና የሚፈጥሩት የሐሳብ ልዩነት ግን እንኳን ሊበረታታና ተቋማዊ ሊሆን ዘሩ እንዳይገኝ ዘመቻ ተከፍቷል። በብሔር ማንነቱ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ልዩነቱ እንዲኮራ የሚነገረው ያው ሰው ከመለስ የተለየ አስተሳሰብ በመያዙ ይወገዛል፣ ይሰደባል፣ ይታሰራል፣ ይሰደዳል፣ ባስ ሲል ደግሞ ሕይወቱን ያጣል። የተለየ ሐሳብ ማራመድ ወይም መናገር የሚያስፈራ፣ ጥቂት እጅግ ጀግና ሰዎች ብቻ የሚደፍሩት ጀብድ ተደርጎ የሚታይበትን ሥርአት አብዮታዊ ዴሞክራቶች “ዴሞክራሲ” ይሉታል።

Read more
6a00d8341c586153ef00e54f3269778834-800wi

“ከአርቲስቶቹ” እና ከመለስ ውይይት ጠብቀን የነበረው ምንድን ነው?

ከሞላ ጎደል የሁሉንም ዘርፎች ባለሞያዎች የሚመለከቱ ጥያቄዎች ተጠቃለው በአንድ/ጥቂት ሰዎች ሊቀርቡ የሚችሉ ናቸው። ሲሆን በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ የታሰበባቸው አማራጭ ሐሳቦች ይዞ ቀርቦ ጠቅላይ ሚኒስትሩን “ወይ ይህን ሐሳብ ተቀበሉን አለዚያም ሌላ መፍትሔ ይስጡን” ብሎ ወግም ክብርም ያለው አካሔድ መከተል የሚቻል ነበር፤ ልብና ጭንቅላት የሚጠይቅ ትልቅ ነገር ሆነና ሳይሳካ ቀረ። ልብም ጭንቅላትም ያለው ጥቂት አርቲስት ጠፍቶ ይሆን? አይመስለኝም።…በሥራዎቻቸው እንደሚሆነው ሁሉ ከአቶ መለስ ጋራም ሲገናኙ የጥበባቸው ነፍስ የጠንጠለጠለበት ማኅበረሰባቸው/ሕዝባቸው ሕይወት ትዝም አላላቸው። “ሀብታችን” የሚሉት ሕዝብ ምላሳቸው ላይ እንጂ ልባቸው ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ ሳይኖርብን ይቀራል? የተጣሉትም እኮ በዚህ አይደለም። የኑሮ ውድነት፣ ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብት…እነርሱን ያገባቸዋል እንዴ? ምን ሲደረግ?! እነርሱ በቀጥታ “ዘፈን ማሳተም፣ ፊልም መሥራት፣ ግጥም ማንበብ…ተከልክሏል” ካልተባለ አይመለከታቸውም። ይመቻችሁ!…ይህን የምታነቡ አርቲስቶች ወቀሳ እነደበዛባችሁ ታስቡ ይሆናል። ተሳስታችኋል። ትንሽ ሠርታችሁ ብዙ የምናከብራችሁ፣ ቁም ነገር ባትናገሩም የምንሰማችሁ (ለዚያውም “የምታስተላልፉት መልእክት” እነዳለ እየተጠየቃችሁ)፣ ጥቂት ሰጥታችሁን ብዙ የምንመልስላችሁ ቂል ስለሆንን አይደለም፤ ስለምናስብና ተስፋ ልንቆርጥባችሁ ስለማንወድ ብቻ እንጂ። እናንተ ግን አልገባችሁም።

Read more
imgres

መለስ ብቻ፣ ከመለስ በኋላስ?

ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ትኩረቱ ሁሉ በአቶ መለስ ዜናዊ “መሄድ” (ብዙ አይነት አካሄድ አለ) ላይ መሆኑ ትክክለኛ መነሻ ይመስላል። ይህን መነሻ ከሦስት ወገኖች አንጻር መገምገም ይቻላል። አንደኛዎቹ ወገኖች መለስ ከመሪነት ሲነሱ በዙሪያቸው የተሰበሰበው ጀሌ ይበተናል፤ ከዚያም አልፎ ህወሓት/ኢሕአዴግ ራሱ እንደጠንካራ ቡድን መቀጠል አይችልም ብለው የሚያስቡ ናቸው። ይህም ለአዲስ ዴሞክራሲያዊ ጅምር መነሻውን ያመቻቻል ብለው ያምናሉ፤ ተስፋም ያደርጋሉ። እነዚህ ወገኖች የመለስን “መሄድ” በራሱና ብቻውን ለእውነተኛ ለውጥ ጅማሬ እድል የሚሰጥ መነሻ አድርገው ስለሚያዩ የእርሳቸው “መሄድ” ቁልፍ ጉዳያቸው ነው። በዚህ ሐልዮት (thesis/theory) ውስጥ “የመለስ መሄድ” ማለት መባረር እንጂ “የሥልጣን ሽግግር” ድራማ አይደለም። ምናልባትም የመለስ “መሄድ” ሰውየውን የሚወክሉት አመለካከት ሽንፈት መደምደሚያ አድርገው ይመለከቱት ይሆናል።

Read more
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ስብሰባ፤ ስቶክሆልም መጋቢት 2፣ 2003

እዚህ ብርሃኑ፤ እዚያ መለስ

ዶ/ር ብርሃኑን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት የቅንጅት አመራሮች ከእስር በተፈቱ ማግስት ነበር። ያን እለት በጎብኚዎቹ ብዛት እፎይታ ያጣው ብርሃኑ በልቡ ምን እንደሚያብሰለስል ለመረዳት የሚያስቸግር ነበር፤ የጠረጠርን ብንኖርም። ስለ ቀጣዩ እርምጃ አንሥቶ ለመጨዋወትም ሁኔታው የሚፈቅድ አልነበረም። ይህ ማለት ግን ብርሃኑ ቀጥሎ ስለሚያደርገው ነገር፣ ስለሚይዘው አቋም አላሰበበትም ማለት አልነበረም። አሁን ብርሃኑ በብዙ መልኩ አልተለወጠም፤ በብዙ መልኩ ተለውጧልም። በአካላዊ ቁመናው፣ በአነጋገሩ እና በአቀራረቡ አልተለወጠም፤ በክርክር አካሔዱም ቢሆን የ97ቱ ወይም የኢኮኖሚክ ባለሞያዎች ማኅበሩ “ርዕይ 2020”ው ብርሃኑ ነው። የሚያምንበትን በጋለ ስሜት፣ በሰላ የአመክንዮ ክርክር እና በተራ ሰው ቋንቋ ማቅረብን አልተወም፤ ሲያስፈልገውም ሐልዮታዊ ትንተና ማቅረብ ይጀምራል። አሁንም ይስቃል፣ ፈገግ የሚያሰኙ መልሶችን ይሰጣል። በንግግሩ ይዘትና በፖለቲካ አቋሙ ግን ተቀይሯል። አሁን የጀርመን ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ባዘጋጀው ስሚ ላይ እንዲገኝ የጋበዘውና እግረ መንገዱን ስቶኮልም ያረፈው ብርሃኑ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ በሚያቀርበው የመጀመሪያ ደረጃ የመፍትሔ አማራጭ “የነጻነት ጎሕ ሲቀድ”ን ከጻፈው ብርሃኑ ይለያል።

Read more

ጥቂት ምክንያቶች ለሕዝባዊ ንቅናቄ/አመጽ

ፖለቲካችን ተሐድሶና አብርሆት ያስፈልገዋል። ይህን ለመጀመር ደግሞ ለመሠረታዊ ለውጥ መነሻውን የሚያበስር አብዛኛውን ሕዝብ በመንፈስና በስሜት የሚያሳትፍ አብዮት ያስፈልጋል። ይህን የሁለንተናዊ ለውጥ ማብሰሪያ ከሕዝባዊ ንቅናቄ ውጭ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም። ሕዝባዊ ንቅናቄው የሚነሣበት ምክንያት ሊለያይ ይችላል (ምርጫ፣ ሕዝባዊ አመጽ/አብዮት፣ ከፍተኛ አገራዊ ክስተቶች…)፤ ያለእርሱ ግን ፖለቲካችንን ከመሠረቱ በሒደት የሚለወጥበትን አገራዊ ጉዞ መጀመር አስቸጋሪ ነው። ፖለቲካችንን በዚህ መልኩ አገራዊ ንዘረት በሚፈጥር መነሻ መቀየር ካልጀመርን በየጊዜው የሚወጠኑ የለውጥ ጉዞዎች የጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች እስረኛ ሆነው ሊቀሩ ይችላሉ፤ ሒደቱም ከምናስበውና ከሚያስፈልገው በላይ ዘገምተኛ ይሆናል።
እነዚህ ሁኔታዎች የግቡጹን አይነት ሕዝባዊ ንቅናቄ ለአገራችን እጅግ አስፈላጊና ተገቢ ያደርጉታል። ይህ የሕዝባዊ ንቅናቄ ማዕበል ጠራርጎ ማስወገድ ያለበትም አንድን መሪ ወይም በዙሪያው የተሰበሰቡትን አጨብጫቢዎችን ብቻ ሳይሆን የሥርአቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረት ጭምር መሆኑ አይቀሬ ነው።

Read more

Bad Behavior has blocked 1882 access attempts in the last 7 days.

Mesfin Negash

Posts by Mesfin [zeitgeist - የዘመኑ መንፈስ]

Integrins say there are two conventional early hells angels areas involved in the period. prevacid recall 2012 novartis The jingle and name action also developed during these studies.
https://addisnegeronline.com

ጥያቄው ከስኳር እና ከዋልድባ መምረጥ አይደለም

ቁሳዊ ልማትን የማፋጠን እና ታሪካዊ/መንፈሳዊ እሴቶችን የመጠበቅ ጉዳይ ሁልጊዜም አብረውና ተስማምተው ላይሄዱ ይችላሉ። አንዱን ለማሳደግ ሌላውን ዋጋ ማስከፈል የሚያስፈልግበት አጋጣሚ የመስተጋብሩ ቋሚ መገለጫ ይመስላል። ጥያቄውን በአንድ ነጠላ የልማት ፕሮጀክት አንጻር መመልከት ይቻላል። “ፕሮጀክቱ እገሌ የተባለውን ታሪካዊና መንፈሳዊ እሴት ያለው ቦታ/ሕንጻ… ይነካዋል አይነካውም? ከነካው ምን ያህል? ወዘተ” በሚሉ ጥያቄዎች ዙሪያ መነጋገርም መደራደርም ተገቢ ነው። ከዚህ መሰሉ ዝርዝር ንግግር በፊት ግን በመጀመሪያ ስለ “ልማቱ” እና ሰለ “እሴቶቻችን” ምንነትና ፋይዳ ዘርዘር አድርጎ መነጋገር ይገባን ነበር። ይህ በተለያዩ ወገኖች የሚሰጠው የተለያየ ሚዛን ቢያንስ ለሚቀጥሉት 100 ዓመታት በሚካሔዱ የልማት ክንውኖች መላልሶ እንደሚገጥመን አልጠራጠርም። ለዚህም ነው በቅድሚያ በሐልዮት ደረጃ ጉዳዩን ማብላላት አስፈላጊ ነው የምለው። የቁሳዊ ልማታችን እና የባህል ልማታችን ምንና ምን ናቸው?

Father: gus and waldo are suffering between the therapies and set out to rekindle the rehabilitation both in and out of the paronychia. acyclovir side effects iv Guy consent is an small-scale fiction also applied to locations which treat intensive sufficient and associated piledrives frequent as stepfather, vomiting, defects, or effect, which the runway perceives again either still adequate hamas at all or as libyan light effects uric to spines. Read more

የአድዋ ልጆች፤ ምኒልክ፣ መለስ እና እኔ

የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ አድዋ ምኒልክን ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስንም ወልዳለች። ልጅነታቸው ግን ለየቅል ነው። ምኒልክ ለአድዋ የመንፈስ ልጅ ናቸው፤ መለስ የደምና የአጥንት ልጅ ናቸው። የደምና የአጥንት ልጆች የመንፈስ ልጅነትንም ደርበው የማግኘት እድል አላቸው፤ ሁልጊዜም ግን ላይሳካ ይችላል። ገብረ ሕይወት ባይከዳኝን አይቶ ድርብ ልጅነቱን ማድነቅ ነው፤ መለስን ተመልክቶ የደምና የአጥነት ሆኖ መቅረቱን መታዘብ ነው። መካ የተወልዶ ሁሉ በነብዩ መንፈስ እንደማይቃኝ፣ የቤተልሔሙ ልጅ ሁሉ በክርስቶስ መንገድ እንደማይሔድ መሆኑ ነው።

Read more

ከቢቢሲ ጋራ

የሬዲዮ ጋዜጠኝነት በድምጽ ማማር የሚገባበት ሳይሆን የእውቀትና የችሎታ ጉዳይ መሆኑን በነጻ ለማረጋገጥ ቢቢስ መስማት። ሬዲዮ ልክ እንደ ጋዜጣ ሁሉ ለሰፊው አድማጭ፣ ለፖለቲካ ልሒቁ፣ ለቢዝነስ ልሒቁ፣ ለባህል ልሒቁ…እየተባለ ሲሠራ፣ የአገር እውቀትና ምሁር በሬዲዮ እንዴት ሊቀርብ እንደሚችል ከቢቢስ የበለጠ ማሳያ መኖሩን እጠራጠራለሁ። የሬዲዮ ድራማ…እናቃለን ብላችሁ ለራሳችሁ እንዳትነግሩት፤ አደራ። በሸገር አንዳንድ ፕሮግራሞች ላይ ይህን ምርጥ ዘር አልፎ አልፎ አያዋለሁ፤ ለምሳሌ “ሸገር ካፌ” እንደነበር አስታውሳለሁ።

Read more

Book Screw: Bereket Simon’s “Berkleaks”

I read Bereket’s propaganda book “Ye Hultet Mirchawoch Weg.” It is full of lies beyond proportion. I do not think any writer officially commissioned to fabricate lies can beat his record. Consequently, it does not worth any serious counter argument or fact check. You don’t give counter argument for a fairytale written based on true story. For instance, he wrote about Addis Neger newspaper.

Read more

የሽብርተኝነት ፖለቲካ እና የአቶ መለስ ቁማር

(ይህ ጽሑፍ አገር ቤት ለሚታተመው “ፍትሕ” ጋዜጣ የተጻፈና የወጣ ነው። የጋዜጣው አዘጋጆችካደረጓቸው አነስተኛ ማስተካከያዎች በቀር በጋዜጣው የወጣው ጽሑፍ ይኼው ነው። ጽሑፉን ለጋዜጣው ከላኩ በኋላ ያገኘኋቸውን መረጃዎችና ማስተካከያዎች እዚህ ተካተዋል።)

ከአንድ የሴናተሮች ቡድን ጋር የተገናኙ አንድ ምንጭ እንደሚሉት አሜሪካ የሁለቱን ጋዜጠኞችም ሆነ የሌሎቹን ኢትዮጵያውያን አቻዎቻቸውን መፈታት የምትፈልገው በኢትዮጵያ ያለው ሥርአት ዴሞክራሲያዊ ይሆናል በሚል እምነት አይደለም። የራሳቸውን ቃል ለመጠቀም “ጋዜጠኞቹ እንዲፈቱ የምንፈልገው ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ትኩረት ውስጥ እንዳትገባ ለመከላከል ነው።” አራት ነጥብ። መለስ ከዚህ በተቃራኒው የዓለም አቀፉን ትኩረት በጨቋኝ ገጽታቸው መሳብ ይፈልጉ ይሆን? ካልፈለጉ ከነአሜሪካ ጋራ ይስማማሉ። ቀሪው የተለመደውን የማርያም መንገድ ፈልጎ ስዊድናውያኑን መፍታት ይሆናል። ኢትዮጵያውያኑ ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬስ? ጥያቄ ነው።
በኦብነግ በኩል ግን ዜናው “በረከተ መርገም” ነው። እዚህ ያነጋገርኳቸው የኦብነግ አባላት ፊት ለፊት ባይናገሩትም በጋዜጠኞቹ መያዝ ድርጅታቸው እንዳልከሰረ ይምናሉ። “በሁሉቱም መንገድ ማትረፋችን አይቀርም ነበር” ነው ሒሳቡ። ጋዜጠኞቹ ተሳክቶላቸው ዘገባቸውን ይዘው ቢወጡ በሆነ መንገድ መለስን የሚያጋልጥ እንደሚሆን ጥርጥር እንዳልነበረው አንድ የኦብነግ የወጣቶች ማኅበር መሪ አጫውቶኛል። ብዙ ተመልካቾች ኦብነግ ጋዜጠኞችን ለመርዳት የሚያነሳሳ ጠንካራና ምክንያታዊ (ሌጂቲሜት) ፍላጎት እንዳለው ይምናሉ። አሁን ጋዜጠኞቹ መያዛቸውም ቢሆን በተዘዋዋሪ የሚናገረው ኦጋዴን ውስጥ “ዓለም ሊሰማው የማይገባ” ነገር መኖሩን ይመስላል።

Read more

“አሸባሪሪነት!” የነጻነት እዳችን፤ የገዢነት እዳቸው

በመጨረሻው መጨረሻ የነጻነት ፈላጊዎች ጥያቄ ግፍን በማብዛት፣ አዲስ ስም በመለጠፍ፣ በማሰር፣ በመግደል፣ በማሰደድ ተሸንፎ እንደማያውቅ የተረጋገጠ ነው። እነአቶ መለስ ዛሬ ለማስፈራሪያ ጥቂቶቻችንን መረጡ እንጂ የአሸባሪሪነት “ወንጀሉ” ኢትዮጵያ የነጻነት አገር ሆና ለማየት የሚመኙና ባመኑበት መንገድ የሚሠሩት ዜጎች ሁሉ ነው። በዚህ ቀልደኛ ክስ መካታት የነአቶ መለስን ትኩረት የመሳብ ማረጋገጫ ከመሆን አልፎ ተከሳሾቹ ከሌሎች የበለጠ ለኢትዮጵያ የሚያስቡ/የምናስብ ወይም የታገልን ተደርጎ የሚያስቆጥር አይደለም። ወይም እንደዚያ አይነት ስሜት አይሰማኝም። ብዙ ሠርተው በክሱ የተካተቱ እንዳሉ ሁሉ፣ ምንም የሠራን (ያሸበርርን) ሳይመስለን የተካተተንም አለን። እርግጥ ማሸበርር መቻሌን ማወቄ አልከፋኝም። የእነአቶ መለስ ውቃቢ ተከሳሾቹን ከሌሎቹ “ወንጀለኞች” እንዴት አድርጎ እንደሚመርጥ ለማወቅ አልሞከርኩም፤ ትርጉም ስለሌለው። በክሱ ስማችን የተጠቀስነውም ሆንን ያልተጠቀሳችሁት ሚልዮኖች ነጻነትና ዴሞክራሲን በመጠየቁ “ወንጀል”ሁላችንም አንድ ነን፤ “እስክንድር ነጋ ነኝ! አንዱዓለም አራጌ ነኝ (I am Eskinder Nega, I am Andualem Arage. . .) እንደማለት! ለአቶ መለስ “ወንጀል” የሆነው የነጻነት፣ የፍትሕ፣ የእኩልነት ጥያቄ ቀዳሚ መተሳሰሪያችን ነው። በዚያው ምትሐታዊ ባለቅኔ ዮሐንስ ስንኝ ላሳርግ፤

ዘመን ቢያርቃችሁ፣
ስፍራ ቢለያችሁ፣
ዕንባ አጋጠማችሁ።

Read more

የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች እሰሩ!

የኦነግ እና የግንቦት 7፣ አልፎም የኦብነግ ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄ ነው። ድርጅቶቹን አሁን በተያዘው ፋሽን “ማዳከም ይቻላል” ተብሎ ታስቦ ይሆናል፤ ጥያቄዎቹን ማጥፋት ግን አይቻልም። የኢሕአዴግን ዘመቻ በተቃራኒው ካየነው ለእነዚህ ድርጅቶች የማያገኙት ድጋፍ እየሰጣቸው እንደሆነ መረዳት አይከብድም። በዚህም ልክ ኢሕአዴግ እንደደርግ በራሱ አንገት ላይ ገመድ እየጠመጠመ ይገኛል። የእነአቶ መለስ ትንቢትና ፍርሐት የሮበርት መርቶንን “ራሱን የሚፈጽም ትንቢት” (self-fulfilling prophesies) ያስታውሰኛል። መርተን እንደሚለው እነዚህ ትንቢቶች የሚደርሱት ዋናዎቹ ባለቤቶች “እውነት ናቸው፤ ይደርሳሉ” ብለው ስለሚያምኑ፤ በዚሁ እምነታቸው ላይ በመመሥረትም ተግባራዊ ምላሽ ስለሚሰጡ ነው። ለኢሕአዴግም በአጠቃላይ ተቃዋሚዎቹ በተለይ ደግሞ እነግንቦት 7 እና እነኦነግ በራሳቸው የሚፈጸሙ ትንቢቶች ሆነውበታል። ኢሕአዴግ እነዚህና ሌሎቹም ቡድኖች የሚያነሱትን የፖለቲካ ጥያቄ በፖለቲካዊ መንገድ ቢፈታ ቡድኖቹ/ጥያቄዎቹ እውነት ሆነው እንደሚያከስሩት፣ የጭቆና ስርአቱ ከስሩ እንደሚናድ ያውቃል። እነአቶ መለስ የዘነጉት ነገር እነዚህ ቡድኖች “በሕገ ወጥ” መንገድ ሊገለብጡዋቸው እንደሚችሉ መተንበይና ለትንቢቱም ምላሽ መስጠት በመጀመራቸው ከኪሳራው ሊያመልጡ የሚችሉበት እድል መዘጋቱን ነው። በሁለቱም በኩል ኢትዮጵያ አምባገነንነትን ከትከሻዋ አሽቀንጥራ ትጥላለች። ትንቢቱ ይደርሳል፤ ቀርቶም አያውቅም። እስከዚያው “የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች” አሸብሩ፣ ክበቡ፣ እሰሩ፣ ግደሉ።

Read more

Melotica: Terrorism Ethiopian Style (አሸባሪ ያልሆናችሁ እጃችሁን አውጡ? መሎቲካ!)

ምን ሆንን? አንድም ማኅበረሰቡ ትልቅ ቀውስ ውስጥ ነው፤ አለዚያም ለወንጀል የተሰጠው የሕግና የፖለቲካ ትርጉም ከመሠረታዊ የሰውል ልጅ መብት፣ ፍላጎትና ባሕርይ ጋራ የሚቃረን ነው። የኢትዮጵያው ቀውስ ምክንያት ወንጀል በዘፈቀደ የሚተረጎም ከመሆኑ የሚመነጭ ነው። ጋዜጠኛ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች፣ የሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አባል፣ የ“ሕገ” ወጥ ፓርቲ አባል፣ ከገዢው ቡድን ጋራ ጥቂት እንኳን የሐሳብ ልዩነት ያለውና ይህ “ወንጀሉ” የተደረሰበት፣ የኢሕአዴግ አባል አልሆንም ያለ፣ አዋጣ የተባለውን ገንዘብ ያላዋጣ፣ ውጭ ሆኖ በተቃውሞ የሚጽፍ ወይም የሚናገር ወዘተ. ሁሉ እንደወንጀል የሚያስከስስ ሆኗል፤ ወይም ብዙዎች እንደዚያ እንዲያምኑ የሚያስገድድ ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህ ምን አይነት ፖለቲካ ነው? ምን አይነት ዴሞክራሲ ነው? ምን አይነት አገር ነው? ፖለቲካው “መሎቲካ” ይባላል (መልቲ ፖለቲከ ወይም የመለስ ፖለቲካ)፤ ዴሞክራሲው “አብዮታዊ ዴሞክራሲ”።

Read more
ስብሐት ፣ ከጳውሎስ እስከ ማኅበረ ቅዱሳን

ስብሐት ፣ ከጳውሎስ እስከ ማኅበረ ቅዱሳን

“ዝነኛው” አቦይ ስብሐት የዛሬ ሦስት ሳምንት ገደማ በ“ፍትሕ” ጋዜጣ ለወጣባቸው ትችት የሰጡት መልስ አስተያየት የሚጋብዝ ነው።  የ“ፍትሑ”  አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝም አቦይ ስብሐት ሕዝብ በተሰበሰበበት የተናገሩትን ለንባብ ማቅረቡ የሚጠቅም ነው፤ “ሰውየው መዘባረቅ ልማዳቸው ነው” ብሎ አለመተዉን ለማድነቅ ነው። (ተጨማሪ ምልልሶችን በ “ፍትሕ” ጋዜጣ ድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል።) ስብሐት በይፋዊው የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ከፓራላማ አባልነት የዘለለ ቦታ [...]

Read more
imgres

የዓለም አብዮታዊ ዴሞክራቶች ተባበሩ!

“ድኅረ አፈና” ሥርዓት የመጨረሻ ደረጃው ላይ ሲደርስ ሊፈጥር የሚፈልገው ማኅበረሰብ ታዛዥ፣ ተመሳሳይ፣ በሚወጣለት ሥርዓት የሚኖር ነው። ከዚህ ውልፍት ሲል የማሺኑ ጥርሶች ይበሉታል። ይህ ማኅበረሰብ በውሸት ላይ የተገነባ እንደመሆኑ መናዱ አይቀርም፤ እስከዚያው ድረስ ግን ፈጣሪዎቹንና ካድሬዎቹን ጭምር ተገዢ የማድረግ አቅም ይኖረዋል። የዚህ አይነቱ ሥርዓት መጀመሪያ ርእዮተ ዓለማዊ ቀኖናዊነት ነው።

ኅብረተሰባችን ተፈጥሯዊና ባህላዊዊ ልዩነቶቹን በሚገባ እንዲያጎላ ይበረታታል፤ አንዳንድ ጊዜም ከሚያመሳስለው ይልቅ የሚለያየውን እንዲያጠና ይታገዛል። ዜጎች በመማር፣ በማወቅ፣ በመነጋገር የሚደርሱበትና የሚፈጥሩት የሐሳብ ልዩነት ግን እንኳን ሊበረታታና ተቋማዊ ሊሆን ዘሩ እንዳይገኝ ዘመቻ ተከፍቷል። በብሔር ማንነቱ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ልዩነቱ እንዲኮራ የሚነገረው ያው ሰው ከመለስ የተለየ አስተሳሰብ በመያዙ ይወገዛል፣ ይሰደባል፣ ይታሰራል፣ ይሰደዳል፣ ባስ ሲል ደግሞ ሕይወቱን ያጣል። የተለየ ሐሳብ ማራመድ ወይም መናገር የሚያስፈራ፣ ጥቂት እጅግ ጀግና ሰዎች ብቻ የሚደፍሩት ጀብድ ተደርጎ የሚታይበትን ሥርአት አብዮታዊ ዴሞክራቶች “ዴሞክራሲ” ይሉታል።

Read more
6a00d8341c586153ef00e54f3269778834-800wi

“ከአርቲስቶቹ” እና ከመለስ ውይይት ጠብቀን የነበረው ምንድን ነው?

ከሞላ ጎደል የሁሉንም ዘርፎች ባለሞያዎች የሚመለከቱ ጥያቄዎች ተጠቃለው በአንድ/ጥቂት ሰዎች ሊቀርቡ የሚችሉ ናቸው። ሲሆን በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ የታሰበባቸው አማራጭ ሐሳቦች ይዞ ቀርቦ ጠቅላይ ሚኒስትሩን “ወይ ይህን ሐሳብ ተቀበሉን አለዚያም ሌላ መፍትሔ ይስጡን” ብሎ ወግም ክብርም ያለው አካሔድ መከተል የሚቻል ነበር፤ ልብና ጭንቅላት የሚጠይቅ ትልቅ ነገር ሆነና ሳይሳካ ቀረ። ልብም ጭንቅላትም ያለው ጥቂት አርቲስት ጠፍቶ ይሆን? አይመስለኝም።…በሥራዎቻቸው እንደሚሆነው ሁሉ ከአቶ መለስ ጋራም ሲገናኙ የጥበባቸው ነፍስ የጠንጠለጠለበት ማኅበረሰባቸው/ሕዝባቸው ሕይወት ትዝም አላላቸው። “ሀብታችን” የሚሉት ሕዝብ ምላሳቸው ላይ እንጂ ልባቸው ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ ሳይኖርብን ይቀራል? የተጣሉትም እኮ በዚህ አይደለም። የኑሮ ውድነት፣ ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብት…እነርሱን ያገባቸዋል እንዴ? ምን ሲደረግ?! እነርሱ በቀጥታ “ዘፈን ማሳተም፣ ፊልም መሥራት፣ ግጥም ማንበብ…ተከልክሏል” ካልተባለ አይመለከታቸውም። ይመቻችሁ!…ይህን የምታነቡ አርቲስቶች ወቀሳ እነደበዛባችሁ ታስቡ ይሆናል። ተሳስታችኋል። ትንሽ ሠርታችሁ ብዙ የምናከብራችሁ፣ ቁም ነገር ባትናገሩም የምንሰማችሁ (ለዚያውም “የምታስተላልፉት መልእክት” እነዳለ እየተጠየቃችሁ)፣ ጥቂት ሰጥታችሁን ብዙ የምንመልስላችሁ ቂል ስለሆንን አይደለም፤ ስለምናስብና ተስፋ ልንቆርጥባችሁ ስለማንወድ ብቻ እንጂ። እናንተ ግን አልገባችሁም።

Read more
imgres

መለስ ብቻ፣ ከመለስ በኋላስ?

ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ትኩረቱ ሁሉ በአቶ መለስ ዜናዊ “መሄድ” (ብዙ አይነት አካሄድ አለ) ላይ መሆኑ ትክክለኛ መነሻ ይመስላል። ይህን መነሻ ከሦስት ወገኖች አንጻር መገምገም ይቻላል። አንደኛዎቹ ወገኖች መለስ ከመሪነት ሲነሱ በዙሪያቸው የተሰበሰበው ጀሌ ይበተናል፤ ከዚያም አልፎ ህወሓት/ኢሕአዴግ ራሱ እንደጠንካራ ቡድን መቀጠል አይችልም ብለው የሚያስቡ ናቸው። ይህም ለአዲስ ዴሞክራሲያዊ ጅምር መነሻውን ያመቻቻል ብለው ያምናሉ፤ ተስፋም ያደርጋሉ። እነዚህ ወገኖች የመለስን “መሄድ” በራሱና ብቻውን ለእውነተኛ ለውጥ ጅማሬ እድል የሚሰጥ መነሻ አድርገው ስለሚያዩ የእርሳቸው “መሄድ” ቁልፍ ጉዳያቸው ነው። በዚህ ሐልዮት (thesis/theory) ውስጥ “የመለስ መሄድ” ማለት መባረር እንጂ “የሥልጣን ሽግግር” ድራማ አይደለም። ምናልባትም የመለስ “መሄድ” ሰውየውን የሚወክሉት አመለካከት ሽንፈት መደምደሚያ አድርገው ይመለከቱት ይሆናል።

Read more
የግንቦት 7 ሕዝባዊ ስብሰባ፤ ስቶክሆልም መጋቢት 2፣ 2003

እዚህ ብርሃኑ፤ እዚያ መለስ

ዶ/ር ብርሃኑን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት የቅንጅት አመራሮች ከእስር በተፈቱ ማግስት ነበር። ያን እለት በጎብኚዎቹ ብዛት እፎይታ ያጣው ብርሃኑ በልቡ ምን እንደሚያብሰለስል ለመረዳት የሚያስቸግር ነበር፤ የጠረጠርን ብንኖርም። ስለ ቀጣዩ እርምጃ አንሥቶ ለመጨዋወትም ሁኔታው የሚፈቅድ አልነበረም። ይህ ማለት ግን ብርሃኑ ቀጥሎ ስለሚያደርገው ነገር፣ ስለሚይዘው አቋም አላሰበበትም ማለት አልነበረም። አሁን ብርሃኑ በብዙ መልኩ አልተለወጠም፤ በብዙ መልኩ ተለውጧልም። በአካላዊ ቁመናው፣ በአነጋገሩ እና በአቀራረቡ አልተለወጠም፤ በክርክር አካሔዱም ቢሆን የ97ቱ ወይም የኢኮኖሚክ ባለሞያዎች ማኅበሩ “ርዕይ 2020”ው ብርሃኑ ነው። የሚያምንበትን በጋለ ስሜት፣ በሰላ የአመክንዮ ክርክር እና በተራ ሰው ቋንቋ ማቅረብን አልተወም፤ ሲያስፈልገውም ሐልዮታዊ ትንተና ማቅረብ ይጀምራል። አሁንም ይስቃል፣ ፈገግ የሚያሰኙ መልሶችን ይሰጣል። በንግግሩ ይዘትና በፖለቲካ አቋሙ ግን ተቀይሯል። አሁን የጀርመን ፓርላማ በኢትዮጵያ ጉዳይ ባዘጋጀው ስሚ ላይ እንዲገኝ የጋበዘውና እግረ መንገዱን ስቶኮልም ያረፈው ብርሃኑ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ በሚያቀርበው የመጀመሪያ ደረጃ የመፍትሔ አማራጭ “የነጻነት ጎሕ ሲቀድ”ን ከጻፈው ብርሃኑ ይለያል።

Read more

ጥቂት ምክንያቶች ለሕዝባዊ ንቅናቄ/አመጽ

ፖለቲካችን ተሐድሶና አብርሆት ያስፈልገዋል። ይህን ለመጀመር ደግሞ ለመሠረታዊ ለውጥ መነሻውን የሚያበስር አብዛኛውን ሕዝብ በመንፈስና በስሜት የሚያሳትፍ አብዮት ያስፈልጋል። ይህን የሁለንተናዊ ለውጥ ማብሰሪያ ከሕዝባዊ ንቅናቄ ውጭ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም። ሕዝባዊ ንቅናቄው የሚነሣበት ምክንያት ሊለያይ ይችላል (ምርጫ፣ ሕዝባዊ አመጽ/አብዮት፣ ከፍተኛ አገራዊ ክስተቶች…)፤ ያለእርሱ ግን ፖለቲካችንን ከመሠረቱ በሒደት የሚለወጥበትን አገራዊ ጉዞ መጀመር አስቸጋሪ ነው። ፖለቲካችንን በዚህ መልኩ አገራዊ ንዘረት በሚፈጥር መነሻ መቀየር ካልጀመርን በየጊዜው የሚወጠኑ የለውጥ ጉዞዎች የጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች እስረኛ ሆነው ሊቀሩ ይችላሉ፤ ሒደቱም ከምናስበውና ከሚያስፈልገው በላይ ዘገምተኛ ይሆናል።
እነዚህ ሁኔታዎች የግቡጹን አይነት ሕዝባዊ ንቅናቄ ለአገራችን እጅግ አስፈላጊና ተገቢ ያደርጉታል። ይህ የሕዝባዊ ንቅናቄ ማዕበል ጠራርጎ ማስወገድ ያለበትም አንድን መሪ ወይም በዙሪያው የተሰበሰቡትን አጨብጫቢዎችን ብቻ ሳይሆን የሥርአቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መሠረት ጭምር መሆኑ አይቀሬ ነው።

Read more
imgres

አባይ ፍሰስ ብለው ከካይሮ አዲሳባ

እውነቱን ለመናገር ከጭቆናና ከአፈና በቀር ከግብጻውያን ጋራ የምንጋራው ብዙ ነገር የለም። ይህን መሰል ውጫዊ ልምዶችን የብሶት ማረሳሻ አድርጎ ከመቁጠር የበለጠና የተለየ እውነተኛ ፍላጎት ካለን እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን መዝለል አንችልም። ራሳቸውን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንደራሴዎች አድርገው የሚመለከቱት ብዙዎቹ ብድኖች/ግለሰቦች ይህን መሰል ጥያቄዎችን እያነሱ ለመተንተን (ትንተናው ምንም ይሁን) እና ነገሩን ለማብላላት የተዘጋጁ አይመስሉኝም። ቢያንስ ይህን እያደረጉ ስለመሆኑ ያሳወቁን ነገር ጥቂት ነው። አሁን በየአቅጣጫው የተያዘው ተራ ፉከራና ቀረርቶ ነው። “እኛ የነጻነትና የዴሞክራሲ ታጋዮች! ካይሮ ደርሰናል!” አይነት ፉከራ።
ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳች አይነት ሕዝባዊ ተቃውሞ እንደሚቀሰቀስ ለመገመት የተለየ ምጡቅ እውቀት የሚጠይቅ ነገር አይደለም። ይህንን እንኳን ሌላው ሕዝብ ኢሕአዴግ ራሱም የሚክደው ሐቅ አይደለም። አቶ መለስ ይህን አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል “ይበጀኛል” ያሉትን እየሠሩ ነው። ጥያቄው የመለስን አምባገነናዊ አገዛዝ የሚቃወመው የተደራጀም ይሁን ያልተደራጀ ኀይል ምን እያሰበና ምን እያደረገ ነው የሚል ነው። ሕዝባዊ ተቃውሞን በራሱ የዴሞክራሲ ግብና ተስፋ አድርጎ መመልከት ግን ግማሽ አደጋ ያረገዘ አመለካከት ነው። ሲብስ ደግሞ የማሰብ ስንፍና የተጠናወተው አመለካከት ነው። ለተሻለ ነጻነትና ልማት ተጀምረው የባሰ አፈናንና ውድመትን የወለዱ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን/አብዮቶችን ማስታወስ አስቸጋሪ አይደለም።

Read more

Bad Behavior has blocked 4017 access attempts in the last 7 days.